የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሕገ መንግስት እና በሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚደረግ ወንጀል ተከሰሱ። አቶ ደጀኔ ክስ የቀረበባቸው ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26 ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
አዋሽ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለጊዜው አገልግሎቱን አቋረጠ!
በአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ በማጋጠሙ ከቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ጣቢያው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ II እና III ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲሳሳ ገልሜሳ አስታውቀዋል፡፡ላለፉት 49 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡ከተርባይን ወለል እስከ ተርባይን ሮተር ማገናኛ ዘንግ (Turbine Rotor Coupling Shaft) ድረስ ያሉት የኤሌክትሮ-መካኒካል እቃዎች በውሃ በመዋጣቸው የጉዳቱን መጠን ለማወቅ እንዳልተቻለ አቶ ዲሳሳ ተናግረዋል፡፡
[EEPCo]

በበርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የደረሰው ጥቃት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ!
በቅርብ በጀርመን - በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የደረሰው ጥቃት ለኤምባሲው በቂ ጥበቃ ባለመኖሩ የተከሰተ መሆኑንና በድርጊቱም ማዘኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ተወካይ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ተቃውሞ አለን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ኤምባሲውን ተቆጣጥረው ሰንደቅ ዓላማ ማውረዳቸው በቂ ጥበቃ አለመኖሩን ያማለክታል ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ መሰል ድርጊት በፈፀሙ አካላት ላይ ጀርመን አስፈላጊውን እርምጃ አለመውሰዷን እንዳሳዘናቸውም ነው አምባሳደር ሬድዋን የተናገሩት፡፡
ዜጎች ተቃውሞቸውን መግለፅ መብታቸው መሆኑን ኢትዮጵያ ትገነዘባለች ያሉት ሚኒስትር ድኤታው አቶ ሬድዋን፣ ተቃውሞ እንኳን ቢኖር የኤምባሲው መደበኛ ስራ ማስተጓጎል አልነበረበትም ብለዋል፡፡አዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ተወካይ ሄይኮ ኒዣኬ በበኩላቸው በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የደረሰው ጥቃት ተቀባይነት እንደሌለው ጠቁመዋል፡፡የጀርመን መንግስት ድርጊቱን በቅርብ በመከታተል አጣርቶ አስፈላጊን ማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፌስ ቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
[ኢቢሲ]

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም/አብቁተ/ ወደ ባንክ አደገ፡፡
የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮነን የለውም ወሰን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማይክሮ ባንኩ ለዘጠኝ አመት ሲጠይቀው የቆየው የሽግግር ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ተናግረው ከ3 እስከ 6 ወር ባለ ጊዜ ውስጥ ስራ ለመጀመር ሰራተኞችን በቂ ስልጠና የመስጠትና ቢሮዎችን በማደራጀት ስራ እንደሚሰራ ተናግረው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በብቃት በብቃት ለመጠቀም የዳታ ቤዝ ማዕከሉን በዘመናዊ መንገድ ለመጠቀም በቂ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አቶ መኮነን አክለውም ተቋሙ ወደ ባንክ ሲሸጋገር በ8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መነሻ ካፒታል የሚጀምር ሲሆን በ 53 ነባር የተቋሙ ቅርንጫፎች ተደራሽ እንደሚሆን ተናግረው ከዚህ በፊት ብድር ለወሰዱ ደመበኞች ሁለት አማራጭ የተቀመጠ ሲሆን የመጀመሪያው መጀመሪያው ውል መሰረት መጨረስ ሁለተኛው አማራጭ የወሰዱትን ብድር መልሰው በአዲስ መጠየቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከዚህ በፊት የሰራቸውን መልካም ስራዎች በመቀመር አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው የሚስተዋሉ ችግሮችን በማረምና በማስተካከል የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል፡፡የክልሉ መንግስት ድርሻ 98 በመቶ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደባንክ ሲያድግ ከ70 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት መመሪያው ሲለሚገድብ 30 በመቶው ለግል አክሲዎን የሚሸጥ ይሆናል ብለዋል፡፡
[የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን]

ሳኖፊ ኬቭዛራ ከተሰኘው መድሃኒት የኮሮና ክትባትን ለማዘጋጀት ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ አቋረጠ!
ፈረንሳዊው መድሃኒት አምራች ኩባንያ ሳኖፊ ኬቭዛራ ከተሰኘው የሩማቶይድ አርትራይተስ (የመገጣጠሚያ ችግር) መድሃኒት የኮሮና ክትባትን ለማዘጋጀት ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡ሳኖፊ ሙከራውን ያቋረጠው መድሃኒቱ የቫይረሱን ታማሚዎች ከመፈወስ ይልቅ ተጓዳኝ የጤና እክሎችን በመፍጠሩ ነው፡፡በመሆኑም ከአሁን በኋላ ሪጀነሮን ከተባለ ተቋም ጋር በመቀናጀት ያመረተውን መድሃኒት (ኬቭዛራ) ለኮሮና ክትባቶች ግብዓትነት ለመጠቀም የሚያደርገውን ክሊኒካዊ ሙከራ ማቋረጡን አስታውቋል ፡፡
መድሃኒቱ ህመሙ እምብዛም ያልጸናባቸውን ታማሚዎች እንኳን እጅግም ሊረዳ እንዳልቻለ ከአሁን ቀደም በተደረጉ ሙከራዎች መረጋገጡንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡ሳኖፊም ጉዳዩን በማስመልት ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡እንዳስታወቀው ከሆነም በጽኑ የቫይረሱ ታማሚዎች ላይ የተደረገው የሶስተኛ ደረጃ ክሊኒካል ሙከራ ሂደት የተፈለገውን ውጤት አላስገኘም፡፡“ሙከራው ተስፋ ያደረግንበትን ውጤት ባያስገኝም ቡድናችን ሲያደርግ በነበረው ጥረት ኮርተናል”ያሉት የተቋሙ የዓለም አቀፍ ምርምር እና ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጆን ሪድ “አሁንም ክትባት ማዘጋጀትን ጨምሮ ወረርሽኙን ለማዋጋት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ቁርጠኛ ነን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
[Al Ain]

ሳዑዲ ዐረቢያ ኮሮና ቫይረስን እንዳያስተላልፉ በሚል በለይቶ ማቆያዎች ያጎረቻቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ አፍሪካዊያን ከባድ ሥቃይ ውስጥ እንደሆኑ በምስል እና ቪዲዮ አስደግፎ ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ከስደተኞቹ መካከል በርካታ ኢትዮጵያዊያን ይገኛሉ፡፡ እንደ ገሃነም በሚቆጠሩ ማጎሪያ ጣቢያዎች ስደተኞች ከባድ ድብደባ ይፈጸምባቸዋል፤ በርካቶችም በከባድ ርሃብ እና ሙቀት ለህልፈት ተዳርገዋል- ብሏል ዘገባው፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ ዛሬ ዘገባውን አጣራለሁ ብላለች፡፡
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (OCHA) በኢትዮጵያ 15,2 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ ርዳታ እንሚያሻቸው ዐስታወቀ።
ርዳታውን ለማከናወን የ929,6 ሚሊዮን ዶላር ክፍተት መኖሩንም ኦቻ አሳስቧል። ጽ/ቤቱ ይኽን ያለው ከኢትዮጵያ «ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን» ጋር ዛሬ በጋራ ይፋ ባደረገው ዘገባው ነው።በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ እና ከምግብ ውጪ ለኾኑ የርዳታ አቅርቦቶች 1,44 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ኦቻ አስጠንቅቋል።
በሀገሪቱ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ መንጋ መስፋፋት በሰብል ምርት ላይ ከባድ ጥፋት ማድረሱ ችግሩን አባብሷል ብሏል። በጎርፍ መጥለቅለቅ እና በአካባቢዎች አለመረጋጋትም ሰዎች መፈናቀላቸው ሌላኛው ተግዳሮት መኾኑን ጠቅሷል። እንደ ኮሌራ ያሉ ተዛማች በሽታዎች መከሰታቸውም ለምግብ እጥረት መባባሱ ተጨማሪ ምክንያቶች መኾናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመግለጫው አትቷል።
የኮቪድ-19 ተሐዋሲ ስርጭት የተዘረዘሩት ችግሮች ላይ ጥላውን ሊያጠላ አያሻም አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል ብሏል። ኢትዮጵያ በአኹኑ ወቅት በዋናነት ትኩረቷ የኮቪድ-19 ስርጭትን መከላከሉ ላይ መኾኑን የመንግስት ተወካይ መናገራቸውን የተመድ መግለጫ ይጠቅሳል። የመንግሥት ተወካዩ ያም ኾኖ ዘርፈ ብዙ የኾኑት የሰብአዊ ርዳታ ተግዳሮቶች ከትኩረት ዕይታቸው ውጪ አለመኾኑን ተናግረዋል።
ኦቻ የኮቪድ-19 ተሐዋሲ የአደጉም ኾኑ አዳጊ ሃገራት ላይ ቢስፋፋም ብርቱ ተጽእኖ ያሳረፈው በአዳጊ ሃገራት ላይ ነው ብሏል። ኾኖም በኢትዮጵያ አስቸኳይ የሰብአዊ ርዳታ አሳሳቢነቱ ከተሐዋሲው ስርጭት በፊት የነበረው ዛሬም መቀጠሉን ኦቻ ጠቅሷል።
[DW]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,173 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,160 የላብራቶሪ ምርመራ 1,173 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 493 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 53,304 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 828 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 19,484 ደርሷል። በፅኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 306 መድረሱን ጤና ሚኒስተር ገልጿል።

ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ የዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለነገ ቀጠሮ ሰጠ!
ፍርድ ቤቱ በወንጀል ጉዳይ የተጠረጠሩት እነ አቶ ጀዋር መሐመድ ላይ የዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ።የዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ቁጥር 215585 አቶ ጀዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ቀርበዋል።
የፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ችሎት ልደታ አዳራሽ ዛሬ ጠዋትና ከሰዓት በኋላ በተጠርጣሪዎች ላይ ምስክሮችን ሲሰማ ውሏል።በዕለቱ ከተሰሙ ምስክሮች ውስጥ አራተኛው ምስክር ላይ መስቀለኛና ማጣሪያ ጥያቄ በማቅረብ ጀምሮ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ችሎቱ ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ ያየ ሲሆን፤ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በ24 ሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስረኞች አስተዳደርን ለችሎቱ አስሮ እንዲያቀርብ የሰጠውን ትዕዛዝ አይቷል።በዚሁ መሰረት በችሎቱ የቀረበው የአዲስ አበባ ፖሊስ እስረኞች አስተዳደር ማብራሪያ ሰጥቷል።በሰጠው ማብራሪያ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለሁሉም ተጠርጣሪዎች መደረጉን ገልጿል።
ነገር ግን ተጠርጣሪዎቹ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አንድ ጊዜ የተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ጥያቄያቸውም ድጋሚ እንዲደረግላቸው መሆኑን አብራርተዋል።በዚህም መሰረት ተጠርጣሪዎቹ ምርመራ እንዲደረግላቸውና ውጤታቸው እንዲገለጽ የመጨረሻ ትዕዛዝ ሰጥቷል።ዛሬ የተሰማው የምስክሮች ቃል ተገልብጦ ከመዝገብ ጋር እንዲያያዝ ያዘዘው ችሎቱ፤ ቀሪ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
[ኢዜአ]

የሕወሓት የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በዋስትና ተለቀቁ!
የሕዝባዊ ወያነ ኣርነት ትግራይ ሕወሓት የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዲለቀቁ ተወስኗል። ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሽብር ቡድኖች መረጃ አቃብላችኋል በሚል ተጠርጥረው የስር ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ቢወስንላቸውም ፖሊስ ሳይለቃቸው ቀርቶ ነበር።
[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝባዊ ወያነ ኣርነት ትግራይ ሕወሓት የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዲለቀቁ ተወስኗል። ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሽብር ቡድኖች መረጃ አቃብላችኋል በሚል ተጠርጥረው የስር ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ቢወስንላቸውም ፖሊስ ሳይለቃቸው ቀርቶ ነበር።
[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ሸዋ ዞን 11 ወረዳዎች በደረሱ ተፈጥሯዊ አደጋዎች 57 ሺሕ 333 ሰዎች ለችግር መጋለጣቸውን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።በ13 ወረዳዎች የጣለ በረዶ በ6 ሺሕ 950 ሔክታር መሬት ላይ የነበረ ሰብል ማውደሙን ገልጿል።በእንሳሮ ወረዳ 604 የመኖሪያ ቤቶች በከባድ በረዶ በመመታታቸው የመጠለያ ችግር መፈጠሩን፤2 ሺሕ172 ሔክታር መሬት ላይ የተዘራ ሰብል መውደሙን፤በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በ64 ሔክታር መሬት ላይ የነበረ የጤፍ እና የስንዴ ሰብል ውሃ ስለተኛበት አስታውቋል።ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በእንሳሮ ወረዳ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 3 ሰዎች፤ በአንኮበር ወረዳ ሌሎች 2 ወጣቶች በአጠቃላይ 5 ሰዎች መሞታቸው የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት አስታወቋል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መመሪያ የኮሮና ቫይረስ እለታዊ ሪፓርት
ዛሬ በላብራቶሪ የተመረመሩ ብዛት :- 382
ዛሬ የተያዙ :- 8
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ :- 1
ዛሬ ከበሽታው ያገገሙ :- 23
_________________________
በአጠቃላይ የተመረመሩ :- 10,591
በበሽታው የተያዙ :- 1032
በአሁን ሰዕት ህክምና ላይ ያሉ :- 484
ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ያገገሙ :- 538
እንዲሁም በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 974 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከግል ተቋራጮች ጋር አብሮ ለመስራት ልየታ ጀመረ!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞቹ ፍትሀዊ ተደራሽነትን ያረጋገጠና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከማድረስ አንጻር ሁሉንም ስራዎች በራሱ አቅም ብቻ ለመሸፈን ከመጣር ይልቅ የሶስተኛ ወገን ወይንም የግል ተቋራጮችን ለማስገባት የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት ላይ እንደሚገኘ አስታወቀ።ይህም የተነገረው ተቋሙ ያለፈውን በጀት አፈፃፀምና የ2013 በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚመለከት ባሳለፍነው ሀሙስ ነሐሴ 21/2012 በሒልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
[Addis Maleda]

የበለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተንሳፋፊ ሳርና የመለዋወጫ አቅርቦት ስራውን እያስተጓጎለበት መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ ገለፁ፡፡
ኃላፊው አቶ ፍቃዱ ደምሴ እንደገለፁት ወደ ጣቢያው የውሃ መቀበያ እየተገመሰ የሚመጣው ተንሳፋፊ ሳር ለኃይል ማመንጫው የኦፕሬሽን ሥራ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ ነው፡፡ተንሳፋፊ ሳሩ ከሐምሌ 9-11 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያውን እስከማስቆም ደርሶ እንደነበረ የገለፁት ኃላፊው ባለፈው ዓመትም በተንሳፋፊ ሳሩ ምክንያት ከ10 ቀን በላይ ጣቢያው መቆሙን አስታውሰዋል፡፡ጣቢያውን መልሶ ሥራ ለማስጀመር ኤክስካቬተር በመከራየትና ዋና በሚችሉ የጣቢያው ሠራተኞችን በመጠቀም የኃይል ማመንጫውን ውሃ መቀበያ የዘጋውን ተንሳፋፊው ሣር ለጊዜውም ቢሆን በማስወገድ ሥራ ማስጀመር መቻሉን አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡ጣቢያውን ከተንሳፋፊ ሳር ለመጠበቅ የሚያግዝ መከላከያ (Taff Boom) ያለው ቢሆንም በዘንድሮ ዓመት ከሃይቁ ዳር እየተገመሰ የሚመጣው የሳር ደሴት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ ቀደም ሲል የተገጠመው መከላለያ ሊመልሰው አልቻለም፡፡በመሆኑም በየጊዜው ወደ ኃይል ማመንጫው ለሚመጣው ተንሳፋፊ ሳር ዘላቂ መፍትሄ ካልተሰጠው በቀር ጣቢያውን እስከ መዘጋት ሊያደርሰው እንደሚችል አብራርተዋል፡፡

አምባሳደሮች እና ሚሲዮኖች በተከለሰው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ እየተወያዩ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
38 ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ የሚጠይቁና ከ 424 ሺ ሄክታር መሬት በላይ የሚያለሙ ነባርና አዳዲስ ዘጠኝ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን የመስኖ ልማት ኮሚሽን ገለጸ።
በኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ 38 ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ የሚጠይቁት ፕሮጀክቶቹ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቁ 424 ሺ 538 ሄክታር መሬት በማልማት 162 ሺ አርሶ አደሮችንና አራት የስኳር ፋብሪካዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ።
[EPA]

የግል ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ ማድረግ እንደማይችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የ 2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከ ነሃሴ 20 ጀምሮ እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ተከትሎ ከተማሪዎች ምዝገባ እና ከትምህርት ክፍያ ጋር ተያይዞ ወላጆች ቅሬታን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
ይህንንም ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍያ መመሪያን ተላልፈው ምዝገባ እያከናወኑ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ከመመሪያ ውጪ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለወላጆች ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ሚኒስተር ዴኤታዋ አክለውም የ2013 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ላይም ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል እና እንደሚያስጠይቅም ተናግረዋል፡፡ትምህርት ቤቶችም ምዝገባ ሲያከናውኑ ከዚህ በፊት ይጠቀሙበት የነበረውን የክፍያ አቀባበል ዘዴ መቀየር የማይችሉ መሆኑን እና ከዚህ በፊት በነበረው የክፍያ ስርዓት መቀጠል እንዳለባቸውም ተገልጿል።ከዚህም በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ የትምህርት ክፍያ እና ከመመዝገቢያ ክፍያ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ ክፍያ ማስከፈል ማይቻል መሆኑም ተነግሯል፡፡
የቀጣይ አመት ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን በተመለከተም ሚኒስትር ዴኤታዋ ትምህርት ሚኒስቴር እስከሚያሳውቅ ድረስ ማንኛውም ትምህርት ቤት ትምህርት መጀመር እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡
Via Ministry of Education
@Yenetube @FikerAssefa

የአዋሽ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ መተሐራ ከተማ በጎርፍ መጥለቅለቋ ተሰማ!
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በመተሐራ ፣ አዲስ ከተማና መርቲ የአዋሽ ወንዝ ከመደበኛ መፍሰሻው ወጥቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአል ዐይን ገለጹ፡፡ነዋሪዎቹ እንዳሉት አሁን ላይ የነፍስ አድንሥራ እየተሰራ ነው፡፡
የሥኳር ፋብሪካው በሚገኝበት መርቲና ከመተሃራ ወደ ሥኳር ፋብሪካው በሚወስደው መንገድ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አዲስ ከተማ ላይ ነው ወንዙ ሰብሮ ጉዳት ያደረሰው፡፡ በጎርፍ አደጋው የደረሰው የአደጋ አይነት እና መጠን በዝርዝር አልታወቀም፡፡
በአሁኑ ሰዓት ጎርፉ አዲስ ከተማን ማጥለቅለቁንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ ከተማ አንቀጸ ሰላም መድኃኒዓለም ገዳም በጎርፉ እንደተጥለቀለቀ የተገለጸ ሲሆን ካህናቱና ዲያቆናቱ የቃልኪዳን ታቦታቱን እና ንዋየ ቅዱሳቱን ይዘው በመተሐራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንደሚገኙም ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡