በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ የተቀሰቀሰዉ ግጭት እየተባባሰነዉ ተባለ!
በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌያት ከባለፈው እሁድ ጀምሮ የተነሳው ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ እንዳሉት በአዋሳኝ ቀበሌያቱ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከቀናት በፊት በተነሳው ግጭት አሁንም ሰዎች እየሞቱ ፣መኖሪያ ቤቶችም እየተቃጠሉ ይገኛሉ። የኮንሶ ክላስተር በተባለ ስፍራ ነዋሪ ነኝ ያሉ አንድ የዓይን እማኝ ቦርቆራ ቀበሌ ከለንጎ በተባለ መንደር ሰዎች ሲገደሉና ቤቶች ሲቃጠሉ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
የከለንጎ መንደርን ጨምሮ በእነኝሁ አካባቢዎች እስከአሁን አስራ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን እንደሚያውቁ የዓይን እማኙ ለዶቼ ቨለ በስልክ ገልጸዋል።የኮንሶ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ሃሰን ወላሎ በሁለቱ የማህበረሰብ አባላት መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሌሎች ቀበሌያት በመስፋቱ በቀላሉ ለመቆጣጠር መቸገራቸውን ገልጸዋል። ሃላፊው እስከትናነት ደርሶኛል ባሉት መረጃ አስራ አንድ ሰዎች መገደላቸውንና በሁለት መንደሮች ውስጥ የነበሩ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተናግረዋል።
ከባለፈው እሁድ አንስቶ በአካባቢው የተከሰተው ግጭት ከዚህ በፊት ከታዩት የከፋ መሆኑን የጠቀሱት የመምሪያው ሃላፊ በአሁኑ ወቅት የክልሉ የጸጥታ አባላት ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ሁኔታውን ለመቆጣጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌያት በተከሰተው ግጭት ዙሪያ የደቡብ ክልል መስተዳድርም ሆነ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ያሉ ነገር የለም።
#DW
@YeneTube @FikerAssefa1

ወለጋ ዉስጥ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነዉ!
በቄለም ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ከባለፈው እሁድ አንስቶ 12 ሰዎች መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የታሳሪ ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡ በነቀምቴ ከተማ ከሁለት ሳምንት በፊት የአርቲስቲ ሀጫሉ ሞትን ተከትሎ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ሀዘናቸውን በገለጹበት ወቅት በተፈጠረው አለመግባባትን ሰዎች መታሰራቸውን ተገልጸዋል፡፡ በደምቢዶሎ ከተማም እስከ ትናንት ድረስ የታሰሩ ሰዎች እንዳሉ የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጅቢሪል መሐመድ እንደተናገሩት የአርቲስት ሐጫሉ ሞትን ተከትሎ በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ሁከትን ለመቀስቀስ የሞከሩ ግልሰቦችን የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባራት እያከናኑ መሆናቸውንና በምዕራብ ኦሮሚያም የተደረገው የተለየ ነገር የለውም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች መኖራቸውን በመጥቀስ የታሰሩት ሰዎች ቁጥርም ከዚህ በላይ ሊጨምሪ ይችላል ብለዋል፡፡
በቀሌም ወለጋ ዞን የደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪዎች በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በአደባባይ ወጥቶ ከገለጹ መካከል ናቸው፡፡ ከከተማው ራቅ ባሉት ስፍራዎች ከተፈጠሩት አለመግባባቶች ውጭም በዕለቱ በከተማው የተፈጠረ ግጭት አልነበረም፡፡ነዋሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ተሳባስበው በሰላማዊ መንገድ ሀዘናቸውን ገልጸው ወደ የቤታቸው በወቅቱ መለመላሳቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ከሰሙኑ ደግሞ ግጭት ለመቀስቀስ ሞክራቹሀል የተባሉ 5 ሰዎች በከተማው መታሰራቸውን አንድ ወንድማቸው የታሰረባቸው የከተማው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡"ከዚህ በፊት የታሰሩትን ጨምሮ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በከተማው ፖሊስ ጣቢያ፣ የወረዳ ፖሊስ፣ እና ፖሊስ ካፒም ውስጥ ብዙ ሰዎች ታስረዋው ይገኛሉ፡፡ አንድ ዓመትም፣ ሰባት ወርም ታስረው የቆዩ አሉ፡፡ በዚህን ሳምንት ብቻ ደግሞ አምስት ሰዎች ታስረዋል፡፡ እስከ ትናንት ድረስ ሰዎች ታስረዋል፡፡አንድ ጣቢያ ውስጥ ከ20 እስከ 24 ሰዎችም ታስረው ይገኛሉ" ብለዋል።
በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማም በተመሳሳይ ከባለፈው እሁድ አንስቶ ሰባት ሰዎች መታሰራቸውን አንድ የከተማው ነዋሪ በስልክ ገልጸዋል፡፡ ከታሰሩት መካከከልም የአነግ የምስራቅ ወለጋ ዞን ጽ/ቤት አስተባባሪ የነበሩ አቶ ዲማ ቢቂላ የተባሉ እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በከተማው ተፈጥረው በነበረው አለመረጋጋትም በርካታ ሰዎች ታስረው እንደነበር ጠቁመዋል፡፡የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ የታሰሩ ግለሰቦች ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል፡፡በህግ የሚፈለጉ በርካታ ሰዎችም ተሰውረው እንዳሉም ተናግረዋል፡፡በቄለም እና ምስራቅ ወለጋ እንዱሁም በሌሎች ዞኖችም ታስረው ለሰባት ወራት እና ለአንድ ዓመት ያህልም ክስ ሳይቀርብባቸው ያሉ ሰዎች ስለመኖራቸው ለተነሳው ቅሬታም አቶ ጅብሪል ሲመልሱ ቅሬታው የተለመደና የውሸት ውንጀላ ነው ብለዋል፡፡በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችም ጉዳያቸው ታይቶ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ነጻ ከሆኑ በቶሎ እንደሚለቀቁ ተናግረዋል፡፡ ከፖለቲካ አመለካከቱ እና የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆኑም የታሰረ ሰው አለመኖሩንም አቶ ጅብሪል አክለዋል፡፡