YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሻሸመኔ ከተማና በምእራብ አርሲ በ10 ወረዳዎች በሁከትና አመጽ ወንጀል የተጠርጣሩ 1 ሺህ 523 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ፍርድ ቤት የቀረቡት 1 ሺህ 523 ግለሰቦች የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ÷ በሻሸመኔ ከተማ እና በምእራብ አርሲ 10 ወረዳዎች በተፈጠረ ሁከትና አመጽ፣ በሰው ህይወት ላይ ለደረሰው ጥፋት ፣በንብረት ላይ ለደረሰው ውድመትና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው።በሻሸመኔ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና በምዕራብ አርሲ 10 ወረዳዎች በሚገኙ ፍርድ ቤቶች በቀረቡ ተጠርጣሪዎች ላይ መርማሪ ፖሊስ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ድርጊት ገልጿል።

የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የጥምረት መርማሪ ፖሊሶች በሻሸመኔ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአጠቃላይ 553 ተጠርጣሪዎችን ያቀረቡ ሲሆን ÷ከዚህ ውስጥ 97ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።በሌላ በኩል በምእራብ አርሲ ዞን በ10 ወረዳ ፍርድ ቤቶች 970 ተጠርጣሪዎች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 54ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል።ተጠርጣሪዎቹ በተጠቀሱት አካባቢዎች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ÷ በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ለደረሰ የሰው ህይወት መጥፋት ፣ የግልና የመንግስት ንብረት ፣ መውደም እና ዘረፋ ተጠርጥረው ምርመራ እየተከናወነባቸው መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

የአስከሬን ምርመራ እና የወደመው ንብረትን በባለሙያ ለማስገመት እየሰራ መሆኑን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ የሰውና የተጠርጣሪ ቃል መቀበሉን ተናግሯል።ከዚያም ባለፈ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለመሰብሰብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ሲል ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው በዋስ እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን÷ የሻሸመኔ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የምዕራብ አርሲ ወረዳ ፍርድ ቤቶች የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜን ፈቅደዋል።የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅ ከሃምሌ 28 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል፡፡ገንዘቡ በኢትዮጵያ ኪቪድ19ኝን ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለህክምና ቁሳቁስ መግዣ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በማቅረብ የጤና ስርአቱን ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት ይውላልም ነው የተባለው፡፡በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ድጋፉ በኢትዮጵያ ኮቪድ19ኝን ጨምሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እንደሚውል ተናግረዋል፡፡

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1