YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የፀሀይ ግርዶሽ እይታ በአላማጣ

#Tigray_TV
@YeneTube
የፀሐይ ግርዶሽ በእንጅባራ ዛሬ ጠዋት 1:55 ሰዓት

#Awi_Communication
@YeneTube
የፀሐይ ግርዶሽ በዱከም

Via ኦዜል ~ @YeneTube
ኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቀዳዳ የተሰራላቸው ማስኮችን ወደ ሀገር እንዳይገቡ አገደች።

የኢትዮጲያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚል ጥቅም ላይ ከሚውሉ ማስኮች ውስጥ ቫልቭ ወይም የመተንፈሻ ቀዳዳ የተሰራላቸው ማስኮችን ወደ ሀገር እንዳይገቡ ትዕዛዝ ማስተላፉን አስታውቋል፡፡ባስልጣኑ ከዚህ ቀደም ቫልቭ ወይም የመተንፈሻ ቀዳዳ የተገጠመላቸው ማስኮች የቫይረሱን ስርጭት ለመጨመር አስተዋፆ አላቸው በሚል ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ባለስልጣኑ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት ህብረተሰቡ እነዚህን ማስኮች ከመጠቀም አልተቆጠበም እና ምን አይነት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም በባለስልጠኑ የመድሀኒት ምዝገበ እና ፍቃድ ዳይሬክተር አቶ አብደላ ቃሰውን ጠይቆ እነዚህ ቫልቭ ወይም የመተንፈሻ ቀዳዳ የተገጠመላቸው ማስኮችን ቫይረሱን ለመከላከል በሚል ዓላማ እናስገባ ለሚሉ ሰዎችም ሆነ ሀገር ውስጥ ለማምረት ፍቃድ ለሚጠይቁ ሰዎች ፈቃድ መስጠት አቁመናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ቫይረሱን ለመከላል በሚል ዓላማ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡም ለጉምሩክ ኮሚሽን ደብዳቤ መፃፉን ነግረውናል፡፡እነዚህ ማስኮች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ሲደረግ የተሰሩበት ዓላማ በሽታውን ለመከላከል በሚል ባለመሆኑ እና ማስኮቹ በተገጠመላቸው የመተንፈሻ ቀዳዳ አማካኝነት ቫይረሱን ከመከላከል ይልቅ ለስርጭቱ ከፍተኛ አስተዋፆ ስለሚያደርጉ ማህበረሰቡ ማስኩን ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሰጠንቅቀዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ግብጽ የህዳሴ ግድቡ ላይ በሚደረጉ ድርድሮች ወቅት “ ‘የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ተፈፃሚ አይሆኑም’ በሚል በኢትዮጵያ ዘንድ የሚነሳው ጥያቄ አግባብ አይደለም፤ ስምምነቶቹ አሁንም ተፈፃሚ ናቸው” ስትል ከትናንት በስቲያ አርብ፤ ሰኔ 12፤2012 በድጋሚ ለጸጥታው ምክር ቤት በላከችው አቤቱታ አመለከተች።  

የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ በማመመልከቻቸው አባሪ ላይ ኢትዮጵያ በ1894 ዓ.ም ከታላቋ ብሪታኒያ እና ከጣሊያን ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ዋቢ በማድረግ “ውሉ ተፈጻሚ ነው” ሲሉ መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡ ሳሜህ “ኢትዮጵያ በቅኝ ተገዝታ አታውቅም። አባይን በተመለከተ የፈረመቻቸው ማንኛውም አይነት ስምምነቶች ነፃ አገር ሆና ስለፈረመቻቸው ገዢ ናቸው” ሲሉም ሞግተዋል።

“ኢትዮጵያ በአባይ ላይ የሚደረግ እና የውሃውን ፍሰት ሊይዝ የሚችል ማንኛውንም አይነት ግንባታ ላለማካሄድም ወይም እንዲካሄድ ላለመፍቀድ፤ በ1894ቱ ስምምነት ላይ ቃል ብትገባም ይህንን መቃወሟን ቀጥላለች” ስትል ግብጽ ኢትዮጵያን ወንጅላለች።ግብጽ በአጼ ምኒልክ በኩል የተፈረመውን ይህንን ስምምነትም አባሪ አድርጋም ለምክር ቤቱ ልካለች።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 63 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4457 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4532 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (5 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ከአንድ የ75 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ከዚህ በተጨማሪ በለይቶ በህክምና ማዕክል ውስጠ ክትትል ላይ የነበረች የ34 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በጠቅላላ ሁለት ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አራት (74) ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 63 ሰዎች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(42) ሴት(21) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ14-76 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 91 ሰዎች(67 ከአዲስ አበባ፣ 2 ከኦሮሚያ፣ 4 ከአማራ፣ 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና 16 ከሶማሊ ክልሎች) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1213 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(31)፣ ከኦሮሚያ ክልል(5)፣ከአማራ ክልል(3) ፣ ከትግራይ ክልል(1)፣ከሶማሊ ክልል(9)፣ ከሀረሪ ክልል(1)፣ ከድሬዳዋ(4)፣ ከአፋር ክልል(4)፣ ከደቡብ ክልል(2) እና ከጋምቤላ ክልል(3) በድምር 63 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4532 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 32 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 2 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 74 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖች ጋር ተወያዩ።

ከመከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች ጋር በአዲሱ የመከላከያ ግንባታ ስትራቴጂ ዝግጅት እና በተቋማዊ የግንባታ ሂደት ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ለዘመናት አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየው የጣና በለስ አየር ማረፊያ ዛሬ የሙከራ በረራውን አካሄደ።

በሙከራ የበረራ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሳነ መስተዳደሮች ተገኝተዋል።አካባቢው የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰላጫ በመሆኑ መደበኛ የበረራ ፕሮግራሙን ለማካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰሩ ርዕሳነ መስተዳድሮች ገልጸዋል።የአካባቢውን ሰላም በአንጻራዊነት በማረጋጋት ቀጠናውን ወደ ልማት በሚደረገው ሂደትም የሁለቱ ክልል መንግስታት በትኩረት እንደሚሰሩ ተጠቁሟል።

ባለሃብቱ በራሳቸው ተነሳሽነት የአየር መንገዱን ለማስጀመር ያደረጉትን ተነሳሽነት በማመስገን በክልሉ ውስጥ ለሚያደርጉት የልማት እንቅስቃሴ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ አሻድሊ ሃሰን ተናግረዋል።የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ መንግስት ምላሽ ለመስጠት በሚደርገው ሂደት ውስጥ የባለሃብቱ ሚና የጎላ እንደሆነ ገልጸው ሌሎችም ለማገዝ መንግስት እንደሚሰራ ተናግረዋል።ተቋርጦ የነበረውን የጣና በለስ አየር ማረፊያ በአዲስ መልክ ለማስጀመር በኢትዮጵያዊው ባለሃብት አቶ ወርቁ አይተነው እየተከናወነ ይገኛል።

ምንጭ: የመተከል ዞን ኮ/ን መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
የወላይታ ዞን ምክር ቤት ራሱን ችሎ በክልልነት ለመደራጀት ባቀረበው ጥያቄ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ጉባኤ ጠራ።

ነገ ሰኞ ሰኔ 15፤ 2012 በሶዶ ከተማ፣ ጉተራ አዳራሽ ይካሄዳል የተባለው አስቸኳይ ጉባኤ በክልል ጥያቄ ቀጣይ አካሄዶች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።የወላይታ ዞን የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊ ሶልያና አዴሎ የነገው ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ “የክልል አደረጃጀት የደረሰበት ደረጃ ላይ መወያየት እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ” መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። “በዋናነት አጀንዳው የክልል ጥያቄው አሁን የደረሰበትን ደረጃ መገምገም ነው። አባላቱ ናቸው ተወያይተው አቅጣጫ የሚያስቀምጡት” ብለዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የሉቴናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የአዲስ አበባ ጉብኝት "ከሱዳን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እውቅና ውጪ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ምክር የተከናወነ ነው" በሚል የተሰራጨን መረጃ የሱዳን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት "ሐሰት" ሲል አጣጣለ።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
💻ከNat mobile & Computers
ማንኛውንም አይነት Laptop በተመጣጣኝ ዋጋ እንገዛለን

በተጨማሪም
🔴#ጥራት   ያላቸውንና   ምርጫዎን  የጠበቁ  ላፕቶፖች እና ታብሌቶች  ሳይለፉ   ሳይደክሙ  ከኛ ይሸምቱ ከሙሉ ዋስትና ጋር  

Dell i5 7th 17500br
HP i5 14500br

ስልክ
+251911522626
+251953120011

Inbox @Natyendex

🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA

አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ in front of angla burger
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች በዋስትና

A01 2019 /16 GB/ 5,500 ብር
A10S 2019 /32 GB/ 6,699 ብር
A20S 2019 /32 GB/ 8,499 ብር
A30S 2019 /64 GB/ 10,499 ብር
A30S 2019 /128 GB/ 10,999 ብር

A50S 2019 /128 GB/ 4GB 13,499
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 13,999
A31 2020 /128 GB/ 4GB 12,499
A51 2020 /128 GB/ 6GB 14,499 ብር

A60 2019 /64 GB/ 6GB 12,999 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 15,999 ብር
A71 2020 /128 GB/ 6GB 19,499 ብር
A71 2020 /128 GB/ 8GB 19,999 ብር

M30S 2019 /64 GB/ 4GB 11,499
M30S 2019 /128 GB/ 4GB 12,499
📌M31 2020 /128 GB/ 6GB 14,499

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175 @heymobile
0925927457 @eBRO4
0910695100 @Roviii

@HEYOnlinemarket
#ስለምታስበው_አስብ
#ሁለተኛው_ዕትም_በገበያ_ላይ

በቀን ከ12 ሺ እስከ 60 ሺ ሀሳቦች በአእምሯችን እንደሚመላለሱና ከ80 እስከ 95 ፐርሰንት የሚሆኑት ሀሳቦች አሉታዊና የተደጋገሙ እንደሆኑ ያውቃሉ?

#ስለምታስበው_አስብ የተሰኘው መጽሐፍ አላስፈላጊ ሀሳቦቻችንን ተቆጣጥረን እንዴት ጥርት ባለ ሁኔታ ማሰብ እንዳለብን የሚያሳይ፣ አሉታዊና ትርኪምርኪ የሆኑ ሀሳቦቻችንን ለማጽዳት የሚረዳ መጽሐፍ ነው!

“አዕምሯችን እንዴት እንደሚሰራ እንደ ርችት ፍንትው ባለ ህብረቀለም የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ ትንሽም ቢሆን የአስተሳሰብ እክል አለብኝ ብለው ካሰቡ ይሄ አስገራሚ መጽሐፍ #እንደ_መድሃኒት_ቢታዘዝልዎት_አይከፋም፡፡
ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ

#የምናስብ_ከሆነ_ይህ_መጽሐፍ_የግድ_ያስፈልገናል!!!

#በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች_እጅ_ያገኙታል
http://tttttt.me/teklutilahun