YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 115 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 115 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1625 መድረሱን የከተማው ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦
አዲስ ከተማ 18፤
ልደታ 5፤
ጉለሌ 10፤
ኮልፌ ቀራንዮ 13፤
ቦሌ 42፤
አራዳ 5፤
የካ 5፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 4፤
አቃቂ ቃሊቲ 2 ፤
ቂርቆስ 9 እና የ2 ሰዎች ክፍለ ከተማ በመጣራት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

#AMN
@YeneTube @FiksrAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ይካሄዳል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ በሚደረገው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ እና 5ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን መርምሮ በማጽደቅ የዕለቱ መደበኛ ስብሰባ የሚጀምር ይሆናል፡፡ምክር ቤቱ በነገው ውሎ የፌዴራል መንግስት የ2013 ረቂቅ በጀት ላይ በመወያየት ረቂቅ የበጀት አዋጁን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ የሚመራ ሲሆን አራተኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ለማራዘም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ለማቅረብ የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የገቢ፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ስለማዛወር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa