YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኤልስ ሜድ የተባለ የእስራኤል የሕክምና ቁሳቁስ አምራች ኩባንያ ስድስት ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 50 የሕጻናት አልጋዎች እና 18 ኢንፍዩዥን ፓምፕ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የኩባንያው የኢትዮጵያ ፓርትነር እና ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ሓይሉ እና ፓርትነር እና ማናጀር አቶ ውበቱ ይመር በጋራ በመሆን ድጋፋቸውን ለኮሌጁ ፕሮቮስት ዶር ወነድማገኝ ገዛሀኝ አስረክበዋል፡፡ኤልስሜድ የተሰኘው ኩባንያ ለቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከዚህ ቀደም ሙሉ የመጸዳጃ ቤት ስራዎችን በነጻ በመስራት ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

Via SPHMMC
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ወልቃይት ኦራሪት ተቃውሞውን አስተባብራችኋል የተባሉ 340 ሰዎች መታሰራቸውን አረና ገለፀ።

በትግራይ በተቃውሞው ተሳትፋችኋል የተባሉ ታፍነው እየተወሰዱ በመሆኑ ወጣቱ በፍራቻ ወደ በረሀ ወርዷል ብሏል አረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፡፡የትግራይ ህዝብ ከገበሬ እስከ ተማረው ፤ ፍትህ ሲጎድልበት ጭቆና ሲያይልበት በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን መግለፅ መቀጠሉን የገለፀው አረና 11 ሺህ ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን ባሰማባት ኦራሪት ወልቃይት የአካባቢውን ምክትል አስተዳዳሪ ጨምሮ ተቃውሞውን መርታችኋል፣አስተባብራችኋል የተባሉ 340 ሰዎች ታፍነው ተወስደው ታስረዋል ብሏል፡፡የአረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አምዶም ገብረስላሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገተናገሩት የትግራይ ህዝብ በቅቶታል ብለዋል፡፡

በተለይ በዋጅራት፣ በማይሀንሰን ፣ ኦራሪት ወልቃይት፣ በሌሎች አካባቢዎችም የተስተዋሉት ታቃውሞዎችና ቁጣዎች የትግራይ ህዝብ በደሉ ከሚሸከመው በላይ እንደሆነበት ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።የተዘጋው መንገድ የተከፈተው አሁን ላይም የተረጋጋ የሚመስለው ህወሀት ለተቃውሞዎቹ በሀይልና በጠመንጃ በሰጠው ምላሽ ነው ብለዋል አቶ አምዶም፡፡በተለይ በ ኦራሪት ወልቃይት፣ በርካታ ሰዎች ተደብድበዋል፣ ቆስለዋል፣ ሌሊት የመኖርያ ቤታቸው በር እየተሰበረበረ እየተወሰዱ ነው ያሉ ሲሆን ወጣቱ በፍራቻ ከመኖርያ ቤቱ ሸሽቶ በረሀ ነው ያለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ግፍ የዳረጋቸው ለመብታቸው መታገል መጀመራቸው ነው ያሉት አቶ አምዶም በትግራይ የለውጥ ፍላጎቶቹ ንረዋል፤ አረና ህወሀት እንደሚለው ይሄን የታቀውሞ ሰልፍ ባይጠራም ፤ የህዝቡ ጥያቁ ጥያቄያችን ስለሆነ እስከመጨረሻው ከህዝቡ ጎን ነን ብለዋል፡፡ህወሀት ምርጫ እንደማያሸንፈን ያውቀዋል ያሉት አቶ አምዶም ለዛ ነው አሁን በኮሮና ግርግር ህዝብ በነፃነት ወጥቶ በማይመርጥበት ሁኔታ አሸነፍኩ ለማለት ምርጫው ይደረግ እያለ ያለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ህዝቡ ህወሀትን አንቅሮ እንደተፋው እናውቃለን፣ እኛ ሳንሆን ራሱ ህወሀት ያውቀዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልልን አስተያየት ለማካተት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት እየተዘጋጀ ነው!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማዕከልነት እየተዘጋጀ መሆኑን የአካዳሚው የውድድር እና ስልጠና ዳይሬክተር አቶ አብዮት ተስፋዬ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን ወደ ጊዜያዊ የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያነት ለመቀየር እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚጠናቀቅ ኃላፊው ተናግረዋል።የህክምና ባለሙያዎች ከአራት ቀናት በፊት ጀምሮ ማዕከሉን ለማረፊያነት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ዳይሬክተሩ ጨምረው ጠቁመዋል።አካዳሚው በአስር የተለያዩ የስፖርት አይነቶች በጊቢው ውስጥ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ከ300 በላይ ሰልጣኞችን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሱን ኢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ከፍተኛ መጠን ያለው አደንዛዥ ዕጽ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እየገባ እንደሆነ የኬንያው ዘ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ሞያሌ ከሻሸመኔ ለሚገባው እና ባለሃብቶች ለሚሳተፉበት 75 በመቶ የዕጽ ኮንትሮባድ ዋና መገበያያ ናት፡፡ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ድንበሩ ቢዘጋም፣ በአዳዲስ መስመሮች በመኪና እና ሞተር ሳይክል ወደ ናይሮቢ በስፋት እየገባ ነው፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የሩስያዉ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ በሚገኘዉ ክሬምሊን ቤተመንግሥት ለዓመታት ተደላድለዉ ተቀምጠዋል የሚል የተቃዉሞ ሰልፍ ተጠራ።

የሩስያ የተቃዉሞ ኃይላት የጠሩት ይህ የተቃዉሞ ሰልፍ «ዘላለማዊ ፒቱንን አንፈልግም» የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የክሪምሊን ቤተ-መንግሥት ዋንናዉን ባለስልጣን በመቃወም ይህን ተቃዉሞ የሚደግፍ ዜጋ ሁሉ ከኢንተርኔት የተለያዩ መፈክሮችን በማዉጣት በተለያዩ ቦታዎች እንዲለጥፍ በኢንተርኔት የተለያዩ መፈክሮች ተበትነዋል ተብሎአል። የሩስያ ተቃዋሚ ኃይላት ፕሬዚዳንት ፑቲን በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ሕገ-መንግሥቱን መሻር ይፈልጋሉ ሲሉም ይከሳሉ። የሩስያ ባለስልጣናት ሩስያ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ይደረግ አይደረግ ሲሉ ለፊታችን ሰኔ 24 ሕዝበ ዉሳኔ ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ ይዘዋል። ሕገ መንግሥቱ ከተሻሻለ አንዴ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዴ ፕሬዚዳንት እየሆኑ ለ 20 ዓመታት ሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት የቭላድሚር ፑቲን የእስከ ዛሬዉ የስልጣን ዘመን ሁሉ በዜሮ ተባዝቶ ፤አንድ ሲል የሚጀምር ይሆናል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በለይቶ ማቆያ የነበሩ የሆስፒታሉ ሰራተኞች በሙሉ ከኮቪድ 19 ነጻ መሆናቸው ተረጋግጦ ወጥተዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በለይቶ ማቆያ የነበሩ የሆስፒታሉ ሰራተኞች በሙሉ ከኮቪድ 19 ነጻ መሆናቸው ሁለት ጊዜ በምርመራ ተረጋግጦ ዛሬ ግንቦት 28/2012 ዓ.ም ከውሸባ ወጥተዋል፡፡ የህከምናና የጤና ባለሙያዎቹ ከነበሩበት የለይቶ ማቆያ ሲወጡ የጎንደር ከተማ አስ/ ም/ከንቲባና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በጋራ የቁርሰ ግብዣና የምስጋና ፕሮግራም ተደርጓል፡፡

ምንጭ: ዩንቨርስቲው
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ፍርድ ቤቶቹ ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ መወሰናቸውን ለሚድያ ተቋማት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሕግ አስከባሪዎች በኦሮሚያ ክልል ሐኪሞች እና ሆስፒታል ሠራተኞች ላይ በተደጋጋሚ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃት ይፈጽማሉ ሲል የኦሮሚያ ሐኪሞች ማኅበር በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ማክሰኞ’ለት ጸጥታ ሃይሎች ነቀምቴ ሆስፒታል ቀዶ ጥገና ክፍል ገብተው፣ ሐኪሞችን እና ሠራተኞችን ድብድበዋል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from HEY Online Market
Playstation 4PRO (Slim)
With 2 controllers
1000 GB storage
With FIFA 2019 CD

Price 23,999 Birr

Contact us :
0953964175
0925927457 @eBRO4
0910695100
@heyonlinemarket
Forwarded from Kídus
⚜️SHEBA - ሺባ⚜️

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን

ጥራት ያለው ጌጣጌጥ 💎በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ይህንን::

⚠️(ሺባ) የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበርን ስለሆነ ‼️ነፃ ‼️ሰዐት ለማግኘት ከዌብ ሳይታችን ላይ ማንኛዉንም እቃ ይግዙ፡

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼

Website - www.shebasluxury.com

Telegram - https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ

Contact Admin @ki_d_us

📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን🏍
Forwarded from EthioNova🇪🇹
Access 100+ both free and Paid online courses from leading institutions worldwide. Gain new skills and earn a certificate of completion. Join today.

Contact +251939560060 or @yenecademy

yenecademy.com/
በከፋ ዞን ሁለት ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስክሬናቸው ላይ በተደረገ ምርመራ ሟቾቹ በኮቪድ-19 ተይዘው እንደነበረ ተረጋግጧል።

ባሳለፍነው እሁድ በከፋ ዞን በሰው እጅ የተገደሉት ግለሰብ እስክሬናቸው ላይ በተደረገው ምርመራ ግለሰቡ በኮቪድ-19 ተይዘው እንደነበረ መረጋገጡን የቦንጋ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዘሪሁን መንገሻ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ግለሰቡ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ድብደባውን ተከትሎ የአስክሬን ምርመራ ሲደረግ በዚያው ኮቪድ-19 ሲመረመር እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ ነግረውናል፡፡

አስክሬኑ አሁንም ሆስፒታል እንደሆነ የገለጹት አቶ ዘሪሁን፤ ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ያላቸው ቤተሰቦች፣ አስከሬን ያነሱ ሰዎች፣ አስከሬን የወሰዱ የፖሊስ አባላት፣ የወንጀል መርማሪዎች፣ አሽከርካሪዎች እና የአስከሬን መርማሪዎች ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ወደ ተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ገልጸውልናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በጠቅላላ በአዴ ወረዳና በዴቻ ወረዳ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ቴሌቪዥን “የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር የምያንማሯ መሪ አንግ ሳን ሱ ኪ የገጠማቸው አይነት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ይኖራቸዋል” ሲል ቢቢሲ ዘገበ በማለት ያቀረበው ዜና ፍጹም ሐሰት ነው።

ትግራይ ቲቪ በቅርቡ፤ ከወራት በፊት በዘጋቢያችን ቃልኪዳን ይበልጣል የቀረበን የድምጽ ቅጂ ቆርጦ በማውጣት ለዚህ ዘገባው ተጠቅሞበታል። ነገር ግን ቢቢሲ ይህን የመሰለ ዘገባ ፈጽሞ አልሰራም ሲል ቢቢሲ በፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያና በጎረቤት ሃገሮች የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ ሁኔታ
@Yenetube @Fikerassefa
“ስለ አገር አንድነት ማቀንቀን አሀዳዊ የሚያሰኝ ከሆነ ልሁን” – አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

አገር አንድ እንድትሆን፣ አገር እንዳትበተን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሰላምና በመቻቻል አብረው እንዲኖሩ፣ የመንቀሳቀስና የመስራት ነጻነት እንዲያገኙ አቀነቅናለሁ። ይህ ስለአገር አንድነት ማቀንቀኔ አሀዳዊነት ካሰኘኝ ልሁን ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ።ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት፤ አገር አንድ እንድትሆን፣ አገር እንዳትበተን፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሰላምና በመቻቻል አብረው እንዲኖሩ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ዜጎች የመንቀሳቀስና የመስራት ነጻነት እንዲያገኙ አቀነቅናለሁ። ይህ ስለአገር አንድነት ማቀንቀኔ አህዳዊነት አይደለም ብለዋል።

በአሀዳዊና በአንድነት መካከል ልዩነት መኖሩን የገለጹት አቶ ሙስጤፌ እኔን የአሀዳዊነት የፖለቲካ አቀንቃኝ ነህ የሚሉ ካሉ ስህተት ነው። እኔ የአንድነት ፖለቲካ አቀንቃኝ ነኝ ብለዋል።ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ላላት ኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀር ይጠቅማታል ብለው በግላቸው እንደሚያምኑ የገለጹት አቶ ሙስጠፌ የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀር ግን ከአንድነት ጋር እንደማይጋጭ ተናግረዋል።

በፌዴራል ሥርዓት አስተዳደር ስር በተዋቀሩት ክልሎች የአንዱ ብሄረሰብ የበላይነት የሚሰፍንበት፤ ሌላው የሚጨቆንበት፣ አንዱ ልጅ ፤ሌላው የእንጀራ ልጅ የሚሆንበት ሥርዓት መፈጠር የለበትም ያሉት አቶ ሙስጠፌ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሶ በሰላም አብሮ የሚኖርበትና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ያለባት አንድ ኢትዮጵያን እንደሚመኙና ለአገራችንም የሚያዋጣው ይህው ነው ብለው በግላቸው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።የአገር አንድነት ማቀንቀንና አሀዳዊነት የመንግስት አስተዳደር የተለያዩ መሆናቸውን ገልጸው አሀዳዊና ፌዴራላዊ ሥርዓት የመንግስት የአስተዳደር ዘዬ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

አዲስ ዘመን ግንቦት 28/2012
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
43a1fb6d-e9a4-4b6f-8df3-d5317f1f7e5d_48k
<unknown>
"የህወሓት ታጣቂዎች ከኦነግ ሸኔ ጋር ተደባልቀው አየተንቀሳቀሱ ነው" - የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት

በርከት ያሉ የህወሓት ታጣቂዎች ከኦነግ ሸኔ ጋር ተደባልቀው አየተንቀሳቀሱ ነው ሲል የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ወንጅሏል።የክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር ግርማ ገላን ለመገናኛ ብዙሃን እንዳሉት ከሥልጠና ቦታ ጠፍተው የመጡ ወጣቶችም ማን እንዳስለጠናቸው እና ተልዕኮ እንደሰጣቸው በግልፅ ይናገራሉ ብለዋል።

የድምፅ ዘገባውን ከላይ አያይዘነዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ማሊ ውስጥ በተካሄደ ዘመቻ በሰሜን አፍሪካ የአል-ቃይዳ መሪ የነበረው አብድልማሊክ ድሮክዴል መገደሉን ፈረንሳይ አስታወቀች።

የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስትር ፍሎረንስ ፓርሊ እንዳሉት ድሮክዴል እና የቅርብ አጋሮቹ በዕለተ ረቡዕ በሰሜናዊ ማሊ በተደረገ ዘመቻ ተገድለዋል።ሚኒስትሯ አክለውም በሌላ ዘመቻ የኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ቡድን አዛዥ የሆነ ሰው በፈረንጆቹ ወርሃ ግንቦት ላይ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስታውቀዋል።"በኃያልነት የተወጣናቸው ዘመቻዎች ለአሸባሪ ቡድኖቹ ትልቅ ኪሳራ ናቸው" ሲሉ ሚኒስትሯ የዘመቻውን ውጤት ተናግረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም የጤና ድርጅት፣ ሰዎች በሚያዘወትሯቸው ሁሉም ቦታዎች የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ሊደረጉ ይገባል ሲል መከረ፡፡

አንዳንድ የዓለማችን አገሮች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስኮችን) ማድረግን በአስገዳጅነት ስራ ላይ እንዳዋሉት ቢቢሲ ፅፏል፡፡ቀደም ሲል የዓለም የጤና ድርጅት ሁሉም ሰው ጭንብል ማድረጉን አይደግፈውም ነበር ተብሏል፡፡ ጭንብል ማድረግ ያለባቸው ከሕሙማን ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው፣ ሕሙማኑን የሚያክሙ እና ራሳቸው ሕሙማኑ ብቻ ናቸው የሚል አቋም ነበረው፡፡ አሁን ግን ጭንብል የማድረግን አስፈላጊነት በጥናት አረጋግጫለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ስለዚህም እገሌ ከእገሌ ሳይባል ሰዎች ጭንብል እንዲያደርጉ መክሯል፡፡በዓለም ዙሪያ 6.7 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ 400 ሺህ ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸው ማለፉ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

Via BBC/Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
💻ከNat mobile & Computers
ማንኛውንም አይነት Laptop በተመጣጣኝ ዋጋ እንገዛለን

በተጨማሪም
🔴#ጥራት   ያላቸውንና   ምርጫዎን  የጠበቁ  ሞባይሎች፣ ላፕቶፖች እና ታብሌቶች  ሳይለፉ   ሳይደክሙ  ከኛ ይሸምቱ ከሙሉ ዋስትና ጋር  

Dell i5 7th 17500br
HP i5 14500br

ስልክ
+251911522626
+251953120011

Inbox @Natyendex

🔶 ለበለጠ መረጃ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAELbSrbiTDHFnicnnA

አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ እስታር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ in front of angla burger
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም መሰረት፣

1. በሊዝ የተያዙና ከአሁን ቀደም አግባብ ባለው አካል የይዞታ ማረጋገጫ በሊዝ ሥራአት እንዲሥተናገዱ በተወሠነላቸውና በቀጥታ በሊዝ በተያዙ የመኖረያ ይዞታዎች ላይ
በአልሚዎች ተይዘው የሊዝ ክፍያ ፍሬ ግብር እንዲከፍሉ ነገር ግን ወለድና ቅጣት እንዲነሳላቸው፤

2. መሬት አግባብ ባለው የሊዝ ሥራአት ወስደው በወቅቱ ግንባታ ያልጀመሩና ያላጠናቀቁ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም ተቋማት የግንባታ ፈቃዳቸውን ያለቅጣት እንዲያድሱና ተጨማሪ የኣንድ ዓመት የማራዘሚያ ጊዜ እንዲሰጣቸው፤

3. በሪልስቴት ከተያዙት ውጪ የመኖሪያ ይዞታዎች ወለድና መቀጫ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳላቸው፤

4. ለቢዝነሥ በተለይም በሆቴልና ቱሪዝም ይዞታዎች መቀጫን ሙሉለሙሉ ወለድ ደግሞ 30% እንዲቀር የተወሰነ ሲሆን ውሣኔው የከተማ አሥተዳደሩን እሥከ አንድ ቢልየን ብር ገቢ የሚያሣጣ ቢሆንም የተቀዛቀዘውን የከተማችን ኢኮኖሚ በተለይም የኮንሥትራክሽን ዘርፋን በማነቃቃት ረገድ ከሚኖረው ሚና ባሻገር ውዝፍ ገቢዎች እንዲሠበሠቡ የሚያሥችልና ከ50 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ወቅታዊ ውሣኔ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡በክስ ሂደት ላይ ያሉ አልሚዎችም ከቅጣቱና ከወለድ ክፍያ 30 በመቶ ተነስቶላቸው እንዲከፍሉ ተወስኗል።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa