ጣናን በዘላቂነት መጠበቅ ለነገ የማይባል ተግባር ነው:: ተግባሩም በፌደራል መንግስት አስተባባሪነት እና ግንባር ቀደም ተሳትፎ ሊመራ ይገባል:: የክልሉ መንግስት ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል::
-Prez Temesgen Tiruneh
@YeneTube @FikerAssefa
-Prez Temesgen Tiruneh
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል አንዲት እናት 4 መንትዮች በሰላም ተገላገለች!
በደቡብ ክልል፣ በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በሰነና ገሬራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ዜኖ ሸምሱ በቅበት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደረገላት የቀዶ ህክምና 3 ሴት እና 1 ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች፡፡በስልጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ሀኪም መሀመድ ኡስማን እንደገለፁት በአካባቢው 4 መንትዮችን መገላገል እምብዛም የተለመደ ተግባር እንዳልነበር አስረድተዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት 4ቱም ህፃናት በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
ምንጭ: የክልሉ መ/ኮ/ቢሮ

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላን በይፋ ለማስጀመር ሀዋሳ ከተማ ገቡ!
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎችም ጥቁር ውሃ ላይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሀዋሳ ሀይቅ ዳር በሚገኘው ታቦር ተራራ ላይ ችግኝ በመትከል ሀገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ ቀን በይፋ እንደሚያስጀምሩ ይጠበቃል።
Via ENA

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋቱን ተከትሎ የትራፊክ ፍሰቱ ቢቀንስም የትራፊክ አደጋው መጠን ግን ከቀድሞው እየጨመረ ነው አለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፡፡
በመጋቢት ወር መጀመሪያ አካባቢ በአገራችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በመዲናችን አዲስ አበባ የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች ፍሰት የቀነሰ ቢሆንም በትራፊክ አደጋ እየደረሰ ያለው የአደጋ መጠን ግን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር መጨመር አሳይቷል።የተሸከርካሪ ፍሰት መቀነስ የአደጋውን ቁጥር ሊቀንስ ይችላል ተብሎ በህብረተሰቡ ዘንድ ቢታሰብም የትራፊክ አደጋ ቁጥር መጨመር እና መቀነሱ በተሽከራካሪዎች ቁጥር መጨመር እና መቀነስ የሚገደብ ሳይሆን በአሽከርካሪው እና በእግረኛው የጥንቃቄ ልክ የሚወሰን ነው ብሏል፡፡በመሆኑን አሽከርካሪዎች መንገዶች ነፃ ናቸው በሚል ምክንያት ከሚፈቀደው የፍጥነት መጠን በላይ ከማሽከርከር መቆጠብ እንዳለባቸው እና እግረኞችም ራሳቸውን ከትራፊክ አደጋ በመጠበቁ ሂደት የግል ጥንቃቄ ሊለያቸው እንደማይገባ አሳስቧል።
Via አሐዱ ሬዲዮ

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ኳራንታይን ውስጥ የነበሩ ሁለት ነፍሰ ጡር እናቶች ልጆቻቸውን በሰላም ተገላግለዋል።
በሀረማያ ዩንቨርስቲ የኮሮና ቫረስ ወረርሽኝ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ የነበሩ የሶማሌ ላንድ የጉዞ ታሪክ የነበራቸው ሁለት ኢትዮጵያዊያን ነብስ ጡር እናቶች ልጆቻቸውን በሰላም መገላገላቸውን የዩንቨርሲቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ያለምሸት ተሾመ ተናግረዋል። በተጨማሪም አሁንም በዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ ውስጥ 3 ነፍሰ ጡር እናቶች አሉ። ለእነዚህ እናቶችም የቅድመ-ወለድ የጤና ክትትል እና እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ: አሐዱ ሬዲዮ

የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ሠራተኞች ኮሮናን ለመከላከል የ50 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ!
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችና ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ኮቪድ -19ን ለመከላከል የ50ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንና የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በድጋፍ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጀኔራል አደም መሐመድ ድጋፉን ለብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክበዋል።
ምንጭ: ኢዜአ

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቺቺንያ አካባቢ በወሲብ ንግድ ይተዳደሩ የነበሩ 120 ሴተኛ አዳሪዎችን ወደ መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል መግባታቸው ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በከተማዋ በተለምዶ ቺቺኒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በወሲብ ንግድ ተሰማርተው የነበሩ 120 ሴተኛ አዳሪዎችን ወደ መልሶ ማቋቋም ማዕከል ማስገባቱን ተናግሯል፡፡ በአጠቃላይ በሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ የተለዩ 11 ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች በከተማዋ እንደሚገኙ የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ እነዚህን ሴቶች ወደ ማዕከል ለማስገባት ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ቢሮው አስታውቋል፡፡ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሴቶች ኤልሻዳይ ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በመሆን ወደ መልሶ ማቋቋም ማዕከል ለማስገባት ቅድመ ስራ መሰራቱን ነው የተገለፀው፡፡ቢሮው እነዚህን ሴቶች ወደ ማዕከል የሚያስገባው ከዚህ ህይወት ወጥተው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ነው ትብሏል፡፡በተጨማሪም እነዚህ ዜጎች ከወቅቱ የኮሮና ቫይረስ ለመታደግ እነደሆነም ቢሮው ገልጿል።
Via Ethio FM

ኬንያ የለይቶ ማቆያ ማከሚያዎች በመሙላታቸው ህክምናው በቤት እንዲሰጥ ወሰነች!
በኬንያ የኮሮናቫይረስ ህክምና የሚሰጥባቸው የለይቶ ማቆያ ማከሚያ ማዕከላት መሙላታቸውን ተከትሎ ለህሙማኑ ህክምና በቤት እንዲሰጥ መወሰኑን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታውቀዋል።ሚኒስትሩ ሙታይ ካግዌ እንዳሉት በመጀመሪያ ደረጃ በቤት ውስጥ ለሚደረገው ህክምና የሚያገለግል መመሪያ እንደሚወጣና በመቀጠልም የጤና ማዕከላቱን ነፃ ለማድረግም ህሙማኑ ወደየቤታቸው የመላክ ስራ ይሰራል ብለዋል።በቤታቸው ሆነው ከኮሮናቫይረስ የሚያገግሙ ህሙማንም ላይ መገለልና አድልዎ እንዳይኖር ሚኒስትሩ ተማፅነዋል።በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ሁለት ለይቶ የማቆያ ህክምና መስጫ ማዕከል የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም መሙላታቸው ተገልጿል።
ሃገሪቷ በትናንትናው ዕለት 124 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መመዝገቧን ተከትሎ፤ አጠቃላይ ቁጥሩንም 2 ሺህ 340 አድርሶታል። ከነዚህም መካከል 592 ሲያገግሙ 78ቱ ህይወታቸውን አጥተዋል።በቤታቸው ሆነው ከኮሮናቫይረስ የሚያገግሙ ህሙማን ከሰዎች ጋር መቀላቀልን ማስወገድ፣ የራሳቸው የመኝታ ክፍልም እንዲኖራቸውም የአለም አቀፍ ጤና ድርጅት መመሪያ ያዛል።ከህሙማኑ ጋር በጋራ እቃዎችን አለመጠቀም ወይም ፀረ- ተህዋሲያን (ዲስ ኢንፌክታንት) መርጨት እንዲሁም እንክብካቤ የሚሰጡ ግለሰቦችም መከላከያ ሊያደርጉ እንደሚገባም መመሪያው ያትታል።
Via BBC

ሲሚንቶ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንዲያከፋፍሉ ተወሰነ!
በሲሚንቶ ምርት ላይ የታየውን ችግር ለማቃለል አምስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችና 12 አከፋፋዮች ብቻ ምርቱን እንዲያከፋፍሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወሰነ፡፡የመሸጫ ዋጋው መንግሥት በሚያወጣው የዋጋ ተመን ብቻ እንደሚከፋፈልም ተገልጿል፡፡ሚኒስቴሩ በሲሚንቶ ምርት ላይ የተከሰተውን እጥረትና የዋጋ ንረትን ለመቀነስ በተወሰደው እርምጃ ላይ ዛሬ ለኢዜአ መግለጫ ሰጥቷል፡፡የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ መንግሥት በአገሪቱ የተከሰተውን የሲሚንቶ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የስርጭት መጠኑን ወደነበረበት ለመመለስ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በቻይና የኮሮናቫይረስ የማህበረሰብ ስርጭት መቆሙ ተነገረ።
የኮሮናቫይረስ መነሻ የሆነችውና የቫይረሱንም መዛመት ለመግታት ቀዳሚ ትግል ስታደርግ በነበረችው ቻይና የማህበረሰብ ስርጭት መቆሙ ተነግሯል።
የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች እንዳስታወቁት በማህበረሰቡ ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት እንዳቆመና ህመምተኞችም እየመዘገቡ እንዳልሆነ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ሆኖም ከሌላ ሃገራት የሚመጡ መንገደኞች በቫይረሱ መያዛቸውም ተገልጿል። በሻንግሃይ እንዲሁም በሲቹዋን ግዛቶችም አምስት ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው በትናንትናው ዕለት ሪፖርት ተደርጓል።በቻይና በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 83 ሺህ 27 ደርሷል።
Via :- BBC
@Yenetube @Fikerassefa

በሊባኖስ ባለፈው ወር ለሽያጭ ቀርባ የነበረችው ናይጄሪያዊት ወደ ሃገሯ እንደማትመለስ መግለጿን የናይጄሪያ ዲያስፖራ ኮሚሽን አስታውቋል።
ግለሰቧ ለሽያጭ የቀረበችው በፌስቡክ ላይ በወጣ ማስታወቂያ ነበር። ግለሰቧንም ለመግዛት የቀረበው የገንዘብ መጠን አንድ ሺ ዶላር ነበር።
በማስታወቂያው ላይም የግለሰቧ የፓስፖርት ፎቶ በግልፅ የሚታይ ሲሆን በርካታ ሰዎች መጋራታቸውን ተከትሎም፤ ቁጣና ውግዘትም አስተናግዷል።
በማስታወቂያው ተሳትፏል የተባለው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል።የ30 አመቷ ናይጄሪያዊት በሊባኖስ ሌላ ስራ እንዳገኘችም አስታውቃለች።
Via:- BBC

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 169 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5798 የላብራቶሪ ምርመራ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1805 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5798 የላብራቶሪ ምርመራ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1805 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 19 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ35 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ ህይወት አልፏል። ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 19 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ35 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ ህይወት አልፏል። ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 19 ደርሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 169 ሰዎች አንዱ አሜሪካዊ ሲሆን፣ 168ቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(111) ሴት(58) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ1-78 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል 2 ሰዎች ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከህመማቸው ሲያገግሙ በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 262 ደርሷል።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(138)፣ ከኦሮሚያ ክልል(11)፣ከትግራይ ክልል(4)፣ ከደቡብ ክልል(4)፣ አማራ ክልል(6)፣ ከሶማሌ ክልል(5) እና ከሀረሪ ክልል(1) በኮሮና የተያዙ በድምር 169 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,805 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 18 ደርሷል።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 1 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 19 ደርሷል።

በአዲስ አበባ በሚገኙ 90 ት/ቤቶች የከተማ ግብርና መጀመሩ ተገለጸ፡፡
ኢ/ር ታከለ ኡማ በኮከበ ፅባህ ት/ቤት በመገኘት በጠባብ ቦታ ላይ የተተገበረውን የከተማ ግብርና ተመልክተዋል።በት/ቤቶች እየተተገበረ ያለው የከተማ ግብርና በአንድ በኩል ለተማሪዎች ስለከተማ ግብርና መማሪያ እንዲሆን የታሰበ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ምርቱ ለተማሪዎች ምገባ እንዲውል የታለመ መሆኑን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።የከተማ ግብርና በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች እየተተገበረ እንደሚገኝም ተገልጿል።
Via AMN

በአዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 138 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1343 መድረሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቫይረሱ ዛሬ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ ደረጃ:
አዲስ ከተማ 20
ኮልፌ 12
ቦሌ 23
ጉለሌ 19
ቂርቆስ 6
ልደታ 8
አቃቂ ቃሊቲ 9
አራዳ 4
የካ 24
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 8
አድራሻቸው በመጣራት ያሉ 5 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ቫይረሱ ዛሬ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ ደረጃ:
አዲስ ከተማ 20
ኮልፌ 12
ቦሌ 23
ጉለሌ 19
ቂርቆስ 6
ልደታ 8
አቃቂ ቃሊቲ 9
አራዳ 4
የካ 24
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 8
አድራሻቸው በመጣራት ያሉ 5 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ አራት (134) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ኬንያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,474 ደርሷል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ዘጠኝ (79) ደርሷል፡፡643 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
አትሌት ወንድወሰን ከተማ አበረታች መድኃኒት በመጠቀሙ የአራት ዓመት እገዳ እንደጣለበት የብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ጽህፈት ቤቱ አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ታኅሣሥ 1/2019 በቻይና ሻንዚቢ ዓለም አቀፍ የግል ማራቶን ውድድር ላይ በስፖርት የተከለከለ አበረታች መድኃኒት (ዶፒንግ) መጠቀሙን በመረጋገጡ ለአራት ዓመታት የእግድ ቅጣት ተጥሎበታል ብሏል።አትሌቱ በማንኛውም አገር አቀፍ ይሁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ ነው ቅጣቱ የተጣለበት።
በዚህ ውድድር ላይ ብቻ ያስመዘገበው ውጤትና ሽልማት እንዲሰረዝ ዉሳኔ መተላለፉን የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈትቤት አስታውቋል።በተጨማሪም ሁለት አትሌቶች በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በግላቸው በተሳተፉባቸው ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን መጠቀማቸው ጥርጣሬ በመኖሩ ጉዳያቸው በመጣራት ላይ መሆኑን ተገልጿል።የሁለቱ አትሌቶች ዉሳኔው እንደተጠናቀቀም ቅጣቱንና ሥም ዝርዝራቸው ይፋ እንደሚሆነም ተጠቅሷል።ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ስፖርታዊ ውድድሮች ለጊዜው ቢቋረጥም የስፖርት አበረታች ቅመሞች ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።