YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት (12) ደርሷል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 85 ሰዎች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(51) ሴት(34) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ1 ወር-65 አመት የሆኑ

➡️19 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️18 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️48 የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው።

➡️ተጨማሪ 3 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 217 ደርሷል።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(72)፣ ከኦሮሚያ ክልል(5)፣ ከትግራይ ክልል(4) አማራ ክልል(1) እና ከሶማሌ ክልል(3) በኮሮና የተያዙ በድምር 85 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,257 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 4 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 1 ሞት የተመዘገበ ሲሆን ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 12 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አስጎብኚ ድርጅቶች ከቀረጥ ነፃ ያስገቧቸውን መኪኖች ማከራየት እንዲችሉ ተፈቀደ!

በኮሮና ተህዋስ እጅጉን ከተጎዱ የቢዝነስ ዘርፎች ማካከል የሆነው የቱሪስት አስጎብኚ ዘርፍ መሆኑ ይታወሳል፡፡ መንግስትም ይህን ዘርፍ ለመታደግ በማሰብ በርካታ የድጋፍ አማራጭ ሲያቀርብም ቆይቷል፡፡በቅርቡ እንደተሰማው ደግሞ በአስጎብኚ ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶች ከፍተኛ ደረጃ ያለቸውን ከቀረጥ ነጻ የገቡ ተሽከርካሪዎች ለእርዳታ ድርጅቶች እና መሰል ተቋማት በማከራየት እግሩ እስኪፈታ ድረስ ገቢ እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡በመደበኛው ግዜ እነዚህ ተቋማት ከቀረጥ ነጻ ያስገቧቸውን ተሸከርካሪዎች ከመማስጎብኘት ስራ ውጭ ለኪራይ እንዲያውሉ አይፈቀድም፡፡ አከራይተው ከተገኙም ከፍተኛ መጠን ያለውን ቀረጥ እና መቀጮ እንዲከፍሉ ይደረጉ ነበር፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የካቲት አጋማሽ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ቻይናዊ እጮኛ ሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

ዶክተሩ ኮሮናቫይረስ መጀመሪያ በተገኘባት ዉሃን ከተማ ይሠሩ ከነበሩ ሀኪሞች አንዱ ነበር። ህሙማንን ለማከም ሲል የካቲት መጀመሪያ ላይ ሊካሄድ የነበረውን ሠርጉን ሰርዟል።በዉሃን በከፍተኛ ሁኔታ በታማሚዎች ተጨናንቀው ከነበሩ ሆስፒታሎች በአንዱ ውስጥ ነበር የሚሠራው። ሕይወቱ ሲያልፍ እጮኛው የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ነበረች።በቻይና ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት የሠርግ ልብስ ለብሰው ፎቶ ይነሳሉ። ሀኪሙ ሲሞት የቻይና መገናኛ ብዙሃን ከእጮኛው ጋር የተነሳውን ፎቶዎች ያሳዩ ነበር።የሠርጋቸው መጥሪያ ሳይላክ በሀኪሙ ቢሮ ውስጥ እንደተቀመጠ ይገኛል። የጨቅላዋ መወለድ ‘መባረክ’ ነው ያሉ በርካቶች ቢሆኑም፤ ‘ጀግና’ አባቷን በማጣቷ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋን በማናር በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ነው!

የአትክልት ተራ ዋጋን መነሻ በማድረግ የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋን በማናር በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የኮረና ቫይረስ መከሰት ጀምሮ የንግዱን ማኅበረሰብም ሆነ ሸማቹን በፍትሐዊ መንገድ ተጠቃሚ ለማድረግና የበሽታውን ተጋላጭነት ለመከላከል በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጿል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ የንግድ ተቋማት በተለይ በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ላይ የተሰማሩ አንዳንድ የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴዎች ከአትክልት ተራ ዋጋ በላይ በተጋነነ ዋጋ በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ቢሮው ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር ማረጋገጥ መቻሉን አመልክቷል፡፡ማንኛውም በዚህ ዘርፍ የተሰማራ ነጋዴ የአትክልት ተራ ዋጋን መነሻ በማድረግ በአማካኝ ማንጎ የሀበሻ 10 ብር፣ ኤክስፖርት ኳሊቲ 20 ብር፣ አቮካዶ 10 ብር እንዲሁም ሙዝ 10 እስከ 12 ብር በመሸጥ ማስተካከያ እንዲያደረግ ቢሮው አሳስቧል፡፡በተቀመጠው ማስተካከያ መሠረት ተግባራዊ በማያደርጉ ነጋዴዎች ላይ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድ ቢሮው ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በሰነድ ማረጋገጥ ሂደት ላይ QR code መጠቀም ጀመረ!

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ (ሰማምኤ) ባለፉት አመታት አሰራሩን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማቀላጠፍ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አስታውሶ በተቋሙ በርካታ ሶፍትዌሮችን እንዳለማም አስታውሷል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ እንዳሉት በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራን ከመከወን አንፃር ከሳምንታት በፊት በኪው አር መለያ (QR code) የታገዘ የሰነድ ማረጋገጥ ስራ መጀመሩን ገልፀው፡፡ አዲሱ አሰራር የሰነዶች እውነተኛነትን ከማረጋገጥ አንፃር ትልቅ እርምጃ ነው ብለውታል፡፡“ቀደም ሲል ለውክልና የተሰጠን ሰነድ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንደ ባንክ ያሉ ተቋማት ሰራተኞቻቸውን ወደ ሰማምኤ ይልኩ ነበር ያም ግዜና ገንዘብን ያላግባብ እንዲባክን ያረግ ነበር ሆኖም አዲሱ አሰራር መለያውን በQR code ማንበቢያ በማስነበብ በቀላሉ ሰነዱ ከሰማምኤ የወጣ ለመሆኑ ማረጋገጫ ያገኛሉ፣” በማለት አቶ ሙሉቀን የአዲሱን ቴክኖሎጂ ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እና መምህራን ትምህርታዊ መረጃዎችን በነፃ ማግኘት እንዲችሉ ማድረጉን አስታወቀ።
መረጃዎቹ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያዘ የገጽ ለገጽ ትምህርቶች መቋረጣቸውን ተከትሎ የተዘጋጁ መሆናቸውን በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመላክቷል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን እና ተማሪዎች አጋዥ መረጃዎችን http://ndl.ethernet.edu.et/ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ በነጻ ማግኘት ይችላሉ ነው ያለው።
ድረ ገጹ ከግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ነው በኩባንያው የቀረበው።
በተጨማሪም ህብረተሰቡ የኮሮና ወረርሽኝን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚያገኝባቸውን ድረ ገጾች አዘጋጅቶ በነጻ ማቅረቡንም አስታውቋል።

@Yenetube @FikerAssefa
በመዲነዋ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 889 ደረሰ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ አጠቃላይ በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 889 ደርሷል፡፡ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 72 ሰዎች በክ/ከተማ ደረጃ ሲታይ

አዲስ ከተማ 28፣
ቦሌ 12 ፣
አራዳ 8፣
ልደታ 7፣
የካ 5፣
ጉለሌ 3፣
አቃቂ ቃሊቲ 4፣
ቂርቆስ 3፣
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 2፣
ኮልፌ ቀራንዮ 0

መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።ይህም የሚያሳየው በአዲስ አበባ ከተማ በሽታው በህብረተሰቡ ውስጥ ከዕለት ዕለት በፍጥነትና በስፋት እየተሰራጨ መሆኑን ሲሆን ፤ እያንዳንዳችን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የመያዝ እድላችን ከፍተኛ ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል ሲል ጤና ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
በቴሌግራም @Orangebusinessnetwork ን በመጎብኘት ለእርሶ እና ለድርጅቶ እድገት የሚረዱ መረጃዎች ፤ሀብቶችን እና ማበረታቻዎችን ያገኙ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
T.me/Orangebusinessnetwork
በደቡብ ክልል አዲሱ የሥራ ምዘናና የደረጃ አወሳሰን(JEG) ክፍያ ከግንቦት 25 ቀን 2012 ጀምሮ ተከፋይ መሆን ይጀምራል፡፡

በዚህም መሠረት ከክልል እስከ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ድረስ ያሉ መዋቅሮች የግንቦት ወር ክፍያን በአዲሱ የደመወዝ መጠን ፔይሮል አዘጋጅተው መክፈል እንዳለባቸው የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አጥብቆ አሳስቧል፡፡በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፋይናንስ ቢሮ ባለፉት 24 ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን የሰው ኃይል መረጃ የማጣራት ሥራ ያጠናቀቀ ሲሆን ከግንቦት 25/2012 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ለሚገኙ መዋቅሮች ክፍያው እንደሚተላለፍ አስታውቋል፡፡

ቢሮው በተጨማሪ እንደገለጸው ምንም እንኳን ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ክፍያውን እንደሚፈጽም ያስታወቀ ቢሆንም ጥራት ያለውን መረጃ በወቅቱ ያደረሰ መዋቅር ባለመኖሩ እስካሁን ሊዘገይ ችሏል፡፡ ሆኖም ለታችኛው መዋቅር በተደረገው የባለሙያ ድጋፍና ሰፊ የማጣራት ዘመቻ ክፍያ ለመፈጸም በሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ለዚህም የክልሉ ሠራተኞች ላሳዩት ትዕግሥትና መረዳት ያለውን አድናቆት በአንክሮ ገልጿል፡፡

ምንጭ: የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአገር ውስጥና የትምህርት ሚንስቴር መሥሪያ ቤቶች፤ የእምነት ተቋማትና ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የሚያደርጉትን ምክክር እንዲያፋጥኑ አዘዙ።

ኬንያ “ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረባት አገር ናት” ያሉት ፕሬዘዳንቱ “አማኞች በሐይማኖታዊ ሥርዓቶች መሳተፍ አለባቸው” ሲሉ ተናግረዋል።ኬንያታ ትምህርት ቀስ በቀስ እንደሚጀመርም ተናግረዋል።ዛሬ 'ማዳራካ' ወይም የአገሪቱ የነፃነት ቀን ሲከበር ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር፤ በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ መመሪያዎች እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።አገር አቀፉ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ወደ መዲናዋ ናይሮቢ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የተጣለው እገዳ ከሳማንት በፊት በ21 ቀናት ተራዝሟል።በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙት 1,962 ሰዎች ናቸው። 64 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በብራዚል በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን አልፏል። ይህም በዓለም ሁለተኛ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ120 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማስገባት ወርሃዊ ወጪውን ሸፍኖ ለአገር ኢኮኖሚ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ዋና ሥራአስፈጻሚው ተናገሩ።

ዋና ሥራአስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት አየር መንገዱ ፈጥኖ ወደ ካርጎ አገልግሎት መግባቱ ውጤታማ አድርጎታል።ኮቪድ- 19 በዓለም ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ በአየር መንገዱ ላይም ተመሣሣይ ጉዳት ማድረሱን ገልጸው፤ በርካታ አየር መንገዶች በድጎማና በብድር ውስጥ በገቡበት ወቅት አየር መንገዱ ወጪውን ሸፍኖ ለመንግሥት ድጋፍ ለማድረግ በቅቷል ብለዋል።ለውጤታማነቱ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኮቪድ- 19 መከላከያ ቁሳቁስ የሚተላለፍባት ምቹ ቦታ ተደርጋ መወሰዷና አየር መንገድ በዓለም ገበያ ላይ አበባ ለማጓጓዝ ተመራጭ እንዳደረገው አመልክተዋል።

አየር መንገዱ በቀን ከ200 እስከ 300 ቶን አበባ ወደ ተለያዩ አገሮች በማጓጓዝ በኢትየጵያ ያለውን የአበባ ምርት እንዲበረታታና በውጭ ምንዛሪ ኢኮኖሚውን እየደገፈ ነው ብለዋል።በረመዳን ወቅት ሥጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በማጓጓዝ ገቢ ማግኘቱን ዋና ሥራአስፈጻሚው አብራርተዋል።አየር መንገዱ ወጪውን ሸፍኖ ለአገሪቱ ኢኮኖሚው ድጋፍ ማድረጉ በዓለም ካሉት አየር መንገዶች ጠንካራ ያስብለዋል ብለዋል።በቀጣይም የዓለም አቀፉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማየት ተጨማሪ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ጭነት ማመላለሻነት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ተወልደ አስታውቀዋል።የአየር መንገዱ 90 በመቶ የመንገደኞች አውሮፕላኖች የኮሮና ቫይረስ ባመጣው ተፅዕኖ ምክንያት ሥራ አቁመዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
3 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 በተያዙባት ኮንጎ ኢቦላ ተቀሰቀሰ!

ከሦስት ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙባት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ኢቦላ በድጋሚ መቀስቀሱ ተገለጸ። የጤና ሚንስትሩ ኢቲኒ ሎንጎንዶ እንዳሉት፤ በምዕራባዊቷ ምባንዳካ ከተማ አራት ሰዎች በኢቦላ ሳቢያ ሞተዋል። ከተማዋ በአገሪቱ አሁን ወረርሽኙ ካለበት ምሥራቃዊ አካባቢ በአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በተያዘውና በቀጣዩ ሳምንት ከሳዑዲ አረቢያና እና ከኩዌት 1,484 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ባለፉት 15 ቀናት የኮሮናቫይረስ ስርጭት በ310% መጨመሩ ተገለጸ!

በኢትዮጵያ ባለፉት 15 ቀናት የኮሮናቫይረስ ስርጭት በ310 በመቶ መጨመሩን የኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር የሚኒስትሮች ኮሚቴ አስታወቀ።ኮሚቴው እስካሁን ባለው ሂደት ወረርሽኙን ለመከላከል በመንግስትና በህብረተሰቡ የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።የኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር የሚኒስትሮች ኮሚቴ አስተባባሪ ሴክሬታሪያት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የኮሚቴውን መደበኛ ውይይት በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫቸውም ባለፉት 2 ወር በ4 ቀናት ውስጥ 53 ሺህ 600 ሰዎች ተመርምረው 286 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።

ባለፉት 15 ቀናት ደግሞ 55 ሺህ 845 ሰዎች ተመርምረው 886 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።ይህም ሚያሳየው ባለፉት 15 ቀናት የቫይረሱ ስርጭት በ310 በመቶ ማደጉን ነው ብለዋል፡፡በዚህ ወረርሽኝ የህብረተሰቡ የመረዳዳት ባህል እያደገ መምጣቱን የገለፁት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ህብረተሰቡ አሁን ያለው የወረርሽኙ ስርጭት አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት የፀጥታ አካላትን በራሱ ተነሳሽነት ማገዝ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ከተማዋ ከአራቱም አቅጣጫ ሰዎች የሚገቡባትና የሚወጡባት በመሆኑ የቫይረሱ ስርጭት እንዳይስፋፋ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ዜጎች ምግብ የማቅረብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው ስራው ተጠናክሮ እነደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ቆራሪት ከተማ ትናት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች መንገዶች ዘግተዋል።

ተቃውሞው ከወረዳ አከላለል፣ ከመሬት ካሳ፣ ከመሰረተ ልማት እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa