በአሜሪካ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ፖሊስ ጣቢያ አቃጠሉ!
በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለ ጆርጅ ፍሎይድ ሕይወቱ ካለፈች በኋላ ለሦስተኛ ቀን በቀጠለ ተቃውሞ ሰልፈኞች ሚኒያፖሊስ ውስጥ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በእሳት አጋይተዋል። ፍሎይድ ምንም እንኳን ‘’መተንፈስ አልቻልኩም ‘’ እያለ በተደጋጋሚ ቢጮህም ይዞት የነበረው ፖሊስ በጉልበቱ አንገቱን ተጭኖት ለረዥም ጊዜ ቆይቷል።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ‘ወሮበላዎች’ የፍሎይድን ክብር በመጥፎ ተግባራቸው እያቆሸሹት ነው በማለት የአገሪቱ ብሔራዊ ዘብ በአካባቢው ጸጥታ እንዲያስከብር አዘዋል።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

እያነጋገረ ያለውና በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ከፍተኛ አመፅ ከቀሰቀሰው ከጆርጅ ፍሎይድ አሟሟት ጋር በተያያዘ በ46 አመቱ አፍሪካ አሜሪካዊው አንገት ላይ በእንብርክክ ቆሞበት የሚታየው ፖሊስ ደርክ ቸውቪን በፖሊስ ተይዞ መታሰሩን NBC ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ቁጥር እየጨመረ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 1289 አዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች። 34 ተጨማሪ ሰዎችም ሞተዋል። እስካሁን በሀገሪቱ 22,082 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 879ኙ ሲሞቱ 5511 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
በአፍሪካ የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ ሲሆን የCDC አሁናዊ መረጃ የሚከተለውን ይመስላል:
➡️ሁሉም የአፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።
➡️131,564 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
➡️3,834 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።
➡️55,000 ሰዎች አገግመዋል።
ምንጭ:CDC Africa and Daily news Egypt

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በቁጥጥር ስር የዋለው የቀድሞው ሚኒያፖሊስ ፖሊስ አባል ደርክ ቸውቪን የግድያ ወንጀል ክስ(Third degree murder and Manslaughter) እንደተመሰረተበት አቃቤ ህግ ማይክ ፍሪማን ተናግረዋል።
ምንጭ:NBC
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:NBC
@YeneTube @FikerAssefa
ትራምፕ የአሜሪካና የዓለም ጤና ድርጅትን ግንኙነት አቋረጡ
በዋይት ሃውስ በሰጡት መግለጫ “ዛሬ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ያለንን ግንኙነት እናቋርጣለን። እናደርግ የነበረውን ድጋፍ ወደሌሎች ዓለም አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና በጎ አድራጊዎች እናዘዋውራለን” ብለዋል።
አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት ግንባር ቀደም ነበረች።
@Yenetube @Fikerassefa

ትዊተር ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጽሑፎች አንዱን ግጭት ያበረታታል በሚል መልዕክታቸው በገጻቸው ላይ እንዳይታይ አድርጓል።
ጽሑፉ ከገጻቸው ላይ እንዲጠፋ ባይደረግም፤ አንባቢዎች እውነተኛነቱን እንዲያጣሩ የሚጠቁም መልዕክት ተያይዞ ተለጥፏል።
ትዊተር ጽሑፉን ሰዎች ለማንበብ ይፈልጋሉ በሚል ሳያጠፋው እንደቀረ አስታውቋል። ትዊተርና የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር አንድ ሁለት መባባል ጀምረዋል።
በሚኒያፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ አፍሪካ አሜሪካዊ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ሕዝብ ተቃውሞውን እያሰማ ነው። ፕሬዘዳንቱ “የአገር መከላከያ ይላካል። ማውደም ከተጀመረ መተኮስ ይጀመራል” ሲሉ ትዊት አድርገዋል።
ትዊተር “ማውደም ከተጀመረ መተኮስ ይጀመራል” የሚለውን ትዊት ነው በትራምፕ ገጽ እንዳይታይ ያደረገው።
Via:- BBC

የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ የቀነሱ እና ከሥራ ያሰናበቱ 14 ሆቴሎች ተለዩ!
የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ ያልከፈሉ፣ የቀነሱ እና ሠራተኞቻቸውን ከሥራ ያሰናበቱ 14 ሆቴሎች መለየታቸውን የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር የኮምኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እጅጉ እንደሻው ትናንት እንደገለጹት ፤መንግስት የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን ለመደገፍ ድጎማ ቢያደርግም አንዳንድ ሆቴሎች ሠራተኞቻቸውን እያሰናበቱ እና ደመወዛቸውን እያስቀሩና እየቀነሱ ነው፡፡ ሆቴሎችን መለየት የተቻለው ማህበሩ በመሰረተው የቴሌግራም የመገናኛ ዘዴ መሆኑን ጠቁመው፤ ሠራተኞች የደረሰባቸውን ችግርና ሥራ የለቀቁበትን ደብዳቤ ይዘው መጥተዋል፡፡ማህበሩ የተገኙ የደብዳቤ ማስረጃዎችን በመያዝ ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን ማሳወቁን አመልክተዋል፡፡ ‹‹ተበድረን ለሠራተኛ አንከፍልም፤ መንግስት እንደሚያደርግ ያድርጋችሁ›› ያሉ ሆቴሎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ እጅጉ፤ መንግስት ያወረደውን መመሪያና ድጎማ ተፈፃሚ የሚያደርጉ አሰራሮችን እንዲያመቻች አሳስበዋል፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ ➡️https://telegra.ph/Hotel-employees-05-30
Via ኢፕድ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ከሚያዋስኑ አገሮች ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ አካላት የሚጠብቃቸው የጤና ምርመራና ድንበር በመጣሳቸው ደግሞ የህግ ተጠያቂነት መሆኑን የክልሉ ግብረ ኃይል ጸሐፊና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ ሀምደኒል ገለጹ፡፡
ወረርሽኙን እንደ ትልቅ መሳሪያ በመጠቀም ጥቃት እንዳይኖርም እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
ኮሚሽነር መሀመድ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ድንበር ጥሶ የሚገባ አካል ምርመራ የሚደረግበት በሁለት መልኩ ነው፡፡ የመጀመሪያው ሰውዬው በኮሮና ቫይረስ መያዝ አለመያዙን ለማረጋገጥ የሚያስችል የጤና ምርመራ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ደንቡን በመጣሱ ተጠያቂ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ዋና ምክንያቱ የወረርሽኙ ጉዳይ እየከፋ በመምጣቱ ዋጋ እንዳያስከፍል ህጉን ጠበቅ ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡
እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ በግልጽ በህግ የተቀመጡ መግቢያ ኬላዎች አሉ፡፡ እነዚህም ሶስት ሲሆኑ፤ በተለይ ከሱዳን ጋር የሚያዋስኑ ናቸው፡፡ ይሁንና ዝግ በመሆናቸው በፌዴራል ፖሊስ የሚጠበቁ ናቸው፡፡ ከደቡብ ሱዳን ጋር ግን ህጋዊ የሆኑ ኬላዎች ስለሌሉ ሰዎች በአቋራጭ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን መንገዶች በሰው ኃይል ዝግ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ተንጠባጥቦ የሚመጣውን ሰርጎ ገብ ግን ጸረ ሽምቅ ኃይልና ሚሊሻ ስለተቋቋመ ጥበቃው የተጠናከረ በመሆኑ ተጠያቂ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ይገባሉ፤ በሰሩት የህግ ጥሰት ደግሞ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
Via EPA

በልደታ ክፍለ ከተማ ለእንቅስቃሴ ዝግ የሆነው አካባቢና በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ለሚገኙ 1000 ለአደጋ ተጋላጭ ነዋሪዎች ለ3 ወር የሚቆይ የምግብ አቅርቦት ተጀመረ።
የምግብ አቅርቦቱን የደገፈው ቢልጌትስ ፋውንዴሽን ነው።የምግብ አቅርቦቱን ያስጀመሩት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ ችግሮች ብዙዎች ችግር ውስጥ ሊወድቁ ስለሚችሉ ከመንግስት ድጋፍ ባለፈ እርስ በእርስ መረዳዳት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ደርሰናል ብለዋል።የምግብ አቅርቦቱ በየሁለት ቀኑ ለነዋሪዎቹ የሚከፋፈል ይሆናል።
Via Mayor Office

ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ (ከግንቦት 12-21/12 ዓ.ም) ከ25.4 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ የወጣላቸውና ግምታዊ ዋጋ ያልወጣላቸው የተለያዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ እቃዎች እና የጦር መሳሪያ በጉምሩክ ሠራተኞችና በፀረ-ኮንትሮባንድ ግብረ-ሃይል በጋራ በሰሩት ስራ በጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች ላይ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ ሆስፒታል በመገንባት ላይ የሚገኘው ኢትዮ-አሜሪካን ዶክተርስ ግሩፕ በኢትዮጵያ የCovid19 ን ስርጭት ለመግታት ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ባሰበሰው ገንዘብ ለጤና ሙያተኞች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን በ50,000 የአሜሪካን ዶላር ግዢ ፈጽሟል:: እርዳታው በቅርብ ቀን ተጏጉዞ አዲስ አበባ ይደርሳል::
Via Ambassador Fitsum Arega
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ambassador Fitsum Arega
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ አንዲት ሴት ከታጣቂ ሚሊሻ በተተኮሰባት ጥይት መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ።
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ ትናንት ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት አንዲት ሴት ከታጣቂ ሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት መገደሏን የመቀለ ከተማ ወንጀል መከላከልና ምርመራ ፅ/ቤት ለቢቢሲ ገልጿል።ከፖሊስ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በስም ያልተጠቀሱት ግለሰቦቹ በሥራ ክፍያ ሳይስማሙ ቀርተው አለመግባባታቸው ተባብሶ ታጣቂው ተኩሶ ገድሏታል። ታጣቂው በተኮሰባት ጥይት የተመታቸው ሴት፤ ህይወቷ ወዲያውኑ አልፏል ብሏል ፖሊስ። ታጣቂው ግድያውን ከፈፀመ በኋላ ራሱ ላይ በመተኮሱ ለጉዳት ተዳርጎ ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዱን እና በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ተደርጎለት በፖሊስ ጥበቃ ሥር ሆኖ ህክምና እየተከታተለ እንደሚገኝ ፅ/ቤቱ አስታውቋል።

👍1
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 95 ሰዎች ሲሆኑ ከአንድ ህንዳዊ በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው፣ በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(71) ሴት(24) ናቸው
➡️ዕድሜያቸው ከ15-80 የሆኑ
➡️30 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው
➡️4 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው
➡️61 የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው።
➡️ተጨማሪ 11 ሰዎች (2 ከትግራይ ክልል ፣ 9 ከአፋር ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 208 ደርሷል።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(56)፣ ከአፋር ክልል(1)፣ ከአማራ ክልል(5)፣ ከኦሮሚያ ክልል(22)፣ ከድሬዳዋ(2)፣ ከሶማሌ ክልል(3)፣ ከትግራይ ክልል(1)ና ከሀረሪ ክልል(3) በኮሮና የተያዙ በድምር 95 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,063 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 5 ደርሷል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን በሚመለከት ያወጣው መግለጫ የተሳሳተና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ብሏል የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ።
አምነስቲ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በመንግሥት ኃይሎች የሰብአዊ መብት ጥሰት አለ ብሏል።ይሁን አንጂ መግለጫው ሚዛናዊነት የጎደለውና የተሳሳተ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገልጸዋል። መግለጫው የአንድ ወገን መረጃን ብቻ በመያዝ ሚዛኑን ያልጠበቀና የተሳሳተ በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል ብለዋል።ሪፖርቱ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበና በተለይ ነፍጥ ያነገቡ ታጣቂዎች በተለያዩ አካባቢዎች በሕዝብና የመንግሥት ኃይሎች ላይ የሚፈፅሙትን ወንጀል መካዱንም አብራርተዋል።
ምንጭ: ኢዜአ

ዛሬ ከድሬዳዋ በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ በሀገር አቀፍ ሪፖርት ከተገለጹት ሁለቱ ሰዎች አንደኛው ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ሲሆን ሌላኛው በለይቶ ማቆያ የሚገኝ የጅቡቲ ተመላሽ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በሀረሪ ክልል በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ በሀገር አቀፍ ሪፖርት የተገለጹት ሶስቱም ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው እንዲሁም የውጪ ጉዞ ታሪክም የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል።በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር 8 ደርሷል። ዝርዝር ሪፖርቱን ከላይ ይመልከቱ ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ እና ጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደርች በሰፈራና ስግሰጋ ለማስፈር ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መዘጋጀቱን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ገለጿል።
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa