YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በደቡብ ኮሪያ ወረርሽኙ አገርሽቷል ተባለ!

በደቡብ ኮሪያዋ መዲና ሴውል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኙ ማገርሸቱን ተከትሎ ወደ ቀውስነት ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚችል ያላቸውን ስጋት የጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል።በባለፉት ሃያ አራት ሰአታት ውስጥ 79 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ይህም ቁጥር በአገሪቱ በሁለት ወራት ውስጥ ከተያዙት መካከል ከፍተኛ ነው ተብሏል።በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎችም መነሻ ነው የተባለው በሃገሪቷ ምዕራብ ግዛት የሚገኝ ቡቸን የተባለ ትልቅ የዕቃዎች ማከፋፈያ ማዕክል ነው። በማዕከሉ ውስጥ የሚሰሩ በርካታ ሰራተኞች ጫማና አልባሳትም ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኝቷል ተብሏል።የጤና ባለሙያዎችም አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ካላቸው አካባቢዎች አቅራቢያ መገኘታቸው ስጋትን ፈጥሯባቸዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር ለኤካ ኮተቤ እና ለጳውሎስ ሆስፒታሎች ከ800 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የገዛቸውን የህክምና ቁሳቁስ እና ታብሌቶችን ድጋፍ አደረገ።

ከ800 በላይ የአውሮፕላን አብራሪዎችን በአባልነት የያዘው የአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር (ኢትዮጵያ) ከተመሠረተበት 1965 ዓም ጀምሮ ስለበረራ ደህንነት እንዲሁም ስለአብራሪዎች ሙያዊ ብቃት አና መብት ላይ እየሰራ ያለ ሙያዊ ማህበር ነው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን ጦር እና ኢትዮጵያ ታጣቂዎች መካከል “አልቃድሪፍ” አካባቢ ከባድ ጦርነት መጀመሩን ሮይተርስ ዘገበ!!

ባለፉት 3 ቀናት በሱዳን ጦር እና ኢትዮጵያ ታጣቂዎች መካከል ድንበር ላይ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል አሚር መሃመድ አል ሃሰን አስታወቁ።ቃል አቀባዩ ይህን የተናገሩት በሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ነው።ለታጣቂዎቹ የኢትዮጵያ ጦር ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።በዚህም ውጊያ አንድ የሱዳን ጦር መኮንን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው ታውቋል። ውጊያው እየተካሄደ ያለው አልቃድሪፍ ተብሎ በሚጠራው ድንበራማ አካባቢ ነው።አካባቢው ከዚህ ቀደም በእርሻ ቦታ ምክንያት ተደጋጋሚ ግጭቶች ይስተዋሉበታል።

Via @tesfaget55
@YeneTube @FikerAssefa
በአዳማ ከተማ ክልከላዎችን የተላለፉ 766 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በአዳማ ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የክልከላ ድንጋጌዎችን ተላልፈው ተገኝተዋል የተባሉ 766 ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስል ማዋሉን አስታወቀ።በከተማው የኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል አባልና የአዳማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለኢዜአ እንደገለፁት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የአዋጁን ክልከላዎች ተላልፈው በተለያዩ አካባቢዎች ተሰባስበው እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሳያደርጉ በመገኘታቸው ነው። ግለሰቦቹ የተገኙት በቤተ እምነቶች ፣ በጫት ቤት፣ በመጠጥ ቤት፣ በፑል ቤቶች፣ በትራንስፖርትና ገበያ አካባቢዎች መሆኑን አመልክተዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ዘግናኝ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመዋል ሲል አመለከተ።

ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሰፋ ያለ መግለጫውን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ፀጥታን ለማስከበር በተካሄዱ ዘመቻዎች አስገድዶ መድፈር፣ የዘፈቀደ እስር፣ ከሕግ አግባብ ውጪ ርምጃዎች መውሰድ እና ቤቶች ማቃጠል ተፈጽሟል ብሏል። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት እንደሚለው፤ በተጠቀሱት ሁለት ክልሎች ውስጥ በዚህ ዘመቻ ቢያንስ 140 ሰዎች ተገድለዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል ብሏል።

ከጎርጎሪዮሳዊው 2018 ታኅሣስ እስከ 2019 ታኅሣስ ወር ያሉትን ጊዜያት በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ይዞታውን በቃኘበት ዘገባው ምንም እንኳን ሺህዎችን ከእስር የመልቀቅ፣ ሲቪክና ፖለቲካዊ ምሕዳሩን የማስፋት እንዲሁም ጨቋኝ ሕጎችን የማሻሻል ሂደቶች ቢኖሩም የፀጥታ ኃይሎች አስከፊ የሰብያዊ መብቶች ጥሰት መፈጸማቸውን አመልክቷል። የድርጅቱ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪቃ ዳይሬክተር ዲፕሮስ ሙቻና፤ «የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የሀገሪቱን ጥቁር የሰብዓዊ መብቶች ሪከርድ ለማሻሻል ትርጉም ያላቸው መሻሻሎችን ቢያደርጉም የፀጥታ ኃይላት ያለምንም ተጠያቂነት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲፈጽሙ መፍቀዱ ተቀባይነት የለውም።» ብለዋል።

አክለውም፤ ምርጫ በቅርብ ርቀት በሚታሰብበት በዚህ ወቅትም መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሥራቸውን በሕግ አግባብና ያለአድልዎ እንዲያከናውኑ ለማድረግ አፋጣኝ ርምጃ ካልወሰደ በቀር ጥቃትና ወከባው ተባብሶ ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን እንደሚችልም አሳስበዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ውስጥ ተጨማሪ 137 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5015 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት (137) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት (968) ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 8ኛው ሞት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመዝግቧል!

በተጓዳኝ ህመም ህክምና ላይ የነበሩ የ62 አመት ወንድ የምርመራ ናሙና ተወስዶ ውጤቱ ሳይታወቅ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ቫይረሱ እንደነበረባቸው ተረጋግጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 137 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ በፆታ ወንድ(86) ሴት(51) ናቸው

➡️ዕድሜያቸው ከ4-75 የሆኑ

➡️20 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️8 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️109 የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው።

➡️ተጨማሪ 6 ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 197 ደርሷል።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(109)፣ ከአፋር ክልል(1)፣ ከአማራ ክልል(17)፣ ከኦሮሚያ ክልል( 8)፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል(2) በኮሮና የተያዙ በድምር 137 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 968 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል አምስት መገናኛ ብዙሃንን ሐሰተኛ ዘገባዎችን ዘግበዋል በሚል ከሰሰ።

የክልሉ የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በጻፈው ደብዳቤ እንዳመለከተው አራት የፌደራል መንግስት ንብረት የሆኑ እና አንድ የክልል መገናኛ ብዙሃንን ከሷል። ተከሳሽ መገናኛ ብዙሃኖቹም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እና የኣማራ መገናኛ ብዙሃን ናቸው። እነዚህ መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል ያልተፈጠረ ነገር በሀሰት ዘገባዎችን እየሰሩ በመሆኑ ባለስልጣኑ ጉዳዩን መርምሮ እርምጃ እንዲወስድ በክልሉ መንግስት ተጠይቋል።

ምንጭ:አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እያደረሱ ነው – አምንስቲ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ተሟጋች ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እያደረሱ መሆኑን የሚያጋልጡ  ማስረጃዎች ይፋ አደረገ። የሰብአዊ መብት ጥሰቶቹ በተለይም በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የከፉ መሆናቸውን ተቋሙ አስታውቋል።አምንስቲ ይህን ያስታወቀው በኢትዮጵያ ለአንድ አመት የደረገውን የሰብአዊ መብቶች ክትትል በተመለከተ ዛሬ አርብ ግንቦት 21፤ 2012 ባወጣው ሪፖርት ነው። ሰባ ሁለት ገጾች ያለው ሪፖርቱ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን እስከ ካለፈው ታህሳስ ወር ድረስ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ገምግሟል።ተቋሙ ለሪፖርቱ ጥንቅር ሰማንያ ግለሰቦችን ከአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ሃርቀሎ፣ ባላምቤል፣ አዶላ፣ ሻኪሶ እና ሃዋሳ ከተሞች በቃለ መጠየቅ ማሳተፉን ገልጿል። ከሰማንያዎቹ ውስጥ አብዛኞቹ “በፀጥታ ኃይሎች ጥቃት የደረሰባቸው ናቸው” ተብሏል። ጥቃት ከተፈጸመባቸው ውስጥ ሃያ አንዱ ሴቶች መሆናቸውን ያመለክተው ሪፖርቱ ከእነርሱ ውስጥም አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና መምህራን እንደሚገኙበት ጠቁሟል። 

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብልሹ አሰራር የተዘፈቀ እና የአገሪቱን ኢኮኖሚ ያሽመደመደ ተቋም እንደሆነ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ልዩ ስብሰባ የልዩ የመንግስት እዳ ሰነድ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ረቂቅ አዋጁን ለዝርዝር እይታ ለገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመራበት ወቅት ነው፡፡የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ መሀመድ አብዱሽ በዚህ ወቅት እንዳሉት ባንኩ ከ40 በመቶ በላይ የብድር ብልሽት ያለበት እና የአገሪቱን ክፍለ ኢኮኖሚ ያሽመደመደ ተቋም ነው፡፡በመሆኑንም ባንኩ የካፒታል ማሻሻያ ይደረግለት የሚለውን ሃሳብ የሚመራለት ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዮን በትኩረት ሊመለከተው ይገባል ብለዋል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 2 ወራት ዉስጥ 2ሺህ 500 የካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ታሽገዋል ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ ባለፉት 2 ወራት ውስጥ 20ሺህ የሚሆኑ የካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረጉን አስታዉቋል፡፡በተደረገዉ ክትትልና ቁጥጥር የንጽህና ጉድለት የታየባቸዉ 10ሺህ ቋማት ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል ተብሏል፡፡ከነዚህም ዉስጥ 2ሺህ 500 የሚሆኑት እንዲታሸጉ መደረጋቸዉ ተነግሯል፡፡

Via Ahadu Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ጎረቤት ሀገር ኬንያ ባለፉት 24 ሰዓታት 4 ሰዎች ሲሞቱባት 127 አዲስ የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች።

ይህንንም ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 62 ሲደርስ የተያዙት ደግሞ 1745 ደርሰዋል፣ በአንጻሩ 438 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ: የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
አጣሪ ጉባኤው ምርጫን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ የውሳኔ ሀሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቀረበ!

የኢፌዴሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ ምርጫን በወቅቱ ማካሄድ ባለመቻሉ እንዲሁም የምክር ቤቶቹንና እና የአስፈፃሚ አካላትን የስራ ዘመን አስመልክቶ የቀረበለትን የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ምላሽ ሰጠ።ጉባኤው ከምክር ቤቱ ጥያቄው ከቀረበለት ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩን ከተለያዩ አቅጣጫዎች አንፃር መመርመሩን ገልጿል።

ውሳኔ ወይም የውሳኔ ሀሳብ ከመስጠቱ በፊት በአዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀፅ 9 መሰረት በሕገ መንግስት የትምህርት ዘርፍ የተሰማሩና ልምዱ ያላቸውን ባለሙያዎች፣ ሕገ መንግስቱን በማርቀቅ ሂደት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳትፎ ያላቸውን ግለሰቦች፣ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን ተቋማት፡ የኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድን ሀሳብ ለሕብረተሰቡ ግልፅ በሆነ መንገድ በተለያዩ ሚዲያዎች በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት በማስተላለፍ በጉባኤውም ሆነ በሀገሪቱ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የመስማት ሂደት ማከናወኑን ነው ያመለከተው።

ከመስማት ሂደቱ ጎን ለጎን ጉባኤው ባደረገው ጥሪ መሰረት በፅሁፍ የቀረቡ በርካታ ሀሳቦችን እንደተመለከተ አስታውቋል።በተጨማሪም ሀሳብ ለማጎልበት የሚረዱ ጥናቶችን በጉባኤው ፅህፈት ቤት ባለሙያዎች ያስጠና ሲሆን፥ እነዚህን መሰረት አድርጎ ጉባኤው ባስቀመጣቸው ዋና ዋና ጭብጦች ላይ ለሁለት ሳምንታት ያህል ተከታታይና ጥልቅ የሆነ ውይይት በማድረግ ምላሽ በማዘጋጀት የውሳኔ ሀሳቡን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረቡን ገልጿል።

ጉባኤው በምላሹ ላይ ሕገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ የፍርድ ቤት ክርክርን አስታከው የመጡ ሕገ መንግስታዊ ሂደቶችን ብቻ ሳይሆን ሕገ መንግስታዊ የትርጉም ስርአትን ሊያሰፉ የሚችሉ አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትንተናና ብይን በመስጠት ጉባኤውም ሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ የተጣለባቸውን የሕገ መንግስት ትርጉም የማሳደግ ሀላፊነትንም ከግምት ውስጥ አስገብቻለሁ ብሏል።ጉዳዩ ለጉባኤው ቀርቦ ፊት ለፊትም ይሁን በፅሁፍ የባለሙያዎችን አስተያየት ለመሰብሰብ በመወሰን ጥሪ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በተለያየ መንገድ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ሙያዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል ያላቸውን አካላት አመስግኗል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በግላቸው ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ በሚከተለው መልኩ እንዲተገበር ተወስኗል፡፡

1. በክፍያ ለሚሰጥ ትምህርት በሙሉ ተቋሙ በሚከተለው የክፍያ ስርዓት መሰረት ውሳኔው ከተላለፈ ቀን ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ስርዓት እንዲቀጥል እስከሚወሰንበት ቀን ድረስ የሚቆይ ተማሪዎች ሊከፍሉ ከሚጠበቅባቸው በሁሉም የትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎች፣ የትምህርት ደረጃዎችና መስኮች ቢያንስ የ25% ቅናሽ እንዲደረግ፣ ይህም ማለት አንድ ተማሪ ይጠበቅበት ከነበረው ክፍያ ከ75% በላይ መክፈል እንደማይገባው፤

2. የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይህን ውሳኔና እንደአስፈላጊነቱም በኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ የተላለፈውን ውሳኔ ጨምሮ ተቋማዊ በማድረግ ከተቋሙ ተማሪዎችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት በመፍጠር እንዲተገበር

3. የመጀመሪያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ) ትምህርትን በሚመለከት
3.1. በየቤታቸው ለሚገኙ ተማሪዎች የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም ተገቢውን ድጋፍ (follow up and academic advisership) በመስጠት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ (Engaging students to learning activities) አስፈሊጊው እገዛ እየተደረገ በማንኛውም የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ በመማር ላይ ላሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምንም አይነት ምዘና(ፈተና) መስጠት፣ ከሴሚስተር ወደ ሴሚስተር ወይም ከዓመት ወደ ዓመት ማዛወርና ማስመረቅ የማይቻል መሆኑን፤
3.2. ተማሪዎች ወደ ተለመደው የመማር ማስተማር ሂደት ሲመለሱ በቂና ምክንያታዊ የዝግጅት ጊዜ፣ የፊት ለፊት የማካካሻ ትምህርትና ምዘና ወይም ፈተና ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በመስጠት የጀመሩትን ትምህርት እንዲያጠናቅቁ እንዲደረግ፤

4. የሁለተኛና የሶስተኛ ዲግሪ (ድህረ ምረቃ) ተማሪዎች በኦንላይን የመማሪያ ዘዴ በቴክሎጂ የታገዘ በቂ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው ትምረታቸውን እንዲቀጥሉ ምዘና(ፈተና) እንዲሰጣቸው፣ የድግሪ ማሟያ ጽሑፍ፣ ፕሮጄክት፣ ምርምር ሥራ ምዘና እንዲደረግ፣ ከሴሚስተር ወደ ሴሚስተር ወይም ከዓመት ወደ ዓመት እንዲዛወሩ እና እንዲመረቁ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተወሰነው መሰረት እንዲፈጸም አሳስባለሁ፡፡

ምንጭ፡ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ በተደረጉ የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራዎች 342 ሰዎች የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ በተደረጉ የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራዎች ስድስት መቶ ስልሳ አንድ(661) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ከነዚህም ውስጥ 342 ሰዎች የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡በአዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ 109 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ ፦

አዲስ ከተማ 21
ልደታ 4

ጉለሌ 42

ኮልፌ ቀራንዮ 19

ቦሌ 1

የካ 5

ንፋስ ስልክ ላፍቶ 1

ቂርቆስ 3

አቃቂ ቃሊቲ 3 ሲሆኑ አድራሻቸው በማጣራት ላይ ያለ 10 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት የታገዙ ጸጥታ ሃይሎች በገዳሪፍ በኩል ድንበር ተሻግረው 1 የጦር መኮንን እና 1 ሕጻን ገድለውብኛል ስትል ሱዳን የኢትዮጵያን ጦር ሃይልን እንደከሰሰች ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡ 6 ወታደሮች እና 3 ንጹሃንም ቆስለዋል፡፡ ግጭቱ የተፈጠረው የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ከአጥባራ ወንዝ ውሃ ሲቀዱ ሲሉ በመከልከላቸው ነው፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
በምሥራቅ ወለጋ ከ97 ሚሊዮን የሚበልጥ የቡና ችግኝ ለተከላ ተዘጋጀ!

በምሥራቅ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከል ከ97 ሚሊዮን የሚበልጥ የቡና ችግኝ ተዘጋጅቶ እንክብካቤ እየተደረገለት መሆኑን የዞኑ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ።ችግኙ የተዘጋጀው በዞኑ 17 ወረዳዎች በሚገኙ የመንግሥትና ግል የቡና ችግኝ ጣቢያዎች መሆኑን በጽህፈት ቤቱ የቡና ልማት ባለሙያ አቶ ነገሮ አበሹ ተናግረዋል።“የቡና ችግኝ በሽታን ለመቋቋም የሚችልና ብዙ ምርት ሊሰጥ የሚችል ነው ” ያሉት ባለሙያው የዞኑ አርሶ አደሮች 91 ሚሊዮን 446 ሺህ 753 የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች መሰናዳታቸውን አመልክተዋል፡፡ለተከላ የተዘጋጀው የቡና ችግኝ 17 ሺህ 803 ሄክታር መሬት ላይ የሚሸፍን ነው ብለዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa