YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የትግራይ ሕዝብ "ለነጻነት እና እኩልነት የሚያደርገውን ትግል"
እንደሚደግፍ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ከተማ አንድ ነጭ የከተማው ፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድ የተባለን የ46 ዓመት ጥቁር አሜሪካዊ አንገቱ ላይ በመንበርከክ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ገዳዩን ፖሊስ ጨምሮ አራት ፖሊሶች ከስራ መታገዳቸው ተነግሯል፡፡

Via Asham TV
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
በኬንያው ደዳብ የስደተኞች መጠለያ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ስድስት ደርሷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር የኬንያ ቢሮ ቃልአቀባይ ድርጅታቸው የቫይረሱን መስፋፋት ለመቆጣጠር ከኬንያ መንግሥት ጋር እየሠራ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ማንዴራ ግዛት ውስጥ ባለው ደዳብ ሠፈር ተጠልለው የሚገኙት ስደተኞች ግን ኑሮ እንደከበደባቸው ይናገራሉ።

Via:- VOA
@Yenetube @Fikerassefa
ህገወጥ የመሬት ወረራ ችግር ተጋርጦብኛል አለ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ በወረራው የተሰማሩ ህገ-ወጦችን ተጠያቂ የማድረግ ስራም ጀምሬያለው ብሏል፡፡በግለሰቦች፤ በህገወጥ ደላሎች እና በእምነት ተቋማት ስም በህገ-ወጥ መልኩ በክፍለ ከተማው በከፍተኛ ሁኔታ የመሬት ወረራ ሲፈፀም መቆየቱን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍቃዱ ካሳሁን ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡እንደርሳቸው ገለፃም ክፈለ ከተማው ይህንን ህገወጥ ድርጊት ለመከላከል በቅድሚያ የውስጥ ችግሩን በማጥራት መጀመሩን እና በዚህም በድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮችን፤ ባለሙያዎችን እና ደላሎችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረጉን ለአሀዱ አስታውቀዋል፡፡አቶ ፍቃዱ በህገ ወጥ የመሬት ወረራ ድርጊት የተሳተፉትን ህገወጦች በህግ ተጠያቂ ከማድረግ ባለፍ በህገወጥ መልኩ የተወረሩ መሬቶችን የማስመለስ ተግባር መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ:አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አንዲት የህክምና ተማሪ በላብራቶሪ ከፍል ውስጥ ሞታ ተገኘች

የአዳማ/ ናዝሬት ተወላጅ የሆነችው የ27 አመቷ የድህረ ምረቃ ተማሪ ምርምር በምታደርግበት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ትምህርት ላብራቶሪ ክፍል ውስጥ ሞታ እንደተገኘች ፊደል ፖስት ከሆስፒታሉ የየስራ ሀላፊዎች አረጋግጧል።

ሐይማኖት በለው የተባለችው ይህች ወጣት የድህረ ምረቃ ትምህርቷን ለማጠናቀቅ ባቀረበቸው ጥናት ላይ በላብራቶሪ ውስጥ ጥናት ላይ አንደነበረችም ታውቋል።

ትናንት ግንቦት 18,2012 አመሻሹ ላይ በላብራቶሪ ክፍሉ ውስጥ ሞታ እንደተገኘች የተገለፀ ሲሆን ፖሊስ አስከሬኗን ወስዶ ከተማሪዋ ሞት ጀርባ ማን እንዳለ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ ነው ።

ሆስፒታሉ “ፓሊስ ምርመራ ላይ ስለሆነ ” በማለት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ሀይማኖት የመጀመርያ ዲግሪዋን በፋርማሲ ትምህርት ከሚዛን ቴፒ ያገኘች ሲሆን በዛው ዩንቨርስቲ ረዳት አስተማሪ ሆናም ሰርታ ነበር።

Via:- fidelpost.com
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ በቀን 180 ናሙናዎችን መመርመር የሚያስችል የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማሽን ስራ ጀመረ!

በክልሉ ስራ የጀመረው የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማሽን በቀን እስከ 180 ናሙናዎችን የመመርመር አቅም እንዳለው የጠቀሱት አቶ ካን ምርመራው ከተጀመረ ወዲህ ሰባት ናሙናዎች ተመርምረው ሁሉም ውጤታቸው ኔገቲቭ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
መጪውን የክረምት ወቅት ተከትሎ ሊከሰት የሚችልን የወባ ስርጭት ለመከላከል፣ የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካሎች ተጋላጭ ለሆኑ ክልሎች እየተከፋፈለ ነው ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እንደተናገው ከ889 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካሎች እያሠራጨ መሆኑን የኤጀንሲው የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭትና ተሽከርካሪ ስምሪት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሺፈራው በቀለ ተናግረዋል፡፡በመጪው የክረምት ወቅት በወባ ምክንያት የሚከሰተውን ህመምና ሞት ለመከላከል ከፍተኛ የወባ ስርጭት ባለባቸው የሀገሪቱ አከባቢዎች የጸረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ከትናንት ጀምሮ እተከፋፈለ ነው ተብሏል፡፡

በመጪው የክረምት ወቅት ከፍተኛ የወባ ስርጭት ያሰጋቸዋል በተባሉት በአማራ፣ ትግራይ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ፣ አፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች ኬሚካሉ እየተሰራጨ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም ከ 5 ሚሊዮን በላይ ለወባ በሽታ መከላከያ የሚውል የመኝታ አልጋ አጎበር እየተሰራጨ እንደሆንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በሌላ በኩል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሁለት ወራት ውስጥ ከ5.8 ቢሊየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸውን መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ማሰራጨቱን ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት በቀን18/09/2012 ዓ.ም የፌዴራል መረጃና ደህንነት ቢሮ ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን በባህርዳር ከተማ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንም ምርመራውን እያጣራ ይገኛል።

Via Amhara Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ለግንቦት 20 የድል መታሰቢያ በዓል ያስተላለፉት መልዕክት ።

@YeneTube @FikerAssefa
በ1937 ዓም በረራ ጀምሮ በ1996 የተቋረጠዉ የደብረ ማርቆስ የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት ዛሬ ጀመረ።

ምንጭ: አዊ ኮ/ን
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 30 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በፆታ ወንድ(22) ሴት(8) ናቸው

➡️ዕድሜያቸው ከ9-60 የሆኑ

➡️11 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️5 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️14ቱ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው።

➡️ተጨማሪ 14 ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 181 ደርሷል።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(15)፣ ከትግራይ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው (2)፣ ከአማራ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው(8)፣ ከሀረሪ ክልል (3)፣ ከኦሮሚያ ክልል(1)፣ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ (1) በኮሮና የተያዙ በድምር 30 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 731 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሰዎች ጉዳይ አሳስቦታል!

በርካቶች በኮቪድ-19 ከሚያዙባት ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ክልሉ የሚገቡ ዜጎች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከ800 በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውንና 8 ሰዎችም መሞታቸውን ዛሬ የወጣ መረጃ ያሳያል።እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያልተመዘገበበት የጋምቤላ ክልል ከዚህች ጎረቤት አገር ጋር በሰፊ ድንበር ይዋሰናል።ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በተገበረችው የአስቿኳይ ጊዜ አዋጅ በድንበር አካባቢ የሰዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል።ይሁን እንጂ የድንበሩን ስፋት ተገን በማድረግ በየዕለቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደቡብ ሱዳናዊያን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢዜአ ገልጿል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ለዲፕሎማቶች እና ለአለም አቀፍ ሰራተኞች የለይቶ ማቆያ ግዴታዎችን አላላች!

ኢትዮጵያ ከውጪ አገር የሚመለስ ማንኛውም መንገደኛ ለለይቶ ማቆያ በተመረጡ ሆቴሎች ለ 14 ቀን ተለይቶ እንዲቆይ ያስቀመጠችውን ግዴታ ለዲፕሎማቶች እንዲሁም በሀገሪቱ ለተመዘገቡ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሰራተኞች አላላች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተቋማቱ በላከው ደብዳቤ ከማክሰኞ ግንቦት 18፤ 2012 ጀምሮ የሚመለሱ ዲፕሎማቶች እና የየድርጅቶቹ ሰራተኞች በመኖሪያ ቤታቸው ወይም በየኤምባሲዎቻቸው ውስጥ ተለይተው መቆየት እንደሚችሉ ገልጿል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
Breaking!

ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እንዳለበት የሚያስገድድ መመሪያ ጸደቀ!

በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀሳቀስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እንዳለበት ግዴታ የሚጥል መመሪያ ጸደቀ።ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት ህይወት ለመታደግ ሲባል ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀሳቀስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማድረግ ግዴታ የሚጥል መመሪያ ጸደቋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንክ 17 ቢሊዮን ብር ፈቀደ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለግል ባንኮችና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፈቀደው 31 ቢሊዮን ብር በተጨማሪ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 17 ቢሊዮን ብር ፈቀደለት፡፡ንግድ ባንክ ተጨማሪ 17 ቢሊዮን ብር እንዲፈቀድለት በመንግሥት የተወሰነ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ይህንን ውሳኔ የሚያረጋግጥ መረጃ ሰጥተዋል፡፡በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሳምንቱ ከሚያካሂደው የግምጃ ቤት ጨረታ የሚያገኘውን ገቢ ወደ ንግድ ባንክ እንዲተላለፍ በማድረግ፣ ባንኩ ለሚፈለገው ዓላማ የሚያውለው እንደሆነ ታውቋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የግል ባንኮች በግምጃ ቤት ጨረታ እንዲሳተፉ የተፈቀደላቸው በመሆኑ፣ መንግሥት ከጨረታው የሚያገኘውን ገንዘብ ለተለያዩ አገልግሎቶች እየዋለ ነው፡፡ ከሰሞኑ ከሚካሄዱ ጨረታዎች ከሚገኘው ገቢ ደግሞ ንግድ ባንክ የተፈቀደለትን ገንዘብ ያገኛል፡፡መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ለግል ባንኮች 15 ቢሊዮን ብር፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 16 ቢሊዮን ብር፣ በአጠቃላይ 31 ቢሊዮን ብር በብድር እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተፈቀደው ሲታከል ደግሞ በጠቅላላው የአገሪቱ ባንኮች የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥማቸው ሲባል፣ እስካሁን 48 ቢሊዮን ብር በብድር ማግኘት ችለዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባት ቀን ወዲህ ሪከርድ የተባለ የአዲስ ኬዝ ቁጥር ተመዝግቦባታል። ባለፉት24 ሰዓታት ከወሰደችው 3077 ናሙናዎች 123 አዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች። 3 ተጨማሪ ሰዎችም ሞተዋል። እስካሁን በሀገሪቱ 1,471 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 55ቱ ሲሞቱ 408 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa