YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአፋር ክልል የዒድ አልፈጥር በዓል እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ ለ41 ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት ገለጸ።

@YeneTube @FikerAssefa
በኒውዮርክ ከሁለት ወር በኋላ በኮሮና ቫይረስ በአንድ ቀን የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች ሆኗል። ትናንት በግዛቲቷ የሞቱ ሰዎች 84 መሆናቸውን የኒውዮርክ ገዢ አንድሬው ኮሞ አሳውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በኮሮና ምክንያት በመተማ አርገው ወደ ምዕራብ ጎንደር እየገቡ ነው።

ከሱዳን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያዊያን በቫይረሱ ምክንያት ወደ ምዕራብ ጎንደር እየገቡ መሆናቸው ታውቋል። ከፍተኛ የሰው ቁጥር በመግባቱ በአካባቢው ያሉት የጤና ተቋማት ዜጎቹን በማቆያ ውስጥ ለ14 ቀናት ለማቆየት አቅማቸው አልፈቀደም ተብሏል።

ምንጭ: አሃዱ ሬዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ለ 1441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የኔቲዩብ በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡

የጤና ባለሙያዎችን ምክር በመከተል የኮሮና ቫይረስን እንዲከላከሉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

@Yenetube @FikerAssefa
Forwarded from Delivery Hawassa
#ዴሊቨሪ_ሀዋሳ_እሁድን_በቤቶ_ይቆዩ

ከታች ከተዘረዘሩት ሆቴል ፣ ካፌ እና ሬስቶራንት እንዲሁም ሱፐር ማርኬቶች የሚፈልጉትን ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የሱፐር ማኬት እቃዎችን ቢያዙን በሀያ ደቂቃ ውስጥ ያሉበት ቦታ እናደርሳለ።

ኬር አውድ ኢ.ተ ሆቴል ሌዊ ሆቴል

ሮም 1960 #ሴፍ_ዌይ ሱፐር ማርኬት

ሌዊ ሆቴል ፒያሳ አሜሪካን በርገር

ታይም ካፌ ለንደን ካፌ

ሲዝን ሱፐር ማርኬት ሌዊ ሆቴል መንኃሪያ

ሴፍላንድ ካፌ ዶልቼ ቪታ

ሀበሻ ሆቴል ቡካ ባር እና ሬስቶራንት

ለማዘዝ ይደውሉ +251927797918
+251927797918

Join - t.me/deliveryhawassa
ዳርፉር የሰፈረው የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥምር ሰላም አስከባሪ ጦር ከሱዳን ሊወጣ ነው።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን የህክምና ባለሙያዎቿን ከጥቃት ለመጠበቅ የፖሊስ ኃይል ልታቋቁም መሆኗን ገለጸች።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መባባሱን ተከትሎ በጤና አጠባበቅ ሰራተኞቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የፖሊስ ሃይል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ነው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተናገረው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ከህክምና ባለሙያዎች ተወያይተዋል።

መንግስት ለህክምና ባለሙያዎች ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ያወጣል ብሏል መግለጫው ።

ባለፉት ሁለት ወራት በመላ አገሪቱ በጤና አጠባበቅ ሠራተኞች እና ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተፈጽመዋል ያለው የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ ነው።

ለአስርት አመታት በጦርነት እና እገዳ ውስጥ የነበረችው ሱዳን የጤና ስርዓቷም ደካማ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ምንጭ፦አልጀዚራ
@Yenetube @Fikerassefa
በምስራቅ ጎጃም እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፈው የተገኙ ከ5 ሺህ በላይ ግለሰቦች በገንዘብና እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ተገለጸ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን እና ሚዲያ አባል ኮማንደር ራሄል አብርሃም ለኢዜአ እንደገለፁት በሁሉም የዞኑ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የአዋጁን የክልከላ ድንጋጌ ለማስከበር ቁጥጥር ሲደረግ ቆይቷል።ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ በተካሄደው ቁጥጥር ድንጋጌውን ተላልፈው ሰዎችን በማሰባሰብ ተስዝካር፣ ሰርግ፣ ክርስትናና ማህበር የደገሱ ከሁለት ሺህ የሚበልጡ ግለሰቦች ተደርሶባቸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ተጨማሪ 88 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4048 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ስምንት (88) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አምስት መቶ ሰማንያ ሁለት (582) ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 88 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ወንድ(51) ሴት(37) ናቸው

➡️ዕድሜያቸው ከ8-75 የሆኑ

➡️13ኙ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው

➡️20ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው

➡️55ቱ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው

➡️ተጨማሪ 1 ሰው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 152 ደርሷል

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(73)፣ ከትግራይ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው ( 8)፣ ከሀረሪ ክልል(1)፣ ከኦሮሚያ ክልል (4)፣ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች (2) በኮሮና የተያዙ በድምር 88 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 582 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከጉምሩክ ኮሚሽን ቃሊቲ ቅርንጫፍ መጋዘን አምስት ተሽከርካሪዎች ተሰረቁ!

ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ቃሊቲ ቅርንጫፍ መጋዘን ተከማችተው ከሚገኙ ተሽከርካሪዎች መካከል፣ አምስት የተለያዩ ተሽከርካሪዎች መሰረቃቸውን የሪፖርተር ምንጮቼ ነግረውኛል ብሏል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች በገቢዎች ሚኒስቴርና በጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ በሚተዳደረገው መጋዘን ተከማችተው የነበሩ ሲሆን፣ የተሽከርካሪዎቹ መጥፋት ለኮሚሽኙ ሪፖርት የተደረገው የዛሬ ሁለት ሳምንት እሑድ ግንቦት 2 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሆነም ታውቋል፡፡

ምንም እንኳን የተሽከርካሪዎቹ ዋጋ በግልጽ ባይታወቅም ከመጋዘኑ የተሰረቁት ተሽከርካሪዎች አንድ ቶዮታ ላንድክሩዘር፣ ሁለት ዮቶታ ኮሮላ አውቶሞቢሎችና ሁለት ራቫ 4 ኮምፓክት ቶዮታ ተሽከርካሪዎች እንደሆኑ ታውቋል፡፡ የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ገለጻ (Specification)፣ የምርት ጊዜ፣ እንዲሁም በመጋዘኑ የነበራቸው ቆይታ ከወንጀሉ ምርመራ ጋር አብሮ እየተጣራ እንደሚገኝም ምንጮች አክለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ https://telegra.ph/Car-Robbery-05-24
በምዕራብ ጎንደር ዞን ሰራባ ግምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከሼህዲ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ፒክአፕ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ 230 የቱርክ ሽጉጥ ተያዘ።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን ይዛ በመሰወር የማስለቀቂያ 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ መያዟን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።ግለሰቧ ድርጊቱ ፈጽማለች የተባለው ግንቦት 10/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ በወረዳው ሙሴ ባንብ በተባለ ከተማ ከግለሰብ ቤት በሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ነው።የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አንተነህ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለፁት ግለሰቧ ከግብረአበሯ ጋር በመሆን ህፃኑን ይዛ በመሰወር ለህፃኑ ወላጅ 600 ሺህ ብር ከከፈሉ ልጃቸውን ልትመልስ እንደምትችል በስልክ ደውላ ታሳውቃለች።የወረዳው የፀጥታ አካል ህፃኑን ይዛ የሄደችበትን አካባቢ ፈጥኖ በማጣራት ባደረገው ጥብቅ ክትትልና አሰሳ ትናንት በወገራ ወረዳ ግራርጌ በተባለው የገጠር ቀበሌ መያዝ መቻሉን አስታውቀዋል።በአሁኑ ወቅት ህፃኑን ወላጆች እንዲረከቡ መደረጉንና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን በሰላም ተገላገለች!

በኮቪድ-19 ተይዛ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ኢትዮጵያዊት ነብሰ ጡር እናት በሰላም መገላገሏን ሆስፒታሉ አስታወቀ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በሆስፒታሉ ዛሬ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ ስጦታ አበርክተዋል። የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው እንደገለጹት በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ነብሰ ጡር እናት ከትናንት በስትያ ልጇን በቀዶ ህክምና በሰላም ተገላግላላች።"በአሁኑ ወቅትም ህጻኑና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ" ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ማገገሚያነት እያገለገለ ባለው በዚሁ ሆስፒታል ዛሬ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

Via ENA/ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲነሳ ተጠየቀ!

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ በኮድ ሁለት የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ፣ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር በመፍጠሩ እንዲነሳ ተጠየቀ።ጥያቄውን ያቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ለመከታተል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት የተቋቋመው መርማሪ ቦርድ ነው። መርማሪ ቦርዱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት የተሰጠውን የሚኒስትሮች ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ባለፈው ሳምንት በገመገመበት ወቅት፣ በግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብን በመሠረታዊነት የሚስማማበት ቢሆንም የተገፈለገውን ውጤት እንዳላስገኘ አመልክቷል።

ተጨማሪ ለማንበብ https://telegra.ph/board-complaints-on-State-on-private-vehicles-embargo-05-24
መንግስት በደምቢ ዶሎ በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ የደረሰበትን መረጃ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገለጸ!

ታግተው የነበሩ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ መረጃ በቅረቡ ለህዝቡ ይፋ እንደሚደረግ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎች መታገታቸው ይታወሳል።እነዚህን ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም በፌዴራል ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከአሃዱ ቲቬ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልነው ነው ያሉት ሃላፊው፤ ጉዳዩን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ መረጃውን ደረጃ በደረጃ መስጠት በሚገባ መልኩ ለመስጠት ቃል ብንገባም ሁኔታው ውስብስብ በመሆኑ ጊዜ ሊወስድ ችሏል ብለዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ https://telegra.ph/Missing-Dambidolo-University-students-Saga-05-24
አሜሪካ ከብራዚል ወደ ሀገሯ የሚደረግ ጉዞን አገደች፡፡

አሜሪካ የጉዞ እገዳዉን የጣለችዉ ብራዚል ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መመዝገባቸዉን ተከትሎ ነዉ ተብሏል፡፡

ብራዚል ከራሷ አሜሪካ በመቀጠል ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ያሉባት መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ አሜሪካ የጣለችዉ የጉዞ እገዳ የንግድ እንቅስቃሴን አይጨምርም ነዉ የተባለዉ፡፡

አሜሪካ ቀደም ሲልም ከቻይና፣ኢራንና ሌሎች የአዉሮፓ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳዎችን ማድረጓ ይታወቃል፡፡

እስካሁን ድረስ እየወጡ ባሉ መረጃዎች፣አሜሪካ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ ሲጠቁ 100 ሽህ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

ይህም በሀገር ደረጃ ቀዳሚዉ ቁጥር ሲሆን በብራዚል ደግሞ 363,211 በቫይረሱ ሲጠቁ 22,666 ደግሞ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

Via:- ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በሰኔ ወር መጀመርያ የእንቅስቃሴ ገደቦችን የምታላላው ደቡብ አፍሪካ መጪው ጊዜ ከቀድሞው የከፋ እንደሚሆንባት በፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በኩል ተናግራለች።

ይህን የተናገሩት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በተህዋሱ ከተያዙት 22 ሺህ ዜጎች ውስጥ አንድ ሦስተኛዎቹ ባለፈው ሳምንት ብቻ መያዛቸውን በገለጹበት ንግግራቸው ነው።
ያም ሆኖ አገራቸውን ላልተወሰነ ጊዜ ዘግተው መቀመጥ የሚቻል ነገር ባለመሆኑ አንዳንድ ገደቦችን ለማላላት ተገደናል ብለዋል።
ሲሪል ራማፈፎሳ ይህን የተናገሩት በጆሀንስበርግ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የወርቅ ማዕድን አውጪ ኩባንያ 164 ሠራተኞቹ ቫይረሱ ይዟቸዋል ማለቱን ተከትሎ ነው።
በደቡብ አፍሪካ በተህዋሱ የሟቾች ቁጥር 429 ደርሷል።

ደቡብ አፍሪካ በሰኔ ወር መግቢያ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የምሽት ሰዓት እላፊን ለማንሳትና የንግድ ተቋማት እንዲከፈቱ ለማድረግ ወስናለች።

በአልኮል መጠጦች ሽያጭ ላይ የተጣለው ገደብም እንደሚነሳ ነገር ግን በሲጋራ ሽያጭ ላይ የተጣለው ገደብ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
ፕሬዝዳንት ራማፎሳ በአገራቸው ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲያነሱ ጫና ሲደረግባቸው ቆይቷል። ይህን ከመረዳትም ነው “መጪው ጊዜ የከፋ እንደሚሆን ልነግራችሁ እወዳለሁ” ያሉት።

የዓለም ጥልቁ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ውስጥ የሚሰሩ 164 ሠራተኞች በቫይረሱ መያዛቸው በደቡብ አፍሪካ ድንጋጤን ፈጥሯል። የሚገርመው አብዛኞቹ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሠራተኞች የበሽታውን ምልክቶች አላሳዩም።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ደቡብ ኮርያ በተለያዩ አገሮች በማደጎ ለሚያድጉ ዜጎቿ ጭምብል ልትልክ እንደሆነ አስታውቃለች።

አገሪቷ 370,000 ጭምብሎች ወደተለያዩ አገሮች እንደምትልክ የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ትላንት ተናግረዋል። ከእነዚህ ጭምብሎች 60 በመቶው ወደ አሜሪካ ይላካሉ ተብሏል።
ከደቡብ ኮርያ በጉዲፈቻ ከተወሰዱ 167,000 ታዳጊዎች ሁለት ሦስተኛው የሚኖሩት አሜሪካ ነው።

በፈረንሳይ፣ ዴንማርክ፣ ስዊድን እና አውስትራሊያ የሚኖሩ ትውልደ ደቡብ ኮርያዊ ልጆችም አሉ።
አገሪቱ ከቻይና ቀጥሎ በኢሲያ በቫይረሱ ከተጠቁ አገሮች አንዷ ናት። ሆኖም ግን አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በርካታ ሰዎችን በመመርመር በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ችላለች።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa