በድንበር አካባቢ የሚደረገው የሠዎች ዝውውር አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር የኮሮና ተህዋሲ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ከፍተኛ ህሙማን ሊመዘገብ እንደሚችሉ የአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን ማህበራዊ ልማት መምሪያ አስታውቋል።
የክልሉ ባለስልጣናት እንዳሉት በአማካይ በቀን ከ100 እስከ 150 ሰዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ክልሉ ይገባሉ።ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከሚደረጉት ከነዚሁ ሰዎች መካከል በምርመራ ኮሮና ተህዋሲ የተገኘባቸው ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም።የመምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ክሽን ወልዴ እንደገለፁት ዞኑ ከጎረቤት ሱዳን 400 ኪሎ ሜትር ይዋሰናል::በዚህም በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ድንበር እያቋረጠ ወደ ዞኑ እንደሚገባ ገልፀዋል::ችግሩ ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ክሽን ዞኑን፣ ክልሉንና አገሪቱን ከሚመጣው አስከፊ ቀውስ ለመታደግ በየደርጃው ያለው አካል አፋጣኝ ትኩረትና ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል::በዘጠኝ አካባቢዎች ለይቶ ማቆያ ቦታዎች እንዳሉ ዘጠኝ መቶ 56 ሰዎች ተለይተው የ236 ሰዎች ናሙና ተወስዶ 12 ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል::
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa

ፕሬዘዳንት ካጋሜ ለመጀመሪያ ልጃቸው ታላቅ ሹመት ሰጡ
የካጋሜ ልጅ የሩዋንዳ የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።
የፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ልጅ ለሩዋንዳ የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል፡፡
የ 30 ዓመቱ ኢቫን ካጋሜ የወላጆቹ የመጀመሪያ ልጅ ነው። ፕሬዘዳንት ካጋሜ አራት ልጆች ያሏቸው ሲሆን ሶስት ወንዶችና አንድ ሴት ሲል አፍሪካን ነውስ ዘግቧል፡፡
ትምህርቱን በአሜሪካን ሀገር የተከታተለው ኢቫን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ ካደረጋቸው አራት አዳዲስ አባላት መካከል አንዱ በመሆን ተሹመዋል፡፡
Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

ከዚህ በኋላ ወደ ሌሎች ሃገራት ለመሄድ ምን ያስፈልጋል?
- ጣሊያን መንገደኞች አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጉዟቸውን ምክንያት የሚያስረዳ ቅጽ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ የሕዝብ ትራንስፖርትን ሳይጠቀሙ ለጤና ባለሥልጣናት እንዲያሳውቁ ይጠየቃሉ፤
- በፈረንሳይ አስገዳጅ ለይቶ ማቆየት የለም፤ ነገር ግን ወደ አገሪቷ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው የውጭ ዜጎች የተለየ የምስክር ወረቀት መያዝ አለባቸው፤
- አሜሪካ ለዓለም አቀፍ በረራ ክፍት ያደረገችው 13 አየር ማረፊያዎችን ብቻ ነው፤
- የካናዳ ሕጎች ደግሞ አየር መንገዶች ለመንገደኞች የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ ይገፋፋሉ፤
- የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው የውጭ አገር ዜጎች ጥብቅ የሆነ የመግቢያ ሕግ አላት፡፡
Via:- BBC

በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ100 ሺህ ማለፉ ተነግሯል።
ዛሬ [ቅዳሜ ጥዋት] አሃዞች እንደሚያሳዩት በአፍሪካ ባሉ አገራት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 103 ሺህ 875 ነው። 3ሺህ 184 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።
ደቡብ አፍሪካ ከ20ሺህ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በመያዝ ቁጥር አንድ ስትሆን፤ ግብጽ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ እና ናይረጄሪያ ሌሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚገኙባቸው አገራት ናቸው።
በቫይረሱ የተያዙ በርካታ ሰዎች የሚገኙባት ደቡብ አፍሪካ አሁንም በርካታ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋጋጡ ሰዎችን መመዝገቧን ቀጥላለች። በቫይረሱ ከተያዙ መካከል ደግሞ 600 የሚሆኑት የፖሊስ አባላት መሆናቸውን የአገሪቱ ፖሊስ ሚንስትር ተናግረዋል።
ደቡብ አፍሪካ ይህን ያክል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ያገኘችው ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝቧን ከመረመረች በኋላ ነው።
አሁን እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ፤ የእንቅስቃሴ ገደቦቹ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ከመርዳታቸው በተጨማሪ፤ በአገሪቱ ይመዘገቡ የነበሩ የወንጀል መጠኖችን እንዲቀንስ አድርጓል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የሜክሲኮ ኤምባሲ ክስ ሊመሰረትበት ነው!
ኤምባሲው ከሶስት ቀን በፊት ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች "አለም አቀፍ የድጋፍ ቀን" አጋርነቱን ገልፆ የፌስቡክ ገፁ ላይ መልእክት አስፍሮ ነበር። ይህን ተከትሎ "ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም፣ ትውልድን ከግብረሰዶም እንታደግ" በሚል ስም የተቋቋመው ማህበር በኤምባሲው ላይ ክስ እመሰርታለሁ ብሎ መረጃ አድርሶኛል።
"ይህ የኤምባሲው ፅሁፍ በሀገሪቱ ህግ ወንጀል ለሆነ ድርጊት ድጋፍ የሰጠ ነው፣ ስለዚህ በቅርብ ቀናት ክስ እንመሰርታለን" ያሉኝ የማህበሩ ፕሬዝደንት መምህር ደረጄ ነጋሽ ዘወይንዬ ናቸው።
Via Elias Meseret

በአዲስ ዘይቤ ዝግጅት ክፍል የተሰናዳ "በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሠራተኞች መብት ጥሰትን" የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ግንቦት 15፣ 2012 ዓ.ም በ9:00 ሰዓት በናሁ ቴሊቪዥን ይታያል ተብሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ከሱዳን የሚገቡ ሰዎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ለይቶ ማቆያ ለማስገባት እገዛ እንደሚፈልግ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳር አስታወቀ፡፡
የክልሉ መንግሥት ችግሩ ሀገራዊ በመሆኑ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር መፍትሔ ለመሥጠት እንደሚሠራ ገልጧል፡፡
ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሥራ ወደ ሱዳን ተሠማርተው የነበሩ የቀን ሠራተኞች ሥራ መጠናቀቁን እና ወረርሽኙ መስፋፋቱን ተከትሎ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡ በሱዳን የወረርሽኙ ስርጭት እየጨመረ ነው፡፡ አሁን ላይ ኢትዮጵያውያኑ የሚመለሱትም የቫይረሱ ስርጭት እንዳለባቸው ከታወቁ የገዳሪፍ ግዛት ዞኖች ነው፡፡ ዋና አስተዳዳሪው አቶ አደባባይ ሙሉጌታ ለአብመድ እንደተናገሩት ዞኑ በድንበር በኩል ስርጭቱን ለመከላከል በቻለው አቅም እየሠራ ነው፡፡ እስከ ትናንት ግንቦት 14/2012 ዓ.ም በመተማ ጉምሩክ ጣቢያ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ቅድመ ለይቶ ማቆያ ማጣሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡
526 ሰዎች አሁንም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ይገኛሉ፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያው ውስጥ ከሚገኙት መካከል 243 የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ14 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ግለሰብ ለሌላ ህክምና ሆስፒታል በሄደበት ጊዜ ምልክቱ ስለታየበት በተወሰደ ናሙና ነው በኮሮናቫይረስ እንደተያዘ የተረጋገጠው፡፡ይህንን ተከትሎ በድንበር በኩል የሚደረገውን እንቅስቃሴ መቆጣጠር ከዞኑ አቅም በላይ በመሆኑ የፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ነው ያሳወቀው።
ምንጭ: አብመድ

ዳርፉር ከዘመተው የአፍሪካ ኅብረት እና የተ.መ.ድ. ጥምር ሰላም አስከባሪ ኃይል (UNAMID) ወታደሮች መካከል ሰባቱ በኮሮና ሳይያዙ እንዳልቀረ አስታወቀ። ወታደሮቹ ምርመራ ተደርጎ ውጤት እየጠበቁ ነው። በሱዳን 3378 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ 137 ሞተዋል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በታሪክ ትልቅ የተባለውን የቀጣዩን ዓመት ከ470 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አዘጋጀ።
➡️ ከአምናው 83 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው።
➡️ 100 ቢሊየን ብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ብድር የሚገኝ ነው ተብሏል ።
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
➡️ ከአምናው 83 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው።
➡️ 100 ቢሊየን ብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ብድር የሚገኝ ነው ተብሏል ።
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ግብር ከፋዩን ያማከለ አስተያየት ሊደረግ እንደሚችል ተገለጸ!
የኮሮና በሽታ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ችግር በመመገንዘብ በቀጣይ ጊዜያት በጥናት ላይ የተመሰረተ እና ሁሉንም ግብር ከፋይ ያማከለ የግብር አስተያየት እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ ጋር በመተባበር 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉንም አመልክቷል።የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ግርማ ትናንትና የዓይነት ድጋፉ በተደረገበት ወቅት በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በኮሮና በሽታ ምክንያት የሚደርሰውን ጫና ለመቋቋም ቢሮው ከንግዱ ማህበረሰብ ጎን በመቆም አጋርነቱን ለመግለጽ ተዘጋጅቷል።በዚህ መሰረት በቀጣይ ጊዜያት በጥናት ላይ የተመረኮዘ እና ፍትሐዊ በሆነ መልኩ የከተማ አስተዳደሩንም ሆነ ነጋዴውን በማይጎዳ አሠራር የግብር አስተያያት ይደረጋል። እስከዚያው ድረስ ግን ግብር ከፋዩ ሥራውን ሳያቋርጥ በፈቃደኝነት ገቢውን የማሳወቅ ተግባሩን ማጠናከር ይኖርበታል ተብሏል።
Via ኢፕድ

የእናቶችና የህፃናት ጤና አገልግሎትን ጨምሮ በመደበኛ የህክምና አሰጣጥ ላይ መዘናጋት መፈጠሩን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታው ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በተፈጠረ ስጋት በሀገር ደረጃ የእናቶችና ህፃናት ጤና አጠባበቅን ጨምሮ ለመደበኛ የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው ትኩረት ቀንሷል።የእናቶችና ህፃናት ጤናን ጨምሮ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ መንግስት በአዲስ መልክ ስትራቴጂ በመንደፍ እየሰራ ነው ብለዋል።
Via ENA

#494
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3757 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ አንድ (61) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አራት መቶ ዘጠና አራት (494) ደርሷል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 61 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ወንድ(43) ሴት(18) ናቸው
➡️ዕድሜያቸው ከ15-70 የሆኑ
➡️11ኙ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው
➡️5ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው
➡️45ቱ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው
➡️ተጨማሪ 23 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 151 ደርሷል
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(48)፣ ከአማራ ክልል ደሴ (1)፣ አፋር ክልል ዱብቲ(3)፣ ከኦሮሚያ ክልል ቡራዩና ሰበታ (2) ፣ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ(7) በኮሮና የተያዙ በድምር 61 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል።

በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኙ ሃያ አምስት ወረዳዎች ውስጥ የወባ በሽታ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ተቋም ገለጸ።
የወባ በሽታው ካለፉት ሁለት ዓመታት ከፍ ባለሁኔታ በወረርሽኝ ደረጃ በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች መከሰቱን ለቢቢሲ የገለጹት የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ተቋም የወባ ክፍል ባለሙያ አቶ አማረ ደስታ ናቸው።"በዚህ ዓመት ወባ በክልሉ ከአምናውም ሆነ ከካቻምናው በበለጠ ጨምሯል" ያሉት ባለሙያው በተለይ በቋራ መተማ፣ ምሥራቅ ደምቢያ፣ ጎንደር ዙሪያ፣ ጃዊ፣ ባህርዳር ዙሪያ፣ ደብረ ኤልያስ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ራያ ቆቦ፣ ቃሉ እና አበርገሌን የመሳሰሉ ወረዳዎች በሽታው በጣም ከጨመረባቸው አካባቢዎች ጥቂቶቹ ናቸው ብለዋል።
ለወባ በሽታው መስፋፋት የተለያዩ ምክንያቶች እንዳሉ የተጠቀሰ ሲሆን በተለይ ቀደም ሲል በሽታውን ለመከላከል ይወሰዱ የነበሩ እርምጃዎች መላላታቸውና በሽታውን ለመከላከል ኅብረተሰቡ ያደርጋቸው የነበሩ ጥንቃቄዎች መቆመቀቸው እንደሆነ ተገልጿል።ከእነዚህ መካከልም "ወባ ጠፍቷል በሚል የአጎበር አጠቃቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ መቀነስ፣ ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን አለማጽዳት፣ የአየር ንብረት ለውጥና ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ የጤና ኬላዎች ትኩረት መቀነስ" ለወባ በሽታ ክስተት መጨመር በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።በክልሉ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘው የወባ ወረርሽኝን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የጤና ጥበቃ ሚንስቴር 260 ሺህ ኪሎ ጸረ ወባ ኬሚካል መላኩን አቶ አማራ ደስታ አስታውቀዋል።
Via BBC

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀምን በማጥበቅ ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል አለብን – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭት አኳያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ማጥበቅና ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም በተመለከተ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ከጊዜ ወደጊዜ ወጥነት ባለው መልኩ እየተሻሻለ ኮሮናቫይረስን እንዳይስፋፋ የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታየ በመሆኑና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ዜጎች ቫይረሱ እየተገኘባቸው መሆኑ የተሰጠውን ትኩረት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል።”በመሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያወጣቸውን ዝርዝር ደንቦች በትክክል እንዲተገበሩ በጥብቅ መከታተል ያስፈልጋል” ብለዋል።“በተለይ በትራንስፖርትና ሌሎች ዘርፎች ላይ የአዋጁን ደንቦች በሚገባ ለማስፈፀም እንዲያስችል ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ አዋጁን ማየት እንዳለብን ተመልክተናል” ሲሉ ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል።
ምንጭ:ኢዜአ

በመተከል ዞን ስር ባሉ ወረዳና ቀበሌዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተካሄደ ባለው የአሰሳ ቅኝት ዘመቻ እስካሁን ከ190 ሺ 500 በላይ ህዝቦች በቫይረሱ መከላከያ መንገዶች ዙሪያ ግንዛቤ መፈጠሩን የዞኑ ጤና ጥበቃ መምሪያ ገልጿል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፎአል፡፡በዚሁ መሠረት
➡️ ከ1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆን
➡️ ከ2008 - 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር በቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፎአል፡፡በሌላ በኩል የከተማዋን ገቢ ለማሻሻል ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያላቸውን አቅም በዝርዝር ፈተሸው ለከተማዋ ገቢ እድገት በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ዙሪያና አፈፃፀሙንም የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መንገድ ላይ ተወያይቷል።
የታክስ መሰረትን በማስፋትም በተለይም ማዘጋጃቤታዊ እና የከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅምና የአስራር በተሻለ መልክ በማደራጀት የ2013 ዓም በጀት በመካከለኛ ገቢ ምጣኔ መሰረት ተዘጋጅቶ ለውይይት እንዲቀርብ ተወስኗል።
Via Mayor Office

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች 62% የሚሆኑት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ!
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 62 ፐርሰንት የሚሆኑት ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡በአገሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 494 ሰዎች ውስጥ 304 ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ፣ በተለይ በልደታና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ይበልጥ መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡ከልደታ ክ/ከተማ 104 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱ ነው የተገለጸው፡፡የቫይረሱ ስርጭት በተስፋፋባቸው ክ/ከተሞች የእንቅስቃሴ እገዳ ሊደረግ እንደሚችል ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክ/ከተሞች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከክልሎች ደግሞ ከጋምቤላ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸውን ዶ/ር ሊያ ገልጸዋል፡፡
Via ETV