አስር የደቡብ ሱዳን ሚኒስትሮች በኮሮናቫይረስ ተያዙ!
አስር የደቡብ ሱዳን ሚኒስትሮች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገለፀ። የሃገሪቷ ማስታወቂያ ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዌይ ለቢቢሲ እንደገለፁት ከጤና ሚኒስትሩ ውጭ በስተቀር ሁሉም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ግብረ ኃይል አባላት በሙሉ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። ሆኖም ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል የሚለውን ሪፖርት አጣጥለውታል።የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻርና ባለቤታቸው በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቁ ሲሆን መከላከያ ሚኒስትሯም አንጀሊና ቴኒም በቫይረሱ ተይዘዋል።በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም ሚኒስትሮች በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሲሆን በሙሉ ጤንነትም ላይ ይገኛሉ ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ የባለስልጣናቱ ጠባቂዎችና ሠራተኞችም በኮሮናቫይረስ ተይዘው በለይቶ ማቆያ ውስጥም ይገኛሉ።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ ሰላትን በየቤቱ እንዲሰግድ አሳሰበ
ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ ሰላትን በየቤቱ መስገድ እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ።የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል።በመልእክታቸውም ህዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን የኢድ በዓል ሲያከብር የኮሮናቫይረስ የተከሰተበት ወቅት በመሆኑ በሽታው እንዳይሰራጭ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።በመሆኑም ሁሉም የኢድ ሰላትን በየቤታቸው ሆነው እንዲሰግዱ አሳስበዋል።በዓሉ ሲከበርም የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን እንዲሁም አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።
1 ሺህ 441ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ ዛሬ ካልታየች እሁድ ተከብሮ የሚውል መሆኑንም ገልጸዋል።የዘንድሮው የኢድ በዓል የሚከበረው መንግስት ለህዝበ ሙስሊሙ በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል የመስሪያ ቦታ ባስረከበ ማግስት መሆኑንም ጠቅሰዋል።በዚህም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ስም ለመንግስት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በመጨረሻም ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች "እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ" ብለዋል።
Via ENA

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ 1441ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን የጾም ወቅት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያሳየውን ጥንቃቄ በበዓሉም ወቅትም መድገም እንዳለበት ጠይቀዋል።የበዓሉን ግብይት ርቀትን በመጠበቅ፣ የፊት ጭምብል በማድረግና የእጅ ንጽህናን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ እንዲያከናውን አሳስበዋል።
በበዓሉ ዕለትም ከቤተሰብ ጋር ማክበር፣ የበሰሉ ምግቦችን መጠቀም እንዲሁም እርድን በተመለከተም ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ: ኢዜአ

ከህግ ውጭ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ከ13ሺ በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡
የገበያ አቅርቦት ክፍተቱን ለመሙላት ዩኒየኖችና ህብረት ስራ ማህበራት ምርት እያሰባሰቡ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል፡፡የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው የኮሮና ወረርሽኝን መከሰት ተከትሎ ያለ አግባብ ከተቀመጠው ህግ ውጭ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 13ሺ 515 የንግድ ተቋማትና ድርጅቶች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል፡
Via SNNPRs Government Communication Affairs Bureau

#429
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3645 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ (30) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አራት መቶ ሃያ ዘጠኝ (429) ደርሷል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 30 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ወንድ(26) ሴት(4) ናቸው
➡️ዕድሜያቸው ከ15-60 የሆኑ
➡️9ኙ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው
➡️17ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው
➡️4 የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው
➡️ተጨማሪ 5 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 128 ደርሷል
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(18)፣ ትግራይ ክልል (3)፣ አፋር ክልል(3)፣ ከኦሮሚያ ክልል (4) ፣ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች (2) በኮሮና የተያዙ በድምር 30 ሰዎች ናቸው።

የምስራቅና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በሦስት የተፈጥሮ አደጋዎች በእጅጉ እንደሚጠቁ ተነገረ!
የምስራቅና አፍሪካ ቀንድ ሀገራት በኮቪድ 19፣ በአንበጣ መንጋና በጎርፍ ክፉኛ እንደሚጠቁ ፎክስኒውስ ዘግቧል።ፎክሰ ኒውስ ዛሬ የዓለም አቀፉን የቀይ መስቀል ፌዴሬሽን የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በጎርፍ አደጋ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ሱማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳና ኡጋንዳ ክፉኛ እንደሚጠቁ ጠቁሟል።በተጠቀሱት ሀገራት በአደጋው ከ500 ሺሕ የሚበልጡ ዜጎች እንደተፈናቀሉና 300 የሚጠጉ ሰዎችም ለሕልፈተ ህይወት እንደተዳረጉ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ፌዴሬሽን አሳውቋል።እንደ ዘገባው ከሆነ የጎርፍ አደጋው ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ ለአንበጣ መንጋ መከሰትና መራባት ምክንያት እንደሚሆን ተቋሙ አሳውቋል።እነዚህም ተደራራቢ ችግሮች ወረርሸኖቹን ለመመከት የሚደረገውን ጥረት አዳጋች እንዳደረገውና በርካታ ሰዎችም ለረሃብ እንዳጋለጡ የተቋሙ የአፍሪካ ሪጅን ዳይሬክተር ዶክተር ሲሞን ሚሲሪ ተናግረዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ የስኳር ፕሮጀክቶችን ወደ ግል የማዘዋወር ስራ እንዲዘገይ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ፕሮጀክቶቹን ለማዘዋወር በሰኔ ጨረታ ይወጣል ተብሎ ነበር።የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ለኢዜአ እንዳሉት የኮሮና ወረርሽን በአገሪቷ በመከሰቱ ወደ ፋብሪካዎቹ በመሄድ የአካባቢ ጥናት እንዳይካሄድ እክል ፈጥሯል።
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሮጀክቶቹን ለማዘዋወር በሰኔ ጨረታ ይወጣል ተብሎ ነበር።የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ለኢዜአ እንዳሉት የኮሮና ወረርሽን በአገሪቷ በመከሰቱ ወደ ፋብሪካዎቹ በመሄድ የአካባቢ ጥናት እንዳይካሄድ እክል ፈጥሯል።
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢድ አልፈጥር በዓል ቀደም ብሎ አራት ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡ በማዕከላቱም ለእስልምና እምነት ተከታዮች የጾም መፍቻ የምግብ ስጦታዎችን አበርክተዋል፡፡ከጎበኟቸውም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1. በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት የተነሣ በኢትዮጵያ የሚገኙ እና ጥቃትን ሸሽተው ካመለጡ በኋላ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 100 የሚጠጉ የሶርያ ስደተኞች፣
2. ከቦሌ ማተሚያ ቤት በስተጀርባ የሚገኘው ካሊድ ነስር እና መሐመድ ዓሊ ቤት፡፡ ሁለቱ ወንድማማቾች በኮቪድ19 የተነሣ መተዳደሪያቸውን ላጡ ከ100 ለሚበልጡ መጠለያ አልባ እና ተጋላጭ ሰዎች ጊዜያዊ መጠለያን በተከራዩት ቤት አዘጋጅተዋል፣
3. አነስተኛ የገቢ መጠን ካላቸው ቤተሰቦች ለተገኙ እና ወላጆቻቸውን ላጡ ሕጻናት ድጋፍ የሚያደርገውን “ለለውጥ እንሥራ የድጋፍ ቡድን” የተሰኘ ዕድር፣
4. ባቡል ኸይር የተሰኘ ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ በሴቶች የተቋቋመ ድርጅት፡፡ የተቸገሩ ቤተሰቦችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚሠራ ሲሆን ለ500 ያህል የልዩ ልዩ እምነት ተከታዮች በቀን ሁለት ጊዜ ምገባን ያካሂዳል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁሉም ቡድኖች ስለሚያደርጉት የማኅበራዊ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ ድጋፍ ለሚደረግላቸውም ሰዎች መልካም የዒድ በዓል እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡
#PMOEthiopia

107 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ የፓኪስታን ኢንተርናሽናል አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡
አውሮፕላኑ የወደቀው በካራቺ ከተማ የመኖሪያ አካባቢ እንደሆነ ሬውተርስ ፅፏል፡፡የመከስከስ አደጋ የገጠመው አውሮፕላን 99 መንገደኞች እና ሰባት ሰራተኞቹን አሳፍሮ እንደነበር ሬውተር አስታውሷል፡፡በሕይወት ተራፊዎች ስለመገኘታቸው በእጅጉ አጠራጣሪ ነው ተብሏል፡፡ዋናው አብራሪ አውሮፕላኑ እክል እንደገጠመው ከመከስከሱ በፊት መልዕክት ማስተላለፉ ተሰምቷል፡፡ከአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በተጨማሪ ሲወድቅ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ላይም ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረ ተነግሯል፡፡በርካታ መኪኖችም መቃጠላቸው ታውቋል፡፡
Via Sheger FM

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ!
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ መልካ በሎ ወረዳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የ7 ሰዎች ህወት ማለፉ ተገለፀ፡፡እንደ ኤፍ.ቢ.ሲ ዘገባ አደጋው የደረሰው በወረዳው ቶኩማ ጃላላ ካብራ ቀበሌ ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ 7 ሰዓት አካባቢ ነው፡፡በአደጋውም ከሞቱት ሰባት ሰዎች በተጨማሪ በንብረት እና በቤት እንስሳቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ገልፀዋል፡፡በተፈጠረው ደራሽ ወንዝ ባስከተለው የተራራ መደርመስ ከሞቱት ሰዎች ውስጥም ስድስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውንም ከዘገባው ለማወቅ ተችሏል፡፡
Via Addis Maleda/FBC

በሀዋሳ ሁሉም አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች የፊት ማስክ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ተደረገ!
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ሁሉም አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎች ከመጪው ሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፊትና የአፍ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታ እንደሚኖርባቸው፤ ይህን መመሪያ በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይም ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡በመላው ሀገሪቱ እየጨመረ የሚገኘውን፤ እንዲሁም ወደ ከተማው የመግባት አዝማሚያ እያሳየ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ይረዳል የተባለው ይህ መመሪያ የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን ጨምሮ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ረዳቶችና ተሳፋሪዎችን፤ እንዲሁም የግልና የመንግስት መኪና አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎችን፤ ብሎም ባጃጅ እና የመሳሰሉትን አነስተኛ የትራንስፖት ዘርፎች የሚያካትት ሲሆን አሽከርካሪዎች ይህንን አውቀው በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የፊት ማስኮችን አድርገው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡
ምነጭ፡ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠ/ሚ አብይ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1441ኛ ዓመተ ሂጅራ ኢድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ ሞዛምቢክ ላይ በአየር እጥረት(asphyxiation) ታፍነው ከሞቱት 64 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጋር የነበሩና በህይወት የተረፉት አስራአንዱ በአውሮፓ ህብረትና በአለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ወደመጡበት አካባቢ በሰላም እንዲመለሱ ተደርጓል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በቀጣዮቹ ወራት አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳድሮችን ጨምሮ በ7 ክልሎች ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስጠነቀቀ።
ኮሚሽኑ እንዳለው ከመደበኛ ውጪ በሚጥል ከፍተኛ ዝናብ የሚከሰት የጎርፍ አደጋ ስጋት ካለንበት የበልግ ወቅት አልፎ እስከ መኸር ሊቀጥልም ይችላል።የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ እንዳሉን በዚህ በበልግ ወቅት በተለይ በቀጣይ ወራቶች ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡
ደቡብ ፣ሶማሌ፣ኦሮሚያ፣ አማራ ፣ትግራይ እና አፋር ፣ ሀረር ክልሎችን ጨምሮ ድሬደዋ እና አዲስ አበባ ከተሞች የጎርፍ አደጋ ስጋት አለባቸው ተብለው ከተለዩት መካከል ናቸው፡፡በያዝነው ግንቦት ወርም ተጨማሪ የጎርፍ አደጋ እንደሚኖር ፤በዚህም 21 ሺ 101 ሰዎች በጎርፍ እንደሚጠቁ እና ከዚህ ውስጥ 19 ሺ 30 ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳይም አቶ ደበበ ለኢትዮ FM ተናግረዋል፡፡ይህ የጎርፍ አደጋ ስጋት አሁን ካለንበት የበልግ ወቅት አልፎም እስከ መኸር ወራት ድረስም ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት አለ ብለዋል፡፡
በተቋሙ የጎርፍ አደጋ ግብረ ሀይል መኖሩንእና በብሄራዊም ሆነ በክልል ደረጃ መረጃዎችን የማሰባሰብ እንዲሁም ለህብረተሰቡ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ የመስጠቱ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ደበበ ገልጸዋል፡፡ጎርፍ ተከሰተ ማለት ተያይዞ የመሬት መንሸራተት እና የመሬት መሰንጠቅ ሊያጋጥም ስለሚችል በንቃት መከታል እና ስጋት ባለባቸው አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ከአካባቢው ማራቅ እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት፡፡
Via Ethio FM

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኙ!
የመደበኛ 24 ሰዓት መግለጫ ከተሰጠ በኋላ በደረሰ መረጃ፣ ከተደረገ 41 የላብራቶሪ ምርመራ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር 4 ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ተገኝተዋል። ግለሰቦቹ ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ29-97 የሆኑ ናቸው። ከአራቱ አንዱ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ሲሆን የተቀሩት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግኑኝነት ካላቸው እየተጣራ ይገኛል ተብሏል። በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 433 ደርሷል ።

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወያይቶ ውሳኔ ከሰጠባቸው አጀንዳዎች አንደኛው የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከልና የሕክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ ሠራተኞች የማበረታቻ አበል ክፍያ እንዲሰጥ የሚል ነበር።
ምክር ቤቱ በሰባት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎች ያሳለፈ ሲሆን የጤና ዘርፍ ሠራተኞች የማበረታቻ አበል ክፍያን ለመወሰን በተዘጋጀው መመሪያ ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ሠራተቹ ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠርና በሚደረገው ጥረት በግንባር ቀደምነት በሙያቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽዖ እጅግ የላቀ ከመሆኑም በላይ፤ የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ጤንነትና ሕይወት ለአደጋ በማጋለጥ የሚፈጸም ሙያዊ አስተዋጽዖ መሆኑን ምክር ቤቱ አምኖበታል። በመሆኑም የጤና ሚኒስቴር ባቀረበው ረቂቅ የማበረታቻ አበል ክፍያ መመሪያ ላይ ከተወያየ በኋላ ምክር ቤቱ ተቀብሎ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
-አሐዱ ቴሌቪዥን