YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማን ከሃላፊነት እንዳነሷቸው ነግረዋቸዋል፡፡

በምትካቸው አዳነች አቢቤን እንደሚተኩም ከ3 ቀናት በፊት ለታከለ ገልጸውላቸዋል አዳነች የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የፌደራሉ ገቢዎች ሚንስትር ናቸው፡፡

ታከለ ለምን ከሃላፊነት እንደተነሱ አልታወቀም፡፡

በሌላ ዜና፣ ኢሕዴግን #የማዋሃድ ሃሳብ የኦሕዴድ/ኦዴፓን ሥራ አስፈጻሚ #ለሁለት ከፍሎታል፡፡ ዛሬ የተሰበሰበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በዚሁ ጉዳይ ላይ ጭምር ይመክራል፡፡

ምንጭ :- አዲስ እስታንዳርድ - ትርጉም ዋዜማ
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን በዋና ከተማዋ ካርቱም የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ #ለሁለት_ሳምታት አራዝማለች።

የመራዘም ሐሳቡን ያመነጨው በመንግሥት ስር የሚገኘው የጤና ኮሚቴ የረመዳን ወር መጨረሻ መድረሱ ጋር ተያይዞ የኢድ አል ፈጥር በዓል መምጣቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ኮሚቴው በበዓሉ ወቅት የእንቅስቃሴ ገደብ ካልተጣለ በስተቀር የሚፈጠረውን መጨናነቅ መግታት አይቻልም የሚል ስጋት ማንሣቱን ራዲዮ ዳባንግ ገልጿል።

የጤና ኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር እና የሉዓላዊ ም/ቤቱ አባል ሲዲግ ታዊር ተጨማሪ መመሪያዎች ይፋ እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።

ሱዳን በአሁኑ ወቅት ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና አንድ (2,591) ዜጎቿ በኮቪድ-19 በሽታ የተያዙ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 105ቱ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

Via:- EBC /BBC
@Yenetube @Fikerassefa