YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሀገር አቋራጭ ስምሪት መስመሮች እና በአውቶቡሶች መውጫ ሰዓት ላይ ሽግሽግ ተደረገ!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማስፈጸም በወጣው የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚወጡ የሀገር አቋራጭ ስምሪት መስመሮች እና የአውቶቡሶች መውጫ ሰዓት ላይ ለውጥ መደረጉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀደም በየዕለቱ ስምሪት ይሰጥባቸው የነበሩ በአማካኝ 232 ልዩ ልዩ የሀገር አቋራጭ መስመሮችን በ60 በመቶ በመቀነስ በየዕለቱ በአማካኝ እስከ 82 መስመሮች ብቻ እንዲወጡ የሚደረግ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም አብዛኛዎቹ ተሸከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ከተርሚናሎች ይወጡ እንደነበረ ሚኒስቴሩ አስታውሶ ከዚህ በኋላ ግን ለተሻለ አፈፃፀም ያመች ዘንድ አውቶቡሶቹ በአራት ተከፍለው በተለያየ ሰዓት እንዲወጡ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡በዚሁ መሰረት በየዕለቱ 40 ከመቶ የሚሆኑት ተሸከርካሪዎች ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ላይ፤ 30 በመቶ የሚሆኑት ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ፤ 20 በመቶ የሚሆኑት ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ እና 10 በመቶ የሚሆኑት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ከሀገር አቋራጭ አውቶቡስ ተርሚናሎች እንደሚወጡ ተገልጿል፡፡

የመስመሮችን ብዛትና መነሻ ሰዓት ያካተተው እና ከላይ ተያይዞ የቀረበው የአገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ሳምንታዊ ዝርዝር ፕሮግራም ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከፕሮግራሙ ውጪ የማይስተናገዱ መሆኑን ገልጿል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!

➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

➡️21,317 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

➡️1080 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

➡️5203 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
📌ማስታወሻ

ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በተመለከተ;

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት የቤት ተሽከርካሪዎች (ኮድ-2) ፈረቃ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መተግበር እንደሚጀመር መነገሩ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ሲሆን ፥ የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ደግሞ መንቀሳቀስ የሚችሉት ማክሰኞ፣ ሀሙስ እና ቅዳሜ ብቻ ነው።

እሁድ እለት ደግሞ ሁሉም ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀስ ተፈቅዶላቸዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ከስራቸዉ ፀባይ አንፃር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፣ በደንቡ ወይም በአፈፃፀም መመሪያዉ የተገለፁት ጉዳዮች ላይ በቀጥታ የሚሳተፋ ሰዎች ከባለስልጣኑ በሚሰጣቸዉ ልዩ የይለፍ ፈቃድ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል።

Via:- Tsefay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የሰባት ወጣቶች ህይወት አለፈ!

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ዲቢቢሳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በዮሃንስ ቤተክርስቲያን ለጊዜው በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ሰባት ወጣቶች ሞተው መገኘታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ እንደገለጹት በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ሞተው ከተገኙት ሁሉም እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ሲሆኑ ከሟቾቹ መካከል አንዷ ሴት ናት።ትላንት ከሎሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ሟቾቹ በተገኙበት ወቅት የመብራት አገልግሎት የተቋረጠ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጀነሬተር እንደተለኮሰ ገልጸው አደጋው ከጄኔሬተሩ ጭስ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ እየተጣራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ከአደጋው ጋር በተያያዘ በአካባቢው 11 ግለሰቦች ተጠርጥረው መያዛቸውንና የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።የሟቾቹ አስከሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል መላኩን የገለጹት ኃላፊው በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ሁሉም ቤተ ዕምነቶች ዝግ መሆናቸውንና አማኞችም በቤታቸው አምልኮ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።ክስተቱ እንዴት እንደተፈጠረና ወጣቶቹ እንዴት ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሊገቡ እንደቻሉ እያጣራን ነው ያሉት ኮማንደሩ ጉዳዩን የሚያጣራ ግብረሃይል ተቋቁሞ የማጣራት ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ሁሉም ሰው ርቀቱን ጠብቆ በዓሉን ማክበር አንደሚገባው ያስታወቁት ኮማንደር አስቻለው በቤተክርስቲያኑ የታየው ነገር አስደንጋጭና ትምህርት ሊወሰድበት አንደሚገባም አሳስበዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ከሰመራ ዩንቨርስቲ የተላከ :-

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርስቲ አካባቢ በሚገኙ የተቸገሩ ህብረተሰብ (100)አንድ መቶ አባወራዎች )የዱቄት፤ ዘይት ፤የእጅ መታጠቢያ ሻምፖ እና በዩኒቨርስቲው የተመረተ ሳኒታይዘር እገዛ አድረገዋል ። እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሰርተዋል።

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ቦታዉ ተገኝተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንቶች እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አግልግሎት ሃላፊነቱን እየተወጣ ሲሆን አሁንም ለማህበረሰቡ ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ እንደዚህ አይነት ስራዎችን ላይ አትኩሮ እንደሚሰሩም ሀላፊዎች ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር #ከ40 ሺ መብለጡ ተነገረ።

ከሞቱት ውስጥ ግማሽ ያህሉ የሚገኙት በኒውዬርክ መሆኑ ተገልጿል።

በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ764 ሺ ከፍ ማለቱ ሲነገር በተለያየ ግዛቶች የሚኖሩ ዜጎች የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የወጣውን ከቤት ቆዩ የሚለውን ትዕዛዝ በመቃወም ድምፅ ማስማት መጀመራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በሌላ ዜና ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለኢራን የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ሀገራቸው ፍቃደኛ መሆኗን አስታውቀዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
የሱማልያ ዘመናዊ ሙዚቃ መስራች ተብሎ የሚነገርለት አህመድ ኢስማኤል ሁሴን ሁዲዲ በኮሮናቫይረስ ታሞ ዛሬ በ91 አመቱ ለንደን በሚገኝ ሆስፒታል ማረፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮናቫይረስ ስጋት ባለችው ባንግላዲሽ በአንድ ቀብር ላይ ከመቶ ሺ በላይ ሰው ተገኝቷል። የቫይረስ ሰርጭቱ እንዳይባባስ ተሰግቷል።

ማኡላና ዙባየር አህመድ የተባለ የሙስሊም እምነት ታዋቂ መምህር ሞቶ ትላንት እሁድ ቀብሩ የተፈፀመ ሲሆን በቀብሩም ላይ ከ100,000 ሰው በላይ የተገኝቷል። ይሄም በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ከ5 ሰው በላይ ለፀሎት እንኳን በአንድ ላይ መገኘት የተከለከለባት ባንግላዲሽን የመምህሩ ቀብር የተገኙ ሰዎች በቫይረስ ከተያዙ ስርጭቱን በማባባስ ለሀገሪቷ ራስ ምታት እንዳይሆኑ ተሰግቷል ። 2,456 የቫይረሱ ተጠቂ ያለባትና 91 ሞት ያስተናገደችውን ቫንግላዲሽን በኮሮናቫይረስ እንደሌላው ቀሪ አለም ፈተና ውስጥ ናት ሲል ሲኤን ኤን ዘግቧል።

Via:- Tsefay Getnet
@Yenetube @FikerAssefa
ጃክ ማ ሶስተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ ነው

ጃክ ማ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶችን ለሶስተኛ ጊዜ ለአፍሪካ ሃገራት ሊልኩ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም 4 ነጥብ 6 ሚሊየን ማስኮች፣ 500 ሺህ ናሙና መውሰጃ እና መመርመሪያዎች፣ 300 የመተንፈሻ መሳሪያዎች፣ 200 ሺህ አልባሳትና 200 ሺህ የፊት መሸፈኛዎች ለሃገራቱ ይላካሉ።

ከዚህ በተጨማሪም 2 ሺህ የሙቀት ኘመለኪያዎች፣ 100 የሰውነት መለኪያ መሳሪያዎች እንዲሁም 500 ሺህ ጥንድ የእጅ ጓንቶችም የሚላኩ ይሆናል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በኮቪድ 19 ዘገባ ምክንያት ሶማሊያ ጋዜጠኞችን እያሰረች ነው።

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኮሮና ቫይረስ/ኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሚዲያ ዘገባ አገልግሎት አስፈላጊ ነው ቢሉም እስካሁን በትንሹ አራት ጋዜጠኞች በዘገባቸው ምክንያት ታስረዋል፡፡

Viia:-ቪኦኤ
@Yenetube @Fikerassefa
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸውን ጨምሮ ለውጭ ሀገር ሰራተኞች ነጻ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ ጀመረች

የአቡ ዳቢ መንግስት ዓላማው ቫይረሱን መቆጣጠርና ሁሉም ነዋሪዎች በቂ የጤና እንክብካቤ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ነው ብሏል።

Via:- Al Ain
@Yenetube @Fikerssefa
ልዩ የስራ ጠባይ ላላቸውና ድጋፍ ለሚሹ የይለፍ ፍቃድ እየተሰጠ ነው

ከኮድ-2 ተሽከርካሪዎች የፈረቃ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ልዩ የስራ ጠባይ ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የይለፍ ፍቃድ እየሰጠ መሆኑን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ጋና የእንቅስቃሴ ገደብን አነሳች

የጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ተጥሎ የነበረውን የመንቀሳቀስ ገደብ እንዲነሳ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ:- #ሮይተርስ #አለአይን
@Yenetube @Fikerassefa
111 ደርሷል

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 111 ደርሷል።

ባለፈው 24 ሰዓት ውስጥ ከተወሰዱ 396 ናሙናዎች ሶስቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 16 ደርሷል።


@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ሪፖርት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሶስቱም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የመኖሪያ አድራሻቸው #ድሬዳዋ ነው።

- ሁለቱም ከጅቡቲ የመጡና በለይቶ ማቆያ ያሉ የ11ና የ15 አመት ታዳጊዎች ናቸው። አንደኛው የ18 አመት ወጣት ሲሆን በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አለው ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የ30 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቀደለት። ለጋዜጠኛው ዛሬ ሰኞ፤ ሚያዝያ 12፤ ዋስትናውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ልደታ ምድብ፤ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

Via:- Ethiopia insider
@Yenetube @FikerAssefa
ለጤና ባለሙያዎች እና ለሚዲያ ተቋማት የተሽከርካሪ ይለፍ ፍቃድ እየተሰጠ ነው!

ከኮድ-2 ተሽከርካሪዎች የፈረቃ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ልዩ የስራ ጠባይ ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የተሽከርካሪ የይለፍ ፍቃድ እየሰጠ መሆኑን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ እንዲተገበር ሆኖ ከወጣው የፈረቃ እንቅስቃሴ መመሪያ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ያላቸው አካላት ወደ ባለስልጣኑ እየመጡ ነው ያሉት የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቀመጠው የልዩ ድጋፍ አሰጣጥ መመሪያ መሰረት እየተስተናገዱ መሆኑን ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

ለጤና እና ፋርማሲ ባለሙያዎች፣ ለሚዲያ አካላት እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው የትራንስፖርት ስምሪት መመሪያ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እየታየ የይለፍ ወረቀት እየተሰጣቸው እንደሆነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ኮድ-2 የቤት ተሽከርካሪዎች ከዛሬ እለተ ሰኞ ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በሰሌዳ ቁጥር ሙሉና ጎዶሎነት በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡

Via:- አል አይን አማርኛ
@Yenetube @Fikerassefa