YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እስራኤል ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተባቸው ሀገራት ወደ ሀገሯ የሚገቡትን 14 ቀን ለይቶ ማቆያ ማስገባት መጀመሯን አስታውቋል።

#ኮቪድ19
@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ጠዋት #ጋቦን#ጋና#ኮንጎ እና #ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የ#ኮቪድ19 መከላከያ ግብአቶችን ተረክበዋል። ከ #ጃክ ማ እና #አሊባባ ቡድን ያገኘናቸው 540 ሺህ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች እና 20 ሺህ ንክኪን የሚከላከሉ ልብሶች ወደ #ኢትዮጵያ እየተጓጓዙ ነው። ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚደረገው ሥርጭት ይቀጥላል።

Via:- abiy Ahmed
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ#ኮቪድ19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አቋቁመዋል። መንግሥት ጠቀም ያለ በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ነገር ግን እንዲህ ያለው ጊዜ የእያንዳንዱን ግለሰብ አስተዋጽኦ የሚፈልግ ነው። እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ ስናልፍ፣ በድል አድራጊነት ለመወጣት የሚያስችሉን በኅብረት እና በሚገባ በመቀናጀት የምናደርጋቸው ጥረቶች ብቻ ናቸው። ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ'ን በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው የ#ኮቪድ19 ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ለግሰዋል።

'ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ'ን በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው የ#ኮቪድ19 አቅርቦት ማሰባሰቢያ ለግሰዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
ስለ #ኮቪድ19 ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠታቸው እና የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት የዓለም የጤና ድርጅት ስለሚያከናውነው ተግባር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖምን አመሰግናለሁ። ትናንትና ያደረግነው የስልክ ውይይት ይህ አስጨናቂ ጊዜ ከምንጊዜውም በላይ የጋራ አመራርን እንደሚጠይቅ አረጋግጦልኛል። አመራራቸው ወቅቱንና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን ነው።

Via Abiy Ahmed
@Yenetube @Fikerassefa