YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ግለሰቦች ጋር ግንኙነት የነበራቸው 70 ያህል ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ማእከል ገቡ።

በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ግለሰቦች ጋር በልዩ ልዩ መልኩ ግንኙነት የነበራቸው 70 ያህል ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ማእከል መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።

ክልሉ እስካሁን 27 ሰዎች ላይ ምርመራ መደረጉን ገልጾ፣ 25ቱ ነፃ ሲሆኑ ሁለት ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ እንዳለባቸው በመረጋገጡ ተገቢ የሆነ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ብሏል።
የአማራ ክልል የኮረና ቫይረስ መከላከል እና መቆጣጠር ኮማንድ ፖስት ከመጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በባሕርዳር፣ በእንጅባራ፣ በአዲስ ቅዳም እና በቲሊሊ ከተሞች የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ይታወቃል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
በብሪታንያ የኮሮና ቫይረስ እያስከተለ ያለው ጉዳት እንደተባባሰ ቀጥሏል። በ24 ሰዓት ውስጥ 544 ሞትና 4,324 አዲስ ኬዝ ተመዝግቧል። ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር 29,474 ሲሆን 2,352 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
#update

በሱዳን በኩል ተቋርጦ የነበረው የነዳጅ አቅርቦት መቀጠሉን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ለ14 ቀናት ባህርዳር እንድዘጋ የወሰነው የአማራ ክልል የጎዳና ተዳዳሪዎች በትምህርትቤቶች በመሰብሰ ላይ ይገኛል።

@Yenetube @Fikerassefa
ፕሬዝደንት ሳህለወረቅ ዘውዴ ከሌሎች 4 የሀገራት ፕሬዝደንቶች ጋር በጋራ የኮሮና ቫይረስን ለመወጋትአለም ዓቀፍ ትብብር ያስፈልጋል ሲሉ በፋይናሻል ታይምስ ጽሁፍ አውጥተዋል።
https://t.co/nl0yVYKOqb
የሶማሌ ክልል መንግሥት ከአጎራባች ክልሎችና ሀገራት ወደ ክልሉ የሚገባ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገደ። ከዚህ በተጨማሪ ከሌሎች አጎራባች ክልሎች የሚገቡ እህል፣ነዳጅና ለዜጎች ኑሮ አስፈላጊ ከሆኑት ምርቶች የያዙት ተሽከርካሪዎች ከሾፌርና ረዳት ውጭ ሌላ 3ኛ ሰው ጭኖ መግባት የተከለከለ መሆኑን ክልሉ ገልጿል።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ቴሌኮም የኢንተርኔት ዋጋ ማስተካከያ እየመከርኩ ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ ቴሌኮም #የኮሮና_ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ተከትሎ የኢንተርኔት ፍላጎትን ታሳቢ በማድረግ እየቀረቡ ያሉ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄዎችን እየመረመርኩ አለ።

ሸገር FM የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስኪያጅ ፍሬህይወት ታምሩ ጋር የስልክ ቶይታ ነበረው በቆይታውም ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የዋጋ ቅናሽ ቢደረግ ሊያስከትል የሚችለው የኔቶርክ መጨናነቅ እያጠናን ነው ብለዋል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር መጨመሩን እንዲሁም የተንቀሳቃሽ WiFi እና የብሮድባምድ አገልግሎት በከፍተኛ ቁጥር መጨመሩን ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

Via:- ሸገር FM
@Yenetube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ በቁሳቁሶች ላይ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል ? #ጤና_ሚንስትር

ከብረት የተሰሩ - 2 ቀናት

ወረቀት ላይ :- 4-5 ቀናት

ከእንጨት የተሰሩ እቃዎች ላይ :- 4 ቀናት

ከፕላስቲክ የተሰሩ እቃዎች ላይ :- 5 ቀናት

የህክምና የእጅ ጓንት (ግላቭ) :- 4-5 ቀናት

@Yenetube @Fikerassefa
በኒውዮርክ ብቻ 391 ሞት ተመዘገብ!

በኒውዮርክ ስቴት ዛሬ 7917 አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው ተነግሯል። በኒውዮርክ ስቴት በ24 ሰአት ውስጥ 391 ሰው ህይወቱን አጥቷል። በዚው ስቴት ከ83,712 በላይ ተጠቂ ይገኝበታል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጣልያን 727 ሞት ተመዘገብ

- ጣልያን በ24 ሰዐት ውስጥ 727 ሰው በቫይረሱ ተጠቅተው መሞታቸው ተነግሯል።

- በቫይረሱ የተያዘ ሰው ቁጥር 110,574 ደርሷል

- በአጠቃላይ 13,155 ሰዎች ህይወታቸውን አተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#Newsalert

በሳምባ ኢንፌክሽን ዛሬ ማለዳ ህይወታቸው ያለፈው የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮናቫይረስ እንዳልነበረባቸው በላብራቶሪ ምርመራ መረጋገጡ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር በተለይ ኮንትራት ሰራተኞች ያለደሞዝ ፍቃድ እንዲወጡ ተደርገዋል አለ።

Via:- ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እንዲሁም በመላው ዞን የመብራት አገልግሎት ለማግኘት አዳጋች እንደሆነባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ለየኔቲዩብ ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ እንደነገሩን የቧምቧ ውሃ በየመንደሩ አንዴ የሚደርስበት ጊዜ እስከ ከ15-30 እንደሚደርስና በዚህ የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ለመከላከል ንፅህና እጅግ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት ይህ ችግር ፈተና እንደሆነባቸው ነው።

የመብራት መቋረጥ ደግሞ ለዞኑ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚቀርብበት (አባ) ሳብስቴሽን በደረሰበት የመናድ አደጋ የቦታ ቅያሪ እንደሚደረግለት ከኮርፖሬሽኑ መልዕክት የተላለፈ ቢሆንም፣ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በፈረቃ ታገኛላችሁ ተብለን የነበረ ቢሆንም መብራት ፈፅሞ እያገኘን አይደለም ብለዋል።

ለዚህም የከተማ መስተዳደሩና ዞኑም ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ይህን ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የንፁህ ምጠጥ ውሃ እጥረትና የመብራት መቆራረጥ(እጦት) ለመቅረፍ የአጭር ጊዜም ሆነ የረጅም ጊዜ መፍትሔ በአፋጣኝ እንዲፈልግላቸው ተማፅነዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የታየው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እድገት!

➡️ January 19: 100 cases
➡️ January 24: 1,000 cases
➡️ February 12: 50,000 cases
➡️ March 6: 100,000 cases
➡️ March 21: 300,000 cases
➡️ March 26: 500,000 cases
➡️ March 29: 700,000 cases
➡️ April 1: 900,000 cases

@YeneTube @FikerAssefa
የኔቲዩብ በቴሌግራም ዜናዎችን ማቅረብ ከጀመረ ዛሬ ሶስት አመት ሞላው።

አብራችሁን ለቆያችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች የናንተም ጥረትና በየጊዜው የምትሰጡን አስተያየት ወሳኝ ነበርና እናመሰግናለን።

እናም 3ኛ አመታችንን ምክንያት በማድረግ በዚህ ወቅት ሀገራችንም ሆነ በመላው አለም እጅግ አሳሳቢ በሆነው ኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ፈጣን መረጃዎችን ከማድረስ ባሻገር አቅማችን በፈቀደው መጠን ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ የንፅህና መጠቀቂያ ቁሳቁሶችን ለ"True love Children Center" አስረክበናል።

ተግባራችን የሚቀጥል ይሆናል!!

ቃል በገባነው መሰረት ቻናላችን ላይ የምታስተዋውቁ ድርጅቶች ድርጅታችሁን እያስተዋወቃችሁ እንዲሁም በጎን ለበጎ አድርጎት እየለገሳችሁ መሆኑ ለማሳውቅ እንወዳለን።

-የኔቲዩብ
@Yenetube @Fikerassefa
የ13 አመት አዳጊን ጨምሮ ኤርትራ ሦስት በኮሮና መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች ማግኘቷን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኤርትራ መንግሥት በረራ ከመከልከሉ በፊት ወደ አስመራ የተጓዙ የ32 አመት ወንድ እና የ52 አመት እንስት ዛሬ በኮሮና መያዛቸው መረጋገጡ ተገልጿል።የ13 አመቷ አዳጊ ተሕዋሲው ከውጭ አገር ወደ አስመራ ከተጓዙ እናቷ እንደ ተላለፈባት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር መግለጫ ይጠቁማል። በአጠቃላይ በኤርትራ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 18 ከፍ ብሏል።

የአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ( Africa CDC) መረጃ እንደሚጠቁመው ከ55 የአህጉሪቱ አገራት የኮሮና ተሕዋሲ 49ኙን አዳርሷል።እስካሁን 5,786 አፍሪካውያን በተሕዋሲው የተያዙ ሲሆን 196 ሞተዋል። 412 ደግሞ አገግመዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካዋ ኮኔክቲከት ገዥ ኔድ ላሞንት በሚያስተዳድሩት ግዛት ከተወለደ 6 ሳምንት ብቻ የሆነው ጨቅላ ህፃን በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተረጋገጠ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ይፋ አድርገዋል። የሞቱ ምክንያት መቶ በመቶ ቫይረሱ ለመሆኑ ማረጋገጫ ባይኖርም ግን እስካሁን በቫይረሱ ተይዘው ከሞቱት ሰዎች በዕድሜ ትንሹ ሆኖ ተመዝግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጌዴኦ ዞን በሦስት ወረዳዎች የበረሀ አንበጣ ጉዳት እያደረሰ ነው!

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን በይርጋ ጨፌ፣ ራፔ እና ቡሌ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 19 ቀበሌዎች ላይ የበርሀ አንበጣ ሰፍሮ በአርሶ አደሩ ሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ።በዞኑ ውስጥ በሚገኙ በሦስቱ ወረዳዎች ለስድስተኛ ጊዜ የተከሰተው የበርሀ አንበጣ፣ እስከ አሁን በዞኑ ተከስቶ ከነበረው የበርሃ አንበጣ ይልቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለውና የከፋ ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የዞኑ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ኃላፊ ተገኝ ታደሰ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa