YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የቀድሞው የሱማልያ ጠቅላይ ሚንስትር ኑር ሀሰን (Nur Hassan Hassein) በኮሮና ቫይረስ ተጠቅቶ በለንደን ከተማ ዛሬ መሞቱ ተነግሯል።

ኑር ሀሰን ከፈረኝጆች ከ2007 እስከ 2009 የሱማልያ ጠቅላይ ሚንስትር ነበሩ። እንዲሁም ለብዙ አመታት የሱማልያ ቀይ መስቀልን መርተዋል። በ82 አመታቸው በኮሮና ቫይረሱ ተጠቅተው መሞታቸው ታውቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ታይቶበት ህይወቱያለፈ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮናቫይረስ እንደነበረበት ማጣራት እየተደረገ ነው ተባለ!

ከሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ህክም ሲደረግለት የነበረ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ ዛሬ ህይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ግለሰቡ በኮሮናቫይረስ ስለመያዙ ለማጣራት ናሙና ተወስዶ ምርመራ እየተደረገበት ነውም ብለዋል።ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለማረጋጋጥ ናሙና ተወስዶ የምርመራ ውጤቱ እየተጠበቀ መሆኑንም አብራርተዋል። የአስከሬን ምርመራም እየተከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ 864 ሞትና 7,719 አዲስ ኬዝ መዝግባለች። ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር ከ100,000 የበለጠ ሲሆን 9,053 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስ/ር ትርፍ በሚጭኑ ታክሲዎችና ባጃጆች ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ከስራ ውጪ ለማድረግ እንደሚገደድ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
"ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ በሚወጡ ሰዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል!" ዶክተር ሊያ ታደሰ

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ በሚወጡ ሰዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ ለኮሮናቫይረስ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከአገር ውስጥና ከውጭ ተቋማት በማስገባት ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስታወቀዋል።

የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል ከመጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም ከውጭ አገር የሚመጣ መንገደኛ በተመረጡ ሆቴሎች ውስጥ በራሱ ወጪ ለ14 ቀናት ተለይቶ እንዲቆዩ የተወሰነ መሆኑ ይታወቃል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከውጭ አገሮች የሚገቡ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንና ይሄን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለይቶ ማቆያዎችን የማስፋት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የድሬኔጅ ፅዳትና የጥገና ስራዎች እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡

Via:- Elu
@Yenetube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ የዳቦ ዋጋ በሚጨምሩ እና ግራም በሚቀንሱ ተቋማት ላይ ህጋዊ አርምጃ እንደሚወሰድ የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ አንዳንድ ዳቦ ቤቶች ያለ ምንም ምክንያት የዳቦ ዋጋ የመጨመር እና ግራም የመቀነስ ሁኔታ እየታየ መሆኑን ለማወቅ አንደተቻለ ነው የገለፀው።ሆኖም ምንም አይነት የአቅርቦት ችግር በሌለበት በአሁኑ ወቅት በዚህ ድርጊት ውስጥ መሳተፍ በህግ የሚያስጠይቅ አንደሆነ ቢሮው ገልጿል።ቢሮ በሚያደርገው ክትትል እና ጥቆማ መሰረት ከዚህ በኃላ በድርጊቱ ውስጥ በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ባህርዳርና የአዊ ዞን ዋና ከተማ እንጅባራ የ14 ቀኑን የእንቅስቃሴ እገዳ ተከትሎ ጭር ብለዋል።

ፎቶ: ELU & Awi Communication
@YeneTube @FikerAssefa
በባሕር ዳር ከተማ እምብርት የሚገኘው ድብ አንበሳ ሆቴል ለኮሮና ወረርሽኝ የለይቶ ሕክምና መስጫና ማቆያ አገልግሎት መስጫ እንዲሆን ባለቤቱ ሰጡ፡፡

የሆቴሉ ባለቤት አቶ ሺባባው የኔአባት ‘‘እኔ በሕዝብ ሀብት የገነባሁትን ንብረቴን ነው የለገስኩት፤ ያደላቸውና ለሙያቸው የቆሙ የሕክምና ባለሙያዎች ሕይወታቸውን ሲሰጡ ይደንቃል’’ ብለዋል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ከተከሰተው በበለጠ ሁኔታ ወረርሽኙ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል በመስጋት ሆቴላቸውን ለሕሙማኑ ለይቶ ማቆያና ሕክምና መስጫ እንዲውል መስጠታቸውን አቶ ሺባባው ተናረዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በከተማዋ መገኘቱን ተከትሎ፣ የአማራ ክልል መንግስት ግማሽ ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ የሚኖርባትን የባህር ዳር ከተማን ለ14 ቀናት ዘግቷል።

📸 Antex Sisay
@Yenetube @Fikerassefa
#Addis_Ababa ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አሁን ውኃ ለነዋሪዎች እያደረሰ ያለው በፈረቃ ሲሆን በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚጠፋ ባለሥልጣኑ ባሉት 28 ቦቴ ተሽከርካሪዎች ለደንበኞቹ ውኃ እንደሚያከፋፍል ገልጸዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ሞያሌ አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በኬንያ መንግሥት ሠራተኞች ላይ ተኩስ እንደከፈቱ የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡ ከወታደሮችም ጋር ተኩስ ተለዋውጠዋል፡፡ ሠራተኞቹ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል መተላለፊያዎችን በመቆፈር ላይ ነበሩ፡፡ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አልደረሰም፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአበባ አምራቾች በኮቪድ19 ምክንያት ሠራተኞቻቸውን ሊቀንሱ ነው!

የዓለም ዐቀፍ ስጋት በሆነው በኮቪድ-19 ምክንያት በተፈጠረ የገበያ መቀዛቀዝ ምክንያት የአበባ አምራቾች ሠራተኞቻቸውን ከሥራ ሊቀነሱ መሆኑን የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎች ማኅበር ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።ድርጅቶች ሠራተኛ ላለመቀነስ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የተናገሩት የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ዘውዱ፣ ሥራ ባይኖርም ሠራተኞች እንኳን በሥራ ላይ እንዲቆዩ ለማድረግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በህገ-ወጥ መንገድ ከነዳጅ ማደያ ተቀድቶ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ 39 በርሜል ቤንዚን ከእነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በቤታቸው ብቻ እንዲጸልዩ ውሳኔ አስተላለፈች።

ቤተክርስቲያኗ ዛሬ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ የኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ በመምጣቱ የዕምነቱ ተከታዮች ጸሎታቸውን በቤታቸው ብቻ እንዲያካሂዱ መወሰኗን አስታውቃለች። ቤተክርስቲያኗ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ስራ 3 ሚሊዮን ብር መለገሷን ገልጻለች።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር ተወሰነ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከከተማው የፀጥታ አካላት ጋር አትክልት ተራ አካባቢ እየታየ ባለው መጨናነቅ ዙሪያ ተወያይተዋል።ቦታው የከተማዋ ከፍተኛ የአትክልት ምርት ማከፋፈያ ሲሆን ከፍተኛ የሰው ጭንቅንቅ በየእለቱ የሚታይበትና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘም ለቁጥጥር አስቸጋሪ መሆኑ ተገምግሟል።ስለሆነም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአትክልት ግብይቱ በጊዜያዊነት ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር ተወስኗል።አትክልት ተራ ለጊዜው ለነጋዴዎቹ እንደ እቃ ማስቀመጫ(ስቶር) ብቻ እንዲያገለግል ተወስኗል።ጃንሜዳ ቦታው ሜዳማ እንደመሆኑ ለእንቅስቃሴ ምቹ መሆኑና ለቁጥጥር አመቺ መሆኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው የአትክልት ግብይቱ ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር መደረጉን የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

Via Mayor Office/Fana
@YeneTube @FikerAssefa