YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቋማት አገልግሎት ሊያቆሙ ነው።

ተቋማቱ አገልግሎቱን የሚያቆሙት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንደሆን የፓትርያርክ ጽህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

ይሁንና አገልግሎት የሚያቆሙት የትኞቹ ተቋማት እንደሄኑ እስካሁን አልታወቀም።

በጉዳዩ ዙሪያም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ውድ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አድማጮች እና ተከታዮቻችን መግለጫውን ተከታትለን እናስደምጣችኋለን።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር ቆይታ አድርገዋል

ባለሃብቶቹ የኮሮና ቫይረስ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት እንደ ሃገር ለመመከት አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ያለውን የመከላከል ስራ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ ባለሃብቶቹ በራሳቸው ተነሳሽነት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም ወረርሽኙን ለመግታት ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለሚሰራቸው ስራዎች አድናቆት እንዳላቸው የጠቆሙት ወጣት ባለሃብቶቹ በቀጣይነትም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅርበት ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

Via:- አ.አ ከንቲባ ፅ/ቤት
@Yenetube @Fikerassefa
ኒው ቴክ ኢትዮጵያ ( @NewTekEthiopia ) እጃችንን እንታጠብ በሚል መርህ የውሀ ታንከሮችን ህዝብ በብዛት ባለበት ቦታ እየተከለ ህብረተሰቡን እያገለገለ ይገኛል።

እጃችንን በመታጠብ እራሳችንን እና ማህበረሰባችንን ከቫይረሱ እንጠብቅ!
@Yenetube @Fikerassefa
የዌልሱ ልዑል ቻርለስ በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የእንግሊዙ ዘውድ ወራሽ የሆኑት ልዑል ቻርልስ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውንና መጠነኛ ምልክት እንደታየባቸው ከቤተ መንግሥቱ የወጣው መረጃ ያስረዳል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሩዋንዳ መንግሥት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሶ በመውጣት አሳ ለማስገር የሄደው ግለሰብ በአዞ መበላቱ ተሰማ።

ግለሰቡ የሚኖርበት የደቡብ ካሞኒ አውራጃ ከንቲባ የሆኑት አሊስ ካይቴሲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ግለሰቡ ቤት ተቀመጡ የሚለውን ደንብ ተላልፎ ወጥቶ ነበር፤ በአካባቢው ከጥቂት ሰዎች ጋር በመሆን ኮሮናቫይረስን ለመግታት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ አያከብርም ነበር" ብለዋል።

የሩዋንዳ ባለሰልጣናት ሙሉ በሙሉ የመንቀሳቀስ ገደብ የጣሉት እሁድ ዕለት ነበር።

በሩዋንዳ እስካሁን ድረስ 40 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ይህም በምስራቅ አፍሪካ አገራት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታማሚ ያለባት አገር አድርጓታል።

-BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ላልተወሰነ ጊዜ የፓስፖርት አገልግሎት መስጠት ማቆሙን አስታውቋል። ኤጀንሲው የኢ-ቪዛና ተደራሽ ኦን አራይቫል ቪዛም አገልግሎት መስጠት አቁሟል።

በተጨማሪም የመኖሪያ ፈቃድ እና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል።

@Yenetube @FikerAssefa
 በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘዞ ክፍለ ከተማ 873 ሺህ 900 ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር 5ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቻላቸው የኔነህ ሀሰተኛ ዶላሩ ከህብተሰቡ በመጣ ጥቆማ ሊያዝ እንደቻለ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ከኢፌዴሪ ጉምሩክ ባለስልጣን የጎንደር ከተማ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ እና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል ጠቅላይ መምሪያ መረጃ ክፍል ጋር በተሠራ ኦፕሬሽን ሐሰተኛ ገንዘቡ መያዙን ገልፀዋል።

አንድ ግለሰብ ከነግብረ አበሮቹ በጉዳዩ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል፡፡

ዋና ተጠርጣሪው በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ስሞች የሚጠራ እና በሐሰተኛ መታወቂያዎች የሚንቀሳቀስ መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል።

ፖሊስ እንዳለው 873 ሺህ 900 ሐሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ጨምሮ ዘጠኝ ኪሎ ግራም የሚመዝን ነሐስ፣ ጌጣጌጦች፣ ማዕድናት፣ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች የሚመስሉ ሐሰተኛ ቁሶች፣ የሐሰተኛ ዶላር ኖቶች ማባዣ ማሽን እና ሌሎች ዕቃዎች ጋር ነው ተርጣሪዎቹ መያዛቸውን አብመድ ዘግቧል

Via :-Fana
@Yenetube @Fikerassefa
ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉና ተማሪዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ውሳኔ ማሳለፍ ይታወቃል ፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቤታቸው በሚያደርጉት ቆይታ ከትምህርት ውጪ መሆን ስለሌለባቸው በራሳቸው የጥናት ፕሮግራም በማውጣት ማንበብ ማጥናትና የተለያዩ መልመጃዎች እየሰሩ እንዲቆዩ ማድረግ ይገባል፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች በሚከተሉት አማራጮችን በመጠቀም

 የኢንተርኔት አገልግሎት ያላቸው አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ የተለያዩ ማቴሪያሎችን የትምህርት ሚኒስቴርን ዌብ ሳይት
www.moe.gov.et በመግባት መጠቀም፣
 ትምህርት በሬድዮ በፕሮግራሙ መሰረት እየተሰራጨ ስለሆነ መከታተል፣
 በትምህርት ቴሌቭዥን እየተሰራጩ ያሉ ትምህርቶችን በፕሮግራም በመከታተል ምንም የሚባክን ጊዜ እንዳይኖር ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

ወላጆችም ትምህርት ቤቶች የተዘጉት ስርጭቱን ለመቆጣጠር እንዲቻል መሆኑን ተረድተው ልጆቻቸው ከቤት እንዳይወጡ ንክኪ እነዳይኖራቸው በማድረግ በሽታውን ከመከላከል ጎን ለጎን ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አድርገው እንዲያጠኑ በመከታተል የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።

Via:- Ministry of Education
@YeneTube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበረከቷል፡፡

የአካባቢው አርሶ አደሮችም ከተማ አስተዳደሩ በማቆያ እንዲገቡ ላደረጋቸው አቅመደካማዎች የሚውል የሰብል ምርቶች በስጦታነት አበርክተዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ ለአርሶ አደሮቹ የተበረከቱትን የንጽህና ማጠበቂያ ቁሳቁሶች አስረክበዋል፡፡በተለያየ የጥበብ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አርቲስቶች በርክክቡ ወቅት ተገኝተዋል፡፡

የንጽህና መጠበቂያዎቹን ያበረከቱት ኢ/ር ታከለ ኡማ ጊዜው ከምንም ጊዜው በላይ መደጋገፍንና ወንድማማችነትን የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡አርሶ አደሮቹ ያደረጉት የሰብል ድጋፍም መደጋገፍን በተግባር ያሳየ እንዲሁም ለብዙዎች ትምህርት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡ኢ/ር ታከለ የተለያዩ መሰረታዊ ፍላጎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች "ተግባራችሁ ህገወጥ ብቻ ሳይሆን ልኩን ያለፈ ኢሰብአዊነት ነው፡፡እንዲህ አይነት ተግባር ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችን ጉዳይ በተለየ መልኩ በከፍተኛ የህግ ጥሰት የሚታይ ነው" ብለዋል፡፡ህገወጥ ተግባራት እንዲቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ አይፈቅድም የተጠናከረ እርምጃም ይወስዳል ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች፣ የጡረታ መውጫ ጊዜያቸው የደረሱ ሰራተኞች፣ የቆየ እና በሀኪም ማስረጃ የተደገፈ የጤና እክል ያለባቸው የመንግስት ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ወሰነ።

@Yenetube @Fikerassefa
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከ70% በላይ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ሥራቸውን በቤት ውስጥ ሆነው እንዲያከናውኑ መወሰኑን አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassfa
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዛሬ በፋይናሻል ታይምስ ( FinancialTimes ) ላይ ባወጡት ጽሁፍ፣ የበለጸጉ ሀገሮች የኮሮና ተህዋሲን ለመዋጋት ድንበር ዘለል የድርጊት መርሐግብር እንዲከተሉ ጠይቀዋል።

Link :- https://amp.ft.com/content/c12a09c8-6db6-11ea-89df-41bea055720b?__twitter_impression=true
@Yenetube @Fikerassefa
ከዛሬ ጀምሮ በቤታቸው ውስጥ ሆነው ይሥሩ የተባሉት የፌደራል መሥሪያ ቤት ሠራተኞች 300 ሺህ ያህል መሆናቸውን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኬንያ መንግሥት ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት የሰዓት ዕላፊ ማወጁን ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታ አስታወቁ። በኮሮና ተሕዋሲ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱን፤አንድ ሰው ከሕመሙ ማገገሙን ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ልጅ ሚካዔልና ጓደኞቹ በእስር ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን 40 ሺሕ ብር የሚያወጡ የንፅሕና መጠበቂያዎች (የገላ ሳሙናዎች፣ ሳኒታይዘር፣ ሶፍት፣ዲቶል እና ላርጎ) አሰባስበው መስጠታቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ገለጸ።

Via:- Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ6ኛ አመት የሕክምና ተማሪዎች በቀር ተማሪዎቹን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አዟል። ዩኒቨርሲቲው እንዳለው በራሳቸው መጓዝ ለማይችሉ እስከ ክልል ከተሞች የሚያደርሳቸው መጓጓዣ አዘጋጅቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
የወሎ ዩኒቨርሲቲ በደሴና በኮምቦልቻ የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ አዲስ አበባ፣ መቐለ፣ ባሕርዳር፣ ጎንደርና አፋር የሚያደርሷቸው መኪኖች ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እስከ አዲስ አበባ መጓጓዣ አዘጋጅቷል

@Yenetube @Fikerassefa
#Breaking

የቀድሞው የነቀምት ከተማ አስተዳደር እና የፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸው ተሰማ፡፡ የቀድሞው የከተማዋ አስተዳደር እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ተሾመ ገነቴ ዛሬ በ10 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ መገደላቸውን ሰምተናል፡፡ወሬውን ለሸገር የተናገሩት የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ናቸው፡፡አቶ ተሾመ በማን እንደተገደሉ በምርመራ ላይ መሆኑንም የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa