YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልዕክት ለመላው አለም ከካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ሊደመጥ የሚገባው መልክት ነው።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን መልክት ለምታውቁት ሰው እንድታስተላልፉ ጠይቋችዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ አስተማሪ ቪዲዮ ተመልከቱት!!
እንዲሁም ለወዳጆ አጋሩት።

- እንዴት ማስክ ማድረግ እና ማውለቅ እንዳለብን

- እንዴት ሊፍቶችን መንካት እንዳለብን

- እንዴት በሮችን መክፈት እና መዝጋት እንዳለብን

-ሰላምቶቻችን እንዴት መሆን እንዳለባቸው።

@Yenetube @FikerAssefa
በፈረንሳይም እስካሁን የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 1,100 ደርሷል። የ24 ሰዐት ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ደግሞ 2,446 አዲስ ተጠቂዎች የተመዘገቡ ሲሆን 240 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ 22,302 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ የኮሮና ቫይረስ ሰርጭትን ለመግታት ለሁለት ሳምንት ከምሽት አንድ ሰአት እስከ ንጋት 12 ሰአት ያለ እንቅስቃሴን አግዳለች።

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ሰርጭትን ለመግታት የሰዎችን እንቅስቃሴ ጨምሮ የህዝብና የግል መኪኖች ከሮብ መጋቢት 16,2012 ጀምሮ ከምሽት አንድ ሰአት እስከ ንጋት አንድ ሰአት ከሁለት ሳምንት ያክል መንቀሳቀቀስ እንደማይቻል ገልፆ ይሄንም ተላልፎ የተገኘ ሰው 250 የአሜሪካ ዶላር እንሚቀጣ፣ ተናግሯል ።
ምግብ ቤቶች የውጭ ትእዛዝ በመቀበል ቤት ለቤት አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ የተፈቀደ ሲሆን መድሀኒት ቤቶች ግን ክፍት ይሆናሉ ተብሏል።

ግብፅ በቫይረሱ 19 ሰው ሲሞትባት 319 ሰው ደግሞ በቫይረሱ ተይዟል።
@Yenetube @Yenetube
በህንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ 1.3 ቢሊየን ዜጎቿን ለሶስት ሳምንት ከቤት አትውጡ ስትል አዝዛለች። ይህንንም ተከትሎ ህንዳውያን መሰረታዊ የፍጆታ እቃ ለመግዛት በገበያ አዳራሾች ፊት ለፊት ተሰልፈው ታይተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙ ሰው የሞቱባቸው ሀገራት

- ጣልያን 6820
- ቻይና 3277
-ስፔን 2808
-ኢራን 1934
- ፈረንሳይ. 1100
-አሜሪካ 685
-ብሪታኒያ 422
- ኔዜርላንድ 277
-ጀርመን 157
-ሲውዘርላንድ 130
- ቤልጅየም 122
-ደቡብ ኮርያ 120
-ኢንዶኔዥያኛ 55
-ብራዚል 42
-ጃፓን 40
- ስውዲን 37
@Yenetube @Fikerassefa
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ የሚገኙ የወንጌላውያን አማኞች አሁንም በስጋት እና በፍራቻ ውስጥ እንደሚገኙ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።

ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን አመራር እንዳስታወቁት፣ ከመጋቢት 1 እስከ 3/2012 የእነዋሪ ከተማ ነዋሪዎች በሆኑ ወጣቶች በቤተ እምነታቸው እና በአማኞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ቢሆኑም፤ የሚመለከተው አካል ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ጠዋት #ጋቦን#ጋና#ኮንጎ እና #ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የ#ኮቪድ19 መከላከያ ግብአቶችን ተረክበዋል። ከ #ጃክ ማ እና #አሊባባ ቡድን ያገኘናቸው 540 ሺህ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች እና 20 ሺህ ንክኪን የሚከላከሉ ልብሶች ወደ #ኢትዮጵያ እየተጓጓዙ ነው። ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚደረገው ሥርጭት ይቀጥላል።

Via:- abiy Ahmed
@Yenetube @Fikerassefa
ሰላም 🙌

እራሶን እንዲሁም ወዳጆን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንዚህ መስፈርቶች ይተግብሩ።

- እጆች በአግባቡ ይታጠብ

- በሚያስነጥሱበት ጊዜ አፎን ይሸፍኑ

- አይን እና አፊንጫዎን አይንኩ

- አ ካ ላ ዊ ፈ ቀ ቅ ታ ን ይ ተ ግ ብ ሩ
@Yenetube @Fikerassefa
የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ሌፍተናንት ጄነራል ጀማል አልዲን ኦማር ለስራ በተጓዙበት ደቡብ ሱዳን በልብ ድካም ህይወታቸው አለፈ። የጦር አዛዡ በመንግስት እና ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ባለው የሰላም ድርድር ላይ እየተሳተፉ ነበር።

ምንጭ:- ተስፋ አለም ወልደየስ
@Yenetube @Fikerassefa
SOCIALDISTANCIG ምን ያህል ይጠቅማል?

ፎቶው በአማርኛ የተዘጋጀ ነው ይመልከቱት
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በንግድ መደብሮች ላይ በተደረገ ቁጥጥር በተጋነነ ዋጋ ምርቶችን ሲሸጡ የተገኙትን ህግ ፊት ላቀርባቸው ነው አለ፡፡በዚሁ ምክንያት የታሸጉ የንግድ መደብሮች ቁጥር ከ1 ሺ 250 በላይ ደርሷል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የገንዘብ ሚንስትር ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል 43% የሚሆኑት ሰራተኞች ከዛሬ ጀምሮ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ተወስኗል እንዲሁም 57 % የሚሆኑት ደግሞ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ተነግሮናል።

@Yenetube @Fikerassefa
በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት እና ለመከላከል መንግስት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መደረግ እንዳለባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሄራዊ የአደጋ ስጋት መከላከል እና ምላሽ ሰጪ ግብረ~ሃይል ከጤና ቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በቅንጅት የመንግስትን ውሳኔዎች ተፈፃሚ እንዲያደርጉ እና እንዲከታተሉ ብሄራዊ ስምሪት መስጫ መድረክ ተካሂዷል።

ብሄራዊ ግብረ~ሃይሉን እና የቴክኒክ ኮሚቴውን በበላይነት የሚመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት÷የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት እና ለመከላከል መንግስት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማደረግ ይገባል ነው ያሉት።

- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት ለ4011 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት ለ4011 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ለ4011 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ዓቃቢተ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

በይቅርታው የተካተቱ ታራሚዎች

1ኛ. እስከ 3 ዓመት የሚደርስ ቀላል እስራት የተፈረደባቸው ታራሚዎች

2ኛ. በማረሚያ ቤት ሆነው አንድ ዓመት የአመክሮ ጊዜ የሚቀራቸው ታራሚዎች

3ኛ. በግድያ ወንጀል ያልተከከሰሱ የሚያጠቡ እና ነፍሰ-ጡር እናት ታራሚዎች

4ኛ. ከግድያ በመለስ የተለያዩ ወንጀሎች ውስጥ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲለቀቁ እና ወደ የመጡበት ሀገሮች እንዲላኩ መወሰኑን ጠቅላይ ዓቃቢተ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

በይቅርታው የተካተቱት ታራሚዎች በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ባሉ አምስት ማረሚያ ቤቶች ማለትም በቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት፣ ቂሊንጦ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ዝዋይ እና ድሬድዋ የሚገኙ ታራሚዎች ናቸው።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ጋዜጠኛ ፍቃዱ ከእስር እንዲለቀቅ ተወሰነ!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተናገሩት፦

"አንድ ጋዜጠኛ ከዚህ በፊት በምህርት አጠቃላይ የሀገራችን ጋዜጠኞች በሚታዩበት ሰዓት ጉዳዩ አልታየም ነበር በውጭ ቆይቶ በኃላ ወደሀገር ውስጥ ሲመጣ ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ነው ያለው እስካሁን ድረስ ባለው የመረጃ ማጥራት ሂደት የቆየ ነው ከለውጡ በኃላ ነው ፍርዱ የተወሰነበት፣ ስለዚህ ይሄም ጋዜጠኛ ታይቶ እንዲወጣ፣ ይቅርታ የተደረገበት ሁኔታ አለ። በቅድሙ አንድ አመት የቀራቸው የሚለው ውስጥ ስለማይካተት ነው የሱን ለብቻው ልገልፅላችሁ የፈለኩት። ተፈርዶባታል ከአንድ ዓመት ያህል በማረሚያ ቤት ቆይቷል ስለዚህ በቀሪው ሌሎች የሀገራችን ጋዜጠኞች ባየንበት ማዕቀፍ መታየት ስላለበት የሱም 'ፍቃዱ ማህተመወርቅ' እንዲታይ የተወሰነበት ሁኔታ አለ።"

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
20 ሰዎች የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ያሳለፉቸውን ውሳኔዎች ተከትሎ በየደረጃው ያለውን ተፈጻሚነት በሚኒስትሮች ደረጃ የተቋቋመው ከሚቴ በበላይነት በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡ከቀን 14፣2012 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ከውጭ ሀገር የሚመጣ መንገደኛ በሆቴል ውስጥ ለ14 ቀናት ተለይቶ እንዲቆይ በተወሰነው መሰረት በትላንተናው እለት ወደ ሀገራችን የገቡ ከ473 በላይ መንገደኞች በተመረጡ ሆቴሎች ማቆያ ውስጥ ናቸው ተብሏል፡፡

በሀገራችን 12 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው መሆኑን ቀደም ብሎ በተሰጡ መግለጫዎች ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡ ይሁንና ከ12 ታማሚዎች ውስጥ ሁለቱ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆኑ ሌሎች ታማሚዎች በለይቶ የህክምና መስጫ ማዕከል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን ሁሉም ታማሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።ወደ ሀገር ውስጥ መግቢያ ጣቢያዎች እየተደረገ የሚገኘው ምርመራ የተጠናከረ ሲሆን 668 ሺህ 476 ሰዎች በሙቀት መለያ ተደርጎላቸዋል።

በሙቀት መለያ ካለፉት 12 ሺህ 245 ያህሉ በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው ተብሏል፡፡በአሁኑ ሰዓት 1 ሺህ 923 የሚሆኑት ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሰዎች ለ14 ቀን የጤና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ሲሆን 1 ሺህ 772 የሚሆኑት ለ14 ቀናት ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው የኮሮና በሽታ ምልክት ያልታየባቸው በመሆኑ ክትትላቸው ተቋርጧል፡፡

እስከ አሁኑ ሰዓት 446 ሰዎች የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ መቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጎ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን 431ዎቹ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡በአሁኑ ሰዓት የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ 20 ናቸው፡፡

➡️ ከዚህ በፊት ከተሰራጩት የህክምና መስጫ ግብአቶች በተጨማሪ ከሁለት ሚሊየን በላይ የፊት ማስክ ለሁሉም ክልሎች መሰራጨቱም ተገልጿል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የዩናይትድ ኪንግደም አልጋወራሽ ልዑል ቻልረስ የኮሮና ተህዋሲ ተገኘባቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ#ኮቪድ19 ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን የሚያሰባስብ ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አቋቁመዋል። መንግሥት ጠቀም ያለ በጀት መደቦ የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢከሰት ለመቋቋም የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ነገር ግን እንዲህ ያለው ጊዜ የእያንዳንዱን ግለሰብ አስተዋጽኦ የሚፈልግ ነው። እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ ስናልፍ፣ በድል አድራጊነት ለመወጣት የሚያስችሉን በኅብረት እና በሚገባ በመቀናጀት የምናደርጋቸው ጥረቶች ብቻ ናቸው። ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ'ን በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው የ#ኮቪድ19 ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ለግሰዋል።

'ተረጋግቶ አስተዋጽኦ ማድረግ'ን በቀዳሚነት ተግባራዊ በማድረግ የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለብሔራዊው የ#ኮቪድ19 አቅርቦት ማሰባሰቢያ ለግሰዋል።

@YeneTube @Fikerassefa