YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አሜሪካ ሕክምና ላይ የሰነበቱት የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ወደ ክልሉ ተመለሱ። ሕክምናቸውን አጠናቀው መመለሳቸውን የገለጸው የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት "ከገጠማቸው የጤና እክል አገግመው በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ" ብሏል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
64 ኢትዮጵያዊያን ሞዛምቢክ ውስጥ በጭነት መኮና ውስጥ ሞተው ተገኙ!

ከማላዊ ወደ ሞዘምቢክ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ውስጥ ቢያንስ 64 ኢትዮጵያዊያን በመተፋፈን ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን ባለስልጣናት አስታወቁ።ዛሬ ጠዋት በሞዛምቢክ ምዕራባዊ ግዛት በምትገኘው ቴቴ በተባለችው ክፍለሃገር ውስጥ በተገኘው ተሽከርካሪ ውስጥ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 14 ሰዎች በህይወት ተገኝተዋል። "የሞዛምቢክ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ሰራተኞች የጭነት መኪናውን ሞአትዜ በተባለችው የግዛቲቱ ከተማ ውስጥ አስቁመው ሲፈትሹ ነው ሟቾቹን ያገኙት" ሲሉ የቴቴ ክፍለ ሃገር የጤና ባለስልጣን የሆኑት ካርላ ሞሴ ተናግረዋል።

ባለስልጣኗ እንዳሉት በጭነት መኪናው ላይ የተሳፈሩት ሰዎች ህይወታቸው በምን ምክንያት ሊያልፍ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያዊያኑ ህይወት ያለፈው በአየር ማጣት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።የሞዛምቢክ ብሔራዊ ኢሚግሬሽን አገልግሎት ቃል አቀባይ የሆኑት አሜሊያ ደሪዬሮ እንደተናገሩት ሟቾቹን ያሳፈረው የጭነት መኪና ሾፌር እንዲቆም ሲጠየቅ ፍላጎት አልነበረውም ብለዋል።

ጨምረውም የኢሚግሬሽን ሰራተኞቹ ከመኪናው ውስጥ ድምጽ በመስማታቸው ስደተኞች በውስጡ ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳረባቸውና እንዲቆም እንዳረጉ ገልጸዋል።ይህ የሞዛምቢክ ክፍለ ግዛት ወደ ደቡብ አፍሪካ በሕገ ወጥ መንገድ ስደተኞች በስፋት የሚዘዋወሩበት አንዱ ቦታ መሆኑ ይታወቃል።በህይወት የተረፉት 14ቱ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንደተደረገላቸው ቃል አቀባይዋ ጨምረው ተናግረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የ2020ው ኦሎምፒክ ጨዋታወዎች አስተናጋጅ ጃፓንና የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን ለሚቀጥለው አመት ለማስተላለፍ ተስማሙ።

@YeneTube @FikerAssefa
ሳንሸንግ ፓርማሲውትካል የተባለ ኩባንያ በምስራቅ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሳኒታይዘር ማምረት ጀምሯል። በቀን 24,000 ሊትር ያመርታል የተባለ ሲሆን የCovid-19ን ወረርሽኝ ተከትሎ ያለውን ፍላጎት ለማድረስ እየተሰራ እንዳለም ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ አለማየሁ የትዊተር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ከቤት ሆነው እንዲሠሩ ተወሰነ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከነገ ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ድረስ ሥራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ወስኗል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ የጣለውን ሕጋዊ ያልሆነ የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙት በአፋጣኝ እንዲመልስና በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸው እንዲከበር፣ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ መንግስት ሰራተኞች ከነገ ጀምሮ ወሳኝ የሥራ ሂደት ሰራተኞች ከሆኑት ውጪ ላልተወሰነ ጊዜ ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ተወስኗል።

@Yenetube @Fikerassefa
ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር በተላከው አቅጣጫ መሰረት ግቢውን ለቀችሁ እንድትወጡ ዩንቨርስቲው አሳስቧል።

ነገር ግን እኛ ባለን መረጃ መሰረት የሳይንስ እና ከፍተኛ ሚንስትር ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ ከግቢ እንዳይወጡ እንዲሁም እንዳይገቡ ነበር ትእዛዝ ያስተላለፈው።

--አዲስ ነገር ካለ የምናሳውቅ ይሆናል!!--
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስን ለመግታት ትምህርት ሚንስትር እና ተጠሪ ተቋማቱ ከ1544 ሰራተኞች 196(12.7%) ብቻ በማስቀረት ቀሪዎቹ ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲሰሩና መንግስት ስርጭቱን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መወሰኑን የትምህርት ሚንስቴር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ መውሰኑን አስታውቀዋል

ምንጭ: Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
Breaking AAU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ቤታችሁ እንድትሄዱ ተወስኗአል::

@YeneTube @Fikerassefa
በአዳማ ከተማ “በኮሮናቫይረስ ምክንያት ረዳቱን መልስ አይጠይቁ” የሚል መልዕክት ለጥፈው የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት አሽከርካሪ እና ረዳት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስተወቀ።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Breaking AAU የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ቤታችሁ እንድትሄዱ ተወስኗአል:: @YeneTube @Fikerassefa
በመላው ሀገሪቱ ያሉ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎችን ከግቢ ለቃችሁ ውጡ የሚል ማስታወቂያ እየተለጠፈ እንደሆነ የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በትራንስፖርት ጊዜ ችግር እንዳይፈጠር የራሱን ትራንስፖርት ስለሚያዘጋጅ ሁሉም ተማሪዎች Student Council ቢሮ እየመጣችሁ ስም እና የሚሄዱበትን ሀገር እንዲያስገባ እናሳስባለን ሲል አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አስታውቋል ።

AAU/ EiABC
@Yenetube @Fikerassefa
ዩንቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንዲያሰናብቱ መወሰኑን የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ውሳኔው የተወሰነው በኮሮና ቫይረስ መክንያት ተማሪዎች የከፋ ችግር እንዳይደርስባቸው እንደሆነ ተገልጿል። ዩንቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በራሳቸው ትራንስፖርት ወጪ አጓጉዘው ወደ የቤተሰቦቻቸው አንዲያደርሱ መወሰኑን በሚኒስቴሩ የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደቻሳ ጉርሙለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ዩንቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን የሚያሰናብቱት ለምን ያህል ጊዜ ነው? በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም አቶ ደቻሳ አሁን ላይ ለዚህ ያህል ጊዜ ማለት የሚከብድ በመሆኑ የቫይረሱ ስርጭት ሰዎችን በማይጎዳበት ጊዜ ለተማሪዎቹ ጥሪ ይደረግላቸዋል፣ አስከዛው ግን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይቆያሉ ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።አሁን ላይም በርካታ ዩንቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለማጓጓዝ እንዲያመች በሚል ተማሪዎቹ አድራሻዎቻቸውን እንዲሞሉ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከዩንቨርሲቲዎች አረጋግጧል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው መርካቶ ምዕራብ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አልኮልን ከእስፕሬይ፣ ፎርማሊን እና ሽቶ ጋር ቀይጠው የሸጡ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢምግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ፓስፖርት መስጠት አቆማለሁ አለ፡፡

ኤጀንሲው አዲስም ሆነ የሚታደስ ፓስፖርት ከነገ ጀምሮ እንደማይሰጥ የነገሩን የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ደሳለኝ ተሬቻ ናቸው። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል ውሳኔው መተላለፉን ከኃላፊው ሰምተናል፡፡ለመንግስታዊ ቁልፍ ጉዳዮች ብቻ ካልሆነ በየትኛውም የድጋፍ ደብዳቤ ለተገልጋዮች ፓስፖርት መስጠት እንደሚቆም ነግረውናል፡፡

የመግቢያ ቪዛን በተመለከተም የትኛውንም አይነት የመግቢያ ቪዛ ከነገ ጀምሮ መስጠት እናቆማለን ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ከዚህ ቀደም 4 ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ቢሮ ሲሰጥ የነበረው የመውጫ ቪዛ አገልግሎት ደግሞ ወደ ዋናው መስሪያ ቤት መዛወሩን ሰምተናል፡፡ለመንግስታዊ ቁልፍ ስራዎች ለሚጓዙ ሰዎች ይሰጣል የተባለው ፓስፖርትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መብረር ወዳቆመባቸው ሀገራት ለሚሄዱት የተከለከለ መሆኑን ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
1
በአርሲ ዞንና በአዳማ ከተማ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ግለሰብ ጋር ንኪኪ የነበራቸው 22 ግለሰቦች ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ዛሬ ወደ ቤታቸው መሸኘታቸውን የአዳማ ጤና መምሪያ ገለጸ።ጃፓናዊው ወደ አርሲና አዳማ ከተማ ጉዞ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
በጣሊያን እስካሁን የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 6,820 ደርሷል። የ24 ሰዐት ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ደግሞ 5,249 አዲስ ተጠቂዎች የተመዘገቡ ሲሆን 743 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ 69,176 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከማሳቹሴትስ

በቦስተን ማሳቹሴት ከተማ ዛሬ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማሳቹሴት ከተማን ማጠኗን ማሳቹሴት የሚገኝ የቻናላችን አባል ነግሮናል።

@Yenetube @Fikerassefa