YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጋምቤላ ኤርፖርት እስካሁን የመንገደኞች ሙቀት እየተለካ አለመሆኑ ተገለጸ።

በቀን ሁለት ጊዜ ማለትም ከአዲስ አበባ በአሶሳ አድርጎ ወደ ጋምቤላ እና ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው የሃገር ውስጥ በረራ እንደቀጠለ ነው፡፡ነገር ግን ተጓዦች ከጋምቤላ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ሊሄዱ ሲሉ እንዲሁም ከ አዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ የሚገቡ ተጓዞች ወደ አየር ጣቢያው ሲደርሱ ምንም አይነት የሙቀት መለኪያ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ካን ጋሏክ ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳን ክልሉ አምስት የሙቀት መለኪያ ማሽኖች እንዲኖሩት ቢደረግም እነዚህን ማሽኖች ከ ደቡብ ሱዳን ጋን በሚዋሰኑ አምስት ጣቢያዎች እንዲከፋፈሉ መደረጉን ነግረውናል፡፡ይሁን እንጂ ይህ መሳሪያ በ ከተማው በሚገኘው ኤርፖርት ተግባራዊ ያለመደረጉ ወረርሽኙን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን የጥንቃቄ ስራ እንደሚያጎድል ሃላፊው ገልጸዋል። በተጨማሪም መሳሪያውን ወደ ስፍራው ለማስገባት ጥረቶች ማድረጋችን መቀጠላቸውም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር-ኦነግ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቢሮውን መዝጋቱን አስታወቀ።

ምንጭ: ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ እና አፍጋኒስታን የኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችል ድጋፍ ሊያጸድቅ ነው!

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ40 ሃገራት የኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ መቀነስና መከላከል የሚያስችል የ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።ድጋፉ ኢትዮጵያና አፍጋኒስታንን ጨምሮ በሃገራቱ የኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖና ጉዳት ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድም በዚህ ሳምንት ለኢትዮጵያ እና አፍጋኒስታን ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን ሰነድ ተመልከቶ እንደሚያጸድቅ ነው የሚጠበቀው።ድጋፉ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ባንኩ ለአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በሚል ባለፈው ሳምንት ካጸደቀው 14 ቢሊየን ዶላር ለሃገራቱ የሚሰጥ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ አስታውቀዋል።

ባንኩ ባለፈው ሳምንት ዓለም ላይ የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ መቀነስና መከላከል የሚያስችል የ14 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ማፅደቁ ይታወሳል።ከዚህ ባለፈም ባንኩ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ትብብርና ከባንኩ የግሉ ሴክተር ዘርፍ ጋር በመሆን በ24 ሃገራት ተግባራዊ የሚደረግ የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ለመተግበር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች⬆️⬆️⬆️⬆️

@YeneTube @FikerAssefa
የእርዳታ ጥሪ !

የእህታችንን ህይወት የጓጓችለትን ምርቃቷን ሳታይ እንዳትቀጠፍብን የተማሪነት ድርሻችንን እንወጣ።

ምርቃቷን በጉጉት የምትተብቀው ቤተልሄም ተስፋዬ ዛሬ ጥቁር አንበሳ ተኝታ እህት ወንድሞቼ ህይወቴን ታደጓት እያለች የ እርዳታ ጥሪ ታስተላልፋች። በቻልነው አቅም በየትምህርት ክፍላችን በመልቀቅ የ እህታችንን ህይወት እንታደግ።

ዛሬ ብቻ በ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ 12,921 ብር (አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ አንድ ብር) መሰብሰብ ችሏል። ቀጣይ የታሰቡ ስራዎች በመላው ኢትዮጵያ ማስታወቂያ በመስራት የእህታችንን ህይወት እንታደጋለን።

በ አጠቃላይ ለህክምናው የሚያስፈልጋት ወጪ 50,000$ በ ሃገር ደረጃ 1,645,551 ማለትም አንድ ሚሊየን ስድስት መቶ አርባ አምስት ሺ አምስት መቶ ሃምሳ አንድ ብር ነው። በምንጠቀመው ማህበራዊ ሚዲያዎች በመልቀቅ እህታችን የደረሰባትን ህመም በማስተዋወቅ እንታደጋት።

ቤቲየ ተመርቀሽ ስትስቂ እናይሻለን እሺ እህት አለም። ለወገን ደራሽ ወገን ነው።

የንግድ ባንክ አካውንት

- 1000326460568
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የሊግ ካምፓኒ ዛሬ ከሰዓት በፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡን ይፋ አድርገዋል፡፡

ክለቦችም ተጫዋቾችን ለመጠበቅ በዚህ ጊዜ ልምምዶችን ማቋረጥ እንዳለባቸው የእግር ኳሱ አስተዳዳሪው አካል አሳውቋል፡፡

በደብረዘይት በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅታቸውን ሲያደርጉ የነበሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በኮሮና ስጋት ምክንያት ልምምዳቸውን ከነገ ጀምሮ እንደሚያቆሙ ከክለቡ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

via:- Hatric Sport
@Yenetube @Fikerassefa
በመላው ዓለም የተስፋፋውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመግታት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠር፣ በከተማና በመላው ዓለም ለምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በሙሉ!

ወቅታዊ የሰው ልጅ ሥጋት በመሆን በመላው ዓለም በፍጥነት በተስፋፋው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ ሥጋት ስለተከሰተ መንግሥታት ሀገርን ከጥፋት፣ ሕዝብን ከሞት ለመጠበቅ አዋጆችን እያወጡ ይገኛሉ፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ እምነትና ቀኖናን ጠብቆ ሃይማኖታዊ መመሪያ የመስጠት ሐዋርያዊ ኃላፊነት አለባት፡፡

ስለዚህ ቋሚ ሲኖዶስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት መሠረተ እምነትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ለሁሉም ካህናትና ለሕዝበ እግዚአብሔር ደኅንነት ሲባል የሚከተሉትን መመሪያዎች አስተላልፏል፡-

1. በሰሙነ ሕማማት እንደምናደርገው የእርስ በርስ መሳሳም ቀርቶ ራስን ዝቅ በማድረግ፣ እጅ በመንሳት ወይም በእማሄ ሰላምታ በማቅረብ እንዲፈጸም፣

2. ወረርሽኙ በሰዎች መሰባሰብ የሚስፋፋ ስለሆነ ማናቸውም መንፈሳዊ ጉባኤያት፣ የትምህርት ክፍለ ጊዜያት፣ ወደ ገዳማትና አድባራት የሚደረጉ ጉዞዎች እና ምዕመናን የሚሳተፉባቸው ታላላቅ መርሐ ግብሮች ለጊዜው እንዲቋረጡ፣

3. ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገባም ሆነ አሰፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ እጆቻንን በመታጠብና ዘርዘር ብሎ በመቆም ሥርዓተ አምልኮ እንዲፈጸም፣

4. ዓመታዊ የንግሥ ክብረ በዓላት በቅዳሴና በማኅሌት ታስበው ክብረ በዓላቱ በሌላ ጊዜ እንዲከበሩ፣

5. የጉንፋን ምልክት ያለባቸው ለሌሎች እንዳያስተላልፉ በቤታቸው በጥንቃቄ ተለይተው በጸሎትና በሕክምና እንዲቆዩ፣ ከቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋቸውን መንፈሳዊ አገልግሎትም በልዩ ሁኔታ እንዲያገኙ፣

6. በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የተስፋ ልዑክ በመሆን እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ተደራጅቶ ተልዕኮውን በአስቸኳይ እንዲጀምር

7. ሥርዓተ ቅዳሴን በተመለከተ፡-

• በቤተ መቅደስ ቀዳስያን በሆኑት ልዑካን ብቻ ሥርዓተ ቅዳሴው እንዲፈጸምና ሌሎች አገልጋዮች በቅድስቱ ዘርዘር ብለው በመቆም እንዲያገለግሉ፣

• በዕለቱ ለሚቆርቡ ምዕመናን ለአረጋውያን፣ ለወጣቶችና ለሕፃናት የፈረቃ ተራ በማዘጋጀት ቆራቢዎች ብቻ ወደ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ዘርዘር ብለው በመቆም እንዲያስቀድሱ፣

• ሌሎች ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ቢያንስ ሁለት የትልቅ ሰው እርምጃ ያህል በመራራቅ ቆመው እንዲያስቀድሱ፣

• የቅዳሴ ጠበል በየግል መጠቀሚያ ምእመናን በየቆሙበት ቦታ በጥንቃቄ እንዲሰጥ፣

• ሌሎች ከቅዳሴ ጋር የተያያዙ ዝርዝር የአፈፃፀም ጉዳዮችን ግብረ ኃይሉ አዘጋጅቶ በቅዱስ ሲኖዶስ በማጸደቅ ለአህጉረ ስብከት በሚልከው መመሪያ መሠረት ተግባራዊ እንዲደረግ፤

8. ከሥርዓተ ቅዳሴ በተጨማሪ እንደ ስብሐተ ነግሕ፣ ሰዓታት፣ ቁመተ ማኅሌት፣ ጥምቀተ ክርስትና፣ ጸሎተ ፍትሐት፣ የመሳሰሉ አገልግሎቶች ለሥርዓቱ በሚያስፈልገው ቁጥር ብቻ እና በውሱን ሊቃውንት በተራ እንዲፈፀም፣

9. ወረርሽኙ ከዓለም እንዲጠፋ ካህናት ብቻ በቤተ መቅደስ፣ በዐውደ ምኅረትና በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ጸሎተ እጣን በማድረስ ማዕጠንት እንዲፈጽሙ፣

10. በማኅበራዊ ግንኙነት በደስታ፣ በሐዘን፣ በእድር፣ በሥርዓተ ቀብር አፈፃፀምና በመሳሰሉት መሰባሰቦች በሽታው እንዳይሠራጭ አገልግሎቱ በውስን የሰው ቁጥር በጥንቃቄ እንዲፈፀም፤

11. ምዕመናን ራሳቸውን እየጠበቁ በቫይረሱ የተጠቁና አገግመው የወጡ ወገኖችን፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ከሃይማኖትና ከምግባር የወጣ መገለልና ጥቃት እንዳይደርስባቸው በክርስቲያናዊ ፍቅርና በኢትጵያዊ ጨዋነት እንክብካቤ እንዲደረግላቸው፣

12. ለነዳያን እና ለተቸገሩ ወገኖች አስፈላጊው ማኅበራዊ እና ቁሳዊ እገዛ በሁሉም አጥቢያዎች እንዲደረግ፣

13. ቤተ ክርስቲያንን ከማይወክሉና ቀኖናዊ ካልሆኑ አሳሳች መረጃዎች በመቆጠብ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መምህራን፣ ሰባክያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጡ መመሪያዎችን በየአጥቢያችሁና አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ እንድትፈጽሙ እና እንድታስፈጽሙ ተወስኗል፡፡

በአጠቃላይ በበሽታው እስካሁን ለተያዙት፣ በጊዜያዊ ማቆያ ለሚገኙት በሙሉ እግዚአብሔር አምላካችን ምህረቱን እንዲሰጥልን እንጸልያለን፤

በመላው ዓለም ዜጎቻቸውን በበሽታው ለተነጠቁ ሁሉ መጽናናቱን እንዲሰጥልን ያረፉትንም እንዲምርልን እግዚአብሔርን በጸሎት እንጠይቃለን፤

በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን የራሳችሁና የሌሎች ሕይወት ከወረርሽኙ እንዲጠበቅ እንዲሁም የበሽታው ሥርጭት እንዲቆም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እያሳሰብን የተሰጡት መመሪያዎች ወረርሽኙ እስኪጠፋ ድረስ የጸኑ እንዲሆኑ በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡

ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ዓለማችንን ከጥፋት የሰውን ልጅ ሁሉ ከመከራ ሞት ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጣሊያን እስካሁን የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 6077 ደርሷል። የ24 ሰዐት ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ከሆነ ደግሞ 4,789 አዲስ ተጠቂዎች የተመዘገቡ ሲሆን 602 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ 63,927 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጀርመኗ መራሄተ መንግሥት አንጌላ መርክል በምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው መረጋገጡን የጀርመን መንግሥት ቃል አቀባይ ተናገረ!

አርብ ዕለት ለመርክል የፀረ-ኒሞኒያ አምጪ ተህዋስ ክትባት የሰጣቸው ዶክተር በኮሮና መያዙን ተከትሎ፣ መራሄተ መንግስቷ ራሳቸውን አግልለው ነበር፡፡የ65 ዓመቷ መርክል በቀጣይ ቀናትም በተደጋጋሚ ይመረመራሉ ተብሏል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሳሪስ አከባቢ ባቡር ሰው መግጨቱን ሰምተናል።

የተገጨው ግለሰብ በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ተነግሮናል።

@Yenetube @Fikerassefa
በማይነማር የመጀመሪያዎችን ሁለት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘታቸውን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በማስታወቂያ የሚገኝ ገንዘብ ለእርዳታ ስለ ማዋል :-

የኔቲዩብ ፈጣን እና ወቅታዊ ሚዛናዊ መረጃዎች ስናደርስ አመታትን ያሳለፈ ድርጅት መሆኑን እናንተው ቤተሰቦቻችን የምትመሰክሩት እውነት ነው።

አለም አቀፍ ወረርሽኝ እንደሆነ በአለም የጤና ድርጅት የታወጀው የኮቪድ-19ን ለአለም ብሎም ለሀገራችን ስጋት መሆኑን ተከትሎ፣ መረጃዎችን ብቻ እንድናደርስና ማስታወቂያ እንድናቆም የተለያዩ ሰዎች መልዕክቶች እየደረሱን ይገኛሉ የኔቲዩብም የእናንተን ጥያቄ በመቀበል እንዲሁም የደንበኞቻችን ፍላጎት ጋር በማስታረቅ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ኮሮና ቫይረስ ከተጠቂ ከተገኘበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ለየኔቲዩብ ለማስታወቂያ የተከፈሉ/የሚከፈሉ ክፍያዎችን አቅም ለሌላቸው ለክልል ነዋሪዎች፣ የንፅህና መጠበቂያ መግዣ እንዲውል ይደረጋል።

በመጀመርያ እቅዳችን የያዝነው በሀዋሳና አካባቢዋ ለሚገኙት ለማዳረስ ሲሆን እኛ ከምናደርገው እርዳታ በተጨማሪ መርዳት የምትፈልጉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ በ @Fikerassefa ማናገር ትችላላችሁ።

ሀዋሳ የምትገኙ በዚህ ተግባር ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲህም መርዳት የምትፈልጉ በነዚህ አካውንቶች ማናገር ትችላላችሁ።

- በቴሌግራም t.me/Fikerassefa
- በስልክ +251991467259

እናመሰግናለን!
Protect your self from Virus⬆️
እራሳችሁን ጠብቁ ከቫይረሱ

ለወዳጆ ምልክቱን አስተላልፉ
ስለ ኮሮና ቫይረስ ኮቪድ 19 በክልሎች አገልግሎት የሚሰጡ ነጻ የስልክ መስመሮች:-

Tigray:- 6244
Oromia:- 6955
Amhara:- 6982
South N.N.P:- 6599
Dire Dawa:- 6407

#COVIDー19
@YeneTube @Fikerassefa
ለዋሽንግተን ዲ.ሲ. ነዋሪዎች የቀረቡ ጠቃሚ መረጃዎች :-

----- አምባሳደር ፍፅም አረጋ ------

አንዳንድ ዲ.ሲ. ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስ መስፋፋቱን ተከትሎ አስተዳደሩ ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ሌሎች ህጎች ሰራተኞች ከስራ ተለይተው፣ የንግድ ተቋማትም ተዘግተው እቤት በመዋል የቫይረሱን ስርጭት እየተከላከሉ ቢሆንም ኑሮአቸው እንዳሳሰባቸው በገለጹት መሰረት የሚከተሉ መረጃዎች ቀረበዋል:-

1) በዲስትሪክቱ ስለበሽታው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት: https://t.co/89ZVI6ObAh ይጫኑ፣

2) በዲስትሪክቱ በልዩ ሁኔታ እስከ ኤፕሪል 27/20 ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑ ተቋማትን ለማወቅ: https://t.co/qWausMjqlL ይጫኑ፣ ለምሳሌ ቆሻሻ አወጋገድ በተለመደው መልኩ እንደሚቀጥል፤ የንግድ ፈቃድ ኦንላይን በ https://t.co/iuq4Sv17HL ማሳደስ እንደሚቻል፣

3) ከስራ ለተፈናቀሉ ጥቅማጥቅምና መረጃዎችን ለማግኘት: https://t.co/5AFiMeyEFR

4) የአነስተኛ ቢዝነሶችን ጉዳት ለመቀነስ የፌዴራል መንግስት ከከፈተው የብድር ዕድል ለመጠቀም: https://t.co/J100IWqjR5 መመልከትና https://t.co/DVtChsNibj ማመልከት ይችላሉ::


5) በአስቸኳይ ጊዜ አወጁ ወቅት የቤት ኪራይ፣ የኤሌክትሪክ፣ የጋዝ እና የውሃ ክፍያ መጠየቅም ሆነ ማቋረጥ የማይቻል መሆኑን፣ የዲ.ሲ. ፐብሊክ ትምህርት ቤቶቸ የነጻ ምገባ የሚሰጥ መሆኑን፣ ዝርዝሩን (202) 727 5355 በመደወዕል መጠየቅ ይቻላል፣

6) ማደሪያ የሌለው ጊዜያዊ መጠለያ ለማግኘት (202)399 7093 /311 መደወል ይቻላል፣

በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች ለየአካባቢው ተስማሚ መረጃ በማቅረብ እንድታግዙ እየጠየቅሁ ከበሽታው ተጠበቃችሁ ኑሮአችሁ እንዲቃና እመኛለሁ!
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ (1) ተጨማሪ ሰው በመገኘቱ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት (12) ደርሷል፡፡ ይህ ታማሚ የ 34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከዱባይ ወደ ሀገር ውስጥ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም የገባ ነው፡፡

ግለሰቡ የህመም ምልክት የነበረው በመሆኑ በመጋቢት 13፣2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄደ ሲሆን ተቋሙም ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖረት በማደረግ በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ግንኙነት የነበራቸው 15 ሰዎች በክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
መጋቢት 14 ፣ 2012 ዓ.ም
@YeneTube @FikerAssefa
ለኮሮና ቫይረስ ፈዋሽ ነው ተብሎ በፕሬዝዳንት ትረምፕ የተገለፀው ንጥረ ነገር ሰው ገደለ

ፕሬዝዳንት ትረምፕ ለኮሮና ቫይረስ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም ብለው ያሉትን" ኮሎሮኮየን" የተባለ ንጥረ ነገርን የወሰዱ በ60 ዎቹ ያሉ አሜሪካዊ ባልና ሚስቶች ባልያው ትናንት ሲሞት ሚስትዬው በፅኑ ታማለች ሲል የእንግሊዙ ዲይሊ ስታር ጋዜጣ አስነብቧል። ባልና ሚስቱ ገና ኮሮና ቫይረስ ይኑርባቸው አይኑርባቸው ሳይረጋገጥ ነው የህመም ስሜት ሲሰማቸው ነበር ንጥረ ነገሩን መዋጥ የጀመሩት።

Via:- ተስፋዬ ጌትነት
@Yenetube @Fikerassefa
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ማምረት መጀመሩ ተነገረ፡፡

ምርቱን የሚሰራው የዩኒቨርስቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነው ተብሏል፡፡የእጅ ማፅጃው የኮሮና በሽታን ለመከላከል አገልግሎት ላይ እንደሚውልም ሰምተናል፡፡ዩኒቨርስቲው በኢትዮጵያ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር እጥረት መኖሩን ከግምት በማስገባት መስራቱን የኮሌጁ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር ታምራት ባልቻ መናገራቸውን ወላይታ ታይምስ ፅፏል፡፡የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘሩ ትክክለኛ ኬሚካላዊ ኡደትን ተከትሎ የተሰራ ነውም ብለዋል፡፡ለጊዜው የኮሮና ቫይረስን ለመከላል በተቋቋመው ግብረ ኃይል ውስጥ ለሚሰሩ የህክምና ባለሞያዎች የሚከፋፈለው ይህ ምርት በቀጣይ በብዛትና በተሻለ ጥራት ይመረታል ተብሏል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አውቶብስ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው መለስተኛ መናኸሪያ አገልግሎት ወደሌሎች መናኸሪያዎች እንዲዛወር መደረጉን የትራንስፖርት ባለሥልጣን አመለከተ።

ባለሥልጣኑ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመቀነስ በመናኸሪያዎች የሰዎችን ጥግግት ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።ባለሥልጣኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የሰዎች ጥግግትን በመቀነስ ማኅበራዊ ርቀትን ለማስጠበቅ እየተሞከረ ይገኛል። መናኸሪያዎች ከፍተኛ የሕዝብ ምልልስ ያለበትና የተሳፋሪ ጥግግት በብዛት የሚታይበት በመሆኑ ማኅበራዊ ርቀት በማስጠበቅና ንክኪን በመቀነስ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት እየሰራ እንደሚገኝ አመልክቷል።

የሰው ጥግግትን ለመቀነስ በአዲስ ከተማ መለስተኛ መናኸሪያ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሌሎች መናኸሪያዎች በማዛወር አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ጠቁሟል።በዚህም መሠረት የሆሳዕና፣ ቡታጅራ፣ ቱሉቦሎ፣ ወሊሶ፣ ወልቂጤና ሰባት ቤት ጉራጌ ሥምሪቶች በአየር ጤና መናኸሪያ የሚሰጡ ሲሆን የአዳማና ቢሾፍቱ ሥምሪቶች ደግሞ በላምበረት እና በቃሊቲ መናኸሪያዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተዛውረው አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።

ባለሥልጣኑ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት አዲስ አበባ ባሉ መናኸሪያዎች መንገደኞች እጃቸውን እንዲታጠቡ፣ የእጅ ማጽጃ ኬሚካሎችን እንዲጠቀሙና ተሽከርካሪዎች በአልኮል እንዲያጸዱ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል። የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎች ባለሥልጣኑ እያከናወነ ሲሆን ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልም ኮሚቴ አቋቁሞ በሁሉም መናኸሪያዎች ክትትል እያደረገ መሆኑን አመልክቷል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa