YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኮረና ቫይረስ ተጠርጥራ በአክሱም ለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደርግላት የነበረቸው ተማሪ በተደረገላት የናሙና ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆኗ ተረጋግጧል።

-ዩንቨርስቲው
@YeneTube @FikerAssefa
በትምህርት ላይ ያሉ የህክምና ተማሪዎች እራሳችሁን አዘጋጁ - ሪፓርተር

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ኮሚቴው በትምህርት ላይ ያሉትን ጨምሮ፣ ሁሉም የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ተመልከቱት⬇️
https://t.co/t6dbMJQ5I0
የህክምና ቁሳቁሶች መድረሳቸውን በማስመልከት መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል።በስፍራው ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተገኝተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር በአዲስ አበባ የነበራቸውን ስብሰባ አራዘሙ!

የህዳሴ ግድብ ውዝግብ አንደኛው የመወያያ አጀንዳ ነበር የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ሊቀመንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲርል ራማፎዛ፣ በአዲስ አበባ ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓም ከኅብረቱ ኮሚሽን ጋር በአዲስ አበባ ሊያደርጉት የነበረውን ስብሰባ ለመጪው ወር እንዲተላለፍ ወሰኑ።የአፍሪካ መሪዎች ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ ባደረጉት ስብሰባ የኅብረቱ ጠቅላላ ጉባዔ ሊቀመንበር አድርገው የመረጧቸው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ተይዞ የነበረውን ስብሰባ የሰረዙት፣ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በአገራቸው የተፈጠረውን አስቸኳይ ሁኔታ ለመምራት መሆኑ ታውቋል።

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት እንዲፈታ ኢትዮጵያ በያዘችው አቋም መሠረት ጥያቄዋን ለኅብረቱ ሊቀመንበር ፕሬዚዳንት ራማፎዛ ማቅረቧ ያስታወሱት የሪፖርተር የዲፕሎማቲክ ምንጮች፣ ፕሬዚዳንቱ ከኅብረቱ አመራሮች ጋር ሊያደርጉት በነበረው ውይይት ከተያዙ አጀንዳዎች መካከልም ይህ ጉዳይ እንደሚገኝበት ጠቁመዋል።የኅብረቱ ሊቀመንበር በአዲስ አበባ ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ ኃላፊነቱን ከተረከቡ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከኅብረቱ ኮሚሽነሮች ጋር ተገናኝተው ውይይት የሚያደርጉበት፣ እንዲሁም የዓመቱን ቀዳሚ የሥራ ዕቅዶቻቸውን የሚነድፉበት ነበር።

ታስቦ የነበረው ይህ ስብሰባ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በታቀደው ቀን ማካሄድ ባይቻልም፣ የጋራ ስምምነት በሚደረስበት ቀን በቀጣዩ ወር ውስጥ እንደሚካሄድ ታውቋል።የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ በህዳሴ ግድቡ ውዝግብ ላይ እያደረጉ በሚገኘው የዲፕሎማሲ ጉዞ ከተካተቱ መዳረሻ አገሮች መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ የነበረች ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ለፕሬዚዳንት ራማፎዛ የተላከ ደብዳቤ ለአቻቸው የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማድረሳቸው ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች በማምራት ፕሬዚዳንት አልሲሲ የላኳቸውን መልዕክቶች ለየአገራቱ ማድረሳቸው ታውቋል። በኢትዮጵያ በኩልም ተመሳሳይ የዲፕሎማሲ ጉዞዎች በአፍሪካና በአውሮፓ መደረጋቸው ይታወሳል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
የጤና ተቋማት ተገልጋዮችና ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) - ጎንደር ዩንቨርስቲ

ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በሽታዉን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመግታትና ለመቆጣጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ ክትትል የሚሹ የተለያዩ ወሳኝ እርምጃዎች በመወሰድ ላይ ናቸው::

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዚህ ወቅት ወደ ሆስፒታል ወይም ወደ ማንኛውም ጤና ተቋም የሚመጡ የታካሚዎችን፣ የአስታማሚዎችንና የጠያቂዎችን ቁጥር ለተገልጋዮች፣ ለቤተሰባቸውና ለማህበረሰብ ደህንነት ሲባል መቀነስ የግድ ይላል::

ስለሆነም ታካሚዎች፣ አስታማሚዎችና ጠያቂዎች የሚከተሉትን ምክረ ሃሳቦች መተግበር ቢችሉ የበሽታዉን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበርክታሉ::

ሀ. ታካሚዎች

ድንገተኛ እና አጣዳፊ ህመም ካልተከሰተ ወይም ክትትል የሚሻ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር ወደ ጤና ተቋም አለመሄድ:: ከዚህ በተጨማሪም ለኮሮና በሽታ ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ማለትም እድሜአቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የልብ ችግር ያለባቸው፣ የመተንፈሻ አካል ህመም (ለምሳሌ አስም) ያለባቸው፣ የስኳር ህሙማን፣ የካንሰር ታማሚዎች፣ ወዘተ የሚወስዱትን መድሃኒት/ቶች በአግባቡ እየወሰዱ በተቻለ መጠን ከቤት አለመዉጣትና ከሰዎች ጋር ንክኪን በማስወገድ እራስን ከኮሮና ቫይረስ መጠበቅ:: በራስ ለመወሰን አስቸጋሪ ሁኔታ ከገጠመ በ8335 ወይም በ444 ወይም ሌሎች ክልላዊ መስመሮች/የተቋማት ስልክ ቁጥሮች ደዉሎ ምክረ ሃሳብ መጠየቅ::

ለ. አስታማሚዎች
ለህክምና ወደ ሆስፒታል የሚሄዱ ታካሚዎች (ከህፃናት/ልጆች/አቅመ ደካሞች በስተቀር) ከተቻለ ያላስታማሚ መሄድ:: አስታማሚ ይዞ መሄድ የግድ ከሆነ ደግሞ አስገዳጅ ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ አንድ አስታማሚ ብቻ አብሮ እንዲሄድ ማድረግ::

ሐ. ህሙማን ጠያቂዎች
ወደ ሆስፒታልና ጤና ተቋማት ከመሄድ ተቆጥቦ በስልክ ብቻ ከታካሚዎች/ከአስታማሚዎች/ከቤተሰብ ጋር ግንኙነት ማድረግ::

እነዚህ ተግባራት የኮሮና በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ እገዛ ከማድረጋቸዉም ባሻገር በጤና ተቋማትና ሙያተኞች ላይ የሚደርሰውን መጠነ ሰፊ ጫና ለመቀነስ ወሳኝ ናቸው:: በተጨማሪም የጤና ተቋማት ያላቸውን ዉስን የሕክምና ግባት እንዲቆጥቡና ቅድሚያ ለሚሰጠው ታካሚ ቅድሚያ ሰጠው ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላል::

ይህ ወረርሽኝ የጤና ስርዓቱን ከማዳከሙ ባሻገር የሀገር ኢኮኖሚን ስለሚያደቅ ያለውን ዉስን ሃብት በአግባቡ መጠቀም እንዲቻል ተገልጋዮች ግለሰባዊና ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት የጤና ተቋማት መደበኛ ስራቸውን መቀጠል እንዲችሉ ማገዝ ይኖርባቸዋል::
እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎብኘን!

ዶ/ር ወርቅአገኘሁ ኃይሉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኩላሊትና የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት።

Via:- University of Gonder
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️ጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት የጃክ ማ ፋውንዴሽን የተላኩ የፊት መሸፈኛ እና የህክምና ቁሳቁሶች መድረስን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

- Samuel Getachew
@Yenetube @Fikerassefa
ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል!

በመጪው ሃምሌ ወር ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የቶኪዮው ኦሎምፒክ አትሌቶች ሆቴል ገብተው ይሰልጥሉ አይሰልጥኑ የሚለው የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቃላት ጦርነት ውስጥ ግብተዋል።የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ደራርቱ ቱሉ ከ 100 በላይ አትሌት አንድ ሆቴል በግባት የለበትም፣ ይህ ለህይወታቸው ያሰጋል በሚል ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል።ይህንን የተቃወመው በአሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ግን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባገኘሁት ፈቃድ መሰረት አትሌቶችን ሆቴል አስገባለሁ ሲል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ እና ገብረ እግዚአብሄር ገብረ ማሪያም እንዲሁም አባ ዱላ ገመዳ ተገኝተው ነበር።‹‹ሃይሌን እና ገብረ እግዚአብሄር ራሳቸው ቢሆኑ የማያደርጉትን ለሌላ አትሌት ለምን ይወስናሉ፤ ከኮሚቴው ይልቅ እኛ እንቀርባቸዋለን›› ሲሉ አትሌት ደራርቱ ወቅሰዋቸዋል። ‹‹የአትሌቶች ዝግጀት አካላዊ ንክኪ ያለው በመሆኑ፤ ምግብ ሲበሉ እና በአውቶቡስ ሲጓጓዙ የኮሮና ቫይረስ መጋለጣቸው ስለማይቀር ይህንን ውሳኔ አሳልፌአለሁ›› ሲሉም ዛሬ ጠዋት በኢቲቪ ቀርበው ተናግረዋል።

‹‹እኔ አሻንጉሊት አይደለሁም፣ ልንሰራ ነው የተቀመጥነው›› ያሉት ደራርቱ ‹‹የፈረደበት ብሄር ገበቶ ከሆነ ቢታረም፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሎጂሰትቲክስ እንጂ እንደዚህ አይነት ውሳኔ መስጠት አይችልም። አትሌቶቹ ልጆቼ ናቸው፤ ባሉበት ልምምድ መስራታቸውን ይቀጥላሉ፤ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እያለ ያለው ግብፅ አባይ ላይ እያለች ያለውን ነው፤ እንዴት ነው በአትሌቲክስ ጉዳይ ፌዴሬሽኑ የማያገባው›› ሲሉ ደራርቱ ተናረግዋል።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስገዳጅ ምክንያት ካልገጠመን በቀር ቤት እንቆይ:፡
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከመጋቢት 14( ነገ) ጀምሮ ከግቢ መውጣትም ሆነ መግባትም ተከልክሏል።

- ተጨማሪውን ከፎቶው ላይ ያንብቡት
@Yenetube @Fikerassefa
ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ማህበራሰብ በሙሉ ⬆️

- ካፌ ያልሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊውን ገንዘብ ከፍለው ካፌ እንዲጠቀሙ ይደረጋል።

- ቱሪስቶች ወደ ዩንቨርስቲ ግቢዎች መግባት አይቻልም

- ከተማሪ ካፍቴሪያ ውጪ የሆኑ ማንኛውም ምግብ ቤቶች ስታፍ ካፍቴሪያዎች ዝግ ይሆናሉ።

- ትምህርት በኢሜል ይቀጥላል........


----ተጨማሪ ከፎቶው ላይ ያንብቡ ----

@Yenetube @Fikerassefa
ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሰራተኞች በሙሉ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ተማሪዎች የቫይረሱን ምልክቶችና መከላከያ መንገዶቹን ጠንቅቀው በማወቅ እራሳቸውን እንዲከላከሉ አሳስቧል፡፡በመሆኑም ተማሪዎች በዶርማቸው ሆነው ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲቻል ዩኒቨርሲቲው እያሳሰበ ከሰኞ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ፡-

1. ማንኛውም ተማሪ ለማንኛውም አይነት አገልግሎት ከግቢ መውጣትም ሆነ መግባት የማይችል መሆኑን፣

2. የNon-Cafe ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ባሉት ሶስቱ የተማሪ ካፊቴሪያዎች እንዲመገቡ የተመቻቸ መሆኑን፣

3. ከአሁን በፊት ከግቢው ለተግባር ልምምድ የወጡ ተማሪዎች በተመደቡበት ቦታ እየሰሩ እንዲጠብቁ፣

4. በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቤተሰብ የሄዱ ተማሪዎች ወደ ግቢ መግባት እንደማይችሉና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጥንቃቄ እያደረጉ እንዲቆዩ፣

5. ተማሪዎች ወደ ዋናው ምግብ ቤት ሲገቡም ሆነ ሲመገቡም ሳይተፋፈጉ /በቡድን ሳይሆኑ በተናጠል/ ተገቢውን ርቀት ጠብቀው እንዲስተናገዱ እያሳሰብን የመመገቢያ የሰዓት ፕሮግራም በየኮሌጆቻቸው ሊወጣ የሚችል መሆኑን፣

6. የጋራ መጠቀሚያ በሆኑት ፑል ቤቶች፣ዲ.ኤስ.ቲቪ /DSTV/፣ካፍቴሪያዎች ላይ በቡድን ሆኖ መቀመጥና መጠቀም የማይቻል መሆኑን፣

7. የተማሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል ሁሉም መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች መግባት አይችሉም፡፡ሆኖም ለስራው የሚያስፈልጉ የዩኒቨርሲቲው የምግብ ቤት ሰራተኞች፣ ከትምህርት ክፍል በላይ ያሉ የአካዳሚክ ኃላፊዎች/ዲኖችና ተባባሪ ዲኖች/፣ንዑስ የስራ ሂደት መሪዎችና ዳይሬክተሮች፣ ሁሉም ሹፌሮች፣የውሃና የመብራት ጥገና ሰራተኞች፣የክሊኒክ ሰራተኞች፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች መምህራን፣የአመራር ጸሐፊዎች፣ሁሉም የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ሰራተኞች ከበር ላይ እጃቸውን እየታጠቡ እንዲገቡ የተወሰነ መሆኑን፣ እያሳወቀን ሰራተኞችና ተማሪዎች ቫይረሱን ለመከላከል የሚወሰዱ ጥንቃቄዎችን እንዲወስዱ ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

-ደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ(COVID-19) ቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ ሲባል የሚከተሉት ውሳኔዎች አስተላልፏል:-

1. የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ መግታት የሚቻል በመሆኑ ተማሪዎች ከሰኞ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከግቢ መውጣት የማይችሉ መሆኑን

2. ከግቢ ውጭ የሚኖሩ ተማሪዎች በሙሉ እስከ ነገ መጋቢት 14/2012 ዓ.ም ድረስ ወደ ግቢ እንዲገቡ እና የካፌ ተጠቃሚ ያልሆናቹ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው የምግብና መኝታ አገልግሎት እንድታገኙ ያመቻቸ መሆኑ

3. ከዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ውጭ የሆነ ማንኛውም ሰው በቀጣይ እስኪፈቀድ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባት የማይችል መሆኑን እንገልፃለን።

-ዩንቨርስቲው
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው እና በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎች የህክምና ክትትል እያደረጉ የሚገኙበት የየካ ኮተቤ ሆስፒታል
- 22 ዶክተሮች
- 150 ነርሶች
- 500 አልጋዎች ገደማ አሉት
* ሆስፒታሉ እስከ አርብ 174 ሰዎች አስተናግዷል

ምንጭ (ፎቶ)፦ ፎርቹን
@Yenetube @Fikerassefa
በአርባ ምንጭ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ጋር የተጠረጠረ የ36 ዓመት ግለሰብ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተሻለ ማናዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የ36 ዓመት ግለሰብ ጉንፋን መሰል ምልክቶች ታይቶበት አርባምንጭ ሆስፒታል ለህክምና በመጣበት ተጠርጥሮ ለጥንቃቄ ሲባል ለይቶ ማቆያ መዕከል ላይ እንዲቆይና የባለሙያ ክትትል እየተደረገለት ይገኛል፡፡

ግለሰቡም በቀን 07/07/2012 ዓ.ም. ለአንድ ቀን በኬንያ ለንግድ የተንቀሳቀሰ በመሆኑና ኬንያ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት አገር በመሆኑ ምክንያት ግለሰቡ ሊጠረጠር ችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግለሰቡ በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ያሉት አቶ ተሻለ ከግለሰቡ ጋር ንኪኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከተጠርጣሪዉ ግለሰብ በዛሬዉ ዕለት ናሙና ተወስዶ በምርመራ እንዲረጋገጥ ከክልል ጤና ቢሮ ጋር በጥምረት እየተሰራን ይገኛል ፡፡

ህብረተሰቡ በምርመራ ባልተረጋገጠ መረጃ መረበሽና መደናገር እንደሌለበት አቶ ተሻለ አሳስበዋል፡፡
@Yenetube @FikerAssefa
ኤምሬትስ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሁሉንም የመንገደኛ በረራዎቹን፣ ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ እንደሚሰርዝ አስታውቋል።
@Yenetube @FikerAssefa
የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ያልጀመሩና ያቋረጡ ሰዎች ለኮቪድ19 ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው ተባለ!

የዓለም አቀፍ ወረርሺኙ ኮቪድ19 በሽታ የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች ላይ ጫናው የበረታ እንደሆነ የዓለም የጤና ድርጅት በተደጋጋሚ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ከ 600 ሺህ በላይ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ዜጎች አሉ ተብሎ ሲገመት ከዚህ ውስጥ ከ 110 ሺህ በላዩ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተመርምረው ያላወቁ፣ አውቀው መድሃኒት መውሰድ ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ እንደሆኑ ሪፖርቶች ያሳያሉ።ኤች አይ ቪ ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚሰራው የፖፑሌሽን ኢትዮጵያ ባልደረባ የሆኑት ቤዛዊት አድማሱ እንደሚሉት መድሃኒታቸውን ባግባቡ እየወሰዱ ያሉ እና በሽታ የመከላከል አቅማቸው በመደበኛ ሁኔታ ላይ ያሉ ሰዎች የተለየ ስጋት የለባቸውም። ነገር ግን አምስቱን የኮቪድ19 የመከላከያ እርምጃዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም ላላቸው ሰዎች ሲባል ባግባቡ መተግበር ይገባቸዋል ይላሉ።

‹‹ ቫይረሱ ይኖርብኛል ብለው ለመጠርጠር በቂ ምክንያት ቢኖራቸውም ሄደው ለመመርመር ያልደፈሩ፣ ሃኪም የኤች አይ ቪ ቫይረስ እንዳለባቸው ቢያረጋግጥላቸውም መድሃኒቱን ያልጀመሩ ወይም ጀምረው ያቋረጡ ሰዎች ግን ቢቻል ዛሬ ወይም ነገ መድሃኒቱን መጀመር አለባቸው›› ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።‹‹ ከዚህ ባሻገር የአመጋገብ ስርአታቸውን እና የበሽታ መከላከል አቅምን የሚቀንሱ እንደ ሱስ ያሉ ልምዶችን በፍጥነት ማቆም እና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚመከሩ እርምጃዎችን ሳያወላውሉ መፈፀም አለባቸው›› እንደ ቤዛዊት ገለጻ።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ከካርጎ ውጭ ያሉትን ሁሉንም አለምአቀፍ በረራዎች አቋርጣለች። በዛሬው እለት በሀገሪቱ 8 አዲስ ተጠቂዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከ20- 57 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው። ከሰው ጋር በተያያዘ ባሮች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ የተወሰነ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቶች የቅርብ ዘመዶች ብቻ በተገኙበት እንዲፈጸም ተወስኗል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ አርሲ ዞን ከወትሮ የተለየ በረዶ ጣለ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ወቅቱን ያልጠበቀ እና ከወትሮ የተለየ በረዶ ጣለ።ከወትሮ የተለየ በረዶው ምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ወረዳ አሾካ ቀበሌ መጣሉን የዞኑ የመንግስት ኮሙዪኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።በረዶው በአካባቢው ያለውን መንገድ እና መኖሪያ ቤቶች መሸፈኑም ነው የተገለፀው።በአካባቢው የጣለው በረዶም የትራፊክ እንቅስቃሴውን እያስተጓጎለ መሆኑን የገለፀው ጽህፈት ቤቱ፤ አሽከርካሪዎች በስፍራው ላይ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩም አሳስቧል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa