YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
ኮሮና ቫይረስ - ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በመጪው ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ያሳድር እንደው ለመለየት ምርጫ ቦርድ "assessment" እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው። #ምርጫ2012 @Yenetube @Fikerassefa
"ለተራዘመ ጊዜ ችግሩ የሚቀጥል ከሆነ እና ምርጫ ቦርድ ስራውን መከወን የሚቸገር ከሆነ፤ በሚያደርጉት ጥናት መሰረት ውይይት የሚደረግ ይሆናል። የቦርዱ assessment ቀርቦ፣ የጋራ ስምምነት ሲደረስበት የመጨረሻው ውጤት የሚገለጽ ይሆናል"

- ጠ/ሚ አብይ
@Yenetube @Fikerassefa
አብን - ጎንደር ከተማን ችግር አስመልክቶ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ በጎንደር ከተማ እና አካባቢው የፀጥታ ችግር እንዳለ ለማወቅ ችሏል። የችግሩ መነሻ እና ከዚህ ደረጃ የደረሰበትን ምክንያት ምን እንደሆነ በትኩረት በማጣራት ላይ እንገኛለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት ሕግ አስከብራለሁ ብሎ በሚንቀሳቀስበት ማንኛውም ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የዜጎች ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ እንዲሆን አብን ይጠይቃል። ጉዳዩን በትኩረት በመከታተል ከሕዝባችን ጎን እንደምንቆም ለማሳሰብም እንወዳለን።

-አብን
@Yenetube @Fikerassefa
ከዘውዲቱ ሆስፒታል የትላከ መልክት:-

ወደ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ከመምጣቶ በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ይገንዘቡ

• ለአንድ ታካሚ አንድ አስታማሚ ብቻ ነው መግባት የሚፈቀደው

• አሁን ያለውን የ#COVID-19 ስርጭትን ለመግታት ማንኛውንም ታካሚዎች ባሉበት ሆነው በስልክ ብቻ ለመጠየቅ ይሞክሩ

• ለድንገተኛ ህክምና እና የሀኪም ቀጠሮ ከሌላቹ በስተቀር ወደ ሆስፒታላችን ባለመምጣት  ከ#COVID-19 ስርጭት እራሶን እና ቤተሰቦን ይጠብቁ

• እድሜያችሁ ከ 40 አመት በላይ ሆኖ ተላላፊ ያልሆነ ህክምና (ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ልብ ፣ ኩላሊት) ክትትል ያላችሁ በቀጠሮ ቀን የእርሶ ጤና አስችኳይ ሕመም ከሌሎት መድሀኒቱን የሚወስድሎት ወጣት ሰው ከቀጠሮ ካርድ ጋር አብረው እየላኩ ያለቀቦትን መድሀኒት ያሉበት ሆነው እዲወስድሎት ያድርጉ

• መግቢያ በሮች ላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አድርጉ የሚሏችሁን በአግባቡ ተግባራዊ አድርጉ (እጅን መታጠብ፤ የሙቀት ልየታ፤ ርቀትን ጠብቆ መሰለፍ . . .)

• በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፎን እና አፍንጫዎን በክንዶ ወይም መሀረብ/ሶፍት ይሽፍኑ

• አገልግሎት ለማግኘት በሚቆዩበት ጊዜ፤ ሰልፍ እና ወረፋ ሲጠብቁ ርቀቶን ቢያንስ በ1 ሜትር ይጠብቁ


ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል
@YeneTube @Fikeeassefa
በአዲስ አበባ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ለማቅረብ የተላለፈ ጥሪ

"በአዲስ አበባ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ለማከፋፈል ብዙ የውሃ ማመላለሻ ቦቴዎች ያስፈልጋሉ።ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጤና ሚኒስቴር በኩል የውሃ ማመላለሻ ቦቴዎች ለጥቂት ቀናት ማቅረብ የምትችሉ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 12 2012 ከረፋዱ 6 ሰዓት ድረስ በ0911649824 ወይንም 0920552119 በመደወል እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ለዚህም እቅድ ለማውጣት ፣ በፈረቃ ለመጠቀም እና ለተቀላጠፈ ስምሪት እንዲመች የባለቤት ስምምነት ፣ የመጫን አቅም ፣ የሹፌር ስልክ ፣ ታርጋ ቁጥር ፣ እና የመሳሰሉት በምዝገባ ወቅት የሚጠየቁ መረጃዎች ናቸው።የጤና ሚኒስቴር የውሃ ማመላለሻ ላላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች ይህንን መልዕክት በማጋራት እንድትተባበሩን በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስም በአክብሮት ይጠይቃል።"

-የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገራት የታገዱ፣ በአየር መንገዱ የተሰረዙ እና በከፊል የሚሰሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች!

- በሀገራት የታገዱ በረራዎች:
ሶማልያ፣ ጅቡቲ፣ ግብፅ፣ ሊባኖስ፣ ሱዳን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ናሚብያ፣ ባህሬን፣ ቻድ፣ ካሜሮን፣ ኒጀር፣ ማዳጋስካር፣ አንጎላ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ኮንጎ ኪንሻሳ፣ ርዋንዳ፣ ናይጄርያ (በከፊል)።

- በአየር መንገዱ የተሰረዙ በረራዎች:
ጣልያን፣ አየርላንድ፣ ስፔን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ፊሊፒንስ፣ ፈረንሳይ።

- ከዜጎች ውጭ ሌሎች ተጓዦችን የማይቀበሉ ሀገራት:
ካናዳ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጂየም፣ ኦስትሪያ፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኬንያ፣ ማሌዥያ።

Via:- Eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa
ፈረንሳይ ዛሬ ከ1617 ሰው በቫይረሱ ተጠቅቷል 78 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ፈረንሳይ 12,612 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬ በፈረንሳይ 450 ሰው ሞቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጣሊያን ዛሬ ከ5,986 ሰው በቫይረሱ ተጠቅቷል 627 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። በአጠቃላይ ጣሊያን 47,021 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከ ዛሬ በጣሊያን 4,032 ሰው ሞቷል።

የሟቾችና የተጠቂዎች ቁጥር በጣሊያን ዛሬ አሻቅባል ከሌላው ጊዜ በተለየ።
@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በቁጥር :-

- ጀንዋሪ 19: 100 ተጠቂ
- ጀንዋሪ 24: 1,000 ተጠቂ
- ጀንዋሪ 28: 5,000 ተጠቂ
- ፌብራሪ 12: 50,000 ተጠቂ
- ማርች 6: 100,000 ተጠቂ
- ማርች 14: 150,000 ተጠቂ
- ማርች 18: 200,000 ተጠቂ
- ማርች 19: 225,000 ተጠቂ
- ማርች 20: 250,000 ተጠቂ

@Yenetube @FikerAssefa
Protect your self from Virus⬆️
እራሳችሁን ጠብቁ ከቫይረሱ

ለወዳጆ ምልክቱን አስተላልፉ
በዳዉሮ ዞን እና ኮንታ ልዩ ወረዳ ለ15 ቀናት መብራት እንደሚቋረጥ ተገልጿል።

ለረጅም ጊዜ የዳዉሮ እና ኮንታ ህዝብ ሲያገለግል የነበረዉ የአባ ሳብስቴሽን የመሬት መደርመስ አደጋ ስለደረሰበት የቦታ ለዉጥ ለማድረግ ከ15/7/2012 .ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀናት መብራት እንደሚቋረጥ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዩትሊቲ ተገልጿል።

ምንጭ:የዳዉሮ ዞን መ/ኮ/ጉ መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጥፋት እያደረሰ ያለውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል የተለያዩ የጥንቃቄ ርምጃዎችን መውሰዱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ገለጹ፡፡

ከተወሰዱት የጥንቃቄ እርምጃዎች ውስጥ የታወቁ እና የቆዩ ህመም እንደ ስኳር፣የደም ግፊት እና ሌሎች ተመሳሳይ የጤና እክል ያለባቸው እንዲሁም እድሜያቸው የገፋ የኤጀንሲው አባላት በመኖሪያ ቤታቸው እንዲቆዩ ውሳኔ ላይ መደረሱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ሹመቴ ግዛው አስታውቀዋል::

ነፍሰጡሮች ላልተወሰነ ጊዜ ቤታቸው እንዲቆዩ መወሰኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ስርጭቱን ለመከላከል የተፋፈገ የቢሮ አቀማመጥ ያላቸው የስራ ክፍሎች በፈረቃ እንዲሰሩ የማድረግ እና እንደየስራ ባህሪያቸው በቤታቸው በመሆን በኦንላይን (online) ስራዎቻቸውን እንዲያከናውኑ ይሆናል ብለዋል፡፡ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም ከአቅመ ደካሞች እና ከነብሰጡሮች በስተቀር ሊፍት እንዳይጠቀሙ ከማስጠንቀቅ ባለፈ የሰዓት መቆጣጠሪያ (አሻራ) ማቋረጡ የሚታወስ ነው፡

ምንጭ፡-INSA
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ!

የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮጵያ የ500 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ያጸደቀ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 250 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ፣ 250 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ በብድር የተሰጠ ነው፡፡የገንዘብ ድጋፉ የተደረገው በአገሪቱ የተጀመረው የኢኮኖሚ ሪፎርምን ለመደገፍ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ጉግል ትምህርታዊ ኮሮናቫይረስ ድር ገፅ ይጀምራል ከኤን.ኤን.ን. ብራያን ፈንግ ስለ ደህንነት እና ስለ ወረርሽኙ መረጃ የያዘ ጉግል ቅዳሜ አንድ የኮሮናቫይረስ ትምህርት ድር ገፅ ጣቢያ ጀመረ ፡፡

እርምጃው የሚመጣው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፒን ጉግል አሜሪካን ሀገር አቀፍ የመፈተሻ ድር ገፅ ጣቢያን በመገንባት አሜሪካውያን መጠይቅ እንዲመልሱ እና በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የሙከራ አካባቢዎች እንዲሄዱ ሊያደርጉ እንደሆነ ከተናገሩ በኃላ ነው ፡፡ ግን ጉግል የአስተዳደሩን የይገባኛል ጥያቄ በጭራሽ አላረጋገጠም እንዲሁም ቅዳሜ ያስጀመረው ድርጣቢያ የሙከራ መመልከቻን አያካትትም ፡፡

ጣቢያው google.com/covid19 “በትምህርቱ ፣ በመከላከል እና በአካባቢያዊ ሀብቶች ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ ሰዎች በመንግስት ላይ የተመሠረተ መረጃን ፣ የደህንነት እና የመከላከያ ምክሮችን ፣ ከ COVID-19 ጋር የተዛመዱ የፍለጋ አዝማሚያዎችን ፣ እና ለግለሰቦች ፣ ለአስተማሪዎች እና ንግዶች ተጨማሪ መረጃዎች ማግኘት ይችላሉ ፡፡ ፣ ጉግል በብሎግ ልኡክ ጽሑፍ ላይ ተናግሯል:

-CNN #YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
ለአበባና አትክልት አምራችና ላኪዎች ከየካቲት እስከ ግንቦት ያሉት ወራት በአበባ ሥራ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት ነበር፤ አሁን ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ያለው የአበባ ዋጋ ካለፈው አመት አማካይ ጋር ሲነጻጸር በ85 በመቶ መቀነሱን በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ንግስት እሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል፦፡

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል፤ የኮረና ሻይረስን (COVID 19 ) ለመከላከል፤ በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ የተቋቋመዉ ንዑስ ኮሚቴ የመከላከል ስራዉን አጠናክሮ እንደቀጠለ ተገለፀ ።

ይህን የገለፁት ዶ/ር አያኖ ሻንቆ በዩኒቨርሲቲዉ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የን/እ/መ/መ ሆስፒታል ቺቨ ኤግዚኩቲቨ ዳይሬክተር ሲሆኑ የመንግስት መግለጫ ከወጣበት ቀን አንስቶ ፤

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ፤ የኮረና ሻይረስን ( COVID 19 ) የመከላከል ስራን በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል በተቋቋመዉ ዓብይ ግብረ ሃይል ኮሚቴ ስር ንዑሳን ኮሚቴዎችን ካቋቋሙበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ፤

የንግስት እሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል ንዑስ ኮሚቴ እንደ ሌሎቹ ንዑሳን ኮሚቴዎች ፤ የመከላከል ስራዉን አጠናክሮ መቀጠሉን በማስገንዘብ ፤ ለዚህም በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ቀጥተኛ እና አፋጣኝ አመራር ሰጪነት ዩኒቨርሲቲዉ ቋሚ ሁለንተናዊ አመራር እና ድጋፍ እያደረገላቸዉ በመሆኑ ልባዊ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል ።

ዶ/ር አያኖ አክለዉም በሆስፒታሉ የሚገኘዉ ግብረ ሀይል፤ ከመከላከል ስራዉ ጎን ለጎን የህከምና እና የቫይረሱን ስርጭት ለማወቅ የልየታ ስራዎች በተለያዩ የህክምና ማሽኖች ( የትኩሳት፣ የጉሮሮ ህመም እና ሳል ወ.ዘ.ተ መለያዎች ) በመታገዝ እየተሰሩ ቢሆንም ፤

እስካሁን በሆስፒታሉ ምንም ዓይነት ከቫይረሱ ጋር የተገናኘ የህክምና ታሪክ ያለዉ(ያላት) ታካሚ(ት) እንዳልተገኘ በመግለፅ ፤ እንደ ድንገት በከተማችን ዉስጥ የሚወሩ አሉባልታዎች ካሉም ፤ ይህን ቃል መጠይቅ እስከሰጡበት ደቂቃ እና ሰከንድ ድረስ ባላቸዉ መረጃ መሰረት ፈፅሞ ዉሸት መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል ።

ሆኖም ህብረተሰቡ ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ስለሚረዳዉ ፤ በአሁኑ ወቅት በተለያየ ሚዲያ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር ተያይዞ በጤና ሚኒስቴር ፤ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዉት አልያም በሚመለከታቸዉ የጤና ባለሙያዎች የሚተላለፉ ፤ የመከላከያ መንገዶችን በሚገባ በማወቅ ያለማቋረጥ በጥንቃቄ ሊተገብራቸዉ ይገባል ብለዋል ። ለዚህም ዶክተሩ እንደ ምክንያትነት ጨምረዉ ያነሱት ጉዳይ የቫይረሱ ስርጭት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን እና በአስደንጋጭ ሁኔታ የዓለም ስጋት እየሆነ እንዳለ ነዉ ።አያይዘዉም በዚህ ወቅት ከCOVID 19 ጋር ተያይዞ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚያስቀልድ እና የሚፌያስፌዝ ሁኔታ እንደሌለ በአፅኖት በማስገንዘብ ፤

ፀሎት ለአንድ ሀይማኖተኛ ወይንም አማኝ ጥሩ ነገር ቢሆንም ፤ ቤተዕምነቶች አከባቢ ለአምልኮ የሚደረጉ ስብሰባዎች ጥንቃቄ ሊደረግባቸዉ ይገባል ። ማንኛዉም ስብሰባዎች አስቸኳይ እና አንገብጋቢም ቢሆኑም እንኳ በዛዉ ልክ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል። ምክንያትም ምዕመናን ወይንም የስብሰባ ተሰብሳቢዎች ከተሰበሰቡበት ተመልሰዉ ወደ ህዝቡ ሲቀላቀሉ ምን አልባት ቫይረሱ ከሌላ ሰዉ ተላልፎባቸዉ ከሆነ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ ነዉ ብለዋል ።

በመጨረሻም በሆስፒታሉ የመገኘት አጋጣሚ ያላቸዉ ፤ በኢንተርንሺፕ ላይ ያሉ የህክምና ተማሪዎች እና ሀኪሞች ፤ ህሙማን ፣ የህሙማን ጠያቂዎች እና ሁሉም ሰራተኞች ወደ ሆስፒታሉ ሲገቡና ሲወጡ ያለ ምንም መዘናጋት ፤ በሆስፒታሉ የተሰናዱትን የንፅህና መጠበቂያ አቅርቦቶችን(ሳኒታይዘሮችን ) በሚገባ መጠቀም እንደሚገባቸዉ በመግለፅ ፤

በሆስፒታሉ ቫይረሱ የተላለፈበት ታካሚ ተለይቶ በአስፈላጊዉ የመገናኛ ብዙሀን(በ8335) እስካልገለፅን ድረስ ባለመጨናነቅ እራሳቸዉ እና በቅርባቸዉ የሚያገኙዋቸዉን ወገኖች ለመታደግ ፤ ቫይረሱን የመከላከል ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት እንዲደረግ ጥሪያቸዉን በማስተላለፍ ፤ የመከላከል ስራዉ የሁሉም ግለሰብ ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳይ መሆን እንዳለበትም በአንክሮ ገልፀዋል።

በሆስፒታሉ አግኝተን ያነጋገርናቸዉ አንድ አንድ ግለሰቦች በበኩላቸዉ ፤ ለሆስፒታሉ አገልግሎት መሻሻል ለዩኒቨርሲቲዉ ጉልህ አስተዋፆ እዉቅና በመስጠት ፤ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ ያለዉም ጥረት ከፍርሀት እና ስጋት እንዳዳናቸዉ እንዲሁም ስለ ቫይረሱ ምንነት ያላቸዉን ግንዛቤ እዳሳደገላቸዉ ገልፀዉልናል ።

ዘገባዉ የህዝብ ግንኙነት እና ዓለሞ አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነዉ
@YeneTube @FIkerassefa