የግብጽ መገናኛ ብዙኃን አሁንም ዐይናቸው ኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡
የግብጽ መገናኛ ብዙኃን የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ላይ ትኩረት አድርገዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የግብጽ መገናኛ ብዙኃን ትኩረታቸውን ከግድቡ እና ከኢትዮጵያ ብዙም ባያርቁም ከሰሞኑ ደግሞ ዋነኛ አጀንዳቸው አድርገውታል፡፡ የዘገባዎቻቸው ትኩረቶች የኢትዮጵያን አቋም ከማጣጣልና ከባለሥልጣኖቻቸው የቃላት ውርወራ ማስተናገጃነት ባያልፍም በየምክንያቱ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ትናንት የካቲት 24/2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ሰፊ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም የግብጽ መገናኛ ብዙኃን አወዛጋቢ ዘገባዎችን ሠርተዋል፡፡
‹ዴይሊ ኒውስ ኢጂብት› የተሰኘው የዜና ምንጭ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ብቸኛው አማራጭ ድርድር እንደሆነ ሀገራቸው እንደምታምን የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶክተር ኢንጂነር) መናገራቸውን ዘግቧል፡፡ ይህ የዜና ምንጭ በዚሁ ዘገባው ሚኒስትሩ በድርድሩ ጉዳይ ግብጽ ያቀረበችውን ሐሳብ ከዚህ ቀደም ውድቅ ማድረጋቸውንም አስነብቧል፡፡
ትናንት የተሰጠውን መግለጫ በተመለከተ ዴይሊ ኒስው ኢጂፕት በሠራው ሌላ ዘገባ ደግሞ ግድቡን በተመለከተ አሜሪካ የያዘችውን ኢትዮጵያን የሚጎዳና ሌሎችን ብቻ የሚጠቅም ሐሳብ ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው ስለመግለጻቸው ነው ትኩረት ያደረገው፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ ውስጥ በሙሉ ነጻነቷ የምትገነባው በመሆኑ ሐሳቡን እንደማትቀበለው መግለጻቸውንም ዘገባው አካትቷል፡፡
Via:- AMMA
@YeneTube @Fikerassefa

ብልፅግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች ላይ የተሰጡትን ስጦታዎች መቀማቱን አስታወቀ።
በኦሮሚያ ክልል ብልፅግናን እንደግፋለን በማለት ለስጦታ ያዋጧቸውን ሀብቶች በተለይ በሬና ግመሎችን የመቀማት ድርጊት ሲፈፅሙ የነበሩ የአንዳንድ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንደነበሩ ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አወሉ አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ላለፉት 3 ሳምንታት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች ላይ ድንጋይ በመወርወር ፤ መንገድ በመዝጋት እንዲሁም ለፓርቲው የቀረቡ ስጦታዎችን በመቀማት ችግር የፈጠሩ አካላት እንደነበሩ አንስተዋል፡፡
በዋናነት በአወዳይ ፤ ደደር ፤ ባሌ መደ ወላቡና ሀረርጌ አካባቢዎች እነዚህ ችግሮች በስፋት የተስተዋሉባቸው ናቸው ብለዋል አቶ አወሉ።
እነዚህን ሲያደርጉ ከነበሩት የተወሰኑትን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በአብዛኛው ጀማሪ ፖለቲከኞች ስለሆኑና ያልገባቸው ነገሮች ስላሉ ቀስ ብለው ይታረማሉ የሚል እምነት ስላለን በትግስት አልፈናቸዋል በማለት ተናግረዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፎቹ እስከመደባደብና ድንጋይ መወርወር ሁኔታዎች በሰፊው የተስተዋሉ መሆናቸውን ያነሱት አቶ አወሉ የከፋ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ የነበሩት ግለሰቦች የማን አባላት እንደሆኑ በመለየት በህግ አግባብ እንዲታዩ አድርገናል ብለዋል፡፡
ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ተምረው በቀጣይ በሚከናወኑ የድጋፍ ሰልፎች ላይ አባላቶቻቸው ከመሰል ድርጊቶች እያረሙ የሚሄዱበትን ሁኔታዎች ይፈጥራሉ ብለን እናስባለን በማለትም ገልፀዋል፡፡
ለድጋፍ በወጡ አባላቶቻችን ላይ የታየ ምንም የስነ-ምግባር ጉድለት ሪፖርት ያልተደረገ መሆኑን የነገሩን ሲሆን ችግሮች ሪፖርት ሲደረጉልን ግን በስራ ላይ በዋለው የፓርቲ አመራሮችና አባላት የስነ-ምግባር ደንብ መሰረት እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ብለዋል፡፡
Via:- Ethio FM

የ157 ሰዎች ሕይወት ያለፈበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ አንደኛ ዓመት እየተቃረበ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋውን የተመለከተ ጊዜያዊ ዘገባ ፣ የአደጋው አንደ ዓመት ከመድረሱ አስቀድሞ እንደሚያወጣ አስታውቋል። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ አደጋውን በተመለከተ የወጡት መረጃዎች ምን ያህል አጥጋቢ ነበሩ ትላላችሁ? አስተያየታችሁን አካፍሉን።
Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
በአሁን ሰዓት የካቲት 25/2012 ዓ/ም የአርቲስት ውብሸት ወርቃለማው የቀብር ስነስርዓት የሽኝት ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
Via:- ዋልተንጉስ ዘሸገር
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- ዋልተንጉስ ዘሸገር
@Yenetube @Fikerassefa
የህዳሴው ግድብ በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ መነጋገሪያ ሆኗል
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ አነጋግሯል፡፡
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት በተመለከተ የወጣው መግለጫ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን አሜሪካዊያንንም አስቆጥቷል።
ታዋቂ አሜሪካዊያን ፖለቲከኞችና ዲፕሎማቶች አሜሪካ በኢትዮጵያ እንዲፈረም ያቀረበችውን የስምምነት ሰነድ ተችተውታል።
ሚኒስትሩ መኑቺን ትናንት በአሜሪካ ምክር ቤት ቀርበው በነበረበት ጊዜ ጉዳዩ የኮንግረስ አባል በሆነው ስቴቨን ሆርስፎርድ የአሜሪካንን ገለልተኝነት በሚያጠይቅ ሁኔታ ተነስቶ ማብራሪያ ተጠይቆበታል።
ምንጭ፡- ዋልታ
@YeneTube @Fikerasssefa

የኮሮናቫይረስ በተከሰተበትና በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት የምድራችንን የጤና ጉዳዮች በበላይነት የሚከታተለውና የሚመራው የዓለም ጤና ድርጅት መሪ መሆን ከባድ ኃላፊነት ነው።
ኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ከፊት ሆነው በሚመሩበት በዚህ ወቅት በሽታውን ለመግታትና ክትባትም ሆነ ፈዋሽ ህክምና እንዲገኝ ለማድረግ በየዘርፉ እየጣሩ ነው።
https://bbc.in/2TjX5VQ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በተለያዩ አካባቢዎች ለመደራጀት የሚያደርጋቸው ጥረቶች "በብልጽግና ፓርቲ ካድሬዎች" እየተደናቀፉብኝ ነው ሲል ቅሬ አሰማ። ፓርቲው በመተማ እና በቢቸና ከተሞች አደራጆቹ መታሰራቸውንም ገልጿል።
አዴኃን ለውጡን ተከትሎ ከኤርትራ ከተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
#ElU
@YeneTube @Fikerassefa
አዴኃን ለውጡን ተከትሎ ከኤርትራ ከተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
#ElU
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ተራማጅ ፓርቲ (Ethiopian Progressive Party) በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች እንቅፋት እየገጠመው መሆኑን የፓርቲው መሪዎች ተናገሩ።
መሪዎቹ እንደሚሉት በአምቦ ከተማ 538 አባላቶቹ የፈረሙበት ሰነድ የፌድራል ፖሊስ ልብስ በለበሱ ሰዎች የተነጠቀ ሲሆን፣ በቡታጅራ ከተማ ደግሞ የ69 ሰዎች ፊርማ የያዘና የምርጫ ቦርድ ማህተም ያረፈበት ሰነድ በአንድ የከተማው ባለስልጣን ተወስዶበታል።
በአዳማ ከተማም ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ፓርቲው ጉዳዩን በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርቧል።
Via:- #Elu

በኢኦተ ቤተክርስቲያን ዼጥሮሳውያን የቤተክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ያቀረበለትን የቃለመጠይቅ ግብዣ ውድቅ አደረገ።
Via:- #Elu
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- #Elu
@Yenetube @Fikerassefa
የተሰረቁ 4 መኪናዎችንና 8 ሞተር ሳይክሎችን ከ27 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦላይን ይሰጣል " ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር።
በአርትስ ቴሌቪዥን ላይ ተመልክተናል ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚመለከተውን አካል እግኝተን ነገ የተደራጀ መረጃ የምናቀር ይሆናል።
Via:- Arts TV
@YeneTube @FikerAssefa

በትናንትናው ዕለት በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ጠብ አንድ ተማሪ መገደሉን ወሎ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው እንዳለው ለተማሪው መገደል ምክንያት የሆነው ሌላ ተማሪ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
#Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
#Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 71 በመቶ ደረሰ
በመንግሥት እና በሕዝብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 71 በመቶ ላይ መድረሱን የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ግድቡ መጠናቀቅ ከነበረበት በአራት ዓመታት በመዘግየቱ እና ተጨማሪ የገንዘብ ኪሳራ በማስከተሉ ምክንያት የሕዝቡ ተሳትፎ መቀዛቀዝ መታየቱንም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።
ግድቡን ለማጠናቀቅ የሕዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ለ3ኛ ጊዜ የ8100 የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ምንጭ:- ETV