YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኤሌክትሪክ መቋረጥ...

በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ላይ የተፈጠረ ችግር ለመብራት መቋረጡ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ Capital ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኤሌክትሪክ መቋረጥ... በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ላይ የተፈጠረ ችግር ለመብራት መቋረጡ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ Capital ዘግቧል። @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር እቶ ሞገስ መኮንንም የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል::

ለዚህ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለአሁን እለመታወቁን: ነገር ግን ከግልገል ጊቤ ሦስት ከሚቀርበው የኃይል አቅርቦት መስመር ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አቶ ሞገስ ግምታቸውን ተናግረዋል:: አክለውም የድርጅቱ ባለሙያዎች የኃይል መቋረጡን ምክንያት ለመለየትና አገልግሎቱን ለመመለስ እየሰሩ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል::

በአጭር ጊዜ ውስጥም በአዲስ አበባ ያጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እንደሚስተካከልና በተከታይነትም የሌሎቹም አካባቢዎች አገልግሎት እንደሚመለስ አቶ ሞገስ ለቢቢሲ ገልጸዋል::በአንዳንድ ስፍራዎችም ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እየተመለሰ መሆኑን ለማወቅ ችለናል::

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢራን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 210 ደርሷል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

የሀገሪቱ መንግሥት ይፋ ባደረገው መረጃ 34 ሰዎች እንደሞቱ ቢያሳውቅም BBC Persian አገኘሁት ባለው መረጃ እስካሁን 210 ሰዎች ሞተዋል። ይህም መንግስታት የሟቾችን ቁጥር እየደበቁ ነው የሚለውን ጥርጣሬ የሚያጎላ ነው ተብሏል።

ከዚው ጋር በተያያዘ CNN በሰራው ዘገባ መንግስታት መረጃን ሚደብቁ ከሆነ በ1918 ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፈው የእንፍልዌንዛ (Spanish flu) ወረርሽኝ ነገሮችን ወደከፋ ደረጃ ሊያደርስ እንደሚችል ዘግቧል።

Join:- @Coronavirusupdatess

@YeneTube @FikerAssefa
ምን አዲስ ነገር ተሰማ ስለ ኮሮና ቫይረስ

- ቻይና የኬኒያን ዜጎችን አስጠንቅቃለች በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የቻይና ዜጎች በኬንያ መገለል እየደረሰባቸው በመሆኑ ቻይና የኬንያኖችን እንዳስጠነቀቀች ቻይና ፒፕል ዘግቧል።

- ጣልያን በኮሮና ቫይረስ ዛሬ ብቻ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 166 ሲሆን የሞት ቁጥር ደሞ በ4 ጨምሯል በአጠቃላይ በባይረሱ የተጠቁ 821 ሲደርሱ የሞቱ በአጠቃላይ 21 ደርሰዋል።

- አንድ ሆንግ ኮንድ ከተማ የሚገኝ ውሻ ተመርምሮ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ታውቋል።

- ኬንያ ወደ ቻይና በረራ አቁማለች።

📌አዘር ባጃን
📌አምስተርዳም
📌ሜክሲኮ
📌አይስ ላንድ ዛሬ ኮሮና ቫይረስ ሀገራቸው መግባቱ ያረጋገጡ ሀገሮች ናቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
በስራ ፈጠራ እንዲሁም በመዝናኛው ዘርፍ የሚታወቀው ካሌብ ሚያኪንስ በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።

የዛሬ ሳምንት ወደ ለንደን ሊበር በወጣበት ባጋጠመው የመኪና አደጋ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

ለአድናቂዎቹ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን።
@YeneTube @FikerAssefa
በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ካሉት አስር ተርባይኖች ዘጠኙ ብልሽት አጋጥሟቸዋል።

ፎርቹን ለጉዳዩ ቅርበት ካለው አካል ሰምቻለው እንዳለው የሀይል ማመንጫውን ወደነበረበት ለመመለስ ቢያንስ የአንድ ሰአት ስራ(ጥገና) ይፈጃልም ብሏል። ጊቤ 3 ግድብ ለግንባታው 1.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን 1870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል እያመነጨ ይገኛል።

ምንጭ: ፎርቹን
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ፕላጃሪዝም ፖሊሲን መጀመሩን አስታወቀ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ፕላጃሪዝም (Anti-Plagiarism) ፖሊሲ ከየካቲት 22/2012 ዓ.ም ጀምሮ ሊተገብር መሆኑን በይፋ እየገለጸ ይህ ፖሊሲ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በፖሊሲው መሰረት ከዚህ በኋላ ማንኛውም መመረቂያ ጽሁፍ (Thesis/ Dissertation) በኧርከንድ (URKUND) ሶፍትዌር አማካኝነት ተመርምሮ ከፕላጃሪዝም ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥ ዲግሪ እንደማይሰጥ ያሳውቃል፡፡

ፕላጃሪዝም አንድ የምረቃ ፅሁፍ የሚያዘጋጅ ወይም የምርምር ስራ የሚሰራ ሰው ሌሎች ሰዎች የሰሩትን ስራ የራሱ እንደሆነ አድርጎ በመውሰድ የአካዳሚክ እና የምርምር ሕግጋትን በመጣስ የሚፈፅመው ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡ፕላጃሪዝም ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፍ በሚያዘጋጁበት ጊዜ በራሳቸው ጥረት እና ልፋት የራሳቸው የሆነ (original) ስራ ሰርተው እንዳያቀርቡ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ላይ ትልቅ ጉዳት ሲያደርግ የቆየ ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡

ቀደም ሲል የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ፕላጃሪዝም በመጠቀም የመመረቂያ ጽሁፉን በማዘጋጀት 2ኛ ዲግሪ ወስዶ ከነበረ ተማሪ ላይ ድርጊቱ በማስረጃ በማረጋገጡ በሴኔት ሕጉ መሰረት ዲግሪው እንዲነጠቅ አድርጓል፡፡ ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ይህ ችግር በመማር ማስተማሩና በምርምር ስራ ላይ በየጊዜው እያስከተለ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በመገንዘቡ የፀረ-ፕላጃሪዝም ፖሊሲ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በመሆኑም ይህ ፖሊሲ ተግባራዊ ሲሆን ችግሩ ከሞላ ጎደል ይቃለላል የሚል ሙሉ እምነት አለው፡፡

-አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
ከቤጂንግ የመጣው ቻይናዊ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ነው ተባለ!

ከዚህ ቀደም ብሎ አንድ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳየ በማለያ ማእከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት መሆኑን እና ናሙናው ተወስዶ ላብራቶሪ እተሰራ መሆኑን የገለጽን መሆኑ ይታወቃል፣ በመሆኑም አሁን በደረሰን ውጤት መሰረት ግለሰቡ #ከበሽታው_ነጻ (ኔጌቲቭ) መሆኑ በላቦራቶሪ እንደተረጋገጠ መግለጽ እንወዳለን ብሏል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
የግድቡ ውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት መፈረም አለበት፡ አሜሪካ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በውሃ የመሙላትና የሙከራ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም እንዳለበት አሜሪካ አርብ ለሊት ባወጣችው መግለጫ አመለከተች። የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው ቀደም ሲል የነበረውና ግንባታው በታችኛው የተፋሰሱ አገራት ላይ ጉልህ ጉዳት እንዳይደርስ በሚለው የመርህ ስምምነት መሰረት "ግድቡን በውሃ የመሙላትና ሥራውን የመሞከር ሂደት ስምምነት ሳይደረግ መከናወን የለበትም" ብሏል።የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑቺን ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት ከዚህ በፊት በነበሩ ስምምነቶች መሰረት ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም አለበት።

ተጨማሪ👇👇👇👇
https://telegra.ph/Moreonthis-02-29
ኢትዮ ቴሌኮም የሳይበር ጥቃት ደረሰበት

ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮ ቴሌኮም የውስጥ ሲስተም ውስጥ #የራንሰምዌር (Ransomeware ) ጥቃት መድረሱን ሰራተኞችም የኢሜል ልውውጦቻቸው መጠባበቂያ ሳይቀሩ ከዋና ሲስተም ጋር እንዳይገኙ እና ይህንን ካደረጉ ልውውጦቻቸው ሊያጡ እንደሚችሉ አርብ የካቲት 13 ለድርጅቱ ሰራተኞች የተላኩ መልክቶች አረጋገጡ።

ከድርጅቱ የዲጅታል ዲቪዥን የተላከው አጭር የጽሑፍ መልክት አርብ ይድረስ እንጂ ሰራተኞች ግን ከማክሰኞ የከቲት 10 ጀምሮ ሁሉም የቴሌኮም ሰርዓቶች ቀመው እንደነበር አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ታመኝ ምንጮች ገልፅዋል።

ምንጮቹ እንደሚሉት ከሲአርኤም ከተባለው እና የደንበኞች መረጃዎችን ከሚይዘው ሲስተም ውጪ ያሉ የቴሌኮሙ ሰርአቶች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።


የቀረውን ከጋዜጣው ላይ ያንብብ
ምንጭ :- አዲስ ማለዳ ✏️ YeneTube
@Yenetube @FikerAssefa
ሰበር ዜና

አሜሪካ በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ትዕዛዝ ማስተላለፏን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።

አሜሪካ ኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከስምምነት ሳይደርሱ የህዳሴው ግድብ ውሃ መሙላት አይችልም የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ኢትዮጵያም አሜሪካ ባስተላለፈቸው ውሳኔ ዙሪያ እንደ አገር አቋም ለመያዝ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡን ከኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

Via:-Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸዉን ለሚከታተሉ 30 አይነስዉራን ተማሪዎች የላፕቶፕ ስጦታ አበረከቱ፡፡

ስጦታዉ የተበረከተላቸዉ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ለመከታተልና የመመረቂያ ጽሁፋቸዉን ለማዘጋጀት የላፕቶፕ ችግር ያለባቸዉ ተማሪዎች ተለይተዉ ነዉ፡፡ቀዳማዊት እመቤት በፅ/ቤታቸዉ ጠርተዉ ካበረታቷቸዉ በኋላ የላፕቶፕ ስጦታዉን አበርክተዉላቸዋል፡፡ላፕቶፖቹ ታይዋን ከሚገኝ ASHL FOUNDATION ከተባለ ድርጅት በጽ/ቤታቸዉ በኩል የተገኙ ናቸዉ፡፡

Via Office of First Lady
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተጀመረውን ወይይት ወደ አፍሪካ ህብረት ማምጣት እንደሚገባ በናይል ትብብር መድረክ የምስራቅ ናይል አህጉራዊ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ፈቂ አህመድ ነጋሽ ተናግሩ።

አቶ ፈቂ እንዳሉት ኢትዮጵያ የግድቡን ድርድር አሁን እየተደረገ ባለበት መድረክ እንዲቀጥል ማድረግ አልነበረባትም ብለዋል።

ይሁንና አሁን ላይ የእነ አሜሪካ ፍላጎት ግልጽ በመሆኑ ድርድሩን ወደ አፍሪካ ህብረት እና ናይል ተፋሰስ አገራት ማዕቀፍ ማምጣት ይኖርባታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ግድቡን እየገነባች ያለችው በራሷ ሉኣላዊ ግዛት ላይ ነው፣ወንዙም ሉአላዊ ሃብቷ ነው የአሜሪካ ትዕዛዝና መግለጫ ሊገድባት አይገባም ሲሉ አሳስበዋል።

ግብጽና ሱዳን ድርድር ከፈለጉ ግን ኢትዮጵያ ድርድሩን መቀጠል አለባት ነገር ግን ድርድሩ ሚዛናዊነትን በሚያስጠብቅ መልኩ መሆን ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።

Via:- Ethio Fm
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መንግሥት ከጥቂት ሰዓት በኋላ በኅዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ያለውን አቋም የተመለከተ መግለጫ ያወጣል።

አሐዱ ቴሌቪዥን ዩናይትድ ስቴትስ ያወጣችውን "ስምምነት ሳይፈረም የግድቡ ውኃ ሙሌትና ኃይል ማመንጨት እንዳይጀመር" የሚል አቋም ተከትሎ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ስብሰባ መቀመጡን አረጋግጧል።

በዚህም በጥቂት ሰዓት ውስጥ የኢትዮጵያን አቋም የሚያሳውቀው መግለጫ እንደሚወጣ ስብሰባው ውስጥ ካሉ ተደራዳሪዎች መረጃ ደርሶናል።

ምንጭ:-አሐዱ ቴሌቪዥን
@Yenetube @FikerAssefa
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ።

የኢትዮጵያ ፌዴራለዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒሰቴር የአሜሪካ የግምጃ ቤት ዲፓርትመንት ሴክሬታሪ በየካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ28 ፌብሩዋሪ 2020) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችበትን ስብሰባ ተከትሎ የወጣውን የፕሬስ መግለጫ በከፍተኛ ቅሬታ ተመልክተውታል። ስብሰባው የተካሄደው ኢትዮጵያ አስቀድማ ለግብጽ፣ ለሱዳን እና ለአሜሪካ ስብሰባው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ አሳውቃ እያለ ነው፡፡

የግድቡ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በመርሆዎች መግለጫ ስምምነቱ መሰረት የግድቡን ሙሌት ከግንባታው ትይዩ በፍትሐዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም እና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች መሰረት የምታከናውን ይሆናል።

ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ ለማዘጋጀት የሚደረገው ድርድር ተጠናቋል በሚል የተሰጠውን መግለጫ አትቀበልም።

በዋሽንግተን ዲሲ የግብጽ ዐረባዊት ሪፐብሊክ ፈርሞበታል የተባለው “ረቂቅ” የሶስቱ ሀገራት የድርድርም ሆነ የሕግ እና ቴክኒክ ቡድኖች ውይይት ውጤት አይደለም።

የቴክኒክ ጉዳዮች ድርድሩም ሆነ የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅቱ ላይ የሚደረገው ድርድር አልተጠናቀቀም፡፡ ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ የሚዘጋጀው በሶስቱ ሀገራት ብቻ እንደሆነ አቋሟን ቀድማ አሳውቃለች።

ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በሚያውቁት እና በተስማሙበት እንዲሁም በመርሆዎች መግለጫ ስምምነት መርህ አንቀጽ ስምንት አድናቆታቸውን በሰጡት ሂደት መሰረት ሁሉንም የግድብ ደህንነት የሚመለከቱ ጉዳዮች በዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ምክረ ሃሳብ መሰረት የተሰጡትን ምክረ-ሃሳቦች መፈጸሟን ትቀጥላለች።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብን ለማዘጋጀት ቀሪ መሰረታዊ ልዩነቶችን ለመፍታት ኢትዮጵያ ከግብጽ ዐረባዊት ሪፐብሊክ እና ከሱዳን ሪፐብሊክ ጋር የጀመረችውን ሂደት ለመቀጠል ቁርጠኛ ናት።

via :- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ የታላቁ የኅዳሴ ግድብ «የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ ለማዘጋጀት የሚደረገው ድርድር ተጠናቋል በሚል» አሜሪካ ያወጣችውን መግለጫ ውድቅ አደረገች።

የኢትዮጵያ መንግሥት «ሥምምነት ሳይፈረም የታላቁ የኅዳሴ ግድብ የመጨረሻ ሙከራ እና የውኃ ሙሌት ሊከናወን አይገባም» የሚለው የአሜሪካ ግምዣ ቤት መግለጫ ከፍተኛ ቅሬታ እንደፈጠረበት አስታውቋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 80ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

@Yenetube @Fikerassefa