YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ አገራት ቁጥር አራት ደርሷል።

ግብጽ፣አልጀሪያ እና ናይጀሪያ ከዚህ በፊት ቫይረሱ የተከሰተባቸው አገራት ሲሆኑ ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ ሁለት ደቡብ አፍሪካዊያን በዚሁ ቫይረስ መጠቃታቸውን የአገሪቱ ኒወስ 24 የተሰኘው ተነባቢ ጋዜጣ ዘግቧል።

ደቡብ አፍሪካዊያኑ በጃፓን ክሩዝ መርከብ ላይ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ሲሆን ከሌሎች አገራት ዜጎች ጋር መጠቃታቸውን የጃፓን መንግስት መናገሩን እና በቶኪዮ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ ማረጋገጡን ዘገባው ጠቁሟል።

በዚች የጃፓን መርከብ ላይ 12 ደቡብ አፍሪካዊያን ተቀጥረው ይሰሩ የነበረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ #ሁለቱ በቫይረሱ መጠቃታቸው እና ህክምና ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa