YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ተቃዋሚያቸው የነበሩት ሪክ ማቻርን የሀገሪቷ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡

የተቃዋሚ ቡድን መሪው ሪክ ማቻር ሹመት የተሰማው ሁለቱ አካላት የብሄራዊ አንድነት መንግስት ለመመስረት ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ መሆኑን ሲጂቲኤንን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የነዳጅ ሀብት ያላት ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ. በ2011 ከጎረቤት ሰሜን ሱዳን ነፃነቷን ካገኘች ከሁለት ዓመት በኋላ ነበር እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው፡፡

ግጭቱ በ1994 በሩዋንዳ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ወዲህ የ400,000 ያህል ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈና ትልቁን የስደተኛ ቀውስ ያስከተለ ነበር፡፡

ግጭቱ የተፈጠረው በዛን ወቅት የሳልቫ ኪር ምክትል በመሆን በስልጣን ላይ የነበሩት ማቻር ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡

Via:- ኢዜአ /ሲጂቲነ
@YeneTube @FikerAssefa
#OLF #ABO #ኦነግ መግለጫ

የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው

የክስተቱን መንስዔና አጠቃላይ ምንነቱን አስመልክቶ እስካሁን በቂ ግንዛቤና መረጃ ባይኖረንም እንኳ በትናንትናዉ ዕለት (የካቲት 13, 2012) በቡራዩ ከተማ የተፈጸመዉንና የኮሚሽኔር ሰለሞን ታደሰ ሕይወት የጠፋበትን ግድያና የአካል ጉዳት ያደረሰዉን ጥቃት በጽኑ እናወግዛለን። በጠፋዉ ሕይወትና በደረሰዉ አካላዊ ጉዳት ለተጎዱትም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ጓደኞች ሁሉ መጽናናቱን እንመኛለን።

በእንዲህ መሰሉ ጥቃትም ይሁን በሌላ በምንም መልኩ የተወሰኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ዒላማ አድርጎ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና አላስፈላጊ ጫናዎች የሀገሪቱን ችግሮች ይበልጥ ያባብሱና ያወሳስቡ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣሉ ብለንም አናምንም። በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ መንገዶች እየታዩ ላሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ሁሉ ሰላማዊና ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ መንግሥት ከፍተኛዉን ድርሻና ኃላፍነት እንዳለዉ ይታወቃል። የዚህች ሀገር የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉም ይህንን አስመልክቶ የድርሻቸዉን ለመወጣት ግዴታ አለባቸዉ። ሰፊዉ ሕዝብም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሕዝብ የተጋረጡብንን ችግሮች በተመለከተ የችግሮቹን መንስዔና መፍትሄያቸዉን ለይቶ ያሉብን ችግሮች ለዘለቄታዉ መፍትሄ በሚያገኙበት አቅጣጫ ላይ የበኩሉን እገዛ ለማድረግ በንቃት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነዉ ብለን እናምናለን።

ስለሆነም፣ ባሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ አስፈሪና ዘግናኝ የሆነ የስጋት ደመናን አንዣቦ ያሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ልያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ለማፈላለግ ሁሉም ወገኖች ኃላፍነትና ግዴታቸዉን በላቀ የተጠያቂነት/responsibility መንፈስ እንዲወጡ ኦነግ አጥብቆ ይማጸናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ መንግሥት የዜጎች ነፃነትና ደህንነት ልረጋገጥበት የሚችለዉ ሁለንተናዊ መፍትሄ ልገኝ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደመንግሥት የተረከበዉን ታሪካዊ ኃላፍነትና ተጠያቂነት መወጣቱ የወሳኝነት ሚና እንዳለዉ ተገንዝቦ ይህንን ኃላፊነቱን በገንቢ ሁኔታ እንዲወጣ በአፅንዖት እናሳስባለን።

ድል ለሰፊዉ ሕዝብ !
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
@YeneTube @Fikerassefa
እጂግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአንበጣ መንጋ በሶማሌ ክልል በኩል ወደ ሀረር እየገባ ይገኛል፡፡ ብዛቱም እስከዛሬ ከነበሩት እንደሚበልጥ ለየኔቲዩብ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የአንበጣ መንጋ በሀዋሳ ከተማም ዛሬ መታየቱን የየኔቲዩብ ቤተሰቦች ጠቁመዋል።

Photo:- ሀዋሳ ነዋሪው አንበጣውን በጪስ ሲያባር
@Yenetube @Fikerassefa
በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምኦን በጠና ታመዋል ተባለ!

“በፍጥነት ህክምና ካላገኘ ለህይወቱ ያሰጋዋል” - ባለቤታቸው

ላለፉት 27 ዓመታት በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነቶች ላይ ያገለገሉትና በቅርቡ በሙስና ተከስሰው የታሠሩት አቶ በረከት ስምኦን በጠና መታመማቸውን የተናገሩት ባለቤታቸው፤ አስፈላጊውን ህክምና ባለማግኘታቸው ቤተሰቡ በስጋት ላይ መሆኑን ገልጸል፡፡ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ህመም ገጥሟቸው ህክምናቸውን በደቡብ አፍሪካ መከታተል የጀመሩ ቢሆንም፤ ከጥረት ኮርፖሬት ጋር ተያይዞ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በባህርዳር በመታሰራቸው ለቀዶ ህክምና የተሰጣቸው ቀጠሮ ማለፉን የጠቆሙት ባለቤታቸው ወ/ሮ አሲ ፈንቴ፤ጤንነታቸው በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ በእስር የቆዩት አቶ በረከት መታመማቸውን የሰሙት ከሰው መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ አሲ “ቤተሰቦቼን አላስጨንቅም” በሚል እንዳልነገራቸው ይገልፃሉ፡፡ከአቶ በረከት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ያስታወሱት ባለቤታቸው፤ “ጉዳዩ የክልል በመሆኑ ክልሉን አናግሩ፤ እኔ በሌላ የግል ጉዳያችሁ ላይ ችግር ከገጠማችሁ አግዛችኋለሁ” የሚል ምላሽ ከጠ/ሚኒስትሩ እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡

ይሄን ተከትሎም ለአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አቶ በረከትን ጨምሮ ሌሎች አብረዋቸው የተከሰሱ ግለሰቦች በነፃ እንዲሰናበቱ መጠየቃቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ አሲ፤ የአመራሮቹ ውሳኔ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ መሆኑን በጭንቀት ተሞልተው አስረድተዋል፡፡አቶ በረከት በፍጥነት አስቸኳይ ህክምና ካላገኙ ለህይወታቸው እንደሚያሰጋቸው የተናገሩት ወ/ሮ አሲ፤ ይህንን ጉዳይ ሁሉም በትኩረት ሊያየው የሚገባ ነው ብለዋል፡፡አቶ በረከት ስምኦን ከጥረት ኮርፖሬት ጋር በተያያዘ “ምዝበራ ፈጽመዋል፣ ስልጣናቸውን አለአግባብ ተጠቅመዋል” በሚል በአማራ ክልል ክስ ተመስርቶባቸው ከታሰሩ ከአንድ ዓመት በላይ አልፏቸዋል፡፡

ምንጭ: አዲስ አድማስ
@YeneTube @FikerAssefa
Prof Kindeya G.hiwot - M.University President

ሰሞኑን በኔ ዙርያ እየተነሱ ያሉ ጉዳዮች #በሬ ወለደ ናቸው::

በኔ ላይ ጫና ያደረገ አካል የለም:: ሊኖርም አይችልም:: የማደርገውም የምሳተፍበትም ሁሉ በሙሉ እምነትና ፍላጎት ነው:: ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልግ ካለ ለመስጠት ፍቃደኛ ነኝ:: ስራ ላይ ነን::

@YeneTube @Fikerassefa
በእድሜ ትንሹ የህክምና ዶ/ር (ዶ/ር አቤኔዘር) ዛሬ ከጅማ ዩንቨርስቲ ተመርቋል ከወንድሙ ጋር ተመርቋል።

ዶ/ር አቤነዘር ብርሀኑ በ 4 አመቱ ትምህርት የጀመረ ሲሆን በ23 አመቱ ትምህርቱን አጠናቋል። በተለመደው የእድሜ አሰላል እዚህ ማዕረግ ላይ ከሚደረስበት በሦስት ዓመታት ያንሳል።

የዶ/ር አቤኔዘር ጓደኞቹ 'ጢቆ' ይሉታል- ትንሽ እንደማለት። አንዳንዶች ደግሞ ያንግ [Young] የሚል ቅፅል አክለው 'ዶ/ር ያንግ' እያሉ ይጠሩታል።

ከዚህ በፊት Sefiu on ebs ላይ መቅረቡ ይታወሳል።
@Yenetube @Fikeassefa
ኢታ ሪል ኢስቴት በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ድርጅት የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ኢታ ሪል ኢስቴት ወይም የቤት አልሚዎች ድርጅት ሲሆን በአዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል አካባቢ የገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች ዛሬ አስመርቋል።ድርጅቱ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ኢታ ሪል ኢስቴት ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ድርጅት የአንድ ሚሊዮን ብር ስጦታውን ለማዕከሉ አስተባባሪዎች አስረክቧል።በልብ ማዕከሉ እስካሁን ከ7 ሺህ በላይ ህጻናት የልብ ህክምና ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ናቸው።ማዕከሉ አሁን ላይ በቀን እስከ 6 ህጻናት የቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጥ ሲሆን እስከ 8 ህጻናት ደግሞ የአጠቃላይ የልብ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ምንጭ: ኢትዮ ኤፍ ኤም
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዢ የነበሩት አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው በጠ/ሚ አብይ መሾማቸውን ፎርቹን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ እና ፕሬዝዳንት አልሲሲ ተወያይተዋል።

በምን ጉዳይ እንደተወያዩ እስካሁን ባናረጋግጥም እንደተወያዩ የግብፅ ባለስልጣናት በቲውተር ገፃቸው አስፍረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
"የኦሮሚያ ፖሊስ ትላንት በቡራዩ የተፈፀመዉን ወንጀል በማቀነባበር እና በመተግበር የጠረጠራቸዉን 17 ሰዎች በቁጥጥር ስር አዉሏል። ፖሊስ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ሠላምንና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከህዝብ ጋር እንደሚሰራ ቃል ገብቷል።"

አቶ ታዬ ደንደአ-የክልሉ የህዝብ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
"የኦሮሚያ ፖሊስ ትላንት በቡራዩ የተፈፀመዉን ወንጀል በማቀነባበር እና በመተግበር የጠረጠራቸዉን 17 ሰዎች በቁጥጥር ስር አዉሏል። ፖሊስ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ሠላምንና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከህዝብ ጋር እንደሚሰራ ቃል ገብቷል።" አቶ ታዬ ደንደአ-የክልሉ የህዝብ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር @YeneTube @FikerAssefa
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በ4 ሰዎች ላይ ጥቃት የፈጸመው በኦነግ ሸኔ የሚመራው፣ የነፃነት ሰራዊትና አባ ቶርቤ በማለት ራሱን የሚጠራውና በተለያዩ አከባቢዎች ጥቃት የመፈጸም ተልዕኮ ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር በ56ኛ የሕክምና ጉባዔው ዶ/ር ተግባር ይግዛውን አዲስ ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ ላለፉት ስድስት ዓመታት ማህበሩን ሲመሩ የነበሩትን ዶ/ር ገመቺስ ማሞን ይተካሉ፡፡

መረጃውን ያገኘነው ከቅ/ጳውሎስ ሆስፒታል የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦ አፍሪካ⬆️

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ የቻናላችን ቤተሰቦች ነግረውናል።

@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተጨማሪ ቪዲዮ ግርማዊነቶ 🙏

ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት 2012 በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። በነገራችን ላይ ቴዲ አፍሮ ከ15 አመታት በኃላ ነው መስቀል አደባባይ ላይ ኮንሰርት ያቀረበው።

💚💛❤️ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር 💚💛❤️

--Video መላካችሁን ቀጥሉ YeneTube--
@YeneTube @Fikerassefa
ስፖርት!

ሰለሞን ቱፋ በመጪው ክረምት በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በወርልድ ቴኳንዶ ኢትዮጵያን የሚወክልበትን ውጤት አግኝቷል።

ዛሬ አመሻሽ ላይ በተደረገ የማጣሪያ ውድድር የሴኔጋል አቻውን በብቃት አሸንፎ ነው ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወርልድ ቴኳንዶ ኢትዮጵያን እንደሚወክል ያረጋገጠው።

ምንጭ:EOC-Tokyo 2020
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ለባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ 10 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል።

ባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ዛሬ ማታ በኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ አድርጓል በቀጥታም በአማራ ቴሌቨዥን ተላልፏል።

በአጠቃላይም 45 ሚሊዮን ብር ቃል መግባቱን ተመልክተናል።
@YeneTube @Fikerassefa
‹የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ላይ ከፖለቲካ ሴራ እስከ ተዋጊ ጦር በመላክ ወደ ውጊያ እንድንገባ እየተፈታተነን ነው›› ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሕወሓት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

https://ethiopianreporter.com/article/18159
የኢራኑ ቴረሀን ዩንቨርስቲ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተማር አቁማል ምክንያተም በኢራን የኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ መጠን መስፋፋት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተነግራል።

ስለ ኮሮና ቫይረስ ብቻ የምንዘግብበትን Special Channel ተቀላቀሉ⬇️

@Coronavirusliveupdate
@Coronavirusliveupdate

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Corona Virus Updates
Italy's prime minister announced all sports events in Lombardy and Veneto tomorrow will be cancelled.

Atalanta - Sassuolo
Hellas - Cagliari
Inter - Sampdoria Are the games affected
ጾሙ ምዕመናን ከጥላቻ፣ ፍትህን ከማጉደል፣ ከበደልና ዛቻ የሚቆጠቡበት ሊሆን ይገባል-ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

በመጪው ወርሃ ጾም ምዕመናን ከጥላቻ ፣ ፍትህን ከማጉደል፣ ሰውን ከመበደልና ከዛቻ እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳሰበች። የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ነገ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚጀመረውን የአብይ ጾም አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa