YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ5 ሺሕ በላይ ሴቶች በማህጸን ጫፍ ካንሰር በሽታ ለህልፈት እንደሚዳረጉ ተገለጸ።

በሽታው ይዟቸው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ታማሚዎቹ ወደ ህክምና ጣቢያ መምጣታቸው የበሽታውን አስከፊነት እንዳባባሰው ተገልጿል። የግንዛቤ ማነስ፣ በዘርፉ ላይ የሚታየው የህክምና እጥረት እንዲሁም ለምርምር ስራዎች በቂ ድጋፍ አለመደረጉ በሽታውን በሚፈለገው መጠን መከላከል እንዳይቻል ማድረጉ ተጠቅሷል። በየአመቱ 7 ሺህ አዳዲስ ህሙሟን እንሚመዘገቡም ተነግሯል።

ምንጭ:ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ሳፋሪ ኮም በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ብድር እያፈላለገ ነው!

ሳፋሪ ኮም በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ለማግኘት ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ለመጣመር እሞከረ ሲሆን ብድርም እያፈላለገ እንደሚገኝ አስታውቋል። ፈቃዱን ለማግኘት ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ሊያስፈልግ ይችላል ያለው ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተሰማራ ትርፋማ ለመሆን እስከ 10 ዓመታት ድረስ ሊወስድበት እንደሚችል ይፋ አድርጓል።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ከጉራፈርዳ ወረዳ የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ 73 ተጠርጣሪዎች ተያዙ!

የካቲት 8/2012 ዓ.ም በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ ከተከሰተ ግጭት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 73 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ አድማሱ ባኩስ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው ነው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል የወረዳውን ፀጥታ ከማስከበር እና ሕዝብን ከማረጋጋት አኳያ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ያልተወጡ አመራሮችን ጨምሮ 13 የሚሆኑት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንደሚገኙበት አስረድተዋል።ቀሪዎቹ 12 የመንግሥት ሠራተኞች እና 48 የሚሆኑት ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ነው የተናገሩት።የቀድሞ የቤንች ማጂ ዞን በአዲሱ አደረጃጀት ምዕራብ ኦሞና ቤንች ሸኮ ዞን በሚል መከፈሉን አስታውሰው፣ በቀድሞ የቤንች ማጂ ዞን ስር የነበረው የጉራፈርዳ ወረዳ በጥናት እስኪመለስ በጊዜያዊነት በቤንች ሸኮ ዞን ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦችም የመዋቅር አደረጃጀት ጥናቱ ሳይጠናቀቅ በወረዳው በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች ሕጋዊ ዕውቅና የሌለው ሰልፍ ሲካሄድ ተገቢውን የአመራር ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ፣ ሰልፉን ያስተባበሩ እና በችግሩ የተጠረጠሩ ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።በወቅቱ በተከሰተ ግጭትም የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን እና ችግሩ የበለጠ ጉዳት እንዳያደርስ ኅብረተሰቡ እና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ጥረት በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቁመዋል። አካባቢው በአሁኑ ወቅት ወደ ቀደመ ሰላሙ መመለሱንም መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን መሸጥ ይችላል።
ከ2700 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
📞 0953707070
ለብልጽግና ፓርቲ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ዛሬ በሀሮምያ፣ በጋምቤላ፣ በበደሌ፣ በሻሸመኔ እና በሌሎች ከተሞች ሰልፎች ተደርገዋል።

እንዲሁም በአፋር ክልል አዋሽ ከተማ እና በአርጎባ ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲን የሚደግፉ ሰልፎች ተደርገዋል።

ፎቶ :- Social Media
@YeneTube @Fikerassefa
⛔️Graphics Content ⛔️

ዛሬ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን፣ በተለይ በአወዳይ ከተማ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን፣ ፓርቲያቸውን እንዲሁም መንግስታቸውን ለመቃወም አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ከጸጥታ ሀይሎች ጋር ተጋጭተው በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

@YeneTube @Fikerassefa
የታሪክ ትምህርት በዚህ አጋማሽ የትምህርት ዘመን በሁሉም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት እንደሚጀምር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የታሪክ ምሁራን ጋር በታሪክ መፅሐፉ ይዘት ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡በውይይቱም የተለያዩ ኃሣቦች ከምሁራን ዘንድ የተነሱ ሲሆን በተለይ የአኖሌ ታሪክ በመፅሐፉ ውስጥ በመካተቱ ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡

የአኖሌ ታሪክ አሁን በተፃፈው ልክ ይቀመጥ፣ ሙሉ በሙሉ ቃሉን ልንጠቀም አይገባም እና ቃላቶቹን አሻሽለን ተጠቅመን እናስቀምጥ በሚል በሦስት የተለያዩ ኃሣቦች ዙሪያ ካለመግባባት ተደርሷል፡፡ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከታሪክ ትምህርት ነፃ የሆነ ስርዓት ይዘን ስለቆየን ግራ ሊያጋባንና ሊያከራክረን ቢችል የሚገርም አይደለም ሲሉ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ተናግረዋል፡፡

የመፅሐፉ ረቂቅ በተለያዩ ጊዜያት ከታሪክ ምሁራን የቀረበለትን አስተያየት አካቶ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ፕሮፌሰር ሂሩት የታሪክ ትምህርት በዚህኛው አጋማሽ የትምህርት ዘመን እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡መሻሻል ያለባቸው ታሪኮች ወደፊት የታሪክ ምሁራን በማስረጃ ላይ ተመርኩዘው በሚያቀርቡት ጥናት ሊሻሻል እንደሚችልም አስታውቀዋል፡፡

Via Ahadu TV
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል ሰዎች ምንነቱ ባልታወቀ ህመም እየሞቱ እንደሆነ ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡ ሟቾች እና ታማሚዎች በአፍ እና አፍንጫቸው ደም ይፈሳቸዋል፤ ከባድ ትኩሳትም ታይቶባቸዋል፡፡ የጤና ችግሩ የተከሰተው በቻይናው የካሉብ ጋዝ ፕሮጀክት አካባቢ ነው፡፡ ነዋሪዎች የሕመማችን ምክንያት የፕሮጀክቱ ኬሜካል የምንጠጣውን ውሃ ስለበከለብን ነው ብለዋል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ልቤን ያመኛል !!

ከ 7000 በላይ ሕፃናት የልብ ህክምና ለማግኘት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

6710 ላይ "A" ብለው በመላክ ለልብ ሕክምና ማዕከል ድጋፍ ያድርጉ።

ከአሁን ጀምሮ የቻሉትን ያክል ይላኩ በአንድ Text አንድ ብር ብቻ ነው የሚቆርጠው።


እንደላካችሁ Screenshot ላኩልን

እናመሰግናለን
እናመሰግናለን
በቀልዱም ተዝናኑ ⬆️
መልዕክቶች እየደረሱን ነው እናመሰግናለን።
ወደ 6710 መላካችውን ቀጥሉ 🙏
:
:
:
:
ሁላችንም የራሳችን ልጆ ላይ ቢደርስ ብለን ከወዲው የልብ ማዕከሉን እናጠናክር።
ነገ አርብ በ13/06/12 በሀዋሳ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ ይካሄዳል ብሏል ከተማ አስተዳደሩ።

@YeneTube @FikerAssefa
#update

በተጨማሪ ሀዋሳ ሲአን ቅዳሜ 14/2012 በሚሊንየም አዳራሽ ስብሰባ ጠርቷል ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና እንደሚገኝ የስብሰባው አስተባባሪ ጠቁሞኛል።

@YeneTube @Fikerassefa
ለቀድሞው የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር አሚር አማን የምስጋና እና የእውቅና ኘሮግራም ተካሄደ፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
👍1