YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ጉዳት አደረሰ፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ቋሪት ኢየሱስ ቀበሌ ዳሞት ተራራ አካባቢ በረዶ ቀላቅሎ የዘነበ ዝናብ በሰብል፣ በመጠለያ እና በእንስሳት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡የቋሪት ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሠለሞን በቀለ እንደገለጹት ትናንት የካቲት 11/2012ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ገደማ በጣለው ዝናብ በሰብል፣ በመጠለያ ቤቶችና በእንስሳት ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ ባይለው ጉዳቱ በደረሰ በ30 ደቂቃ ልዩነት ወደ ስፍራው እንደሔዱ ገልጸው ከፍተኛ መጠን ያለው በረዶ እንደጣለ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከ25 እስ 30 ሄክታር በሚሸፍን መሬት ላይ በረዶ የቀላቀለው ዝናብ መዝነቡንም ነው የተናገሩት፡፡ይህም በቀሪ እርጥበት በተዘሩት ጓያ እና ሽምብራ እንዲሁም በመስኖ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡ በሰው ላይ ግን ጉዳት አለመድረሱን ነው ያስታወቁት፡፡የጉዳት መጠኑን በማረጋገጥ ውሳኔ ለመስጠት መረጃ የሚያጣራ ባለሙያ መላካቸውንም አቶ አማረ ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ እታገኝ አደመ ደግሞ መረጃው እንዳልደረሳቸው ነው የተናገሩት።በወረዳው አስተዳዳሪ የሚመራ የተቋቋመ ግብረ ኃይል ስላለ ችግር ሲፈጠር የጉዳት መጠኑን በመለዬት ለክልሉ እንደሚልክም ተናግረዋል፡፡ መረጃውን መሠረት በማድረግ የክልሉን ድጋፍ የሚሻ ከሆነ ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት 235 ሚሊዮን ብር ብድር ባለማግኘቱ ስራው እንደተስተጓጎለበት ገለጸ!

የጣና በለስ ቁጥር አንድ የስኳር ፋብሪካ ፐሮጀክት ግንባታ 70 በመቶ መድረሱን ተከትሎ 6ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ለማምረት ዝግጁ ቢሆንም 235 ሚሊዮን ብር ብድር ባለማግኘቱ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ መቸገሩን ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ ዘገበ።የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አንተነህ አሰጌ እንደተናገሩት ከሆነም ባንኮች ብድር እንዲሰጡን የጠየቅን ቢሆንም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።በአሁን ወቅት 13ሺሕ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ የተተከለ ቢሆንም ለምርትነት ዝግጁ የሆነው 2ሺህ ሄክታር ብቻ መሆኑንም ጠቅሰዋል።የፋብሪካው ግንባታ በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው ሙሉ በሙለው ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት በመጪው ግንቦት ወር የሙከራ ምርቱን ለመጀምር በዝግጅት ላይ መሆኑን አንተነህ ገልጸዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🇹🇷#Study_in_Turkey!🇹🇷

ያለምንም ፈተና ቱርክ ሀገር ሄደው መማር ይፈልጋሉ?
90% ስኮላርሺኘ አግኝተው መማርስ?
#Sky_Education_Consultancy ይህን መልካም አጋጣሚ አመቻቸሎት!

Deadline: 22 Feb 2020

👉 Medicine & Health sciences
👉 Engineering
👉 Psychology
👉 Pharmacy
👉 Law
👉 Business Administration
👉 Computer science and IT
👉 Architecture
👉 Finance & banking.. and more

#Education_visa_Guaranteed
#Guaranteed_acceptance_letter

#ዛሬውኑ_ያናግሩን!! LIMITED SEATS
#Sky_Education_Consultancy
0977202020
ግራ አጋቢው ዘመን
አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ

የወባ ትንኞችን ከመግደል ሀሳቦችን ወደ መግደል፤
ከስራ አጥነት ወደ ስራ አልባነት እያመራን ነው… ምን ይሻላል?

ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ መፍትሄ አለው፡፡

መፅሐፉ እንዴት ከጀግንነት ወደለየለት ብሔርተኝነት፣
ከኃይማኖተኝነት ደግሞ ወደ ሽብርተኝነት እያመራን እንዳለን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ መጨረሻችንስ?

መልሱ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡

እንኳን ወደ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ግራ ተጋብተው መጡ!!

የእውነት ይሄ መፅሐፍ አስተሳሰባችሁን ያሰፋዋል!!

በየመፅሀፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል!!
ባይብል ኮድ

ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

በአለም ላይ ስለተከናወኑ ነገሮችና ወደፊትም ስለሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ በስም፣ በቀንና በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ አመት በፊት…

በየቤታችን በሚገኘው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኮድ ተቀጧል!!

በአንድ ምሽት ሽያጭ ብቻ ሪከርድ የያዙት ባይብል ኮድ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2 እና የመጨረሻው ቁጥር 3 ኮዶቹን እየፈቱ ያስደምሙናል፡፡

ሶስቱንም መጽሐፎች በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡
@teklutilahun
Forwarded from HEY Online Market
Samsung _M30s( 64GB )

Camera: 48Mp + 8Mp + 5Mp
Front : 16Mp
Ram:4GB Ram
Storage: 64GB
6000 mAh Battery (3days)

Price:9200

Contact us
0953964175
0925927457
0910695100
Forwarded from YeneTube
📌 Minoxidil የወንዶች ፀጉርና ፂም ማሳደግያ

📌 ፀጉሮት እየሳሳ አስቸግሮታል አልያም ፂም ማብቀል ይፈልጋሉ ? መፍትሔውን ይዘንሎት መተናል

ከቆዳችን ስር የሚገኘውን የፀጉር ጉጥ በማንቃት የሳሳን ፀጉር ወደ ቀድሞው የሚመልስ

📌📌 በ"FDA" እውቅናና ማረጋገጫ የተሰጠው ደግሞም በebay ፣ amazon እና በመሳሰሉት የ online መገበያያዎች ላይ "5" ★★★★★ ኮኮብ ያገኘ ነው

በቀን 2 ጊዜ ለሚጠቀሙ ሰዎች በ 1 ወር ውስጥ ውጤት የሚያሳይ

📞 0993944661
📞 0953928523
አቶ ፈንታ ደጀን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒሰትር ዴኤታ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተሹመዋል፡፡ አቶ ፈንታ በአማራ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ5 ሺሕ በላይ ሴቶች በማህጸን ጫፍ ካንሰር በሽታ ለህልፈት እንደሚዳረጉ ተገለጸ።

በሽታው ይዟቸው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ታማሚዎቹ ወደ ህክምና ጣቢያ መምጣታቸው የበሽታውን አስከፊነት እንዳባባሰው ተገልጿል። የግንዛቤ ማነስ፣ በዘርፉ ላይ የሚታየው የህክምና እጥረት እንዲሁም ለምርምር ስራዎች በቂ ድጋፍ አለመደረጉ በሽታውን በሚፈለገው መጠን መከላከል እንዳይቻል ማድረጉ ተጠቅሷል። በየአመቱ 7 ሺህ አዳዲስ ህሙሟን እንሚመዘገቡም ተነግሯል።

ምንጭ:ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ሳፋሪ ኮም በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ብድር እያፈላለገ ነው!

ሳፋሪ ኮም በኢትዮጵያ ቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ለማግኘት ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ለመጣመር እሞከረ ሲሆን ብድርም እያፈላለገ እንደሚገኝ አስታውቋል። ፈቃዱን ለማግኘት ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ሊያስፈልግ ይችላል ያለው ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተሰማራ ትርፋማ ለመሆን እስከ 10 ዓመታት ድረስ ሊወስድበት እንደሚችል ይፋ አድርጓል።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ከጉራፈርዳ ወረዳ የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ 73 ተጠርጣሪዎች ተያዙ!

የካቲት 8/2012 ዓ.ም በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ ከተከሰተ ግጭት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 73 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ አድማሱ ባኩስ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው ነው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል የወረዳውን ፀጥታ ከማስከበር እና ሕዝብን ከማረጋጋት አኳያ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ያልተወጡ አመራሮችን ጨምሮ 13 የሚሆኑት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንደሚገኙበት አስረድተዋል።ቀሪዎቹ 12 የመንግሥት ሠራተኞች እና 48 የሚሆኑት ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ነው የተናገሩት።የቀድሞ የቤንች ማጂ ዞን በአዲሱ አደረጃጀት ምዕራብ ኦሞና ቤንች ሸኮ ዞን በሚል መከፈሉን አስታውሰው፣ በቀድሞ የቤንች ማጂ ዞን ስር የነበረው የጉራፈርዳ ወረዳ በጥናት እስኪመለስ በጊዜያዊነት በቤንች ሸኮ ዞን ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦችም የመዋቅር አደረጃጀት ጥናቱ ሳይጠናቀቅ በወረዳው በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች ሕጋዊ ዕውቅና የሌለው ሰልፍ ሲካሄድ ተገቢውን የአመራር ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ፣ ሰልፉን ያስተባበሩ እና በችግሩ የተጠረጠሩ ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።በወቅቱ በተከሰተ ግጭትም የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን እና ችግሩ የበለጠ ጉዳት እንዳያደርስ ኅብረተሰቡ እና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ጥረት በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቁመዋል። አካባቢው በአሁኑ ወቅት ወደ ቀደመ ሰላሙ መመለሱንም መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን መሸጥ ይችላል።
ከ2700 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
📞 0953707070
ለብልጽግና ፓርቲ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ዛሬ በሀሮምያ፣ በጋምቤላ፣ በበደሌ፣ በሻሸመኔ እና በሌሎች ከተሞች ሰልፎች ተደርገዋል።

እንዲሁም በአፋር ክልል አዋሽ ከተማ እና በአርጎባ ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲን የሚደግፉ ሰልፎች ተደርገዋል።

ፎቶ :- Social Media
@YeneTube @Fikerassefa
⛔️Graphics Content ⛔️

ዛሬ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን፣ በተለይ በአወዳይ ከተማ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን፣ ፓርቲያቸውን እንዲሁም መንግስታቸውን ለመቃወም አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ከጸጥታ ሀይሎች ጋር ተጋጭተው በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

@YeneTube @Fikerassefa
የታሪክ ትምህርት በዚህ አጋማሽ የትምህርት ዘመን በሁሉም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት እንደሚጀምር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የታሪክ ምሁራን ጋር በታሪክ መፅሐፉ ይዘት ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡በውይይቱም የተለያዩ ኃሣቦች ከምሁራን ዘንድ የተነሱ ሲሆን በተለይ የአኖሌ ታሪክ በመፅሐፉ ውስጥ በመካተቱ ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡

የአኖሌ ታሪክ አሁን በተፃፈው ልክ ይቀመጥ፣ ሙሉ በሙሉ ቃሉን ልንጠቀም አይገባም እና ቃላቶቹን አሻሽለን ተጠቅመን እናስቀምጥ በሚል በሦስት የተለያዩ ኃሣቦች ዙሪያ ካለመግባባት ተደርሷል፡፡ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከታሪክ ትምህርት ነፃ የሆነ ስርዓት ይዘን ስለቆየን ግራ ሊያጋባንና ሊያከራክረን ቢችል የሚገርም አይደለም ሲሉ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ተናግረዋል፡፡

የመፅሐፉ ረቂቅ በተለያዩ ጊዜያት ከታሪክ ምሁራን የቀረበለትን አስተያየት አካቶ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ፕሮፌሰር ሂሩት የታሪክ ትምህርት በዚህኛው አጋማሽ የትምህርት ዘመን እንደሚጀምር ገልፀዋል፡፡መሻሻል ያለባቸው ታሪኮች ወደፊት የታሪክ ምሁራን በማስረጃ ላይ ተመርኩዘው በሚያቀርቡት ጥናት ሊሻሻል እንደሚችልም አስታውቀዋል፡፡

Via Ahadu TV
@YeneTube @FikerAssefa