YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአፍሪካ የምድር ጦር ኃይሎች ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመሯል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የዮሐንስ ቧያለው እና የላቀው አያሌው ከስልጣን መነሳት ተቃውሞ አስነሳ!

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 10/2012 ባደረገው አስቸኳይ ጉዳዔ ላይ የክልሉን ምክትል ርእሰ መስተዳድር ላቀ አያሌው እና የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ ቧያለው ከስልጣናቸው መነሳታቸው ተቃውሞ አስነሳ ፡፡
ለምክትል ርእሰ መስተዳድር በእጩነት በቀረቡት ፈንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ላይ የተቃውሞ ሐሳብ ባይቀርብም ክልሉን በለቀቁ መሪዎች ላይ ግን የምክር ቤት አባላቱ ‹‹ክልሉን ለቅቀው ወደ ፌዴራል የሄዱት አራቱም መሪዎች ለክልሉ በሚያስፈልጉበት ወቅት ላይ እንዲነሱ መደረጉ አግባብ አይደለም፡፡ በዚህ ሰዓት ክልሉን ማደራጀት እና እንዲጠናከር በማድረግ ፋንታ ወደ ፌደራል መላክ ክልሉን የአመራርነት መለማመጃ ከማድረግ የዘለለ ትርጉም የለውም›› ብለዋል፡፡

መላኩ አለበል የፌዴራል ሹመታቸው ቀድሞ በፓርላማ የፀደቀ በመሆኑ እና ዮሐንስ ቧያለውም የፓርቲ ተልዕኮ እንጂ ጉዳዩ በምክር ቤቱ የማይታይ ባለመሆኑ እንዲሁም በላቀ አያሌው እና ፈንታ ደጀን ክልሉን መልቀቅ ላይ ምክር ቤቱ የተወያየበት ሲሆን የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የሰው ኃይል ስምሪቱ የፓርቲያቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ሹመቱን የማጽደቅና አለማፅደቅ ስልጣን የምክር ቤቱ ነው፤ የምክር ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ ነገር ግን የሌሎች አካላት ተፅዕኖ እንዳለበት ተደርጎ መወሰድ የለበትም ሲሉም ማላሽ መስጠታቸውን አብመድን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የድንጋይ ከሰል ከውጪ ማስገባት ሊቆም ነው!

በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት ለመጠቀም እና ከወጪ አገራት የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ለመተካት በመታሰቡ የድንጋይ ከሰል ከውጪ አገራት እንዳይገባ ሊደረግ ነው።ከውጪ አገራት የሚመጣውን የድንጋይ ከሰል ምርት ማስቆም ያስፈለገው፣ ኢንዱስትሪዎች በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል የሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አገኘው ተሻገር ከኃላፊነታቸው ተነሱ!

የክልሉ የሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አገኛው ተሻገር ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸውም ሲሣይ ዳምጤ የቢሮው ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 10/2012 ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ሲሳይ ዳምጤ የቢሮው ኃላፊ እንዲሆኑ በአብለጫ ድምጽ፣ በአንድ ታቀውሞ እና በሦስት ድምጸ ተዓቅቦ ሹመቱን አፅድቋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ ስቴት ሴክሬታሪ የሆኑትን ማይክ ፖምፔዮን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ስቴትን ግንኙነት ስለ ማጠናከር፣ ስለ ቀጣይ የትብብር አቅጣጫዎች፣ ስለ ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ ተወያይተዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአማራ ክልል የሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አገኘው ተሻገር ከኃላፊነታቸው ተነሱ! የክልሉ የሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አገኛው ተሻገር ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸውም ሲሣይ ዳምጤ የቢሮው ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 10/2012 ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ሲሳይ ዳምጤ የቢሮው ኃላፊ እንዲሆኑ በአብለጫ ድምጽ፣ በአንድ ታቀውሞ እና በሦስት ድምጸ ተዓቅቦ…
#update
አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ!

የአማራ ክልል የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አገኘሁ ተሻገር በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ደረጃ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮው በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ አቶ ሲሳይ ዳምጤን የክልሉ ሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል ሲል የዘገበው አብመድ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ እስከ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ምስል መለየት የሚያስችሉ የደህንነት ካሜራዎች ሊገጠሙ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እስከ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ምስል መለየት የሚያስችሉ የደህንነት ካሜራዎችን ለመግጠም እንቅስቃሴ ተጀምሯል።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በዘርፉ ልምድ ካለው ድርጅት ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ቴክኖሎጂውን መዘርጋት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ጀማል በከር የዜጎችን ደህንነት በቴክኖሎጂ ለማስጠበቅ ትኩረት እየተሰራ ሲሆን ቴክኖሎጂው ዜጎች ከደህንነት ስጋት ተላቀው የእለት ተእለት ተግባራቸውን እንዲከውኑ ያግዛል ብለዋል፡፡በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚገጠሙት የደህንነት ካሜራዎች ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል የዜጎች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚስችሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ:Addis Ababa city Admin press Secretariat
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚከተሉት ስድስት ፓርቲዎች የምዝገባ እውቅና ሰጥቷል፡፡

1. ሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
2. መላው አማራ ህዝብ ፓርቲ
3. ነጻነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ህብረት ፓርቲ
4. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ)
5. አፋር ነጻ አውጪ ግንባር ፓርቲ ( አነግፓ)
6. የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ

Via NEBE
@YeneTube @FikerAssefa
ብልፅግና ፓርቲ በ40 ሚሊዮን ብር አዲስ ጽሕፈት ቤት ሊገነባ ነው!

ብልፅግና ፓርቲ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለሦስት ወለል የጽሕፈት ቤት ሕንፃ ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ።ግንባታው በያዝነው ዓመት ተጀምሮ በቀጣይ ኹለት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል የተባለ ሲሆን፣ የፓርቲው የዞን ኃላፊዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ቢሮዎች፣ ሦስት አዳራሾች እና መዝናኛ ክበቦች እንደሚኖሩት ታውቋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሰት ላለፉት ሶስት አመታት ከኤርትራ ድንበር አቋርጠው ለሚመጡ #ኤርትራዊያን የቡድን እውቅናን መሰረት በማድረግ ጥገኝነት በመስጠት ስታስተናድ ብትቆይም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ግን ይህንን ማቆሟን አስታወቀች፡፡

ይህም ከተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ወቀሳ እያስነሳ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት የስተደተኞችን ስምምነት የጣሰ ነው ተብሏል፡፡

የወል ጥገኝነት ማለት የአንድ አገር መንግስት ወይም የተባበሩት መንግሰታት የስደተኞች ኮሚሽን ስደተኞች ከሚሰደዱበት አገር ባለ ሁኔታ፣ አገር አልባ ከሆኑ እና በሌሎች መሰል ምክንያቶች በግል ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያበቃ ምክንያት እንዳላቸው ሳይጠየቁ የዛ አገር ዜጋ ወይም የዛ ቡድን አባል ከሆኑ ብቻ የሚሰጥ የጥገኝነት አይነት ነው፡፡

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ የሚመረቱ የሲጋራ ምርቶች ላይ ኻያ ፍሬ የሚይዝ አንድ ፓኬት ሲጋራ ከዚህ ቀደም ሲሸጥበት ከነበረው 25 ብር ዋጋ ወደ 40 ብር፣ የ15 ብር ጭማሪ አሳየ።

ምንም እንኳን የምርት ዋጋ ላይ ጭማሪ ባይኖርም፣ አከፋፋዮች በኤክሳይስ ታክስ ምክንያት በሚኖረው የዋጋ ጭማሪ ላይ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት በሚል ምርት በመያዛቸው የተፈጠረ እንደሆነም አዲስ ማለዳ ከተለያዩ አካላት አረጋግጣለች።

@YeneTube @Fikerassefa
በደቡብ ክልል ጉራፋርዳ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ከተከሰተው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአሁኑ ወቅት የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ በክልሉ ህግን የማስከበር እና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ በልዩ ሁኔታ መጀመሩን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።በተለይም በህዝቡ ውስጥ የቆዩ ቅራኔዎችን በመፍታት መግባባት ላይ የተመሠረተች ሀገርና መንግስት ለመገንባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲደረግ መቆየቱ ተመላክቷል።በአንፃሩ በተለያዩ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ሰለባ በሆኑ አካላት አንቀሳቃሽነት በተለያዩ አካባቢዎች የዜጎችን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያውኩ ተግባራት ሲፈጸሙ መቆየታቸው ነው የተገለጸው።

ክልሉ የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል እና የተጀመረው ለውጥ እንዳይደናቀፍ የክልሉ መንግስት መሰል ችግሮችን ለማስወገድ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።አሁን ላይም ለህዝቡ ሰላማዊ ኑሮ አስጊ እና ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ መሪ ተዋናይ የነበሩ አካላት ላይ የክልሉ መንግስት ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተመላክቷል።

በዚህ መሰረትም በጉራፋርዳ ወረዳ ትላንት በተከሰተው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የተለያዩ አመራሮችና ባለሙያዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው።በቁጥጥር ስር የዋሉትም አቶ ኩንዲሳ ንጉሴ የወረዳው አስተዳዳሪ፣ አቶ ሃይሉ ይግለጡ የወረዳው ድርጅት ጽህፈት ቤት ሃላፊ፣ አቶ ቢሰጥ ወርቁ የአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ፣አቶ ኦይሳ አለሙ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ፣ አቶ እንዳልክ ደምሴ ሰላምና ጽህፈት ቤት ሃላፊ፣ አቶ ማስቲ ፎልጂ የማዘጋጃ ቤት ሃላፊ፣ አቶ አጥናፉ ግዛው የአስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ፣አቶ ታጋይ ሳሙኤል ኮጃ የማዘጋጃ ቤት ሃላፊ እና ሌሎች ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የሞዴስ እና ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በማሰራጨት ላይ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሞዲስ እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ ለማቅረብ ከባለሃብቶች እና ከበጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች የሰበሰባቸውን ቁሳቁሶች አሰራጭቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ጽህፈት ቤት ሓላፊ እና የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አለምጸሀይ ጳውሎስ እንዲሁም ሌሎች የከተማዋ የስራ ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የሞዴስ እና ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶቹን አስረክበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የተማሪዎች የምገባ ሂደት ምን እንደሚመስል እና በቀጣይ መስተካከል ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትምህርት ቤቱ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከትምህርት ቤቶች እድሳት ጀምሮ የተማሪዎች ምገባ፣ የደንብ ልብስ ፣የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በማቅረብ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ወ/ሮ አለምጸሀይ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@YeneTube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ አዲስ መድኃኒት ለገበያ ሊቀርብ ነው ተባለ፡፡

የቻይና ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንደገለጸው መድኃኒቱን ለገበያ የሚያቀርበው ዠጂያንግ ሂሱን ፋርማሲዩቲካል የተሰኘው ግዙፍ የቻይና መድኃኒት አምራች ኩባንያ ነው ተብሏል።
የኮቪድ-19ን በሽታ የሚከላከለው አዲሱ መድኃኒት ፋቪፒራቪር የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ ለገበያ ለማቅረብ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ፈቃድ ማግኘቱ አስታውቋል።

በመረጃው መሠረት መድኃኒቱ ለገበያ ከቀረበ በኋላም፣ ኩባንያው በመድኃኒቱ ላይ የሚያደርገውን ክሊኒካዊ ፍተሻ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የቻይና ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፋቪፒቪር “በመጠኑም ቢሆን ውጤታማነት አለው” ካለ በኋላ፣ በክሊኒካዊ ፍተሻው ወቅት ቢያንስ 70 ሰዎች መሳተፋቸውን ይፋ አድርጓል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ፣ ለኮቪድ-19 በሽታ ክትባት ለመሥራት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ይወስዳል ብለው እንደነበር ኢቢሲ ሮይተርስ ጠቅሶ ዘግቧል።

Via:- Addis Ababa City Administration
@YeneTube @Fikerassefa
የሱማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ የፕሬዝዳንት ፎርማጆን ይቅርታ እንደተቀበሉ የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ፎርማጆ ይቅርታ የጠየቁት የቀድሞው አምባገነን ዚያድ ባሬ በሱማሌላንድ ሕዝብ ላይ ላደረሱት በደል ነበር፡፡ በተያያዘ፣ ፎርማጆ ሐርጌሳን መጎብኘት እንደሚፈልጉ ዛሬ በይፋ አስታውቀዋል፡፡ ቢሂ ግን ጥያቄውን አልተቀበሉም፡፡

Via:- Wazema
@YeneTube @Fikerassefa
የስልጤ ዞን ርዕሰ መዲና የሆነችው ወራቤ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን ለመቀበል ዝግጅቷን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።

በነገው እለት ማለትም የካቲት 11/2012 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ከስልጤ ዞን ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመወያየት ፕሮግራም መያዙ ይታወቃል።

በመሆኑም ይህን ፕሮግራም በተሟላ መልኩ ለማስኬድና እንግዶችንም በተገቢው ክብር ለመቀበል የዞኑ ርዕሰ መዲና ወራቤ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ውይይቱ የሚደረግባቸው ቦታዎች ማለትም የስልጤ ባህል አደራሽና የወራቤ ስታድየም አስፈላጊው ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው።

መላው የዞናችን ህዝብ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና እሳቸውን ተከትለው ለሚመጡ እንግዶች የተለመደውን የእንግዳ አቀባበል እንዲያደርግና ለውይይቱ ውጤታማነትም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ:- ስ/ዞ/ህ/ግ/ጽ/ቤት
@YeneTube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ በተቀሰቀሰበት ዉሃን ከተማ የሚገኝ ሆስፒታል ዳይሬክተር በኮሮና ቫይረስ ተጠቅቶ መሞቱን የአከባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

#Coronavirus
@YeneTube @Fikerassefa
የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ ከኢትዮጵያ ቴሌኮም ፍቃድ ለማግኘት ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር ለመጣመር በመነጋገር ላይ እንደሆነ ዘ ኢስት አፍሪካን አስነብቧል፡፡ ቴሌኮሙ ለ2 የግል ቴሌኮም ኩባንያዎች ፍቃድ ለመስጠት በሚያዚያ ጨረታ ያወጣል፡፡ ሳፋሪኮም ከሌሎች ጋር የሚጣመረው ጨረታው ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ስለሚጠይቅ ነው፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa