YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የራይድ አባላት የተሰረቀ ተሽከርካሪ ያዙ!

ትናንት ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የተሰረቀን መኪና የራይድ ቤተሰብ ከፖሊስ ጋር በጋራ ተረባርቦ ሰሚት አካባቢ መያዛቸውን ራይድ በገፁ አስታወቀ። ከ40 በላይ የሚሆኑ አባላት በአካባቢያቸው የሚያልፍ የተሰረቀ መኪና እንዲከታተሉ በተበተነ መረጃ መሰረት ነው ከፖሊስ ጋር በመተባበር ሰሚት ፍየል ቤት አቅራቢያ መኪናውን ሊይዙ የቻሉት::

Via Ethio Daily Post
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ 80 የመኖሪያ ቤቶች ለዳኞች ይተላለፋሉ!

የዳኞችን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም፤ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ጉዳይ በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በተያዘው እቅድ መሰረት 80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዳኞች እንደሚተላልፍ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ንዋይ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የዳኞችን ደመወዝ ጥቅማጥቅምና የመኖሪያ ቤቶች ጉዳይ በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል።ከዳኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ ጋር በተያያዘ ግንባታው ከተጀመረ ብዙ ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ በውሉ መሠረት ለማከናወን የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንቅፋት ፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የኮቪድ-19 (የኮሮና ቫይረስ በሽታ) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ
የካቲት 8/2012

➡️ ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ 125,850 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3,538 በሽታውን ሪፖረት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ እንዲሁም 465 የሚሆኑት ደግሞ ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ነገር ግን እስካሁን በለው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺን አልተከሰተም፡፡

➡️ ከጥር 15/2012 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 51 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

➡️ ከነዚህም ጥቆማዎች 16ቱ የበሽታውን ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስላላቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም 16ንም የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

➡️ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚያገለግሉ የተለያዩ ግብዓቶች ለጋንዲ ጠቅላላ ሆስፒታል እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

➡️ የየካ ኮተቤ ሆስፒታል እና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ባለሙያዎች ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የትግበራ ልምምድ አድርገዋል፡፡

➡️ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ቅድመ ዝግጅትና ምላሽ እቅድ ባላድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተዘጋጅቶ ተጠናቋል፡፡

➡️ ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ቁልፍ መልዕክቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ከመዘጋጀታቸውም በላይ በሃገር ውስጥ በሚገኙ በተለያዩ ቋንቋዎች እና በውጪ ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ፡፡

➡️ ለግንዛቤ ማስጨበጫና የስራ መተግበሪያ ቅጾች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡

➡️ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ለተውጣጡ 45 በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ተግባቦት (communication) ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

Via Ministry of Health
@YeneTube @FikerAssefa
የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ያጋጠመው የውሃ እጥረት...

በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል አዳዲስ ማዋለጃ ክፍሎች ተዘጋጅተው አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም በውሃ እጥረት ምክንያት ወላዶች ታጥበው ለመውጣት መቸገራው ተገለጸ።

የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ታሪኩ ደሬሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በሆስፒታሉ በወር ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ እናቶች ይወልዳሉ። በሆስፒታሉ የውሃ አቅርቦቱ በጣም የተቆራረጠ ነው።

ለማዋለጃ ክፍሎች ተብለው የተተከሉ የውሃ ማከማቻዎች ቢኖሩም በቀን አንድ ጊዜ ማታ የሚመጣው ውሃ ሊሞላቸው አልቻለም። በዚህም እናቶች ከወለዱ በኋላ ታጥበው ለመውጣት ተቸግረዋል።

እንደ ዶክተር ታሪኩ ደሬሳ ገለፃ ከሆነ፤ ቀደም ብሎ እናቶች የሚወልዱበትን ስፍራ በመቀየር በአንድ ክፍል ውስጥ ሁሉንም ነገር እንዲጨርሱ የማድረግ አሰራር ተጀምሯል። ነገር ግን፤ በውሃ እጥረት ምክንያት ወላድ እናቶች ታጥበው መውጣት አልቻሉም።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር በሰፊው ከሚሰራጭባቸው ሃገሮች ተርታ መሰለፏ ተገለጸ፡፡

የጦር መሳሪያዎች በቀላሉ መገኘት፤ህብረተሰቡ ጦር መሳሪያ የመታጠቅ ፍላጎት መጨመር፣ እና በጎረቤት ሃገራት ያሉ ክፍት ድንበሮችና ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች አባባሽ የሆኑ ምክንያቶች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሕግ ጥናቶች፤ማርቀቅና ማከፋፈል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይሁን ይርጋ በጉዳዩ ላይ በሰጡን አስተያየት ባለፉት ጥቂት አመታት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በኢትዮጲያ ውስጥ እየጨመረ እንደሚገኝ ነው፡፡

ይህም ሃገሪቱን ወደ አለመረጋጋት እና የደህንነት ስጋት ስለሚከታት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጦር መሳሪያዎች ይዞታ መቆጣጠር እና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል የወጣውን አዲስ አዋጅ ተግባራዊ መደረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የጦር ማሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን በተለመከተ የባለድርሻ አካላት መድረክ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል፡፡በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው ይህ የምክክር መድረክም በሃገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ወቅቶች በሚከሰቱ ግጭቶች የተነሳ ይህ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ፤የሕግና የአሰራር ስርአት የሌለው በመሆኑና በሌሎችም ምክንያች የአዋጁን ተግባራዊነት እንዲፈፀም ባለድርሻ አካለት እንዲመክሩበት የተዘጋጀ ነው፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የክልል ልዩ ሃይል ፈርሶ በሃገር መከላከያ ሰራዊት እንዲጠቃለል ተጠየቀ፡፡

ይህ የተባለው ጽናት ለኢትዮጵያ፣የኢትዮጲያ አሜሪካዊያን ዜጎች ምክክር፣የዘር ፖለቲካ በህግ ይታገድ ዘንድ ግፊት የማድረግ ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትወርክ የተሰኙ የሰብዓዊ ድርጅቶች በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ትንታኔ የሰጡት የዲላ ዩንቨርሲቲ መምህር መስከረም አበራ በሃገራችን እየተካረረ የመጣው አክራሪ ብሄርተኝነት በመገናኛ ብዙሃንና በክልል ልዩ ሃይሎች እየተደገፈ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
እነዚህ ልዩ ሃይሎች በብዛትና በታጠቋቸው መሳሪያዎች ማእከላዊ መንግስቱን እስከመገዳደር መድረሳቸውን የሚናገሩት ተንታኟ፤ አደረጃጀታቸው ህጋዊ ባለመሆኑ ለሚያደርሱት ጥፋት ተጠያቂ የሚሆኑበት የህግ አግባብ የለም ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ ወገንተኝነታቸው ላሰለጠናቸውና ላስታጠቃቸው ክልል ብቻ በመሆኑ በክልሉ ውስጥ ለሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ከለላ ከመስጠት ይልቅ ራሳቸው በዳይ ሆነው የሚገኙበት ጊዜ በርካታ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ልዩ ሃይሎች በወታደራዊ ስነ ምግባር ያልታነጹ መሆናቸውንም መምህር መስከረም ጠቁመዋል፡፡
በተለይም ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ውጤት ላይ የልዩ ሃይሎች መኖር አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚፈጥርና ሃገሪቷን ወደ እልቂት እንዳይወስዳት ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

የአስተዳድርና አመራር ባለሙያው ዶክተር ኤርሲዶ ሌንዴቦ በበኩላቸው ህዝባችን በዚህ ሰዓት ከምንም በላይ የሚያስፈልገው ሰላም፣የተረጋገጠ የምግብ ዋስትና፣ጤና እና መሰረተ ልማት እንጂ እርስ በእርሱ የሚፎካከርበት ታጣቂ አይደለም ብለዋል፡፡

በመሆኑም የክልል መንግስታት ለልዩ ሃይሎቻቸው የሚያባክኑትን በጀት ለዜጎቻቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች ቢያውሉት መልካም ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

የቀድሞ ወታደራዊ መኮንኖችም እኛ የምናውቀው ልዩ ሃይል ወይም ፈጥኖ ደራሽ ማለት ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ ሆነው ለባህር ሃይልና አውሮፕላን እንዳይጠለፍ እንዲሁም አንዳንድ ብሄራዊ ስጋት ለሆኑ አደጋዎች ፈጥነው የሚደርሱ እንጂ ለክልሎች የሚታዘዙ በርካታ ታጣቂዎችን ማሰለፍ ማለት አይደለም ሲሉ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
እናም መንግስት ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ልዩ ሃይሎችን አፍርሶ በሃገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እንዲያጠቃልል በምክክር መድረኩ ላይ ጥያቄ ቀርቧል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እየተፈጠሩ ላሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት ልዩ ሃይሎች ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሶ መንግስት ልዩ ሃይሎችን እንዲያፈርስ መጠየቁ ይታወሳል።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውይይት እየተደረገ ነው።

በውይይቱ ላይ ሚንስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
በመድረኩ ግድቡን አስመልክቶ በመደረግ ላይ ስላሉት ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በውይይቱም ላይ ሚንስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፏቸውን እያደረጉ ነው። በመድረኩም ግድቡን አስመልክቶ በመደረግ ላይ ስላሉት ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ውይይት በመደረግ ላይ መሆንኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via:- Addis Ababa city administration
@YeneTube @Fikerassefa
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ሳኡዲ አረቢያ አቅንተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ወደ ሪያድ ያቀኑት የሳውዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ነው ተብሏል፡፡መሪዎቹ በሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
'ኮሮናቫይረስን ወደ አፍሪካ መውሰድ አልፈልግም''

የ 21 ዓመቱ ካሜሮናዊ ኬም ሴኑ ፓቬል በቻይናዋ ጂንግዙ ግዛት ተማሪ ሲሆን በኮሮናቫይረስ መያዙን ካወቀ በኋላ "ተሽሎሃል ወደ አገርህ ተመለስ እንኳን ቢሉኝ አልመለስም" ብሏል። ምክንያቱ ደግሞ ቫይረሱን ወደ አፍሪካ ይዞ ላለመግባት ነው።

ኬም ሴኑ ፓቬል ከሁለት ሳምንታት ተከታታይ ህክምና በኋላ እየተሻለው መጥቷል። በሲቲ ስካን በተደረገለት ምርመራም ቫይረሱ ከሰውነቱ እንደጠፋ ምልክቶች ታይተዋል።

ፓቬል በገዳዩ ኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሲሆን ሙሉ የህክምናው ሙሉ ወጪ በቻይናዋ ግዛት ተሸፍኗል።

'' ትምህርቴን ሳልጨርስ ወደ አገር ቤት መመለስ አልፈልግም። ወደ ካሜሩን የምምለስበት ምንም ምክንያት የለኝም፤ ሙሉ የሆስፒታል ወጪዬ በቻይና መንግስት ተሸፍኖልኛል''ብሏል።

Via:- Arts TV

@YeneTube @Fikerassefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 79ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2012 የፌዴራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ለተጨማሪ በጀቱ መሰረታዊ መነሻ የሆነው በቅርቡ በመንግስት የተዘጋጀው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሲሆን ዋናው አላማው ኢኮኖሚው አሁን ከገጠመው ተግዳሮቶች የሚላቀቅበትን የፖሊሲ እርምጃዎች ተግባራዊ ለማድረግ ብር 18 ቢሊየን፤ ለልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ትግበራ ብር 2 ቢሊየን እንደዚሁም ለእኩል ስራ እኩል ደመወዝ አገራዊ ትግበራ ብር 7.9 ቢሊየን በድምሩ ብር 27.89 ቢሊየን ተጨማሪ በጀት እንዲጸድቅ የገንዘብ ሚኒስቴር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የተጨማሪ በጀት ረቂቅ እዋጅ ላይ በስፋት ተወያይቶ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የተወያየው በገንዘብ ሚኒስቴር የቀረቡትን ለደብረ ማርቆስ-ሞጣ የመንገድ ሥራ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣ ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የልዕቀት ማዕከል መመስረቻ ፕሮጀክት እና ለሁለተኛው አገር አቀፍ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ሳንቴሽንና ሐይጅን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውሉ የብድር ስምምነቶች እና ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ሲሆን ብድሮቹ ከሀገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ፣ የ10 ዓመት እፎይታ ያላቸው፣ በረጅም ጊዜ የሚከፈሉ እንደዚሁም ወለድ የማይታሰብባቸው በመሆናቸው አዋጆቹ ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡

ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ መዝሙርና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ አገራችን ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን አጋርነት ለማሳደግ፣ ለፓን አፍሪካኒዝምና ለአፍሪካ የውህደት አጀንዳ ተግባራዊነት ያላትን ቁርጠኝነት ለማስቀጠል እንዲሁም የህብረቱ ኮሚሽን አስተናጋጅ አገርነት ሚናዋን ለመወጣት ከምታከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ አላማን ማውለብለብ፣ የአፍሪካ ህብረት መዝሙርን ማዘመር እና አፍሪካ ቀን ታስቦ እንዲውል ማድረጉ አገራችን ለህብረቱ አላማዎች ስኬት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ በመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የግብርና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችን ለማቋቋም በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሌጆቹ ተጠሪነታቸው ለግብርና ሚኒስቴር ሆኖ እራሳቸውን የቻሉ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ተቋማት እንዲሆኑና በግብርናው ዘርፍ በአገሪቱ ልዩ ፍላጎቶች ላይ አትኩረው እንዲሰሩ ማድረግ እንዲቻል የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ም/ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ከላከልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የፀረ ወባ መድኃኒት የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማከም ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የዓለም ስጋት ለሆነው የኮሮና ቫይረስ በሽታ መድኃኒት ለማግኘት የበርካታ ሀገራት ተመራማሪዎች ምርምር በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። በዚህ መሰረትም በቻይና ብቻ በበሽታው መድኃኒት ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉ ከ80 በላይ የቤተ ሙከራ ማዕከላት ተቋቁመው ስራ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።እነዚህ የቻይና ተመራማሪዎች ለወባ በሽታ መድኃኒትነት የሚያገለግለው “ክሎሮኪን ፎስፌት” የተሰኘው መድኃኒት የኮሮና በሽታን ለማከም ውጤታማ መሆኑን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

መድኃኒቱ ተጨማሪ የላቦራቶሪ ሙከራ ከተደረገበት በኋላ በስፋት አገልግሎት ላይ የሚውል መሆኑ ተመላክቷል። በቅርቡ በቻይና ሁቤይ ግዛት ውኃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና በሽታ አድማሱን በማስፋት በተለየዩ የዓለም ሀገራት ውስጥ እየተዛመተ ይገኛል።አሁን ላይ በቻይና ብቻ ከ1 ሺህ 770 በላይ ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል።በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ወደ 70 ሺህ 548 ማሻቀቡን የቻይና ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ሺንዋ/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ተሰርቆ ኔዘርላንድ የተወሰደውን ዘውድ የቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን በነገው ዕለት ልረከበው ነው አለ፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
84,587 የተለያዩ የውጭ አገራት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል ታያዘ!

በደወሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ 17,965 የአሜሪካ ዶላር፣ 2,520 ፖውንድ እና 64,102 የየመን ሪያል በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል በሁለት የመቆጣጠሪያ ጣቢያው ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ የካቲት 08 ቀን 2012 ዓ.ም ተይዟል፡፡ሕገ ወጥ ገንዘቡም ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደdረገ ሲሆን ከዚህ ወንጀል ጋር ተያይዞ አራት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በፌደራል ፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡

Via Ministry of Revenue
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 780 ሚሊዮን የሚጠጉ ቻይናዊያን ዜጎች በጉዞ እግድ ውስጥ በወደቁ አካባቢዎች የሚኖሩ እንደሆኑ CNN ሰበሰብኩት ባለው መረጃ አሳውቋል። ይህም ማለት የሀገሪቱ ግማሹ ህዝብ ወይም የአለም 10% የአለም ህዝብ እንደማለት ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የሶሪያ ሠራዊት 70 አስከሬኖችን የያዘ የጅምላ መቃብር በደማስቆ አቅራቢያ በሚገኝ ቀደም ሲል በአማፅያኑ ተይዞ በነበረ አካባቢ ማግኘቱን የሀገሪቱን የዜና ወኪል ጠቅሶ የዘገበው አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ከ123 ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት ተመርቆ ሥራ ጀመረ፡፡በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በግብርና ዕድገት ፕሮግራም በ2010 ዓ.ም የግንባታ ሥራው የተጀመረው የመስኖ ፕሮጀክት ዛሬ ተመርቋል፡፡

ምንጭ:አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የፊታችን እሁድ ሊካሄድ የነበረው ፍቅር ያሸንፋል የኢትዮጲያ ሩጫ እና ፌስቲቫል ተራዘመ፡፡

ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ በሚል መሪ ሀሳብ የፊታች እሁድ የካቲት 15 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት ፍቅር ያሸንፋል የኢትዮጲያ ሩጫ እና ፌስቲቫል መራዘሙን ሰምተናል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና የመንግስት ሀላፊዎች ያስጀምሩታል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ፌስቲቫል እና ሩጫው ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈበት ምክንያት የካቲት 14 ምሽት ላይ ከሚካሄደው #የድምፃዊ_ቴድሮስ_ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ጋር የመርሀግብር መቀራረብ በመከሰቱ መሆኑን አዘጋጆቹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ውድድሩ መራዘሙን እንጂ ትክክለኛ የሚካሄድበትን የውድድር ቀን ገና አልወሰንም ምክንያቱም የአትሌቲክስ ፌዴሪሽን ፕሮግራሞችን ማጣራት ስለሚኖርብንም ብለዋል አዘጋጆቹ፡፡

ከከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ከፀጥታ ሀይሎች ጋርም ተነጋግረነን የፕሮግራም ሂደቱን ማመቻት ስለሚያፈልግ ቲሸርቶች የገዙ ተሳታፊዎች ትክክለኛውን ቀን ይፋ እስከምናደርግ በትዕግስት ጠብቁን ብለዋል፡፡በተቀያሪው የጊዜ ሰሌዳ አይመቸንም የምትሉ ታሳታፉዎች ካላችሁ ቲሸርቶቹን በመመለስ ገንዘባቹን ማግኘት ትችላላቹ ተብላቹሀል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የዱባይ ዐለም ዐቀፍ ወደቦች ኩባንያ የኤርትራ ወደቦችን ለማስፋፋት እንደተስማማ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ኩባንያው ለወደቦቹ አዳዲስ የሎጅስቲክ መሳሪያዎችን ይገጥማል፤ የወደቦቹን አገልግሎት አቅም ያሳድጋል፡፡ ኤርትራ ስለ ስምምነቱ ያለችው ነገር የለም፡፡ በሌላ ዜና፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለ3 ቀናት የሥራ ጉብኝት ዛሬ ሪያድ እንደገቡ ቃል አቀባያቸው የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

Via:- ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ ጋር በሐርጌሳ ጉብኝት ለማድረግ ያቀረቡትን ጥያቄ የሱማሌላንድ ራስ ገዝ ውድቅ እንዳደረገው ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል፡፡ የጋራ ጉብኝቱን ሃሳብ ለሐርጌሳ ያቀረቡት ዐቢይ ናቸው፡፡

Via:- Horn Diplomat / Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
ለመንግስት ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

ከመጭው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ለሚገኙ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጥ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የሲቪል ሰርቪስ ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ፕሮጀክት መጀመርን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ ፈይሳ እንደገለጹት÷ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናው የሚሰጠው ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የተቃኘ የመንግስት ሰራተኛ እንዲኖርና የወቅቱን የህዝብ ጥያቄ የሚመልስ ኃይል ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ ነው።

https://telegra.ph/yenetube-02-17