YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#NewsAlert

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ምሽት ተፈጥሮ በነበረ ግጭት የሁለት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡

ትናንት ከምሽቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ገደማ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉና ስምንት ተማሪዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ተገለጸ፡፡የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልደትንኤ መኮንን ለአብመድ በስልክ እንደገለጹት ምሽት ተማሪዎች ኳስ በቴሌቪዝን በጋራ ሲከታተሉ አምሽተው ሲመለሱ በተፈጠረ ግጭት ነው የተማሪዎች ሕይወት ያለፈውና የአካል ጉዳት ያጋጠመው፡፡

ጉዳት ካጋጠማቸው ስምንት ተማሪዎች ሦስቱ ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ስለነበር መጠነኛ ሕክምና አግኝተው ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸውንም አቶ ወልደትንሳኤ አስታውቀዋል፡፡የተወሰኑ ተማሪዎችንና የተማሪ ተወካዮችን በችግሩ ዙሪያ ማወያዬታቸውን ያመለከቱት አቶ ወልደትንሳኤ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለመያዝና ለሕግ ለማቅረብ እየተሠራ እንደሆነ አስውቀዋል፡፡ዩኒቨርሲቲውና የአካባቢው አስተዳደር የተማሪዎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እየሠሩ እንደሚገኙ ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው ‹‹ከዚህ በፊት የግጭት ምንጭ የሚሆኑ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እንዲፈቱ በትኩረት ሠርተናል፤ የውኃ፣ መብራትና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲቀረፉም እየተደረገ ነው፤ ብዙ ውይይቶችም ተደርገዋል፡፡ የአሁኑ ግጭት መንስኤ ምን እንደሆነ ግን ገና እየተጣራ ነው›› ብለዋል፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

ሰሞኑን በወልዲያ ዩኒቨርስቲ ግጭት ከተከሰተ እና ሁለት ተማሪዎች ከሞቱ በኋላ ትናንት ሌሊት ደግሞ በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ መገደሉን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል። በሌሎች ከፍተኛ ተቋማትም ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ይታያሉ። ተማሪዎችም ከግቢ መውጣታቸው እና በየቤተ-ክርስትያናት ተጠልለው እንደሚገኙ ተሰምቷል። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ዛሬ ለዶይቸ ቬለ «DW» እንደተናገሩት ተማሪዎን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa