YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
#ለሰባ_አመታት_ተደብቆ_ሳይታተም_የቆየ_መፅሐፍ
#የስኬት_ፍልስፍና

ሰይጣን እንዴት ከስኬታማ ህይወት ወደኋላ እንደሚያስቀረን የሚያሳይ አነጋጋሪ መፅሐፍ!!

ይህ አነጋጋሪ መፅሐፍ ከተዘጋጀ በኋላ የህዝብ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል ተብሎ ለ 70 ዓመታት ሳይታተም ተደብቆ ኖሯል፡፡ የጨለማው አለም ገዢ ሰይጣን የተናዘዘው ኑዛዜ ከ70 ዓመት በኋላ በዚህ መጽሐፍ ሲወጣ ግን በመላው አለም መነጋገሪያ ሆነ!!

መፅሐፉ ሰይጣን ስኬታማና ትርጉም ያለው ህይወት እንዳንመራ እንዴት አዕምሯችንን እንደሚቆጣጠረውና አስተሳሰባችንን እንደሚያበላሸው በማሳየት በንቃት እንድናሸንፈው ይረዳናል!!!

***

“ናፖሊዮን ሂል ህይወቱ ካለፈ ከብዙ አስርት አመት በኋላ እንኳን እስከዛሬም ጥላው የከበደ አሜሪካ አሉኝ ከምትላቸው አሳቢዎች አንዱ ነው፡፡ ለዘመኑ አንባቢ እንዲመጥን ተደርጎ በሻሮን ሌስተር የቀረበው ይህ ድንቅ መጽሐፍ ዲያብሎስ እንዴት አንድን ሰው ከስኬት ጐዳና እንደሚያስወጣው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል!!”
ስቲቨ ፌርብስ
የፎርብስ መጽሄት ዋና አዘጋጅ

“ይህ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ትክክለኛ ጊዜው ደርሶ ታተመ ማለት ነው፡፡ እንዴት ድንቅ ነው!”
ሐርቬይ ማኬይ
የከፍተኛ ሽያጭ መፅሐፍት ደራሲ

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል!
Forwarded from YeneTube
#የመጨረሻ_የሆነው_ባይብል_ኮድ_3_በገበያ_ላይ_ዋለ!

#በአንድ_ምሽት_ሽያጭ_ብቻ_ሪከርድ_የያዘ_መጽሐፍ!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ፡-

*ስለ አርማጌዶን መቅረብና ዓለምን ከጥፋት የማዳን ቁልፍ በኮድ ስለመቀመጡ…

* አሜሪካኖች የሚኮሩበትና አለም የሚያደንቀው ዝነኛው የስለላ ድርጅት ሲ.አይ.ኤ በቸልተኝነት በርካታ ከባባድ ስህተቶችን እንደሚሰራ…

*በዓለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

*ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ እንዲሁም በኮድ ተፅፎ ስለሚገኘው ሚስጥራዊ ቁልፍና በአለም ላይ ስለተከናወኑና ወደፊት ስለሚከናወኑ ድርጊቶች ሁሉ በስም፣ በቀን፣ በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ ዓመት በፊት…

#በመፅሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_በኮድ_ተቀምጧል!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ ኮዶቹን እየፈታ ያስገርመናል፡፡

‹‹#ይህ_መፅሐፍ_እውነትነቱ_በዘመናዊ_ሳይንስ_የተረጋገጠለት_ተአምር_ነው››

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን መሸጥ ይችላል።

ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia

www.sebsibie.com
📞 0953707070
ዲዲ (DIDI) በቻይና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ሲሆን ኮሮኖ ቫይረስ በተከሰተባቸው ከተሞች በዋናነት ዉሃን ከተማ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠጥ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

እኚህ ሹፌሮች ከተማው ምንም እንኳን አስጊ ሁኔታ ላይ ቢሆን ህዝቡን ለማገልገል ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ወደ ስራ ገብተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የመከላከያ ምኒስትሩ ለማ መገርሳ የተካተቱበት የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አስመራ መድረሱን የኤርትራ ማስታወቂያ ምኒስትር አረጋግጠዋል።

Via:- Eshet bekele
@YeneTube @Fikerassefa
ቻይና ስለሚገኙ ዜጎች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የደረሰኝ መረጃ!

- ኤልያስ መሰረት ታዬ -

"በቤይጂንግ የሚገኘው ኤምባሲ እንዲሁም በቾንግኪንግ የሚገኘው የቆንፅላ ቢሮ ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመሆን ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉት ነው። እስካሁን ባለው መረጃ [በኮሮና] ቫይረሱ የተጠቃ ኢትዮጵያዊ የለም።"

ኤልያስ መሰረት ዛሬ ያናገረው አንድ በዉሀን ከተማ ያለ ጋናዊ ተማሪ ደግሞ "ቻይናዎቹ በ WeChat አማካኝነት መረጃ ስንለዋወጥ ሰዎችን እያስደነገጣችሁ እና ስጋቱን እያጋነናችሁ ስለሆነ እረፉ እያሉ እያስፈራሩን ነው። አሁን በአስቸኳይ ከዚህ ቦታ መውጣት እንፈልጋለን፣ ግን አልቻልንም" ብሏል።

ምንጭ:- Elias Meseret
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የመከላከያ ምኒስትሩ ለማ መገርሳ የተካተቱበት የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አስመራ መድረሱን የኤርትራ ማስታወቂያ ምኒስትር አረጋግጠዋል,።

Via:- Eshete bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Ethiopia's Prime Minister Dr. Abiy Ahmed arrived in Asmara in the late afternoon hours today. The Prime Minister and his delegation, which include Defence Minister Lemma Megersa, were accorded warm welcome by President Isaias Afwerki on arrival at Asmara International Airport.

Via:- Yemane G.Mesekel
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት / ( ፓለቲካ )

ዛሬ ለታፈኑ እህቶቻችን ድምፅ የሆኑ የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች ስታድየም ለ1 ሰአት ያህል በፖሊስ ታግደው ነበር። ፖሊስ 6 ያህሉን መርጦ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዷቸውም ነበር። ነገር ግን ከሰዓታት ቆይታ በኋላ እንደተለቀቁ ክለቡ ገልፆል።

ምንጭ:- ጢሞቴዎስ ባዬ
@Yenetube @Fikerassefa
በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ የልኡካን ቡድን ወደ አሜሪካ ተጓዘ!

በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከግብጽ እና ከሱዳን አቻው ጋር ለመወያየት ዛሬ ጥር 17 ቀን 2012 ዓም ማምሻውን ወደ አሜሪካ ተጉዟል።በልኡካን ቡድን ውስጥ የኢፌዲሪ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሽ በቀለን ጨምሮ ከፍተኛ የውሃ ምህንድስና እና የህግ ባለሙያዎች ተካተዋል። የልኡካን ቡድኑ እኤአ ጃንዋሪ 28 እና 29 ቀን 2020 የአሜሪካ መንግስት የትሬዠሪ መ/ቤት እና የዓለም ባንክ ከፍተኛ ሃላፊዎች በታዘቢነት በሚሳተፉበት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል አና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ ህጋዊ ማዕቀፍ ለማስቀመጥ የሚያስችል ውይይት እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

Via Spokesperson of Foreign Ministry
@YeneTube @FikerAssefa
አንድ ሰው በሞተበትና 7 በቆሰሉበት የሐረር የጥምቀት ግጭት ሳቢያ 87 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ ገለጸ።

በዕለቱ
–11 የሕንጻ መስታዎቶች ተሰባብረዋል
–የኮካ ኮላ ማከፋፈያ፣ 1 ሕንጻ፣ 2 መኪኖች 4 ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንት ከስልጣናቸው ተነሱ!!

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ በፋይል ቁጥር DDU/Board/019/2012 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ መሠረት ረ/ፕ አበያ ደገፋ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ልማት ም/ፕሬዝዳንት ሆነው ለአበረከቱት አስተዋጽኦ በመንግስትና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም አመስግኖ ከጥር 16/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ገልጸዋል፡፡

በእዚሁ መሰረት ከጥር 16/2012 ዓ.ም በፋይል ቁጥር DDU/Board/020/2012 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ ለድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ልማት ም/ፕሬዝዳንት እስኪሾም ድረስ በቦታው አቶ መገርሳ ቃሲም ሁሴን ተወክለው እንዲሰሩ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አሳውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ይህን አውቆ ለስራቸው መሳካት ሁሉም በየስራ መስኩ ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳውቋል፡፡

Via:- ድሬደዋ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @Fikerassefa
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ምክር ቤት ጥር 16 እና 17፣ 2012 ዓ.ም 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ የንቅናቄያችንን አጠቃላይ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ፤ የምርጫ ዝግጅት፤ የታሠሩ የአብን አመራሮችና አባለትን፤ የታገቱ አማራ ተማሪዎችን እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ እና አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ አማራ ጠል የተሳሳተ ትርክት በፈርጣጭ ብሔርተኞች መቀንቀን ከጀመረ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያሳለፈ ቢሆንም ለሦስት አስርት ዓመታት መዋቅርና ሕግ ሆኖ አማራን እንደ ህዝብ ለመጨቆን ሥራ ላይ ውሏል። የአማራ ህዝብ የተገንጣይ ብሔርተኞች የተሳሳተ ትርክት እንዲቆም ብሎም ኢትዮጵያዊያን በሰላምና በአንድነት ተከባብረው እንዲኖሩ ሲታገል ቆይቶ በ2010 ዓ.ም ለውጥ እንዲመጣ ቢያድርግም ለውጡን እንመራለን እና እናሻግራለን የሚሉት ተረኛ ነን ባዮች የቆየውን ትርክት ለማስቀጠል በሚያደርጉት ልፊያ ህዝባችን በተደጋጋሚ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል። 


https://telegra.ph/YeneTube-01-26
ሰበር ዜና

ታዋቂው አሜሪካዊ የLA leakers ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብራይንት በ41 አመቱ በሂሊኮፕተር አደጋ ህይወቱ አለፈ።

ከብራይንት ጋር 4 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ተመልክተናል።

ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን...
@Yenetube @Fikerassefa
የልጁም ህይወት አልፏል በአደጋው...

ከኮቢ ብራይት ጋር የ13 አመቷ ልጁ ህይወቷ ማለፉ ታውቋል ።

ብራይት ልጁ ጂጂ WNBA(የሴቶችን የአሜሪካን ቅርጫት ኳስ ውድድር) እንድትጫወት ፅኑ ፍላጎት ነበሩው ይህ በእንዲህ እንዳለ አደጋው የተከሰው ለትሬኒግ አብረው በመጓዝ ላይ ሳሉ መሆኑ ታውቋል።

Via:-TMZ
@YeneTube @Fikerassefa