Forwarded from YeneTube
ሰርግዎን በቅርቡ ለመሰረግ አስበዋል?
እንግድያውስ የዲኮሩን ስራ በእኛ ላይ ይጣሉት
💥LEAD DECOR
በባህላዊ እና ዘመናዊ መልኩ ዝግጅትዎን እናስውባለን::
➡️ለሠርግ
➡️ለመልስ
➡️ለልደት
➡️ለስብሰባ አዳራሽ
እንዲሁም
ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች
0912672317, 0920315163 ደውለው ያነጋግሩን
ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ⬇️
https://tttttt.me/LeadDecor
እንግድያውስ የዲኮሩን ስራ በእኛ ላይ ይጣሉት
💥LEAD DECOR
በባህላዊ እና ዘመናዊ መልኩ ዝግጅትዎን እናስውባለን::
➡️ለሠርግ
➡️ለመልስ
➡️ለልደት
➡️ለስብሰባ አዳራሽ
እንዲሁም
ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች
0912672317, 0920315163 ደውለው ያነጋግሩን
ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ⬇️
https://tttttt.me/LeadDecor
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደቡብ ክልል ዞኖች ከተውጣጡ የማኅበረሰብ አባላት ጋር እየተመካከሩ ነው!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል ዞኖች ከተውጣጡ የማኅበረሰብ አባላት ጋር ምክክር እያካሄዱ ነው።ሕዝባዊ የምክክር መድረኩ ልማትን ለማፋጠን ይቻል ዘንድ፣ የደቡብ ክልል ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ያሏቸውን ፍላጎቶች በቀጥታ ከየማኅበረሰቡ ተወካዮች ለመስማት ይቻል ዘንድ የተዘጋጀ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa

በካርቱም የተጀመረው የኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን የሶስትዮሽ ዉይይት ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
በሱዳን ካርቱም እየመከሩ የሚገኙት የሶስቱም ሀገራት ተወካዮች፣ተከታታይ ዉይይቶችን ያደረጉበት የህዳሴዉ ግድብ ጉዳይ ላይ ተጨባጭ መፍትሄ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ግብጽ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለግብርና ምርቷ በአጠቃላይ ለኢኮኖሚዋ ዋና መሰረት የሆነዉንና ለዘመናት ስትጠቀምበት የነበረዉ የዉሃ መጠንን ይቀንስብኛል በሚል ከፍተኛ ስጋት አላት፡፡ኢትዮጵያ በአንጻሩ ይህ እንደማይሆን በመገለጽ በአህጉሪቱ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅራቢ ለመሆን ታሳቢ አድርጋ እየሰራች ትገኛለች፡፡
በዚህ መካከል ሆነዉ ሀገራቱ ተደጋጋሚ ዉይይቶችን ቢያደርጉም እዚህ ግባ የሚባል ዉጤትን ማምጣት ሳይችሉ ቆይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚንስትር አብይና ፕሬዝዳንት አልሲሲም በተገናኙባቸዉ አጋጣሚዎች ሁሉ በጉዳዩ ላይ ተነጋግረዋል፤ነገር ግን ችግሩን እንፈታዋለን ከማለት ዉጭ ተጨባጭ የሆነ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ራማምፖሳ እንዲያሸማግሏቸው ጠይቀዋል። በሀገራቱ መካከል ለተፈጠረዉ አለመግባባት የግድቡ ዉሃ ሙሌት ጊዜ ገደብ አንዱ መሆኑ ይገለጻል፡፡
ግብጽ የግድቡ ሙሌት ከ12 እስከ 21 ዓመት ባለዉ ጊዜ እንዲካሄድ ስትገልጽ ኢትዮጵያ በአንጻሩ በ7 ዓመታት ዉስጥ ለመሙላት እቅድ እንዳላት በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡ይህ ሁሉ ጉዳይ በእንጥልጥል ባለበት ወቅት ነዉ ሀገራቱ በሱዳን ካርቱም እየመከሩ የሚገኙት፡፡ሶስቱ ሀገራት በካርቱም እያደረጉት ያለዉን ዉይይት ካጠናቀቁ በኋላ የመጨረሻ ስምምነታቸዉን በቀጣዩ ሳምንት በዋሽንግተን የአሜሪካ እና የዓለም ባንክ ተወካዮች በተገኙበት ይቋጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Via Ethio FM

በዩኒቨርሲቲዎች በግማሽ መንፈቅ ብቻ የ 12 ተማሪዎች ሕይወት አለፈ!
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ22 ዩኒቨርሲቲዎች ባካሄደው ምርመራና ቅኝት፣ በግማሽ ዓመት ውስጥ ብቻ የ 12 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን ይፋ አደረገ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከአማራና ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የተወጣጣ ቡድን በማሳተፍ ባካሄደው ቅኝት መቱ፣ ወለጋ፣ ደምቢዶሎ እና ድሬድዋ ለመማር ማስተማር ምቹ ያልሆኑ እና ሰላም የሌላቸው በማለት ለይቷል። በቀይ ምድብ ውስጥ ከገቡት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሆነው ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ካሉት 650 የወንዶች ዶርም፣ 600 ገደማ የሚሆነው በሮቹ በግጭት ወቅት የተሰባበሩ በመሆናቸው ለተማሪዎች አስጊ እንደሆነም ተገልጿል።
Via Addis Maleda

ሰሎሜ ሾው ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ያለውን ውል አቋረጠ!
በፋና ቴሌቪዥን ለአንድ ዓመት ተኩል በሳምንት አንድ ጊዜ እየተዘጋጀ ሲተላለፍ የነበረው ሰሎሜ ሾው ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ያለውን ውል በይፋ እንዳቋረጠ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአዲስ ማለዳ አረጋገጠ።ሰሎሜ ሾው በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነልቦናዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የተለያዩ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ትንታኔ እንዲሰጡ እና በጉዳዮች ላይ እይታቸውን በማጋራት የሚቀርብ ፕሮግራም ነበር። ከአንድ ዓመት በላይም በፋና ቴሌቪዥን ዘወትር ረቡዕ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ሲተላለፍ ሲታይ ቆይቷል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ምደባ ከብሄርና ከማግለል ጋር አይገናኝም ተብሏል፡፡
"ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ በሚኒስትር ደረጃ ሽግሽግና አዳዲስ ሹመቶችን የመስጠት ስራ ተካሂደዋል፡፡ይህም የተለመደና ለስራ ቅልጥፍና የተሸለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ ሲባል በየጊዜው የሚከናወን ስራ ነው፡፡የአሁኑም እንደተለመደው መንግስት የስራ አፈጻጸምን፤ ብቃትንና ሲታዩ የነበሩ ጉድለቶችን ማረም እንዲሁም የስራ አፈጻጸም ጉድለት ያለባቸውን በሌላ መተካትን መሰረት ያደረገ ሽግሽግ አድርገዋል፤ አዳዲስ ሹመቶችንም ሰጥቷል፡፡በመሆኑም ከዚህ ጋር ተያየዞ አንድን ብሄር ለማግለልና ከስራ ለማፈናቀል የተደረገ አድርጎ የሚያቀርቡ አካላት አለማቸው ለነገሮች የተሳሳተ ትሩጋሜ በመስጠት ህዝብን ማደናገር መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን፡፡"
-EPRDF Official

YeneTube
ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ምደባ ከብሄርና ከማግለል ጋር አይገናኝም ተብሏል፡፡ "ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ በሚኒስትር ደረጃ ሽግሽግና አዳዲስ ሹመቶችን የመስጠት ስራ ተካሂደዋል፡፡ይህም የተለመደና ለስራ ቅልጥፍና የተሸለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ ሲባል በየጊዜው የሚከናወን ስራ ነው፡፡የአሁኑም እንደተለመደው መንግስት የስራ አፈጻጸምን፤ ብቃትንና ሲታዩ የነበሩ ጉድለቶችን…
ይህ ማብራሪያ ትናንት አመሻሽ ላይ ህወሓት ባለስልጣናቱና አባላቱ ከፌድራል መንግሥት ሹመታቸው መሻራቸውን በመቃወም ላወጣው መግለጫ የተሰጠ ይመስላል።
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ትናንት ባወጣው መግለጫ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት በፌዴራል መንግሥት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነበራቸው ሥልጣን እየተነሱ ነው ብሏል።«ይህ ተግባር በፍፁም ተቀባይነት የለውም» ያለው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ «ይህ ሆነ ተብሎ እየተፈፀመ ያለው እና ከዚህ ቀደም የተፈፀመ መረን የለቀቀ ተግባር ሊታረም ይገባል» ብሏል። «ካልሆነ ግን ይህንን ተከትሎ ለሚፈጠር ሁኔታ ሀላፊነት የሚወስደው ይህ ህገ-ወጥ ተግባር እየፈፀመ ያለው አካል መሆኑን ግልፅ ሊሆን ይገባል» ሲል አስጠንቅቋል። ህወአት ይህንን መግለጫ ያወጣው የንግድና የኢንዱስትሪ ሚንስትር የነበሩት ፈትለወርቅ ገብረእግዚዓብሔር ከሥልጣናቸው መሻራቸው ትናንት ከተሰማ በኋላ ነው።
-DW

የገቢዎች ሚኒስቴር በተያዘው የበጀት ዓመት አጋማሽ 125.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 127.5 ቢሊዮን ብር፣ ማለትም የዕቅዱን 101% መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አበቤ ዛሬ በአዳማ ከተማ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልፃዋል፡፡እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ የእቅድ አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ28.9 ቢሊዮን ብር (29%) ዕድገት አለው፡፡
ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ከነገ ጥር 15 እስከ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የፕሬስና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስዓለም እንቻለው እንደገለጹት ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያካሂዳል ብለዋል፡፡በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ ከነገ ጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ፣የአዲስ አበባ ከተማ ዉሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ፣ፍርድ ቤቶች ፣የአዲስ አበባ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ እንደሚያቀርቡ አቶ አዲስዓለም ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ምክር ቤቱ የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ፣የአዲስ አበባ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶች ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ: የከተማ መስተዳድሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

#የመጨረሻ_የሆነው_ባይብል_ኮድ_3_በገበያ_ላይ_ዋለ!
#በአንድ_ምሽት_ሽያጭ_ብቻ_ሪከርድ_የያዘ_መጽሐፍ!!
ቁጥር 3 ባይብል ኮድ፡-
*ስለ አርማጌዶን መቅረብና ዓለምን ከጥፋት የማዳን ቁልፍ በኮድ ስለመቀመጡ…
* አሜሪካኖች የሚኮሩበትና አለም የሚያደንቀው ዝነኛው የስለላ ድርጅት ሲ.አይ.ኤ በቸልተኝነት በርካታ ከባባድ ስህተቶችን እንደሚሰራ…
*በዓለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…
*ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ እንዲሁም በኮድ ተፅፎ ስለሚገኘው ሚስጥራዊ ቁልፍና በአለም ላይ ስለተከናወኑና ወደፊት ስለሚከናወኑ ድርጊቶች ሁሉ በስም፣ በቀን፣ በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ ዓመት በፊት…
#በመፅሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_በኮድ_ተቀምጧል!!
ቁጥር 3 ባይብል ኮድ ኮዶቹን እየፈታ ያስገርመናል፡፡
‹‹#ይህ_መፅሐፍ_እውነትነቱ_በዘመናዊ_ሳይንስ_የተረጋገጠለት_ተአምር_ነው››
በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል

Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot
📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞
@CloudTrading @CloudTrading
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot
📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞
@CloudTrading @CloudTrading
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ በእንግሊዝ ጥገኝነት ጠይቋል፡፡ ቢላል ከለንደን የጠፋው ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሰኞ ዕለት ለሥራ በተጓዘበት ወቅት ነው፡፡
ጋዜጠኛው ለቢቢሲ አማርኛ በሰጠው ቃል፣ የኢዲቶሪያል ነጻነት የለም፤ በብሄር እና ሐይማኖት ጉዳዮች ጫናዎች ይደረጋሉ ብሏል፡፡ ኢቢሲ ግን ውንጀላውን አስተባብሏል፡፡
Via:- Wazema
@Yenetube @Fikerassefa

በቴሌኮም ዘርፉ የግል ኩባንያዎችን ለማሳተፍ የተቀመጠው ጊዜ ገደብ እንደሚራዘም ካፒታል አስነብቧል፡፡ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ የውጭ ኩባንያዎች ጊዜ እንዳጠራቸው ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ እናም ኢትዮጵያ ኮምኒኬሽን ባለስልጣን አዲስ የጊዜ ሰሌዳ ያወጣል፡፡ መንግሥት እስከ ሚያዚያ የቴሌኮም ፍቃድ የሚሰጣቸውን 2 የግል ኩባንዎች ለመለየት አቅዶ ነበር፡፡
Via:- Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የመከላከል እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት መጀመሩን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራውን አውከዋል ባላቸው 21 ተማሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራውን በማወክ በተለዩና ተጨባጭ ማስረጃ በተገኘባቸው 21 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው አንዳንድ የትምህርት ክፍሎች ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ሙሉ በሙሉ መጀመሩም ተገልጿል።
@Yenetube @Fikerassefa
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራውን በማወክ በተለዩና ተጨባጭ ማስረጃ በተገኘባቸው 21 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው አንዳንድ የትምህርት ክፍሎች ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ሙሉ በሙሉ መጀመሩም ተገልጿል።
@Yenetube @Fikerassefa
ባለ ሶስት ወለል ጅምር ህንጻቸውን ለሜቄዶንያ የሰጡት ግለሰብ!
ወ/ሮ ዝናሽ መለሰ የተባሉ ግለሰብ ደብረማርቆስ ከተማ የሚገኝ ባለ ሶስት ወለል ጅምር ህንጻቸውን ለሜቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል ሰጥተዋል።
ግለሰቧ ከ400 ካሬ ሜትር በላይ ግቢ ያለውን ባለሶስት ወለል ጅምር ህንጻ (ይህም በአጠቃላይ ከ4 ሚልዮን ብር በላይ ዋጋ የሚገመተውን ህንጻ) ለሜቄዶንያ ለመስጠት ያበቃቸው ድርጅቱ መውደቂያ ያጡ አረጋውያንን አሰባስቦ እንክብካቤ ሲያደርግ ከተመለከቱ በሁዋላ “እኔስ ምን ላድረግ የሚል ሃሳብ ስለመጣብኝ ነው” ብለዋል።
Via ኢፕድ / Elias Meseret
@Yenetube @FikerAssefa

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 78ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረው በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ህጋዊ ሰውነት እንዲሰጠው በሙሉ ድምጽ በመወሰን ረቂቅ አዋጁ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ስ
ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
የጎንደር የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ የሞከሩት በህወሓት የተላኩ ግለሰቦች ናቸው፤ ሲሉ አንድ ከፍተኛ የአማራ ክልል የፀጥታ ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው ብርሌ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳብራሩት ሰለ ተጠርጣሪዎቹ ማንነት የተሟላ መረጃ አለ በቅርቡም ይፋ ይደረጋል፡፡ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኤጀንሲ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ጥቃት ሊፈፀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የላካቸው አካል ማንነትን ይፋ እንደሚደረግ ጠቁሞ ነበር።
የድምፅ ዘገባውን ያዳምጡ!
Via VOA