የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው የ5ኛ 5 ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ 2 ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል፡፡
99 መቀመጫዎች ያሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በ10ኛ መደበኛ ጉባዔው በክልሉ ያልተማከለ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ማሻሻያንና የየእርከኑ የምክር ቤት አባላት ቁጥር መወሰኛን በተመለከተ የወጡትን ረቂቅ አዋጆች ምርምሮ አፅድቋል፡፡በክልሉ ያልተማከለ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የተመለከቱት በመንጌ ወረዳ ስር የነበረው ኡንዱሉ በአዲስ የወረዳ አስተዳደር እንዲዋቀር እንዲሁም 7 አዳዲስ ቀበሌዎች በተለያዩ ወረዳዎች እንዲደራጁ በምክር ቤቱ ይሁንታ አግኝተዋል፡፡
በአንዳንድ የወረዳና የቀበሌ ስያሜዎችም ላይ የስም ማስተካካያ እንዲደረግባቸው በምክር ቤቱ የተመከረ ሲሆን ክልሉም በ21 ወረዳዎችና በ5 መቶ 18 ቀበሌዎች ተዋቅሯል፡፡በክልሉም አዳዲስ ተጨማሪ ወረዳዎች ባለመዋቀራቸው ምክንያት ህብረተሰቡን በሚፈለገው ልክ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ማድረግ እንዳልተቻለ የአሶሳ ወረዳን በማሳያነት የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል፡፡ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ በአንድ ጊዜ ተጨማሪ የወረዳ መዋቅር ጥያቄን ማስተናገድ የክልሉን አቅም የሚፈታተን ነው ብለው በቀጣይ ግን የክልሉ መንግስት ምላሽ ለመስጠት ይሰራል ብለዋል፡፡ምክር ቤቱ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትንና የ2012 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት አዋጅን መርምሮ በማፅደቅና የአንድ የምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት ይመልሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Via BGRS Mass Media
@YeneTube @FikerAssefa

ወጋገን ባክን የዝርፍያ ሙከራ ተፈጸመበት!
ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ የሚገኘው ወጋገን ባንክ የዝርፊያ ሙከራ ተፈፅሞበት ስራ አቁሟል፡፡አሁን ፌደራል ፖሊስ በቦታው ተገኝቶ ምርመራ ላይ ይገኛል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ የሚገኘው ወጋገን ባንክ የዝርፊያ ሙከራ ተፈፅሞበት ስራ አቁሟል፡፡አሁን ፌደራል ፖሊስ በቦታው ተገኝቶ ምርመራ ላይ ይገኛል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ድሬደዋ ፓሊስ መግለጫ❗️
ከድ/ዳ/አስ/ፖ/ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ
የድሬደዋ አስ/ፖሊስ ኮሚሽን በቀጣይ ጊዜያት በዝርዝር መግለጫ የሚሰጥ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን ላይ ጠቅለል ባለ መልኩ የጥምቀት በአልን በተመለከተ የሚከተለዉን መግለጫ ሰቷል።
በድሬደዋ ኦሮቶዶክስ እምነቱ ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት በሚከበረዉ የጥምቀት በአል ሁሉም ታቦታት ወደየ ደብራቸዉ በዚሂ መግለጫ ከታች ከተገለፀዉ ችግር ዉጪ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ በእምነቱ ስርአት መሰረት በታላቅ ድምቀት በሰላም የተመለሱና የገቡ ሲሆን ለዚህም የበአሉ አክባሪ የነበረዉ ህዝበ ምእመኑና በአስተዳደሩ የሚገኙ የሌሎች እምነት ተከታይ ነዋሪዎች ያደረጉት እገዛ ትብብርና አንድነት እጅጉን ደስ የሚያሰኝና የሚያስመሰግንም ነበር ።
ይህ ይሁን እንጂ በሌላ መልኩ ግን የአቡነ ጎርጎሪዮስ ታቦት በሚገባበት ወቅትና በሌሎች በአሉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ ጉዳቶች ደርሰዋል።
በዚህም የግጭቱን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን በአጠቃላይ የሚከተሉት ጉዳቶች ደርሰዋል።
የደረሱ ጉዳቶች
📌 1 ሰው በድንጋይ ተመትቶ ሞቷል
📌 7 ሰው በጥይት ተመቷል
📌 2 መኪና በእሳት ተቃጥሏል
📌 2መኪና ተሰባብሯል
📌1 የከብቶች መኖ መጋዘን በእሳት ተቃጥሏል
📌1 መኖሪያ ቤት በእሳት ተቃጥሏል
📌14 የፖሊስ አባላት ላይ ድብደባ ተፈጽሟል
📌3 መደብር ተዘርፏል ቁጥራቸው ያልተለየ መኖሪያ ቤቶች ተዘርፈዋል ::
በመሆኑም መላዉ ህብረተሰብ የእርስ በእርስ ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ የነዋሪዉን የቀደመ አብሮ ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ባህል በማወክ የከተማዉን ሰላም ከሚያደፈርሱና ጉዳቶችን ከሚጋብዙ ሀይሎችና ተግባር እራሱን በማራቅ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን እያደረገ ያለዉን ተኪ የለሽ እገዛ፣ትብብርና አንድነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጨምሮ ጥሪዉን ያቀርባል።
ምንጭ:- የድ/ዳ/አስ/ፖሊስ ኮሚሽን
@YeneTube @Fikerassefa

ፍርድ ቤቱ እነክርስቲያን ታደለ ተጠርጥረው የተከሰሱበትን ጉዳይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ችሎት የሚያየው ለአንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን ገለፃ።
Via:- The Federal Supreme Court
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- The Federal Supreme Court
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮ ቴሌኮም በምዕራብ ወለጋ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች የተቋረጡት በሰላም እና ደኅንነት ሳቢያ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ስለ አገልግሎቱ መቋረጥ የሚመለከተው አካል መግለጫ እንደሚሰጥበት ኩባንያው መግለጹን ከአዲስ ስታንዳርድ ፌስቡክ ገጽ ተመልክተናል፡፡
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል እና የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ አሶሳ ውስጥ ታሰሩ። የቤኒሻንል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ አቶ መሀመድ እስማኤል ሁለቱ የፖለቲካ የድርጀት መሪዎች በፖሊስ የታሰሩት ትናንት ሰኞ መኾኑን ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል። ሁለቱ ደርጅቶች ባለፈው ሳምንት የጋራ ጉባኤ አዘጋጅተው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ግንባር የሚል ጥምረት መመስረታቸውንም አቶ መሐመድ ገልጸዋል። ከጋራ ጉባኤው በፊት ግን ሁለቱ ፓርቲዎች ላይ ቀደም ሲል ተደጋጋሚ ዛቻዎች ይደርሱባቸው እንደነበርም አክለው ተናግረዋል። የክልሉ ባለሥልጣናት ፖለቲከኞቹ የታሰሩት በወንጀል ተጠርጥረው ነው ብለዋል።
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ሕንጣሎ ወረዳ ወደሒዋነ መቀላቀል የለበትም ‹‹ወረዳችን ይመለስልን›› በማለት መንገድ ዘግተው የሽፍታ በሚመስል መንገድ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ሲሉ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ፡፡
አቶ ጌታቸው ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ፤ በአካባቢው ለተነሳው ጥያቄ መልስ የሚሰጠው ወረዳው መሆኑን አመልክተዋል፡፡አንድ ቀበሌ ውስጥ ያሉ ጥቂት ሰዎች ይህንን ጉዳይ ለእኛ ሲባል መመለስ አለበት ማለት አይችሉም ጥያቄው በሕዝቡ ውሳኔ ይፈታል፤ ለዚህም ሲባል የሕዝብ ተወካዮች ወደቦታው ተልከዋል ሲሉ አመልክተዋል፡፡
ተጨማሪ👇👇👇👇
https://telegra.ph/Report-01-21

Forwarded from YeneTube
#የመጨረሻ_የሆነው_ባይብል_ኮድ_3_በገበያ_ላይ_ዋለ!
#በአንድ_ምሽት_ሽያጭ_ብቻ_ሪከርድ_የያዘ_መጽሐፍ!!
ቁጥር 3 ባይብል ኮድ፡-
*ስለ አርማጌዶን መቅረብና ዓለምን ከጥፋት የማዳን ቁልፍ በኮድ ስለመቀመጡ…
* አሜሪካኖች የሚኮሩበትና አለም የሚያደንቀው ዝነኛው የስለላ ድርጅት ሲ.አይ.ኤ በቸልተኝነት በርካታ ከባባድ ስህተቶችን እንደሚሰራ…
*በዓለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…
*ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ እንዲሁም በኮድ ተፅፎ ስለሚገኘው ሚስጥራዊ ቁልፍና በአለም ላይ ስለተከናወኑና ወደፊት ስለሚከናወኑ ድርጊቶች ሁሉ በስም፣ በቀን፣ በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ ዓመት በፊት…
#በመፅሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_በኮድ_ተቀምጧል!!
ቁጥር 3 ባይብል ኮድ ኮዶቹን እየፈታ ያስገርመናል፡፡
‹‹#ይህ_መፅሐፍ_እውነትነቱ_በዘመናዊ_ሳይንስ_የተረጋገጠለት_ተአምር_ነው››
በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል

ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
0953707070
በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
0953707070
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English
📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ
አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን
አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022
💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥
ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል
T.me/SCHOOLOFAMERICAN

Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot
📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞
@CloudTrading @CloudTrading
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot
📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞
@CloudTrading @CloudTrading
YeneTube
ወጋገን ባክን የዝርፍያ ሙከራ ተፈጸመበት! ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ የሚገኘው ወጋገን ባንክ የዝርፊያ ሙከራ ተፈፅሞበት ስራ አቁሟል፡፡አሁን ፌደራል ፖሊስ በቦታው ተገኝቶ ምርመራ ላይ ይገኛል፡፡ Via Ethio FM @YeneTube @FikerAssefa
ትናንት አመሻሽ ገርጂ በሚገኘው ወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ የተፈጠረው ምንድን ነው?
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍል ከተማ ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ የሚገኘው ወጋገን ባንክ በር ላይ ትናንት 11 ሰዓት አካባቢ ሁለት ሰዎች በግል ጉዳዮች ምክንያት ተጣልተው ድብድብ ይጀምራሉ፡፡
የግለሰቦቹ ጸብም እየተካረረ መጥቶ ከተደባዳቢዎቹ አንዱ አስጥሉኝ በሚል ወደ ባንኩ ይገባል።ደብዳቢውም ተደብዳቢውን ተከትሎ ወደ ባንኩ በመግባቱ ምክንያት በባንኩ ውስጥ ይገለገሉ የነበሩ ደንበኞች እና የባንኩ ሰራተኞች በተፈጠረው ነገር ተደናገጡ።
የባንኩ ሰራተኞችም የተፈጠረው ግርግር ወደ ዝርፊያ ያመራል በሚል በሩን ይዘጋሉ።በመጨረሻም የባንኩ ጥበቃዎች እና በአካባቢው ህግ የሚያስከብሩ ፖሊሶች ደርሰው ሁኔታውን ማረጋጋታቸውን እና ባንኩ በአሁን ሰዓት መደበኛ ስራውን እንደቀጠለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተናግረዋል።

ጋዜጠኛው ለንደን እንደ ደረሰ ጠፋ!
ከምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ጋራ ወደ እንግሊዝ የተጎዘው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ ተሰወረ።የUK አፍሪካ የኢንቬስትመንት ስብሰባ ዛሬ ለንደን ላይ ሲከፈት ዘገባ ለመስራት የተላከው ቢላል እንግሊዝ እንደገባ ቢፈልግ አልተገኘም። ቢላል በኢቲቪ ከአስር አመታት በላይ ሰርቶል በአሁኑ ጊዜ የዜና ክፍል ምክትል ሀላፊ ነበር።ብቁ በስነምግባሩ የተመሰከረለት ታታሪ ሰራተኛ መሆኑን የሚያውቁት ይመሰክራሉ።የጋዜጠኛው መሰወር በኢቲቪ አመራር ዘንድ መደናገጥን ፈጥሮል።ከቢላል በፊት ሌሎችም ጋዜጠኞች ከሀገር በመውጣት ጥገኝነት ጠይቀዎል።የታመኑ ውስጥ አዎቂ ምንጮቼ እንደገለፁልኝ ቢላል በእንግሊዝ ጥገኝነት መጠየቁ በተያያዘ ነገ ለሚዲያዎች እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።
Source: Dagmawi Tariku(HuluAddis on Bisrat FM)

ምርጫ ቦርድም ኦፌኮ ጃዋርን በምን ህጋዊ ማስረጃ አባል አድርጎ እንደተቀበለ እንዲያብራራ ጠይቋል
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት በፊት ገልጿል። ይሁንና የዜግነቱ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲን ተቀላቅሎ መታወቂያም ወስዷል።
ጉዳዩን በተመለከት ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ድብዳቤ ፅፎ ማስረጃ የጠየቀ ሲሆን ፓርቲው በበኩሉ ጃዋር ማስረጃ እንዲያቀርብ በደብዳቤ አሳስቧል። የፓርቲው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ይህን መረጃ ለዋዜማ አረጋግጠዋል።
“የኛ አባል ሲሆን ለምን ይህ ጥያቄ እንደተነሳ ባይገባኝም እኛ ደብዳቤ ፅፈንለታል” ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና።
እንዴት ለዜግነቱ ማረጋገጫ ሳያቀርብ በህግ ባልተፈቀደ መልኩ ጃዋር መሀመድ ፓርቲውን እንዲቀላቀልና መታወቂያ እንዲወስድ እንደተፈቀደለት ከዋዜማ ላነሳንላቸው ጥያቄ መረራ ጉዲና ሲመልሱ ” እኛ የምናውቀው ኢትዮጵያዊ መሆኑን ነው፣ የሀገሩን ቋንቋ ይናገራል፣ ፊቱም ኢትዮጵያዊ ይመስላል፤ መንግስትም ይህን ያውቃል” ሲሉ ቀልድ አዘል ምላሽ ስጥተዋል።
በጃዋር ዜግነት ላይ ከመንግስት የሚነሳው ጥያቄ ፖለቲካዊ ፍላጎትንም ያካተተ ሊሆን ይችላል ያሉት መረራ ጉዲና ጃዋር በቅርብ ዜግነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ እንደሚመጣ ተስፋ እንደሚያደርጉና ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድም በጊዜው ምላሽ እንደሚሰጡ ነግረውናል።
ፓርቲያቸው ከጃዋር መሀመድ ጋር የቆየ ግንኙነት እንዳለው ያመለከቱት መረራ ፓርቲውንም የተቀላቀለው ከዚህ ቀደም በነበራቸው ትብብርና መቀራረብ የተነሳ መሆኑን ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው በፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ መብት የለውም። ጃዋር መሀመድ ከሶስት ወራት በፊት በመጪው ምርጫ ለመወዳደር መዘጋጀቱን ግን ደግሞ ለየትኛው የስልጣን ወንበር እንደሚወዳደር እንዳልወሰነ ሲገልፅ ተደምጧል።
ጃዋር መንግስት ባደረገለት ከፍተኛ የአቀባበል ስነስርዓት ከአንድ አመት ተኩል በፊት ወደ ሀገር ቤት መግባቱ ይታወሳል። በወቅቱም በስልጣን ላይ ካለው መንግስት ጋር ተባብሮ ለመስራት እቅድ እንዳለው በማወጅ የድረ ገፅ ዘመቻ ሲያደርግበት የነበረውን ላፕቶፕ ኮምፒውተር የትግሉን መገባደድ ተምሳሌትነት እንዲሆን በማለት በወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለነበሩት ለማ መገርሳ በሚሊኒየም አዳራሽ በህዝብ ፊት ማስረከቡ አይዘነጋም።
Via:- ዋዜማ ራዲዮ

በእስክንድር ነጋ የሚመራው ፓርቲ እውቅና አገኘ!
በቅርቡ የተመሰረተው እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የተሰኘው አዲሱ ፓርቲ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የእውቅና ሰርተፍኬት አግኝቷል።
ምንጭ:- አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
በቅርቡ የተመሰረተው እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የተሰኘው አዲሱ ፓርቲ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የእውቅና ሰርተፍኬት አግኝቷል።
ምንጭ:- አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጥር 06 ጀምሮ አዳዲስ የሚኒስትርነት ሹመት የሰጡ ሲሆን በዚሁ መሠረት ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር፣ ኢ/ር) የትምህርት ሚኒስትር፣ አቶ መላኩ አለበል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር እንዲሁም አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ከጥር 06 ቀን 2012 ጀምሮ መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጥር 06 ጀምሮ አዳዲስ የሚኒስትርነት ሹመት የሰጡ ሲሆን በዚሁ መሠረት ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር፣ ኢ/ር) የትምህርት ሚኒስትር፣ አቶ መላኩ አለበል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር እንዲሁም አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ከጥር 06 ቀን 2012 ጀምሮ መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። Via ETV @YeneTube…
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚዓብሔር ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ካቢኔ መሰናበታቸው ታውቋል። ከአንድ አመት በላይ የኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር የነበሩት ፈትለወርቅ ገብረእግዚዓብሔር ተሽረዉ በአቶ መላኩ አለበል መተካታቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
አብን የዜግነት ፖለቲካ የሚከተሉ ፓርቲዎች ከአማራ ክልል ውጪ ባሉ ክልሎችም በስፋት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቀረበ።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የዜግነት ፖለቲካ የሚከተሉ አብዛኞቹ ፓርቲዎች ከአማራ ክልል ውጪ ተንቀሳቅሰው የሚሰሩ አይደሉም፤ ኢትዮጵያ ደግሞ አማራ ክልል ብቻ አይደለችም ብሏል፡፡የአብን ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት አማራው ኢትዮያዊ ነኝ ስላለ ብቻ ፤ እረኛ እንደሌለው ከብት ተበትኖ ሲፈናቀልና የሀገር ውስጥ ስደተኛ ሆኖ ነው የኖረው ብለዋል፡፡
አሁን አማራን ፤ የሚወዳትን ኢትዮጵያን እንደ ማታለያ በመጠቀም ድምፁን ማግኘት ሳይሆን የሚያስፈልገው ጉዳቱን ተረድቶ ጥቅሙን ማስከበር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ተንቀሳቅሰው ይሄን የተከፋፈለ ህዝብ አንድ የሚያደርግ የፖለቲካ ስራ ሰርተው ወደ አንድ ጠረጴዛ የሚያመጡ የዜግነት ፖለቲከኞች ጋር ችግር የለብንም ብለዋል አቶ ደሳለኝ፡፡
አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የአማራን ጥቅም ተደራድሮ የሚያስከብር አደራጃጀት አማራጭ የለውም፡፡በአማራነት መደራጀት መተኪያ የሌለው መንገድ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ይሄ ደግሞ ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር የኢትዮጵያን መልክ የምናይበትን መነፅር ብሔር ብቻ ስላደረገው የተፈጠረ ፣ ያለ ሀቅ ስለሆነ ልናወግዘው አይገባም ብለዋል፡፡
ምንጭ:Ethio FM

ኢትዮጵያ ስም አውጪላቸው ለተባለችው ኮከብና ፕላኔት፣ “ቡና” እና “አቦል” የሚሉ ስሞች እንደሰጠቻቸው ተነገረ፡፡
ለኢትዮጵያ የተሰጠውን የህዋ አካል ስያሜን በተመለከተ ስሞችን እንዲመርጥ ሀላፊነት የተሰጠው ብሔራዊ የስም አሰያየም ኮሚቴ እንዳስታወቀው ከሆነ “ቡና” ለኮከቡ የተሰጠ ስያሜ ሲሆን፣ “አቦል” ደግሞ ፕላኔቱ የሚጠራበት ሆኗል፡፡ስያሜው የተሰጠው በሳይንሳዊ አጠራራቸው HD 16175 ለተባለችው ኮከብና ኮከቧ ለምትዞራት HD 16175-6 ለተባለች ፕላኔት ነው ተብሏል፡፡ከግንቦት 2011 ጀምሮ በፅሁፍ መልዕክት፣ በማህበራዊ ድረ ገፆችና በደብዳቤ ከ275 ሺ በላይ ስሞች ተሰብስበው እንደነበር ኮሚቴው ተናግሯል፡፡
በባለሞያዎች ከተተቹ በኋላ ሶስት ስሞች ለዓለም አቀፉ አስትሮኖሚካል ህብረት የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው የቀረቡ ሲሆን ህብረቱ አስፈላጊውን ግምገማ በማድረግ “ቡና” እና “አቦል” የሚሉ ስሞችን አፅድቋል ተብሏል፡፡ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ህብረት ለኢትዮጵያ ይህንን ፕላኔትና ኮከብ የመሰየም እድል የሰጣት የአንድ መቶኛ ዓመት ምስረታውን አስመልክቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
Via Sheger FM