YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ60 የዩኒቨርሲቲው መምህራን የረዳት ፕሮፌሰርነትና የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የማዕረግ ዕድገቱን ያገኙት የዩኒቨርሲቲው መምህራን በተለያዩ ካምፓሶችና ትምህርት ክፍሎች የሚያገለግሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መምህራኑ ከወራት በፊት በየኮሌጆቹ (በየፈካልቲው) ታይቶና ተወስኖ የቀረበውን የታሪከ ማህደራቸውን የዩኒቨርሲቲው ሴኔት መርምሮ ለዕድገቱ የተቀመጡ መመሪያዎችንና መስፈርቶችን አሟልተው መገኘታቸውን ካረጋገጠ በኋላ እድገቱን ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

ወደ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያደጉ መምህራን 18 ሲሆኑ የተቀሩት 42ቱ ደግሞ ወደ ረዳት ፕሮፌሰርነት ያደጉ መምህራን መሆናቸውን የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት መረጃ ያመለክታል፡፡

እንዲህ ዓይነቱን የማዕረግ የደረጃ ዕድገት ሲሰጥ የመጀመሪያው እንዳልሆነ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ከዚህም ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በየእርከኑ የማዕረግ እድገቶች ሲሰጥ መቆየቱን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
መኢሶ ( ሀረር ዚሪያ) ትላንት የመሬት መንቀጥቀት ተከስተ ነበር

ሰኞ ጥር 11/2012 ንጋት አካባቢ መሬት ስትነዘር ሰምተናል ያሉ ሰዎች በማሕበራዊ ድር-አምባዎች ያጋጠማቸውን ሲያጋሩ ነበር።

'አፍሪካ ኢንስቲቲዩት' የተባለ አንድ ገፅም ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀት ተከስቶ እንደነበር የሚጠቁም አንድ ድረ-ገፅ አያይዞ ትዊተር ላይ ፅፎ ነበር።

እውን አዲስ አበባም ሆነ በኢትዮጵያ ሌሎች ሥፍራዎች የመሬት መንቀጥቀት ተከስቶ ነበር?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አታላይ አየለ [ፒኤችዲ] የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪ ናቸው።

ተመራማሪው፤ ከፉሪ እንዲሁም በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ ካሉ አምስት ጣብያዎች በተገኘ መረጃ መሠረት በምስራቅ ኢትዮጵያ መኢሶ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አጣርተናል ይላሉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሰማቸው የመኢሶው ንዝረት ነው ሲሉ ያስረዳሉ።

«መኢሶ አካባቢ በሪክተር ስኬል 5 የሚገመት የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጥሯል። ይህ የሆነው ዛሬ [ጥር 11/2012] 12 ሰዓት አካባቢ ነው። አዲስ አበባ ውስጥም ቢሆን ሰዎች ሊሰማቸው ይችላል። በተለይ ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች የበለጠ ሊሰማቸው ይችላል። በሪክተር ስኬል 5 ማለት እንግዲህ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል አይደለም፤ ነገር ግን ሰዎች ሊሰሙት ይችላሉ።»

በተለይ አዋሽና አሰበ-ተፈሪ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጡ ጎልቶ እንደተሰማ፤ አዲስ አበባ ደግሞ ለስምጥ ሸለቆ ቅርብ በመሆኗ መሰል ክስተቶች ይሰሟታል።

ከዚህ በፊት መሰል የመሬት መንቀጥቀጦች በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ተከስተው ንዝረቱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ሲያስደነግጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ይላሉ ባለሙያው።
«2009 አንኮበር አካባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። 4.7 ሪክተር ስኬል አካባቢ ነበር የተመዘገበው ባልሳሳት። ታኅሣሥ ውስጥ ነበር። የዛኔም አዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ንዝረቱ ተሰምቶ ነበር።»

ባለሙያው አዲስ አበባ መቼ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያጋጥማት ይችላል የሚለውን መገመት ከባድ ነው ይላሉ። አሁን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምናልባት መሬት ላይ ያሉ ቤቶችን ያፈርስ ይሆናል እንጂ ብዙ ጉዳት አያደርስም ይላሉ። የደረሰ ጉዳት እንዳለ ገና አለማረጋገጣቸውንም ይናገራሉ።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ያስተናገደችው 1953 ላይ ሲሆን ካራቆሬ ተበሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በሪክተር ስኬል 6.5 ተመዝግቧል። በወቅቱ በደረሰ አደጋ 30 ሰዎች መሞታቸውም ተዘግቦ ነበር።

ምንም እንኳ አንዳንድ አካባቢዎች በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ቢገኙም የመሬት መንቀጥቀጥ ኢትዮጵያን ይህን ያህል የሚያሰጋት አይደለም።

ምንጭ:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
ቢትኮይን ምንድነው ? What is Bitcoin ?

https://www.youtube.com/watch?v=2_Y2sGBh2Kc
39ኛው የአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀመረ

አፍሪካ እድገት ምቹ ሁኔታ መፍጠርን ያለመ 39ኛው የአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮች ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።

ሰላሟን ከማረጋገጥ አኳያም የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው የተባለው።
የተኩስ ድምፅ የማይሰማበት ቀጠና ለመፍጠር የሚደረግ ውይይት እንደሆነም ተጠቁሟል።

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
የቃና ዘገሊላ በዓል በአዲስ አበባ አየተከበረ ይገኛል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች ታቦቱ ካረፈበት ወደ ነበርበት ወደ ቤተክርስቲያን ለመመለስ እየተንቀሳቀሰ ነዉ ።

ምዕመኑም ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ ታቦተ ህጉን እየሸኘ ይገኛል።
@YeneTube @Fikerassefa
Audio
በትናንትናው ዕለት በጥምቀት በዓል ላይ ሁከት ተቀስቅሶባት የዋለችው ሐረር፣ ዛሬ አንፃራዊ ሰላም እንደሚታይባት ነዋሪዎች ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via:- ሸገር FM
@Yenetube @Fikerassefa
ቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ" በሚል ስያሜ በአርባምንጭ፣ አዲስ አበባ እና ጎንደር የሙዚቃ ድግስ ሊያዘጋጅ ነው!

በዳዊት ዋሲሁን ካሳ

አርቲስቱ ይህን የሙዚቃ ድግስ ከኤቨር ላስት ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር እንደሚያዘጋጀው የፕሮሞሽኑ ማናጀር Mafio Mengistu አረጋግጦልኛል።

ቴዲ አፍሮ በቅርቡ ለአምስት ቀናት በአርባምንጭ ቆይታ አድርጎ ነበር። የሚያዘጋጀው የሙዚቃ ድግስም ያለምንም የመግቢያ ክፍያ ሊሰራ እንደሆነ ታውቋል።

ለዚህ የሙዚቃ ድግስ አቡጊዳ ባንድ ከአሜሪካ እንዲሁም የሳውንድና ላይት ሲስትም ባለሞያዎች ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ እንደሚመጡ የታወቀ ሲሆን ይህን ኮንሰርት በቅድሚያ በአርባምንጭና ጎንደር ለማሰናዳት ትልቅ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ምንጭ:- ዳዊት ካሳሁን /Eliasmeseret
@YeneTube @Fikerassefa
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው የ5ኛ 5 ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ 2 ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል፡፡

99 መቀመጫዎች ያሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በ10ኛ መደበኛ ጉባዔው በክልሉ ያልተማከለ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ማሻሻያንና የየእርከኑ የምክር ቤት አባላት ቁጥር መወሰኛን በተመለከተ የወጡትን ረቂቅ አዋጆች ምርምሮ አፅድቋል፡፡በክልሉ ያልተማከለ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የተመለከቱት በመንጌ ወረዳ ስር የነበረው ኡንዱሉ በአዲስ የወረዳ አስተዳደር እንዲዋቀር እንዲሁም 7 አዳዲስ ቀበሌዎች በተለያዩ ወረዳዎች እንዲደራጁ በምክር ቤቱ ይሁንታ አግኝተዋል፡፡

በአንዳንድ የወረዳና የቀበሌ ስያሜዎችም ላይ የስም ማስተካካያ እንዲደረግባቸው በምክር ቤቱ የተመከረ ሲሆን ክልሉም በ21 ወረዳዎችና በ5 መቶ 18 ቀበሌዎች ተዋቅሯል፡፡በክልሉም አዳዲስ ተጨማሪ ወረዳዎች ባለመዋቀራቸው ምክንያት ህብረተሰቡን በሚፈለገው ልክ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ማድረግ እንዳልተቻለ የአሶሳ ወረዳን በማሳያነት የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል፡፡ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ በአንድ ጊዜ ተጨማሪ የወረዳ መዋቅር ጥያቄን ማስተናገድ የክልሉን አቅም የሚፈታተን ነው ብለው በቀጣይ ግን የክልሉ መንግስት ምላሽ ለመስጠት ይሰራል ብለዋል፡፡ምክር ቤቱ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትንና የ2012 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት አዋጅን መርምሮ በማፅደቅና የአንድ የምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት ይመልሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via BGRS Mass Media
@YeneTube @FikerAssefa
ወጋገን ባክን የዝርፍያ ሙከራ ተፈጸመበት!

ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ የሚገኘው ወጋገን ባንክ የዝርፊያ ሙከራ ተፈፅሞበት ስራ አቁሟል፡፡አሁን ፌደራል ፖሊስ በቦታው ተገኝቶ ምርመራ ላይ ይገኛል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ድሬደዋ ፓሊስ መግለጫ❗️

ከድ/ዳ/አስ/ፖ/ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ
የድሬደዋ አስ/ፖሊስ ኮሚሽን በቀጣይ ጊዜያት በዝርዝር መግለጫ የሚሰጥ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን ላይ ጠቅለል ባለ መልኩ የጥምቀት በአልን በተመለከተ የሚከተለዉን መግለጫ ሰቷል።

በድሬደዋ ኦሮቶዶክስ እምነቱ ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት በሚከበረዉ የጥምቀት በአል ሁሉም ታቦታት ወደየ ደብራቸዉ በዚሂ መግለጫ ከታች ከተገለፀዉ ችግር ዉጪ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ በእምነቱ ስርአት መሰረት በታላቅ ድምቀት በሰላም የተመለሱና የገቡ ሲሆን ለዚህም የበአሉ አክባሪ የነበረዉ ህዝበ ምእመኑና በአስተዳደሩ የሚገኙ የሌሎች እምነት ተከታይ ነዋሪዎች ያደረጉት እገዛ ትብብርና አንድነት እጅጉን ደስ የሚያሰኝና የሚያስመሰግንም ነበር ።

ይህ ይሁን እንጂ በሌላ መልኩ ግን የአቡነ ጎርጎሪዮስ ታቦት በሚገባበት ወቅትና በሌሎች በአሉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ ጉዳቶች ደርሰዋል።

በዚህም የግጭቱን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን በአጠቃላይ የሚከተሉት ጉዳቶች ደርሰዋል።
የደረሱ ጉዳቶች
📌 1 ሰው በድንጋይ ተመትቶ ሞቷል
📌 7 ሰው በጥይት ተመቷል
📌 2 መኪና በእሳት ተቃጥሏል
📌 2መኪና ተሰባብሯል
📌1 የከብቶች መኖ መጋዘን በእሳት ተቃጥሏል
📌1 መኖሪያ ቤት በእሳት ተቃጥሏል
📌14 የፖሊስ አባላት ላይ ድብደባ ተፈጽሟል
📌3 መደብር ተዘርፏል ቁጥራቸው ያልተለየ መኖሪያ ቤቶች ተዘርፈዋል ::

በመሆኑም መላዉ ህብረተሰብ የእርስ በእርስ ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ የነዋሪዉን የቀደመ አብሮ ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ባህል በማወክ የከተማዉን ሰላም ከሚያደፈርሱና ጉዳቶችን ከሚጋብዙ ሀይሎችና ተግባር እራሱን በማራቅ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን እያደረገ ያለዉን ተኪ የለሽ እገዛ፣ትብብርና አንድነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጨምሮ ጥሪዉን ያቀርባል።

ምንጭ:- የድ/ዳ/አስ/ፖሊስ ኮሚሽን
@YeneTube @Fikerassefa
ፍርድ ቤቱ እነክርስቲያን ታደለ ተጠርጥረው የተከሰሱበትን ጉዳይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ችሎት የሚያየው ለአንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን ገለፃ።

Via:- The Federal Supreme Court
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮ ቴሌኮም በምዕራብ ወለጋ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች የተቋረጡት በሰላም እና ደኅንነት ሳቢያ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ስለ አገልግሎቱ መቋረጥ የሚመለከተው አካል መግለጫ እንደሚሰጥበት ኩባንያው መግለጹን ከአዲስ ስታንዳርድ ፌስቡክ ገጽ ተመልክተናል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል እና የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ አሶሳ ውስጥ ታሰሩ። የቤኒሻንል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ አቶ መሀመድ እስማኤል ሁለቱ የፖለቲካ የድርጀት መሪዎች በፖሊስ የታሰሩት ትናንት ሰኞ መኾኑን ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል። ሁለቱ ደርጅቶች ባለፈው ሳምንት የጋራ ጉባኤ አዘጋጅተው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ግንባር የሚል ጥምረት መመስረታቸውንም አቶ መሐመድ ገልጸዋል። ከጋራ ጉባኤው በፊት ግን ሁለቱ ፓርቲዎች ላይ ቀደም ሲል ተደጋጋሚ ዛቻዎች ይደርሱባቸው እንደነበርም አክለው ተናግረዋል። የክልሉ ባለሥልጣናት ፖለቲከኞቹ የታሰሩት በወንጀል ተጠርጥረው ነው ብለዋል።  

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ሕንጣሎ ወረዳ ወደሒዋነ መቀላቀል የለበትም ‹‹ወረዳችን ይመለስልን›› በማለት መንገድ ዘግተው የሽፍታ በሚመስል መንገድ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ሲሉ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ፡፡

አቶ ጌታቸው ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ፤ በአካባቢው ለተነሳው ጥያቄ መልስ የሚሰጠው ወረዳው መሆኑን አመልክተዋል፡፡አንድ ቀበሌ ውስጥ ያሉ ጥቂት ሰዎች ይህንን ጉዳይ ለእኛ ሲባል መመለስ አለበት ማለት አይችሉም ጥያቄው በሕዝቡ ውሳኔ ይፈታል፤ ለዚህም ሲባል የሕዝብ ተወካዮች ወደቦታው ተልከዋል ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ተጨማሪ👇👇👇👇
https://telegra.ph/Report-01-21
Forwarded from YeneTube
#የመጨረሻ_የሆነው_ባይብል_ኮድ_3_በገበያ_ላይ_ዋለ!

#በአንድ_ምሽት_ሽያጭ_ብቻ_ሪከርድ_የያዘ_መጽሐፍ!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ፡-

*ስለ አርማጌዶን መቅረብና ዓለምን ከጥፋት የማዳን ቁልፍ በኮድ ስለመቀመጡ…

* አሜሪካኖች የሚኮሩበትና አለም የሚያደንቀው ዝነኛው የስለላ ድርጅት ሲ.አይ.ኤ በቸልተኝነት በርካታ ከባባድ ስህተቶችን እንደሚሰራ…

*በዓለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

*ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ እንዲሁም በኮድ ተፅፎ ስለሚገኘው ሚስጥራዊ ቁልፍና በአለም ላይ ስለተከናወኑና ወደፊት ስለሚከናወኑ ድርጊቶች ሁሉ በስም፣ በቀን፣ በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ ዓመት በፊት…

#በመፅሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_በኮድ_ተቀምጧል!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ ኮዶቹን እየፈታ ያስገርመናል፡፡

‹‹#ይህ_መፅሐፍ_እውነትነቱ_በዘመናዊ_ሳይንስ_የተረጋገጠለት_ተአምር_ነው››

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል
Forwarded from YeneTube
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
YeneTube
ወጋገን ባክን የዝርፍያ ሙከራ ተፈጸመበት! ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ የሚገኘው ወጋገን ባንክ የዝርፊያ ሙከራ ተፈፅሞበት ስራ አቁሟል፡፡አሁን ፌደራል ፖሊስ በቦታው ተገኝቶ ምርመራ ላይ ይገኛል፡፡ Via Ethio FM @YeneTube @FikerAssefa
ትናንት አመሻሽ ገርጂ በሚገኘው ወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ የተፈጠረው ምንድን ነው?

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍል ከተማ ገርጂ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ የሚገኘው ወጋገን ባንክ በር ላይ ትናንት 11 ሰዓት አካባቢ ሁለት ሰዎች በግል ጉዳዮች ምክንያት ተጣልተው ድብድብ ይጀምራሉ፡፡

የግለሰቦቹ ጸብም እየተካረረ መጥቶ ከተደባዳቢዎቹ አንዱ አስጥሉኝ በሚል ወደ ባንኩ ይገባል።ደብዳቢውም ተደብዳቢውን ተከትሎ ወደ ባንኩ በመግባቱ ምክንያት በባንኩ ውስጥ ይገለገሉ የነበሩ ደንበኞች እና የባንኩ ሰራተኞች በተፈጠረው ነገር ተደናገጡ።

የባንኩ ሰራተኞችም የተፈጠረው ግርግር ወደ ዝርፊያ ያመራል በሚል በሩን ይዘጋሉ።በመጨረሻም የባንኩ ጥበቃዎች እና በአካባቢው ህግ የሚያስከብሩ ፖሊሶች ደርሰው ሁኔታውን ማረጋጋታቸውን እና ባንኩ በአሁን ሰዓት መደበኛ ስራውን እንደቀጠለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛው ለንደን እንደ ደረሰ ጠፋ!

ከምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ጋራ ወደ እንግሊዝ የተጎዘው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ ተሰወረ።የUK አፍሪካ የኢንቬስትመንት ስብሰባ ዛሬ ለንደን ላይ ሲከፈት ዘገባ ለመስራት የተላከው ቢላል እንግሊዝ እንደገባ ቢፈልግ አልተገኘም። ቢላል በኢቲቪ ከአስር አመታት በላይ ሰርቶል በአሁኑ ጊዜ የዜና ክፍል ምክትል ሀላፊ ነበር።ብቁ በስነምግባሩ የተመሰከረለት ታታሪ ሰራተኛ መሆኑን የሚያውቁት ይመሰክራሉ።የጋዜጠኛው መሰወር በኢቲቪ አመራር ዘንድ መደናገጥን ፈጥሮል።ከቢላል በፊት ሌሎችም ጋዜጠኞች ከሀገር በመውጣት ጥገኝነት ጠይቀዎል።የታመኑ ውስጥ አዎቂ ምንጮቼ እንደገለፁልኝ ቢላል በእንግሊዝ ጥገኝነት መጠየቁ በተያያዘ ነገ ለሚዲያዎች እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።

Source: Dagmawi Tariku(HuluAddis on Bisrat FM)
@YeneTube @FikerAssefa