YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጎንደር 3 ሰው መሞቱ ተረጋገጠ...

በጎንድር ከተማ ፋሲለደስ መዋኛ ገንዳ ቅጥር ግቢ ለጥምቀት ታዳሚዎች የተሰራ የእንጨት መቀመጫ ተደርምሶ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን የከተማው አስተዳደሩ አረጋገጠ።

በአደጋው ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና 5ቱ በአስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የአስተዳደሩ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከቆሰሉት ውስጥ አንድ የውጭ ዜጋ እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

Via:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@Yenetube @FikerAssefa
በሀረር ከተማ በሚገኘው የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል ሲሉ የካምፓሱ ዲን አቶ ድርብሳ ድንቁ ለOMN ተናግረዋል።

Via:- ELU/ OMN
@YeneTube @Fikerassefa
1
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
በጎንደር በጥምቀት በዓል ላይ በደረሰ የመወጣጫ መደርመስ አደጋ #ከ100_በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት በጥምቀተ ባሕሩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ሲከታተሉ በነበሩ ሰዎች ላይ ለመቀመጫነት የተሠራ ርብራብ እንጨት ተደርምሶ ድንገተኛ አደጋ አድርሷል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ በተጎዱ ሰዎችና በአደጋው መንስኤ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የአደጋው መንስኤ ለመቀመጫነት የተሠራው ርብራብ እንጨት ድንገት መንሸራተቱ እንደሆነ መምሪያው አሳውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋ መኮንን እንዳሉት በተሠራው ርብራብ እንጨት ተቀምጠው የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ለኅልፈት የተዳረጉ እንዳሉም አረጋግጠዋል፡፡ ኃላፊው የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽም ጉዳቱ ለደረሰባቸው ወገኖች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
አደጋው እንደደረሰም አብዛኞቹ ተጎጅዎች ሕክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡

በሕክምና ላይ ካሉት መካከል አምስቱ ከባድ ጉዳት እንዳጋጠማቸውም ተብራርቷል፡፡ ቀላል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎችና ሁለት የፀጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበት በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

መቀመጫው ከ700 እስከ 1000 ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች ያስተናግዳል ተብሎ የተሠራ ቢሆንም ፣ bባሕረ ጥምቀቱ ይካሄድ የነበረውን ሃይማኖታዊ ሥርዓትና የበዓሉን ድባብ ለማየት በጉጉት ይጠባበቁ የነበሩ በርካታ ሰዎች በእንጨቱ ላይ በመውጣታቸው ችግሩ መፈጠሩን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው ከተፈጠረው አደጋ ውጭ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳልነበርና ታቦታቱ በሠላም ወደ አድባራቱ ገብተዋል ፡፡

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
#በሐረር ከጥምቀት አከባበር ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ምንድን ነው?

በሐረር ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ ትናንት እና ዛሬ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር ተሰምቷል። በዚሁ ዙሪያ የሐረሪ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ናስር ይያ ስለተፈጠረው ነገር ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀናቸዋል።

ኃላፊውም ''የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ለማክበርና አካባቢውን ለማስዋብ የተለመደ እንቅስቃሴያቸውን በሚያደርጉበት ወቅት በዓሉን የማይመለከትና ሕግ የማይፈቅደውን ባንዲራ ለመስቀል ሙከራ ያደረጉ በመኖራቸው አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር'' ብለዋል።

''ይህንን ተከትሎም ትናንት የሀይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ወጣቶችና ቄሮዎችን በማስተባበርና የጸጥታ ኃይሎችንም በማቀናጀት ችግር እንዳይፈጠር ማድረግ ችለናል'' ሲሉ አስረድተዋል።


ኃላፊው እንዳሉት፤ አንድ ሁለት ሰዎች ሰንደቅ አላማውን ለመስቀል በሚሞክሩበት ወቅት ሌሎች ደግሞ 'ይህን አትሰቅሉም' በሚል ግርግር ተፈጥሮ ነበር።

''እነዚህ [ግርግሩን የፈጠሩት] ሰዎች እምነትን ከእምነት ማጋጨት፤ ሕዝብን ከሕዝብ ማጋጨት ነው እቅዳቸው። በሁሉም አካባቢዎች ታቦት በሰላም ወጥቶ ይገባል። ነገር ግን መስጂድና ቤተክርስቲያን በቅርበት በሚገኙባቸው አካባቢዎች ችግር ለመፍጠር ተሞክሯል'' ብለዋል።

ዛሬ በሐረር አለመረጋጋት እንደነበርና ተኩስም እንደተሰማ በስፋት እየተነገረ መሆኑን የጠቀስንላቸው ኃላፊው፤ ጠዋት ላይ አንዳንድ ግርግሮች ተፈጥረው የነበረ ቢሆንም ከሰዓት ከተማው መረጋጋቱን መሆኑን ነግረውናል።


''ዛሬ ታቦት በሚገባበት ወቅት አራተኛ በተባለው አካባቢ ተገቢ ያልሆነ ጭፈራና ንብረት ላይ ድንጋይ መወርወር ጀምረው ነበር። አካባቢው ቤተ ክርስቲያንም መስጂድም ያለበት ከመሆኑ አንጻር በሀይማኖት ስም የተደረገው ነገር ተገቢ አይደለም። ነገር ግን ተፈጥሮ የነበረው ነገር በቁጥጥር ስር ውሏል'' ሲሉ አስረድተዋል።
ንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት ውጪ እስካሁን የተጎዳ ሰው አለመኖሩን ኃላፊው ተናግረዋል። አቶ ናስር የጉዳት መጠኑን በትክክል ለመግለጽ ባይችሉም፤ ወደ ስምንት የሚጠጉ ቤቶች ድንጋይ ተወርውሮባቸው መስታወቶች እንደተሰባበሩ ያስረዳሉ።

ዛሬ ጠዋት ታቦት የሚሸኙ ሰዎች መንገድ ተዘግቶባቸዋል ስለመባሉ የተጠየቁት የጸጥታ ቢሮ ኃላፊው፤ '' ማንም መንገድ የተዘጋበት የለም፤ ማንም መንገድ የዘጋም የለም" ብለዋል።
''ታቦት እንዳያልፍ አልተከለከለም፤ መንገዱም ክፍት ነው። ይሄ ተግባር ውዥንብር ለመፍጠርና ሕዝቡን በእምነት ስም ለማነሳሳት የሚደረግ ጥረት ነው'' ሲሉም አብራርተዋል።
ከትናንትናው እና ከዛሬው ክስተት ጋር በተያያዘ እስካሁን ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምዕመናን በዓሉን አክብረው ወደቤታቸው ገብተው፣ ከተማዋም ሰላማዊ እንቅስቃሴዋን እንደቀጠለች አቶ ናስር ነግረውናል።


ምንጭ:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በሀረር ከተማ በሚገኝ ስቱዲዮው ላይ "በተደራጁ" ባላቸው ሀይሎች ጥቃት እንደደረሰበት አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጎንደር የእንጨት ድልድይ ተደርምሶ 10 ሰው መሞቱን የፈረንሳይ ሚዲያ AFP አስነብቧል።

"At least ten people were killed on Monday and scores injured when a seating area collapsed during a major Orthodox Christian celebration in northern Ethiopia, with fears the death toll could rise"

http://u.afp.com/3Z82
@Yenetube @Fikerassefa
1
ከጥምቀት ጋር በተያያዘ በድሬዳዋ በተከሰተ ግጭት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ፎቶ :- ELU
@Yenetube @Fikerassefa
የቀድሞው የኢህዴግ ባለስልጣን አቶ በረከት ስምዖን አርፈውበታል በሚል በተናፈሰ ወሬ፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የደብረማርቆስ ጎዛምን ሆቴል ከአንድ አመት ተኩል በኅላ ዛሬ በሩን ለደንበኞቹ ከፍቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
ጎንደር የእንጨት ድልድይ ተደርምሶ 10 ሰው መሞቱን የፈረንሳይ ሚዲያ AFP አስነብቧል። "At least ten people were killed on Monday and scores injured when a seating area collapsed during a major Orthodox Christian celebration in northern Ethiopia, with fears the death toll could rise" …
#ጎንደር ጊዛዊ መቀመጫ ርብራብ ተደርምሶ ከአስር ሰው ህይወት ማለፉን ከሰዐታት በፊት AFP አስነብቧል

#አሁን_የደረሰን_መረጃ የሟቾች ቁጥር 14 እንደደረሰ በሆስፒታል የሚሰሩ ሰራተኞች(ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ) የተለያዩ ግለሰቦች ነግረውናል።

እንዲሁም የሪፓርተር ጋዜጠኛ ሳሙኤል ጌታቸው የሟቾች ቁጥር 15 መድረሱን በትዊተር ገፁ አስፍሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
#የመጨረሻ_የሆነው_ባይብል_ኮድ_3_በገበያ_ላይ_ዋለ!

#በአንድ_ምሽት_ሽያጭ_ብቻ_ሪከርድ_የያዘ_መጽሐፍ!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ፡-

*ስለ አርማጌዶን መቅረብና ዓለምን ከጥፋት የማዳን ቁልፍ በኮድ ስለመቀመጡ…

* አሜሪካኖች የሚኮሩበትና አለም የሚያደንቀው ዝነኛው የስለላ ድርጅት ሲ.አይ.ኤ በቸልተኝነት በርካታ ከባባድ ስህተቶችን እንደሚሰራ…

*በዓለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

*ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ እንዲሁም በኮድ ተፅፎ ስለሚገኘው ሚስጥራዊ ቁልፍና በአለም ላይ ስለተከናወኑና ወደፊት ስለሚከናወኑ ድርጊቶች ሁሉ በስም፣ በቀን፣ በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ ዓመት በፊት…

#በመፅሐፍ_ቅዱስ_ውስጥ_በኮድ_ተቀምጧል!!

ቁጥር 3 ባይብል ኮድ ኮዶቹን እየፈታ ያስገርመናል፡፡

‹‹#ይህ_መፅሐፍ_እውነትነቱ_በዘመናዊ_ሳይንስ_የተረጋገጠለት_ተአምር_ነው››

በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል
Forwarded from YeneTube
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረመዳን ኡመር በሰጡት መግለጫ ከጥር 10/2012 ጀምሮ አንዳንድ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡ አካላት በዓሉ በሰላም እንዳይከናወን ጎራ ለይተው ግጭት ለማስነሳት ጥረት እንዳደረጉ ገልፀዋል።

በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያም በአራት(4) ሲቪል ዜጎች እና በአስራ አምስት (15) የፀጥታ አካላት ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም በንብረት ላይም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት መድረሱን ለኮሚሽኑ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በሰውና በንብረት ላይ የደረሱ ጉዳቶችን በሚመለከት ፖሊስ አስፈላጊውን የማጣራት ስራ በማከናወን እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን በማጣራት ለህግ እንደሚያቀርቡና ስለጉዳዩም በዝርዝር ለህዝቡ እንደሚያሳውቁ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

Via:- የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን
@Yenetube @Fikerassefa