YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከተራ በዓል በመቐለ ⬆️
ከተራ በዓል በጃል ሜዳ / አዲስ አበባ
ኬንያ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ሲዘጋጁ ነበር ያለቻቸውን አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሏን አስታወቀች። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል አንድ አሜሪካዊ፣ አንድ ሶማሊያዊ እና ኬንያዊ ሾፌራቸው ይገኙበታል።

ሁለት ሶማሊያውያን እንስቶች የሚገኙበት የተጠርጣሪዎች ቡድን በሰሜናዊ ናይሮቢ ጥቃት ለመፈጸም ቅኝት በማድረግ ላይ እንደነበር የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ መጠጥ ቤቶች በሚበዙበት የናይሮቢ አካባቢ ቅኝት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው ገልጿል።

አል-ሸባብ በኬንያ በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ የአገሪቱ የጸጥታ ጥበቃ ተቋማት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።

Via:- DW
@YeneTube @fikerassefa
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
"ከ50 ዓመታት በኋላ ጥምቀትን በጎንደር ማክበር በመቻሌ ደስተኛ ነኝ"--- በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም

የኤርትራ ልዑክ ጥምቀትን በጎንደር እየታደመ ነው። በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የተመራ የኤርትራ ልዑክ ትናንት ጠዋት ነው የጥምቀት በዓልን ለመታደም ጎንደር የገባው።

አምባሳደሩ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ተብሎ ይጠራ በነበረው በዛሬው ፋሲለደስ የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሆነው ይሰሩ እንደነበርም አስታውሰዋል።

በወጣትነት እድሜያቸው ጥምቀትን ከጎንደር ሕዝብ ጋር ያከብሩ እንደነበር አስታውሰው ከበርካታ ዓመታት በኋላ የዘንድሮውን ጥምቀት በመታደማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

Via:- AMMA ( ELias Meseret )
@YeneTube @FikerAssefa
የጥምቀት በዓል በተለያዩ የአለም ሀገራትም ተከብሯል

በተለያዩ የአለም ሀገራት በሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ዓመታዊ በዓሎች አንዱ የጥምቀት በዓል ነው። በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ያሉ የእምነቱ ተከታዮች የጥምቀት በዓልን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ለዘመናት እያከበሩ እዚህ ደርሰዋል። በዓሉ ከሚከበርባቸው ከእነዚህ ሀገራት መከካል 90 ሚሊየን የኦርቶዶክስ ተከታዮችን የያዘችው ሩሲያ ትጠቀሳለች።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerssefa
1
በጎንደር ከተማ በመከበር ላይ በሚገኘው የጥምቀት በዓል መቀመጫ ተሰብሮ መጠነኛ መረጋገጥ መፈጠሩን የክልሉ የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ አስታውቋል።
via:- Elu

@YeneTube @Fikerassefa
Update #ሐረር_አሁን

ህዝበ ክርስቲያኑ የተዘጋውን መንገድ አስከፍቶ የገብርኤል እና ጊዮርጊስ ታቦቱን አጅቦ እየተጓዘ መሆኑን ከጋዜጠኛ ቆንጂት ተሾመ ተመልክተናል።

ከሰዐታት በፊት ታቦቻቱ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ መንገድ እንደተዘጋባቸው መረጃዎች ደርሶን ነበር።

@YeneTube @Fikerassefa
"ሀረር በሚገኘው የኦፌኮ ቢሮአችን ላይ ዛሬ ጥቃት ደርሷል"--- ፕ/ር መራራ ጉዲና ከደቂቃዎች በፊት በስልክ ከነገሩኝ

// ኤልያስ መሰረት //

ፕ/ሩ እንዳሉት " ዛሬ ከሰአት የብሄር እና ሀይማኖት ግጭት እንዲነሳ የሚፈልጉ ሰዎች ሀረር ያለው ቢሮአችን ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ቢሮው፣ መኪኖች እና ሞተር ሳይክሎች ላይ የመሰባበር ጉዳት አጋጥሟል። በደረሰኝ መረጃ የፀጥታ አካላት ጥሪ ሲደረግላቸው ተገቢውን ምላሽ አልሰጡም" ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጎንደር 3 ሰው መሞቱ ተረጋገጠ...

በጎንድር ከተማ ፋሲለደስ መዋኛ ገንዳ ቅጥር ግቢ ለጥምቀት ታዳሚዎች የተሰራ የእንጨት መቀመጫ ተደርምሶ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን የከተማው አስተዳደሩ አረጋገጠ።

በአደጋው ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና 5ቱ በአስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የአስተዳደሩ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከቆሰሉት ውስጥ አንድ የውጭ ዜጋ እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

Via:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@Yenetube @FikerAssefa
በሀረር ከተማ በሚገኘው የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል ሲሉ የካምፓሱ ዲን አቶ ድርብሳ ድንቁ ለOMN ተናግረዋል።

Via:- ELU/ OMN
@YeneTube @Fikerassefa
1
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
በጎንደር በጥምቀት በዓል ላይ በደረሰ የመወጣጫ መደርመስ አደጋ #ከ100_በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት በጥምቀተ ባሕሩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ሲከታተሉ በነበሩ ሰዎች ላይ ለመቀመጫነት የተሠራ ርብራብ እንጨት ተደርምሶ ድንገተኛ አደጋ አድርሷል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ በተጎዱ ሰዎችና በአደጋው መንስኤ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የአደጋው መንስኤ ለመቀመጫነት የተሠራው ርብራብ እንጨት ድንገት መንሸራተቱ እንደሆነ መምሪያው አሳውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋ መኮንን እንዳሉት በተሠራው ርብራብ እንጨት ተቀምጠው የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ለኅልፈት የተዳረጉ እንዳሉም አረጋግጠዋል፡፡ ኃላፊው የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽም ጉዳቱ ለደረሰባቸው ወገኖች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
አደጋው እንደደረሰም አብዛኞቹ ተጎጅዎች ሕክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡

በሕክምና ላይ ካሉት መካከል አምስቱ ከባድ ጉዳት እንዳጋጠማቸውም ተብራርቷል፡፡ ቀላል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎችና ሁለት የፀጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበት በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

መቀመጫው ከ700 እስከ 1000 ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች ያስተናግዳል ተብሎ የተሠራ ቢሆንም ፣ bባሕረ ጥምቀቱ ይካሄድ የነበረውን ሃይማኖታዊ ሥርዓትና የበዓሉን ድባብ ለማየት በጉጉት ይጠባበቁ የነበሩ በርካታ ሰዎች በእንጨቱ ላይ በመውጣታቸው ችግሩ መፈጠሩን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው ከተፈጠረው አደጋ ውጭ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳልነበርና ታቦታቱ በሠላም ወደ አድባራቱ ገብተዋል ፡፡

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa