YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከመተማ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ላይ ታጣቂዎች በአንድ ተሽከርካሪ ላይ በከፈቱት ተኩስ በ4 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ። #የጎንደር_መተማ_መንገድ በኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ይታወቃል።

ባለፈው ሳምንት በዚሁ መንገድ ሲጓዝ በታጣቂዎች የታገተን አሽከርካሪ ለማስለቀቅ 400ሺ ብር መጠየቁ ይታወቃል።
@Yenetube @FikerAssefa
#የጎንደር ከተማ ሙስሊም ወንድሞቻችን ለመስቀል ባዓል ፒያሳ መስቀል አደባባይ እያፀዱ ነው።

ይህ አኩሪ ተግባር በመላሁ አገሪቱ እንዲቀጥል
ከወዲሁ እናስገነዝባለን።
@YeneTube @FikerAssefa
#የጎንደር እና #አዲስ_አበባ ከተሞች የእህትማማች ከተማ ግንኙነት ምስረታ ስምምነት ተፈራረሙ። የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ማስተዋል ስዩም እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ናቸው ስምምነቱን የተፈረመውት።

ስምምነቱ ከተሞቹ በመንገድ፣ በሰው ሃብት ልማትና ዓቅም ግንባታ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ ልማትና አቅርቦት፣ በቱሪዝም መስፋፋት፣ በባህል ልማት በከተማ ገፅታ ግንባታ ዘርፎች ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ ጥቅም ላይ ማዋላ ላይ ያተኩራል።

ምንጭ:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa