YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
‹‹የሲዳማ ክልል የሚመራበት ህገ መንግስት በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል›› ሲሉ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።

ተቋማትን የመገንባት ስራ ከዚሁ ጎን ለጎን እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።ዋና አስተዳዳሪው አቶ ደስታ ሌዳሞ ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በአሁኑ ወቅት አዲሱ የሲዳማ ክልል የሚመራበት የራሱ ህገ መንግስት በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል።

ህገ መንግስቱን የማርቀቅ ስራ ቀደም ሲል የተጀመረ ሲሆን፣ ከተረቀቀም አንድ ዓመት ያህል ሆኖታል።ረቂቅ ህገ መንግስቱ ላይ የሲዳማ ህዝብ አንድ ጊዜ እንዲወያይበት መደረጉን የተናገሩት አቶ ደስታ፤ በህዝቡ መተቸቱና ማስተቸቱ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት 23 በመቶ ደረሰ!

የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር እስከ አስር በመቶ የሚደረስ ጭማሪ ማስመዝገቡን የብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ዘገባ አመላከተ።ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶች ላይ በክልሉ የተስተዋለው የግሽበት መጠን በ2011 ከነበረበት የ 13 በመቶ የአስር በመቶ ጭማሪ በማድረግ አሁን 23 ከመቶ ላይ እንደሚገኝ የባንኩ ዓመታዊ ዘገባ ያስረዳል። አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በትግራይ ክልል ባለፈው ዓመት 13.9 በመቶ ላይ የነበረ ሲሆን፣ አሁን 19.8 በመቶ ላይ ደርሶ ይገኛል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከትናንት ጀምሮ እየተወያዩ ነው።

ከዚህ ቀደም ሀገራቱ በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተገናኝተው በመወያየት ላይ የሚገኙት።በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ አተኩሮ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ የሀገራቱ የውሃ ሚኒስትሮችም እየተካፈሉ ሲሆን፥ የአሜሪካ መንግስት እና የዓለም ባንክ ተወካዮችም በታዛቢነት ተገኝተዋል። ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው በውሃ ሚኒስትሮች ደረጃ በተለያዩ ዙሮች የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያደረጓቸውን ድርድሮች ውጤት ይመለከታሉ።ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ሲያካሂዱት የቆዩት አራተኛና የመጨረሻው የቴክኒክ ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ውይይቱ ያለስምምነት የተጠናቀቀው ግብፅ የግድቡን የውሃ ሙሌት በተመለከተ አዲስ ሃሳብ ይዛ በመቅረቧ መሆኑንም የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ግብፅ ግድቡ ከ12 እስከ 21 ዓመት እንዲሞላ የሚል አዲስ ሀሳብ ማቅረቧ እና ኢትዮጵያ በበኩሏ ይህን ሃሳብ በማንኛውም መልኩ እንደማትቀበል መግለጿን ነው ሚኒስትሩ በወቅቱ የተናገሩት።ሶስቱ ሀገራት ከዚህ በፊት የህዳሴው ግድብ በ7 ዓመት ውስጥ እንዲሞላ ስምምነት ላይ ደረሰው የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ሶስቱ አገራት በዋሺንግተን ዲሲ በደረሱት ስምምነት አማካኝነት ስምምነት ላይ ካልደረሱ የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በካርቱም የተፈረመው ስምምነት አንቀጽ 10 ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል።የካርቱም ስምምነት አንቀጽ 10 “ሶስቱ አገራት በመርሆዎች ስምምነቱ አተረጓጎምና ተግባራዊነት የተነሱ አለመግባባቶችን በውይይት ወይም በድርድር ይፈታሉ፤ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን አደራዳሪ ሊጠይቁ ወይም ለአገራቸው መሪዎች ሊያሳውቁ ይችላሉ” ይላል።ይህንንም የሚያደርጉት የሶስቱም ሀገራት ስምምነት ሲኖር እንደሆነም አስቀምጧል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
የቲቦር ናዢ የኢትዮጵያ ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናዢ ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ አገራትን ሊጎበኙ ነው፡፡

ረዳት ሚንስትሩ ከጥር 6 እስከ 20/2012 በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ነው የተገለጸው፡፡
በሁለት ሳምንት ቆይታቸውም ከየአገራቱ ከፍተኛ አመራሮችና ዓለም ዐቀፍ የዋሽንግተን አጋር ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ማጠናከር፣ አካባቢያዊ ፀጥታን ማጎልበት፣ ሙስናን መዋጋት እና የንግድና የመዋዕለ ነዋይ ፍሰትን ማበረታታት የታቦር ናዢ ጉብኝት ዓላማ መሆናቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጿል፡፡

ምንጭ:- አሀዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @Fikerassefa
የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞች አሶሳ ላይ መታሰር እና የክልልሉ መልስ!

የትግራይ ቲቪ የአዲስ አበባ ቢሮ አስተባባሪ አቶ አክሊሉ ደባልቀው በስልክ ከነገረኝ:
"የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኛ የሆነው ዳዊት ከበደ እና የካሜራ ባለሙያው በሀይሉ ውቤ ትናንት ምሽት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ሶስት ሰአት ገደማ ታስረዋል። ከቅዳሜ ጀምሮ የተለያዩ ቀረፃዎችን ሲያካሂዱ ቆይተው ትናንት እስካሁን ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት ታስረዋል። እዛ ሆነው የሰሩት እና በቲቪ የተላለፈ ፕሮግራም እንኳን አልነበረም።"

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቃል አቀባይ አቶ መለሰ በየነ የሰጠኝ መልስ:
"እኔ ለስራ ሌላ ቦታ ነኝ ነገር ግን ስልክ በመደወል ለመረዳት እንደቻልኩት ጋዜጠኞቹ የነበረንን አሰራር ተከትለው አልመጡም። ይህ ማለት ወደ ክልሉ ለዘገባ እንደሚመጡ ለክልሉ ኮሚኒኬሽን አላሳወቁም። ምን መስራት እንደሚፈልጉ ነግረውን፣ እኛም ባለሙያ እና አስፈላጊም ከሆነ የፀጥታ አካላት መድበን መሆን ነበረበት። ለምሳሌ እኔ እንደ ክልሉ ኮሚኒኬሽን ሀላፊ ስለመምጣታቸው የማውቀው ነገር የለም። ታሰሩ ሲባል እንደሌላው ሰው ነው የሰማሁት። አሁን ግን የታሰሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ በትክክል አጣርተን እናሳውቃለን።"

ምንጭ:- ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @Fikeeassefa
ግብፅ ከአሜሪካ ባደረገችው የተናጠል ውይይት ታላቁ የኅዳሴ ግድብ ውኃ የሚሞላበትና የሚተዳደርበት ሕግጋት እና አሰራር ምን መሆን እንዳለበት አገራቸው ማስረዳቷን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሕመድ ሐፌዝ ገልጸዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ አዲሱ የመሬት ልኬታ/ካዳስተር/ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የእርሻ መሬት ግብር ክፍያ የተቀየረና የተጨመረ ተደርጎ የሚነሳው ስህተት መሆኑን ገለፀ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር መምሪያና የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በጋራ በመሆን የአርሶ አደሩ የገጠር መሬት ይዞታ አዲስ የመሬት ልኬት /ካዳስተር/ከተሰራ በኋላ የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ግብር ላይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ንጉሴ እንደገለፁት ፤የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ስራ ገቢ ግብር በክልሉ ምክር ቤት አዋጅ ህዳር 2001 ዓ.ም በጸደቀው መሰረት በአርሶ አደሩ መሬት ልክ እንዲከፍል ተደርጎ እየተሰራበት ቆይቷል፡፡

የአርሶ አደሮች የገጠር መሬት ይዞታ የግብር ክፍያ በምግብ ዋስትና የተያዙና ያልተያዙት በስተቀር ልዩነት እንደሌለው ገልጸው ፤በጥማድ 30 እና 40 ብር እንዲከፍሉ ሲደረግ ቆይቷል፤ አሁንም ይህ አሰራር እንደቀጠለ ያለና ያልተቀየረ ሲሆን ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በአንዳንድ አካባቢዎች ከግንዛቤ ማነስ ሊሆን በሚችል የአርሶ አደሩ የመሬት መጠቀሚያ ግብር የተቀየረና የተጨመረ ተደርጎ የሚነሳው ስህተትና ልዩነት አለመደረጉን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ: የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ‹‹ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ›› የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ለመመሥረት በዝግጅት ላይ የነበሩ 10 ግለሰቦች ላይ የእስር ማዘዣ በማውጣት ሰብሳቢውን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ። የፓርቲዉ ምክትል ሰብሳቢ ጌታሁን መርጋ፣ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ጌታቸዉ ወድሻ፣ የድርጅት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጉዮ ፈረደን (ዶ/ር) ሐሙስ ታኅሳስ 30/2012 መታሰራቸውን የቦሮ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ዮሐንስ ተሰማ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
"ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ደብዳቤ ይዘው ስላልተገኙ ነው" የአሶሳ ፖሊስ

ዋና ኢንስፔክተር እስማኤል፤ ሁለቱ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትን ለመዘገብ ከኤጀንሲው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ መላካቸውን እንደነገሯቸው ጠቅሰው፤ ጋዜጠኞቹ ወደ አሶሳ ሲመጡ ደብዳቤ ባለመያዛቸው እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለ ሁለቱ ጋዜጠኞች ወደ ክልሉ መምጣት የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ መታሰራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮ-ቴሌኮም ንብረት የሆኑ በርካታ የስልክ ገመዶችን ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገፀ፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳስታወቀው ጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መርካቶ ጋዝ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለበርካታ ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጡ እና ከመሬት ውስጥ ተቆፍረው የወጡ የስልክ ገመዶችን አከማችተው የተገኙ 2 ተጠርታሪዎች በፖሊስ አባላት ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተመሳሳይ በክ/ከተማው መርካቶ ኢትዮጵያ ዳቦ ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አንድ ተጠርጣሪ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ ንብረትነቱ የኢትዮ ቴሌኮም የሆኑ የስልክ ገመዶችን ቆፍሮ እያወጣና እየቆረጠ ሰርቆ ለመውሰድ ሲሞክር በፖሊስ አጋዥ ሃይሎች እጅ ከፈንጅ ሊያዝ መቻሉን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የነበረው በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ መሆኑን ያስታወሰው ፖሊስ መምሪያው በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የመሰረተ ልማት አውታሮች የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት መረጃ ግንኙነት ያቀላሉ፡ ለሀገራች የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የህዝብ ሀብት ስለሆኑ ፖሊስ ወንጀሉን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ በነቃ ተሳትፎ እንዲያግዝ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
ለፌዴራል መንግስት ከተመደበው 240,179,459,024 ብር ላይ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ (ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለ45ቱ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) 20.15% ድርሻ ይይዛል፡፡

Photo:የአጠቃላይ በጀቱ ክፍፍል
Via MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa
ሰርግዎን በቅርቡ ለመሰረግ አስበዋል?
እንግድያውስ የዲኮሩን ስራ በእኛ ላይ ይጣሉት

💥LEAD DECOR

በባህላዊ እና ዘመናዊ መልኩ ዝግጅትዎን እናስውባለን::
➡️ለሠርግ
➡️ለመልስ
➡️ለልደት
➡️ለስብሰባ አዳራሽ
እንዲሁም
ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች

0912672317, 0920315163 ደውለው ያነጋግሩን

ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ⬇️
https://tttttt.me/LeadDecor
LADIES BOOK NOW👇 👇👇👇👇

Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የበረሃ አንበጣ የኢትዮጵያ ደቡባዊ አካባቢዎች ደርሷል

ለወራት ሰሜን ኢትዮጲያን ሲያስጨንቅ የከረመው የበረሃ አንበጣ አሁን ፊቱን ወደ ደቡብ አካባቢ ያዞረ ይመስላል። የደቡብ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ በክልሉ የአንበጣ መንጋ በስፋት መከሰቱን ለዶቼ ቨለ (DW) አረጋግጠዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
የትንባሆ ዋጋ አሁን ካለበት ዋጋ ሦስት ዕጥፍ ቢጨምር በትንባሆ ምክንያት የሚደርሰውን እና እየደረሰ ያለውን ጉዳት እስከ 40 በመቶ እንደሚቀንሰው የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

Via:- ኢትዮ ኤፍ ኤም /Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2ሽሕ ኹለት መቶ 25 ግብር ከፋዮችን ኦዲት በማድረግ ሊሰወር የነበረ 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማስቀረት እንደተቻለ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርሀኑ አበበ ተናገሩ።

Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ የበረከት ስምዖንን እና ታደሠ ካሳን 2 መከላከያ ምስክሮች መስማቱን የአማራ ብዙኻን መገናኛ ዘግቧል፡፡ በነገው ችሎት ሌሎች ምስክሮች ይቀርባሉ፡፡ ለምስክርነት የተጠሩት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም መቼ እንደሚቀርቡ አልታወቀም፡፡

Via:- wazema
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Samsung CURVED UHD TV
55 7 SERIES NU7300 SMART TV
BRAND NEW
INBOX 📩 @CloudMultiTrading2 📩