YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቴክኒክ ጉዳይ የሶስትዮሽ ውይይት ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል!

Via ኢ.ዜ.አ
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ የታጠቁ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት ሁለት ሰዎች ሞቱ።

የልዩ ወረዳው ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ጥቃቱ ዛሬ ረፋድ ላይ የተፈጸመው በወረዳው ዶርባዴ ቀበሌ ውስጥ በምትገኝ ፈጫቶ በተባለች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው።ታጣቂዎቹ በመንደሩ ነዋሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ በ 14 እና በ 15 ዓመት የአድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የሁለት ታዳጊ ህጻናት ህይወት ማለፉን የልዩ ወረዳው ባህል፤ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ አማረ አክሊሉ ለዶቼ ቨለ ገልጸዋል።

ጥቃቱን ያደረሱት ታጣቂዎች ከአጎራባች የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን መሻገር ወደ ወረዳው የገቡና ማንነታቸውን እንዳይታወቅ የራስ ጭምብል ያጠለቁ መሆናቸውን ከመንደሩ ነዋሪዎች ለማረጋገጥ መቻሉን ኃላፊው ተናግረዋል። ኃላፊው በማያያዝም «የታጣቂዎቹን ጥቃት ተከትሎ በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ወደ መንደሩ በመንቀሳቀስ በጉዳት አድራሾቹ ላይ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛሉ» ብለዋል።

ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን በመነሳት በደቡብ ክልል አማሮ ለዩ ወረዳ ነዋሪዎች ላይ በታጠቁ ቡድኖች ይደርስ የነበረው ጥቃት ባለፈው የሰኔ ወር ላይ በሁለቱ የአካባቢ ባለስልጣናትና በአገር ሽማግሌዎች የሚመራ የሰላም ጉባኤ ከተካሄደ በኃላ ጋብ ብሎ መቆየቱ ይታወሳል። የዛሬው ጥቃት በአካባቢው የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም በማደፍረስ በሁለቱ ተጎራባች ህዝቦች መካከል ግጭትና መጠራጠርን ለመፍጠር ያለመ ነው ሲሉ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አማረ ጨምረው ገልጸዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫው የሚካሄድበት ጊዜ ጁን 28 ነው የሚለውን መረጃ ምርጫ ቦርድ አስተባበለ!

"የተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች የቀጣዩ ብሄራዊ ምርጫ ቀን ጁን 28 ነው የሚል መረጃ ደርሶናል ትክክል ነው ወይ ብለው ጥያቄ እያቀረቡልን ይገኛሉ። በመሆኑም የሚቀጥለው ምርጫ ቀን ጁን 28 ቀን ነው የሚለው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን!" ሲል ቦርዱ ከደቂቃዎች በፊት ምላሽ ሰጥቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube pinned Deleted message
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEO_AwEACCqYXy4L9A. 👈🏾👈🏾👈👈👈 🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
የተከበራችሁ የ SHOPIA®️ ቤተሰቦች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ ❤️ እያልን በዐሉን ምክንያት በማድረግ ከ 25/04/12(ቅዳሜ) ጀምሮ ለ 3 ተከታታይ ቀናት በቻናላችን በኩል በሚሸጡ ሁሉም ዕቃዎች ላይ 5-15%⬇️ ቅናሽ አድርገናል።🤗
🎉🛍 ይግዙ በዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ ቅናሹ የሚቆየው እስከ በዐሉ ዋዜማ ድረስ ብቻ ነው🎁🛒

🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅
⭐️ መልካም የገና በዐል ⭐️
⭐️ SHOPIA ⭐️
🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅🎄🎅👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEO_AwEACCqYXy4L9A
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም አመት በዓል!

ፈረስ ያደርሳል!!

t.me/feresapps
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የአክሱም ሃውልት ጥገና በቀጣዩ ወር ይጀመራል!

የጣሊያን መንግሥት ታሪካዊ ቤቶችን ለማደስ ቃል ገብቷል።ከአክሱም ሐውልቶች መካከል 24 ሜትር ርዝመት ያለውና ‹‹ቁጥር ሦስት›› በመባል የሚታወቀው ሃውልት ጥገናው በጥር ወር 2012 ዓ.ም መጨረሻ ላይ እንደሚጀመር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ፍስሃ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ጥገናውን ለማከናወን ከሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መካከል አብዛኞቹ በመጠናቀቃቸው የሃውልቱ ጥገና በጥር ወር መጨረሻ ላይ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። ከጥር ወር አጋማሽ ጀምሮ ለጥገናው የሚያስፈልጉ እቃዎች ከውጭ ይገባሉ።

ምንጭ: ኢ.ፕ.ድ
@YeneTube @FikerAssefa
HOPE EDUCATIONAL CONSULTANT


YOUR FUTURE - OUR MISSION


አስደሳች ዜና ለውጪ ሀገር ትምህርት እድል ፈላጊዎች በሙሉ


Scholarship የምንሰጥባቸው ሃገራት
1, ስዊዘርላንድ 🇨🇭
2,ካናዳ🇨🇦
3,ፖላንድ🇵🇱
4,ቱርክ 🇹🇷


📚
1. Bachelor Degree
2,masters Degree


📩የ ጥር እና የካቲት ምዝገባ ጀምረናል


የ አገልግሎታችን ተጠቃሚ ስለሆኑ እናመሰግናለን


የ ቻናላችን ሊንክ 👉https://tttttt.me/HopeEducationalConsulants👈

Contact as :
Telegram:@Abditade
Tel :+8613088257750 ( IMO ,what’s up)
WeChat ID :AbdiTade
Email:abditade54@gmail.com
የዩክሬን አውሮፕላን መከስከስ

በኢራን የአየር ክልል ውስጥ በተከሰከሰው የዩክሬን አውሮፕላን ከ170 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ቦይንግ 737 የሆነው አውሮፕላን ከ170 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ከኢራን ኢማ ሆሜኒ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተነሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የመከስከስ አደጋው የገጠመው፡፡

አውሮፕላኑ ወደ ዩክሬኗ ርዕሰ ከተማ ኬይቭ የሚበር ነበር፡፡

አደጋው ከዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ሰሞነኛ ውጥረት ጋር የተያያዘ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው የሚለው ጉዳይ ገና አልታወቀም፡፡

አደጋው ከማሌዥያና የኢዮትጵያ ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ክስተት ቀጥሎ የተከሰት ከባዱ የመከስሰክ አደጋ ሲሆን በሞቱበት ሰዎች ብዛትም ከማሌዥያው በመቀጠል ሁለተኛው ሆኗል፡፡//

Via:- አሀዱ
@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Video circulating of Missiles flying from Iran to Iraq hitting US base
ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ላይ በህዳሴ ግድብ ዙርያ መምከር ጀምረዋል!

የኢትዮጵያ ውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት የአሁኑ ውይይት በግድቡ አሞላል፣ አጠቃቀም እና ድርቅን የመቋቋም አሰራር ዙርያ ይሆናል ብለዋል። አክለውም "እስካሁን ብዙ ጉዳዮች ላይ መክረናል፣ ነገር ግን ስምምነት ላይ እስክንደርስ ድረስ ሁሉም ነገር ክፍት ነው" ብለው ፅፈዋል።

ዛሬ እና ነገ አዲስ አበባ የሚካሄደው ውይይት በቴክኒክ ቡድን ደረጃ ሲካሄድ የነበረው ምክክር የመጨረሻው ነው።

Via:- Elias Mesert
@YeneTube @Fikerassefa
ዶናልድ ትራፕ ኢራን የአሜሪካን ጦር ሰፈር ለመምታት የታቀደ ሚሳኤል መተኮሶን በትዊተር ገፁ አስታውቋል።

ጠዋት ላይ መግለጫ እንደሚሰጥም በገፁ ላይ አስፍሯል።
@YeneTube @Fikerassefa
የአሜሪካና ኢራን ፍጥቻ ማየሉን ተከትሎ ውጥረቱን ማርገብ እንደሚገባ ዩኤኢ አሳሰበች፡፡ ሁኔታዎች እንዳይባባሱ አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያሻም ሀገሪቱ አሳስባለች።

@YeneTube @Fikerassefa
#Breaking

የዩክሬን አይሮፕላን ኢራን ላይ ተከስክሶ 176 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ዩክሬን አውሮፕላነቿ ወደ ኢራን ምንም አይነት በረራ እንዳያደርጉ አገደች።

@YeneTube @Fikerassefa
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ335 ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን ላይ እርምጃ ወሰደ!

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አባተ ጌታሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብሔርና በኃይማኖት ሽፋን በተፈጠረ አለመረጋጋት የመማር ማስተማር ስራው ባለፉት ወራት ውስጥ ለሶስት ጊዜ መቋረጡን አውስተዋል።

በዚህም የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉንና በተወሰኑት ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቅሰው ይህም ከአንድ የእውቀት ምንጭ ተቋም የማይጠበቅ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን ባለፉት ሁለት ወራት ችግር ፈጣሪዎችን ለመለየት በተከናወነው ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራው እንዳይቀጥል ፍላጎት ያላቸውን 332 ተማሪዎች፣ ሁለት የአስተዳደር ሰራተኞችና አንድ መምህር ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል። እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ ከዚህ ውስጥ 12 ተማሪዎችና ሁለት የአስተዳደር ሰራተኞች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ይገኛል።

Via ኢዜአ
@YeneTube @Fikerassefa
ዛሬ ጠዋት ከኢራን ወደ ዩክሬን ሲያመራ የተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍረው የነበሩት ሰዎች ዜግነት ታውቋል!

በዚህም መሰረት 82 ኢራናውያን፣ 63 ካናዳውያን፣ 11 ዩክሬናውያን እና 10 ስዊድናውያን በአደጋው ህይወታቸውን እንዳጡ ታውቋል። ከአደጋው በህይወት የተረፉ ሰዎች እንደሌሉም አሶሼትድ ፕረስ ከቴህራን ዘግቧል።

@YeneTube @Fikerassefa
በአውስትራሊያ በተከሰተው እሳት የተጠረጠሩ 24 ሰዎች ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡ ኒው ሳውዝ ዌልስ ግዛት የአደጋው ዋነኛ ተጠቂ ስትሆን 24 ሰዎችና ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጉ እንስሳት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
በያዝነው ወር(በፈረንጆች) ከመደበኛ ከፍ ያለ የዝናብ መጠን በደቡብ ኢትዮጵያ እንደሚጠበቅ የኢጋድ አየር ትንበያና ትግበራ ማዕከል አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ይቅርታ ስለ መጠየቅ!!

ከዚህ በፊት ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረትም ሆነ ከሌሎች ሚድያዎች የምንወስዳቸውን መረጃዎች በትክክል ምንጭ ጠቅሰን የምንለቅ ቢሆንም ዛሬ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃል።

ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ስህተት የማይደገም መሆኑ ለመናገር እንወዳለን።

እናመሰግናለን!!
@YeneTube @Fikerassefa