YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይና መንግስት ድጋፍ በሸራተን አካባቢ እየተገነባ ያለውን የወንዞች ዳርቻና አረንጓዴ ልማት አካል የሆነውን ፕሮጀክት እየጎበኙ ነው።

@YeneTube @Fikerassefa
በምዕራፍ ሱዳን ዳርፋር 16 ሰዎችን በታጣቂዎች ተገደሉ እንዲህም 12 ሰዎችን ታጣቂዎች ማቁሰላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ሰቬንዲ ኒዊስ ዘግቧል።

Via:- Al Ain
@YeneTube @Fikerassefa
ጂማ ዩንቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች በሙሉ⬆️
HOPE EDUCATIONAL CONSULTANT


YOUR FUTURE - OUR MISSION


🇹🇷 Türkiye'de eğitim🇹🇷


🔔አስደሳች ዜና በ ቱርክ ሀገር የትምህርት እድል ፈላጊዎች በሙሉ 🔔

በቱርክ ሀገር ዋና ከተማ ISTANBUL🌆

📜BACHELOR DEGREE AND MASTERS DEGREE

🔶ልዩ የ ትምህርት እድል ፈጣን እና በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ process

🔶በመሆኑ በ ተመጣጣኝ ዋጋ የምናገለግል ስለሆነ ፈጥነው ቦታዎን ይያዙ

🔶ድርጅታችን የ ረጅም ጊዜ ልምድ ስላለው በ አገልግሎታችን ይኮራሉ

📚 DOCUMENTS
PASSPORT
HIGH SCHOOL CERTIFICATE
TRANSCRIPTS
PHOTO
BANK STATEMENT (250,000 &Above )


የ አገልግሎታችን ተጠቂሚ ስለሆኑ እናመሰግናለን

OLARAK SEÇME İÇİN TEŞEKKÜRLER

Channel link: https://tttttt.me/HopeEducationalConsulants

Contact as :
Telegram:@Abditade
Tel :+8613088257750 ( IMO ,what’s up)
WeChat ID :AbdiTade
Email:abditade54@gmail.com
1
በመተማ ወረዳ በመቃ ቀበሌ የሰሌዳ ቁጥሩ መከ 02488 የሆነ የመከላከያ ኦራል ተገልብጦ በንብረትና በሰው ህይወት ላይ አደጋ ደረሰ

ከባቢ በመቃ ቀበሌ ወደ ገንዳውሃ ከተማ ሲጓዝ እያለ ድንገት መስመሩ ላይ ላም በመግባቷ ላሚቱን አድናለሁ በሚል እሳቤ ኦራሉ በመገልበጡ ሹፌሩና ሌላ አንድ ጓድ ሲሞቱ ሁለቱ ደግሞ ከባድ የአካል ግዳት ደርሶባቸዋል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ በደረሰ የመኪና መገልበጥ አደጋ ሁለት ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በአስራ አራት ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር የሺ አሰፋ እንደገለፁት በሰ/ሸዋ ዞን በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ በትናንትናው እለት ኮድ 3-አአ 23637 ደረቅ አይሱዙ የጭነት መኪና 12፡30 መነሻውን በወረዳው ዋና ከተማ መኮይ መዳረሻውን ግሼ ራቤል በማድረግ የተለያዩ ሸቀጦችን የጫነ ሲሆን ከሸቀጡ በተጨማሪ ከሀያ በላይ ሰዎችን ጭኖ ስለነበር በጉዞ ላይ እያለ በወረዳው በመቅደሳ ቀበሌ ልዩ ስሙ አሮሬሳ ኮፎ ከተባለው ቦታ ሲደርስ ወደ ኋላ በመንሸራተት ሊገለበጥ ችሏል፡፡

በዚህም ሁለት ሰዎች ህይወታቸው ወዲያው ሲያልፍ በአስራ አራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት በመድረሱ ተጎጂዎቹ በአሁኑ ሰዓት በኬሚሴ ሆስፒታል ህክምና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
አሜሪካ ባግዳድ የሚገኘው ኤምባሲዋ በሰልፈኞች ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልታሰማራ መሆኑን አስታውቃለች።

አሜሪካ ባሳለፍነው እሁድ ዕለት በኢራን እንሚደገፉ በሚነገርላቸው እና በኢራቅ በሚንቀሳቀሱ የሂዝቦላህ ታጣቂዎች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 25 የቡድኑ አባላት ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቡታጅራ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ህግ በሚፈቅደው ጊዜ ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት እየቀረቡ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
የፈረንጆቹን 2020 አስመልክቶ ኦነግ (ABO) ለኦሮሞ ህዝብ ; ለአባላቶቹ እንዲሁም ለደጋፊዎች ያስተላለፈው መልክት።

https://telegra.ph/ABO-01-01
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞባይል መተግበርያ (mobile app) ባለፈው ዘጠኝ ወር ብቻ የሁለት ቢልየን ብር ሽያጭ ተከናውኖበታል።"

Via:- BusinessInfoEth
@YeneTube @Fikerassefa
በአፋር እና በሱማሌ ክልል መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት በተካሄደ የምክክር ላይ የቀረበ የአቋም መግለጫ

👇👇👇👇👇
https://telegra.ph/AfarSomali-01-01
በኦሮሚያ በመሰራት ላይ ካሉ 27 የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል 9ኙ ዘንድሮ እንደሚጠናቀቁ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል 9.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦላቸው በመሰራት ላይ ካሉ 27 የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል 9ኙ ዘንድሮ እንደሚጠናቀቁ የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ፍቃዱ እንደገለፁት በክልሉ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ እንዳሉ ጠቁመው በ2012 ዓ.ም ብቻ ለ23 አዳዲስ ፕሮጀክቶች 5.4 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቦላቸዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ የህግ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

👇👇👇👇👇
https://telegra.ph/HateSpeech-01-01
📌አስቸኳይ ማስታወቂያ ለወለጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ
@YeneTube @Fikerassefa
በጊምቢ ወረዳ በተሽከርካሪ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ!!

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ዛሬ ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

በወረዳው ጆብር ቀበሌ ልዩ ስሙ  ቡሉል በተባለ ስፍራ የደረሰው ይሄው አደጋ የታርጋ ቁጥር ኮድ 3- 42548 ኦሮ ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ከነቀምቴ ወደ ጊምቢ ከሚጓዝ የታርጋ ቁጥር ኮድ 3- 58995 ኢት  ከሆነ ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በዞኑ ፖሊስ  የትራፊክ ዲቭዥን ኃላፊ  ሳጅን ጋጃሳ አሰፋ እንዳሉት በአደጋው  12 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ አንድ ሰው ደግሞ ጊምቢ ከተማ አድቨንትስት ሆስፒታል ለህክምና ከደረሰ በኋላ ህይወቱ አልፏል።

ህይወታቸው ካለፈው መካከል አስር ወንዶችና ቀሪዎቹ ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህም የዶልፊኑ አሽከርካሪና  ረዳቱም ይገኙበታል። የጭነት ተሽከርካሪው ሾፌር  እጁን ለፖሊስ መስጠቱን ሳጅን ጋጃሳ አመልክተዋል።

የጊምቢ ከተማ አድቨንትስት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ፍራፍያድ ጉደታ እንደተናገሩት በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው ሌላ ስምንት ሰዎች ከበድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው። ከእነዚህም ሶስት ሰዎች በአስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

Via:- ENA
@YeneTube @Fikerassefa
በሰሜን ሸዋ ዞን ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው።

የሰው ሕይወትን የነጠቁ ግጭቶች ባጋጠሙባቸው ወረዳዎች እርቅ መፈፀሙና ጥብቅ የፀጥታ ቁጥጥር ማድረግ መጀመሩ አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም እንዲኖር ማድረጉንም የዞኑ አስተዳደር ለአሐዱ ቴሌቪዥን ገልጿል። ዞኑ ከኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም በዚያው በአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጋር የሚዋሰን ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የሚነሱ የአስተዳዳር ወሰን ጥያቄዎች፣ የአርብቶ አደሮች ልቅ ግጦሽ እንዲሁም ግጭቶቹ ተከስተው በነበሩበት የ2011 መገባደጃና 2012 መጀመሪያ ወራት በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረ ሕገ ወጥ የታጠቀ ቡድን ተጠያቂ ናቸው ሲል አስተዳደሩ ይከሳል፡፡

እንደ አጣዬና አካባቢው፣ ምንጃር ሸንኮራ እና በረከት ባሉት ወረዳዎች በተከሰቱት ግጭቶች የሰው ሕይወት መጥፋቱን ያስታወሱት የዞኑ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ካሳሁን እምቢአለ፤ በአካባቢዎቹ የግጭት ምንጮች መለየታቸውንና ዳግም እንዳይከሰቱ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል፡፡ኃላፊው አጋጥመው የነበሩ የፀጥታ ችግሮች እንደ አዲስ እየተነቃቃ ባለው የዞኑ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ላይ ጫና አለማሳደሩን ይናገራሉ፡፡ሆኖም በመርሐቤቴ ወረዳ የመንገድ ሥራ ላይ በተነሱ የሥራ እድል ፈጠራ ፍትሐዊነት፣ የአነስተኛ ደመወዝና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የተከሰተው ግጭት ሁለት የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን አቋርጦ ይገኛል፡፡

ምንጭ: አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council የሞጣውን የሽብር ጥቃት አስመልክቶ የተዋቀረው አጣሪ ኮሚቴ ነገ መግለጫ እሰጣለው ብሏል::

@YeneTube @Fikerassefa
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ታሕሳስ 25 እና 26 መስራች ጉባኤ እንደሚያካሂድ ይፋ ኣድርጓል።

ፓርቲው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጠው ይፋዊ መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቅዳሜና እሁድ ፖለቲካዊ ፕሮግራሙን በጉባኤተኞች ያስጸድቃል፣ አመራሮቹን ይመርጣል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ብሄራዊ ድርጅት ሆኖ በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚንቀሳቀስ ነው። የትግራይ ህዝብ እያጋጠሙት ያሉት ሁለንተናዊ ችግሮች ጠንካራ ተቋማዊ አሰራር የሚከተልና ሕግና ስርዓት የሚያከብር ብሄራዊ መንግስት ባለመገንባቱ ነው ሲል ፓርቲው ገልፅዋል። ትግራይ ላይ መሰረት ያደረገ ብሄራዊ ፓርቲና የፖለቲካ ፕሮግራም ባለመኖሩ ህዝቡ ራሱን የሚከላከልበትና የሚለማበት ተቋሞችና ስርዓት መገንባት እንዳልቻለ የገለጸው ፓርቲው፣ ይህ ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት እንደተቋቋመ አብስሯል።

ትግራይ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ የትግል ባህል እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ፕሮግራምና ፖሊሲ እናስተዋውቃለን ያለው ፓርቲው የአክሱም ስልጣኔ፣ ከዛ በኋላ የተካሄዱ በጎ የሆኑ ማሕበረሰባዊ እንቅስቃሴዎችና ህዝባዊ ትግሎች እንደ መሰረት ተቀብሎ፣ አዲስ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ትግል እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

በተጨማሪም የትግራይ ብሄራዊ ጥቅሞች ብሎ ለለያቸው እንደሚታገል ይፋ ኣድርጓል። በጉባኤው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ተወካዮች እንደሚገኙም ኣብራርቷል።

Via:- አውሎ ሚዲያ
@YeneTube @Fikerassefa
የአምራች አድራሻቸው የማይታወቁና ተጭበርብረው የተሰሩ 27 የምግብ ዓይነቶች ገበያ ላይ እየዋሉ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱ ባካሄደው የገበያ ቅኝት መሰረት የታሸጉ ምግቦች የተሟላ የገላጭ ጽሁፍ የሌላቸው፣ አስገዳጅ ብሔራዊ ደረጃን ያላሟሉ፣ የአምራች ድርጅቶቻቸው የማይታወቅና ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፤ የአምራች አድራሻ እና መለያ ቁጥር የሌላቸው፣ የመጠቀሚያና የተመረቱበት ጊዜ በትክክል ያልታተሙ የተለያዩ ምርቶች በገበያ ላይ በተደረገው ቁጥጥር መገኘቱን ባለስልጣኑ አስታውቋል ፡፡የአምራች አድራሻቸው የማይታወቁና ተጭበርብረው ገበያ ላይ ከሚገኙ የምግብ አይነቶች ውስጥ፡-
📌የምግብ ዘይት ዝርዝር

ንጹህ የኑግ ዘይት፣
ኢዛና ዘይት፣
ጣና ዘይት፣
ኦሊያድ ዘይት፣
ስኬት የተጣራ ዘይት፣
በቅሳ የምግብ ዘይት፣
አሚን የምግብ ዘይት፣
ቀመር የምግብ ዘይት፣
ሎዛ የምግብ ዘይት፣
ዘመን የኑግ እና የለዉዝ ዘይት፣
ዘቢብ ቃህ የምግብ ዘይት፣

📌የለውዝ ቂቤ ዝርዝር
ማኢዳ የለዉዝ ቅቤ፣
ሮዛ ክሬሚ ለዉዝ ቅቤ፣

📌ቪምቶ ዝርዝር
ዳና ቪንቶ
ቪንቶ

📌የምግብ ጨው ዝርዝር
አዋሽ የገበታ ጨዉ፣
ሳራ እና ኑስራ ጨዉ፣
ሴፍ የገበታ ጨዉ (በተለያየ እሽግ)፣
ሽናጉ የገበታ ጨዉ፣
ወዛቴ አዮዳይዝድ ጨዉ፣
ቃና የገበታ ጨዉ፣
አስሊ የገበታ ጨዉ፣

📌የማር ዝርዝር
ሲሳይ ንጹህ ማር እና ቅቤ አቅራቢ፣
ወለላ ማር፣

📌የከረሜላ ዝርዝር
ካርቶንስ ካንዲ ፍሩትስ፣
ሊዛ ሎሊፖፕ፣
ክሬሚ ሎሊፖፕ ይገኙበታል ተብሏል፡፡

ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ፤ የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Via Addis TV
@YeneTube @FikerAssefa