YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጃዋር መሐመድ ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መቀላቀሉን የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለቢቢሲ ገለፁ።

ቀደም ሲል ፖለቲካ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ይልቁንም ከዳር ሆኖ በአገሪቱ ለተጀመረው ለውጥ ድጋፍ ማድረግን እንደሚመርጥ ተናግሮ የነበረው ጃዋር በቅርቡ የሃሳብ ለውጥ ማድረጉን እና ፖለቲካ ውስጥ ለመግባት መወሰኑን እንደተናገረ ይታወሳል።

ፖለቲካውን ለመቀላቀል ቢወስንም ተሳትፎው በየትኛው ፓርቲ እንደሚሆን አለመወሰኑንም በወቅቱ ገልፆ ነበር።

ጃዋር ፓርቲያቸውን እንደተቀላቀለ ከቢሯቸው መረጃ የተሰጣቸው ትናንት እንደሆነ የሚናገሩት ፕሮፌሰር መረራ "ኦፌኮ እገባለሁ ብሎ ለቢሯችን ነግሯል" ብለዋል።

ከሦስት ወይም ከአራት ቀናት በፊት ፕሮፌሰር መረራ ባሉበት የፓርቲያቸውን ጽህፈት ቤት መጎብኘቱንም ገልፀዋል።

ጃዋር ወደ ኦፌኮ ለመቀላቀል ከመወሰኑ ቀደም ብሎ ከአመራሩ ጋር ያደረገው ንግግር እንደነበረ የተጠየቁት ሊቀመንበሩ "አባላት ስንመለምል ንግግር የለም፤ እሱ ራሱም እኮ እዚህ ገብቻለው ሊል ይችላል። እኛም ስብሰባ ላይ እኛን ተቀላቅሏል ብለን ልንናገር እንችላለን" የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ቢቢሲ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የጃዋርን አባል የመሆን ጥያቄ ተቀብሎት እንደሆነም ለፕሮፌሰር መረራ ጥያቄ አቅርቦላቸው በሰጡት ምላሽ "ማንም ኢትዮጵያዊ የእኛ አባል ሊሆን ይችላል የምንከለክልበት የተለየ መንገድ የለንም። ወንጀል የሠራ ወይም በሕዝብ ላይ ወንጀል የሠራ እስካልሆነ ድረስ" በማለት መልሰዋል።

ተጨማሪ⬇️
https://telegra.ph/Jawar-12-30
Via:- BBC
@Yenetube @FikerAssefa
"የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በእነ ብ/ጄ ከማል ገልቹ ለሚመራው እና በምዝገባ ሂደት ላይ ላለው “የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ” የሰንደቅ አላማው ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር በመመሳሰሉ እንዲቀይር በደብዳቤ ማሳወቁ በማስከተልም የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ እንደማይመሳል ማብራሪያ ቢያቀርብም በማብራሪያው ያቀረበው ልዮነት ማለትም “የኦነግ ሰንደቅ አላማ ኮከብ ያለው ሲሆን ኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ የለውም” የሚል እንዲሁም “ኦዳን ከቦ ያለው ቢጫው ቀስት የኦነግ ከ30 በላይ ሲሆን የእኛ ግን 22 ነው ( 11 ትላልቅ እና 11 ትናንሽ)” የሚለው ማብራሪያ ለድምጽ ሰጪም ሆነ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያምታታ በመሆኑ እንዲቀይር ቦርዱ መወሰኑን ባለፈው ሳምንት ያሳወቅን ሲሆን የሁለቱ ሰንደቅ አላማዎች መመሳሰልን እና ተያያዥ ጥያቄዎችን ግልጽ ለማድረግ ምስሎቹን ከስር አያይዘናል፡፡"

Via National Election Board of Ethiopia
@Yenetube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም ለአራት ሺሕ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ ደጎመ!

ኢትዮ ቴሌኮም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ13 ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ ስምንት መቶ ተማሪዎች በየወሩ ሲያቀርብ የነበረውን የኪስ ገንዘብ ድጎማ በሁሉም የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በማስፋፋት ለአራት ሺሕ ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ ሊጀምር ነው።የቴሌኮሙ የማኅበራዊ ግዴታ ክፍል ከሰው ኃይል ጋር በመተባበር ያቀናጀው ይህ ድጋፍ፣ በመጪው ማክሰኞ በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ይፋ ያደርጋል። ቴሌኮሙ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰፋፊ የማኅበራዊ ኀላፊነት ድጋፎችን ማድረግ ያጠናከረ ሲሆን፣ በ 2011 ለ 70 ሺሕ በገጠር ለሚኖሩ ሴቶች የሞባይል ስልክ በነጻ ለመስጠት ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱ ይታወሳል።

በተመሳሳይም ለ 32 ሺሕ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ቁሳቁስ ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ 93 ትምህርት ቤቶች የተተገበረ ነው። ለ100 ሴቶችም የፋሽን ዲዛይን ነፃ የትምህርት እድል አመቻችቷል።በ2011 የበጀት ዓመት መባቻ ላይ እስከ 50 በመቶ ድረስ የታሪፍ ቅናሽ ያካሔደው ቴሌኮሙ፣ በበጀት ዓመቱ 36.3 ቢሊዮን ብር ከአገር ውስጥ ገቢዎች የሰበሰበ ሲሆን፣ 98.3 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከዓለም ዐቀፍ አገልግሎት ገቢ ተሰብስቧል። ከዚህ ውስጥም ያልተጣራ ትርፍ 24.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝቷል።

ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃጸር የ5.6 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። ለዓመታት ያልተከፈለ 4.7 ቢሊዮን ብር ግብርን ጨምሮ በአጠቃላይ 16.2 ቢሊዮን ብር ግብር መክፈሉንም ከወራት በፊት አስታውቋል።የኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 43.6 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች 41.92 ሚሊዮን፣ የዳታና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 22.3 ሚሊዮን፣ የመደበኛ ስልክ 1.2 ሚሊዮን እንደሆኑ ታውቋል። በአጠቃላይ የቴሌኮም ተደራሽነት 44.5 ደርሷል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በተደራጀ መንገድ የማታለል ወንጀል እየተበራከተ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ተጠቆመ!

ማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም ሴቶችን በተደራጀ መንገድ የማታለል ወንጀል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠቆመ፡፡
በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ጸጋ እንደገለጹት ከባለፈው አመት ነሀሴ ወር ጀምሮ በተደራጁ አጭበርባሪዎች በፌስቡክና በዋትስአፕ ብቻ 40 የሚደርሱ ሴቶች ተጭበርብረዋል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ👇👇👇👇👇👇

https://telegra.ph/caution-12-30
አቶ እርስቱ ይርዳው በየም ልዩ ወረዳ ከሚገኙ የህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት አደረጉ!

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በየም ልዩ ወረዳ የተለያዩ የመሠረተ ልማት አውታሮችችን ጉብኝት አጠናቀው በሳጃ ከተማ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል ፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በውሀ በመንገድ በትምህርት በጤና እንዲሁም በሌሎችም የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ መሻሻል ስላለባቸው ነጥቦች ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አና የሚመለከታቸው የቢሮ ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Christmas 🎄 gift perfumes
100 ml 👇👇👇👇👇👇
ALL AVILABLE NOW🔥🔥🔥
Contact @kiru04
0931607806

Vercace crystal noir - 1100 birr
Versace bright crystal - 1500 birr
Jadore-1100 birr
YSL -1100 birr
Poison girl dior-1500 birr
Ysl manifesto-1100 birr
Miss dior - 1500 birr
Chanel coco -1100 birr
Dolce &gabaana the one- 1100 birr
Ladi millon - 1100 birr
Vercace dylan blue-1100 birr
Black OPIUM- 1500 birr
Lacoste intense pour femme-1100
Lacoste- 1100 birr
Polo blue - 1100 birr
212 men-1100 birr
Bleu de chanel -1500 birr
Calvin klein eternity -1100 birr
Hugo boss -1100 birr
Giorgio armani-1100 birr
Tom ford -1100 birr
Dior homme-1100 birr
Hugo boss-1100 birr
La casona- 1100 birr
Versace for man -1100 birr
Versace pour homme-1100 birr
Gucci flora-1100 birr
La casona-1100 birr
Dunhill-1100 birr
OLmpea-1100 birr
Gucci flora-1100 birr
Invictus -1100 birr

ALL AVILABLE NOW🔥🔥🔥
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
Forwarded from YeneTube
🎄🎄ታላቅ ቅናሽ 🎄🎄
እንኳን አደረሳቹሁ በአሉን አስመልክቶ ታላቅ ቅናሽ በየቲ ኮስሞቲክስ እንዳያመልጣችሁ አሁኑኑ ሊንኩን በመጫን ቻናላችን ጆይን ያድርጉ

https://tttttt.me/yeticosmo

Yeticosmotics is glad to announce its #holiday discount

1. Apple cider with only 850 br

2. Zara perfume with only 1200 br

2. Tresemme shampoo and
conditioner 1100

3. 1 literJohnson wash and shampoo with only 650 br and we have discount for so many products

Join our telegram channel using

https://tttttt.me/yeticosmo
https://tttttt.me/yeticosmo
የሱዳን ፍርድ ቤት በአንድ መምህር ግድያ ላይ በተሳተፉ የደህንነት አባላት ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ በየካቲት ወር የአልበሽርን መንግስት በመቃወሙ በቁጥጥር ስር የዋለውን መምህር አህመድ አል ኬይርን በገደሉ ሰዎች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡የ36 ዓመቱ ሚስተር አል ኬይር ተቃዋሚዎችን ደግፈሃል በመባል እ.ኤ.አ. በጥር ወር ምስራቅ ከሰላ ከሚገኘው ቤቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዜና ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡

የሱዳኑ መምህራን ማህበር ህብረት ተወካይ የሆኑት ኢትማድ አል ሙጃማር በትናንትናው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጥፋተኝነት ውሳኔው “የፍትህ ድል” ነው ብለዋል፡፡ውሳኔው “የጠፉ መብቶቻችንን ለማስመለስ እያሰብን ያለነው ለሌሎች አብዮታዊ ሰማዕታት እና ቤተሰቦቻቸው መልእክት ያስተላለፈ ነው” ብለዋል ፡፡ፍርድ ቤቱ በቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ላይ በፈጸሙት የሙስና እና ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል የሁለት ዓመት እስር ቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- ዘ ኒውዮርክ ታይምስ /ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ዴሞክራሲዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በመጪው ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታወቀ፡፡

የአዴኃን ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ በዛሬዉ ዕለት ለዶቼ ቬለ (DW)እንደገለፁት ንቅናቄው በመጭዉ ምርጫ ለመሳተፍና በምርጫው ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እያከናወነ ነዉ።ንቅናቄዉ እስካሁን በጎንደር፣ በወልዲያና በጎጃም አንዳንድ አካባቢዎች ዓላማና ፕሮግራሙን ማስተዋወቁንም አቶ ተስፋሁን ገልፀዋል።ሊቀመንበሩ አያይዘውም በምርጫ ሊወዳደሩ የሚችሉ አባሎቻችንን ለይተን በመምረጥ የማብቃት ሥራ እየተሰራን ነዉ ብለዋል።

ለዚህም «የተሸለ ግንዛቤ ያላቸውን፣ የተሻለ ተሰሚነት ላቸውን፣ የኅብረተሰቡን ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉና በኅብረተሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸውን አባሎቻችንን እየመረጥን ሰፊ እንቅስቃሴ እደረግን እንገኛለን” በማለት ተናግረዋል፡፡« ሊበራል» የፖቲካ ፍልስፍና እከተላለሁ የሚለው አዴኃን የኢትዮጵያን መንግስት በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ለ8 ዓመታት በኤርትራ የቆየ ሲሆን በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ አገር ውስጥ የገባ ድርጅት ነው፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
“የሽግግር መንግስት” ይመስረት ያሉ 3 ፓርቲዎች በጋራ ሊሰሩ ነው።

Via:- Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
ኅብረት ባንክ የብድር ወለድ ምጣኔውን ቀነሰ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል ባንኮች በአስገዳጅነት ሲተገብሩት የነበረውን የ27 በመቶ የቦንድ ግዥ መመርያ ካነሳ በኋላ፣ ባንኮች ለብድር ያስከፍሉ የነበረውን የወለድ ምጣኔ እየቀነሱ ሲሆን፣ ኅብረት ባንክም እስከ 4.5 በመቶ የብድር ወለድ ምጣኔውን መቀነሱን አስታውቋል፡፡ባንኩ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ከሚያደርገው ከዚህ ውሳኔ ጎን ለጎን ከሌሎች ባንኮች በተለየ ከ27 በመቶ መመርያ ጋር ተያይዞ ተግባራዊ አድርጎ የነበረውን የሦስት በመቶ የብድር ቅጣት አብሮ ማንሳቱንም አስታውቋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በኢራቅ አንድ ከፍተኛ የሚሊሻ መሪ አሜሪካ ለወሰደችው የአየር ጥቃት በኢራቅ በሚገኙ ወታደሮቿ ላይ ከባድ አፀፋ ሊወሰድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

Via:- Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ በመጭው ግንቦት አክሲዮን ገበያ ልትጀምር እንደምትችል ብሄራዊ ባንክን ጠቅሶ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ብሄራዊ ባንክ አክሲዮን ገበያው የሚመራባቸውን ደንቦች እያዘጋጀ ነው፤ ደንቦቹ በቅርቡ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡ ገበያው በአዋጅ እንዲመራ መንግሥት ከወሰነ ግን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ የሚያወጣ ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአርባምንጭ oilibya ነዳጅ ማደያ ድንገት ቤንዚል ወደ ታንከር በመገልበጥ ላይ እያለ የተነሳ እሳት በድርጅቱ ሠራተኞች ርብርብ fire extinguisher/ በእሳት ማጥፊያ ዱቄት በመጠቀም በቁጥጥር ውሏል።

አደጋው ሊነሳ የነበረው ከነተጎተታቹ ቤንዚል የጫነ ቦቲ መኪና 10 ሠዓት ከ37 አካባቢ ነዳጅ በማራገፍ ላይ እያለ የተነሳ እሳት በድርጅቱ ሰራተኞች ጠፍቷል።

የድርጅቱ ሠራተኞች በፍጥነት የእሳት ማጥያ ኬሚካል ባይጠቀሙ ኖሮ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ ነበር።

Via:- Gamo Zone Administration public Relation office
@Yenetube @Fikerassefa
ወለጋ ዩንቨርስቲ አስቸኳይ ማስታወቂያ

ለአራት ሳምንታት የተቋረጠው ትምህርት እስከ ረቡዕ ታህሳስ 22 /04/2012 ድረስ ትምህርት የማይጀመር ከሆነ :-

የክሪላንስ ፎርም በመሙላት እጃችሁ ላይ ያለውን ማንኛውንም የዩንቨርስቲ ንብረት በመመለስ ግቢውን ለቃችሁ መውጣት ትችላላችሁ።

- ሙሉውን ከፎቶው ላይ ያንብቡ
@Yenetube @FikerAssefa
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአምባሳደር ማይክል ራይነር ጋር ተወያዩ!

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትን ሚስተር ማይክል ራይነር ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ. ም በጽ/ ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። አቶ ገዱ በዚህ ወቅት እንደገለፁት በኢትዮጵና በአሜሪካ መካከል ያለው ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሁለቱን አገራት የጋራ ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ለዘመናት የዘለቀ መሆኑ አንስተዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ በትምህርት፣ በጤና፣ በሰብአዊ ልማት እና በሌሎች ዘርፎች እያደረገችው ያለውን ድጋፍ ክቡር አቶ ገዱ አድንቀዋል።

ሁለቱ አገሮች በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በበርካታ ጉዳዮች በትብብር እየሰሩ መሆኑን አስታውሰው፤ ይህንኑ አጠናከሮ ለማስቀጠል በሁሉም ወገን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ክቡር አምባሳደር ማይክል ራይነር በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በቀጠናው እያደረገች ያለውን አስተዋጽኦ አሜሪካ ታደንቃለችም ብለዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ ግቡን እንዲመታ ድጋፏን አጠናከራ እንደምትቀጥልም ገልጸዋል። የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

ምንጭ: ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ጀዋር መሀመድን በመተካት አቶ ግርማ ጉተማ የOMN ስራ አስኪያጅ ሆነዋል።

ይህ ሹመት በቀጥታ ጃዋር መሀመድ ወደ ኦፌኮ መግባትን ተከትሎ የተደረገ እንደሚሆን ተገምቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
መልካም ቀን ይሁንላችሁ !!