YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለቀድሞ ጣና በለስ ፕሮጀክት በ2007 ዓ.ም ለደለል ማውጫ የተገዛው ማሽን ያለስራ ለአምስት ዓመታት ተቀምጦ ለብልሽት እየተዳረገ መሆኑን የጣና ባህር ትራንስፖርት ድርጅት ገለጸ።

ማሽኑን ወደ ሥራ ለማስገባት ከ30ሺህ ዶላር በላይእንደሚያስፈልግ የውሃ መስኖና ኢነርጂሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የጣና ሀይቅ ትራንስፖርት ድርጅት የጎርጎራ ወደብ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ውበቱ ወርቅነህ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የደለል ማውጫ ማሽኑን በ2007 ዓ.ም ከውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአደራ መልክ ቢቀበሉም እስካሁን ድረስ ሥራ ሳይጀምር ጸሀይና ዝናብ እየተፈራረቀበት ተቀምጧል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ርስቱ ይርዳው ከጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ጋር ዛሬ በዲላ ከተማ ተወያይተዋል። ነዋሪዎቹ የጌዴኦ ህዝብ ከደቡብ ክልል ህዝቦች ጋር በአንድነት ለመኖር እንደሚፈልግና ለዚህም የክልልነት ጥያቄ አለማንሳቱን ገልጸዋል።ሆኖም የሲዳማ ክልል በመመስረቱ ምክንያት ከክልሉ ጋር ያላቸው የየብስ ግንኙነት በመቋረጡ አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
አምባሳደር ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ከስልጣናቸው ተነሱ

የኢትዬጲያ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ሆኖ ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ከስልጣን መነሳታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ዶ/ር አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከስልጣናቸው መነሳት ምክንያት እንደማያውቁና ከስራቸው መነሳታቸውን የሚያሳውቅ ደብዳቤ ብቻ እንደደረሳቸው ያገኘነው መርጃ ያመለክታል።

Via:- SMN
@Yenetube @Fikerassefa
ድምፃዊት ራሔል ጌቱ ወደ አውሮፓ እንዳትገባ እገዳ ሊጣልባት ነው።

ድምፃዊቷ 'ጥሎብኝ' በተሰኝ ነጠላ ዜማዋ ተወዳጅነትን ያተረፋች ሲሆን ከዛ በፊትም የ የኛ ሙዚቃ ቡድን ውስጥ ትታወቃለች።

ራሔል በሀገር ውስጥ የተለያዩ ኮንሰርቶች ከሰራች በኃላ ከኢትዮጵያ ወጥታ ወደ አውሮፓ በመጓዝ ስራዎቿን አቅርባለች። ድምፃዊቷ ከአውሮፓ ወደ ሐገር ውስጥ ስትመለስ ከተሰጣት የቪቫ ቀን አስልፋ ማለትም አውሮፓ ውስጥ መቆየት ከተፋቀደላት ጊዜ በላይ ቆይታ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰችው ይላል የኢትዮፒካሊንክ ዘገባ።

በዚህም መሰረት ራሔል ከተሰጣት አሳልፋ የቆየችበት በቂ ምክንያት እስካላቀረበች ድረስ ከዚህ በኃላ ወደ አውሮፓ እንዳትገባ እግድ ሊጣልባት ይችላል።

Via:- ዳሰሳ አዲስ
@Yenetube @Fikerassefa
አቶ እርስቱ ይርዳው ከጉራጌ ዞን ማህበረሰብ ጋር ለመወያየት አገና ከተማ ተገኝተዋል!

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከዞኑ ተወላጆችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመምከር በጉራጌ ዞን አገና ከተማ ላይ ተገኝተዋል፡፡መድረኩ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በዚሁ ጊዜ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት ከዚህ በፊት በአገራችን የነበረውን ኢፍትሀዊነት ለማስቀረት የጉራጌ ህዝብ ለዓመታት ትግል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በሀገሪቱ የተጀመረው ለውጥ እውን እንዲሆን በርካታ ወጣቶች የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን የተናገሩት አቶ መሀመድ የጉራጌ ህዝብ ከተፈጠረው ለውጥ ጎን በመሆን ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ለህዝቦች ፍትህና እኩልነት ያደረገው ትግል ቀላል አይደለም ብለዋል፡፡እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለፃ የለውጡ መሪዎች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ሀገር እንዲተራመስ እና ለውጡ እንዲቀለበስ ሌት ተቀን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት አላማቸው እንዳይሳካ በማድረግ ረገድ የዞኑ ህዝብ ሚናው ከፍተኛ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ: የደቡብ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለ29ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ ሰራዊት አባላት ዛሬ እያስመረቀ ነው።

የፖሊስ ሰራዊት አባላቱ በአርሲ ዞን ዶደታ ወረዳ አዋሽ ቢሸላ ማሰልጠኛ ማእከል ለአምስት ወር የተሰጣቸውን ስልጠና ያጠናቀቁ ናቸው።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስለ ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ በመወያየት ላይ ናቸው።
@Yenetube @Fikerassefa
የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን አሸኛኘት ተደረገላቸው::

ሚኒስትሩ አሸኛኘት የተደረገላቸው በአዲስ አበባ ከተማ ሽሮ ሜዳ አካባቢየሚገኘውን ብራይት ስታር የበጎ አድራጎት ድርጅትን ከኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ከሌሎች ሚኒስትሮች ጋር በመሆን በጎበኙበት ወቅት ነው::ዶ/ር አሚር አማን የተዘጋጀላቸውን ስጦታም ከኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተቀብለዋል::ዶ/ር አሚር የስራ መልቀቂያ ጥያቄ አቅርበው ጥያቄቸው ተቀባይነት ማግኘቱ የሚታወስ ነው።

Via Addis TV
@YeneTube @FikerAssefa
የሳተላይቷ ወግ ከፍትህ መጽሄት በአለማየው ገላጋይ | ፍትህ ጋዜጣ

https://www.youtube.com/watch?v=j3UZ4nn23Fs
ስለ የኔቲዩብ አስፈላጊ መረጃዎች ⬆️
-91588 member
-222000 view per day
- 80483445 view
- 36.51 Citation
- 12.8% Engagement
በአዲስ አበባ ከተማ 8 ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮች በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሊገነቡ ነው።

ኢ/ር ታከለ ኡማ በመጪው ሳምንት ጎተራ አካባቢ ግንባታው የሚጀመረውን እና አፋር መንደር የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮጀክት ላይ ያለውን ዝግጅት ተመልክተዋል።የአፋር ተወላጅ በሆኑ ባለሀብቶች በጎተራ አካባቢ የሚገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የግል ይዞታቸው በሆነ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው።መኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶችንና አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ያካተተ ነው።

ከዚህ ቀደም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በቻይና ኩባንያዎች የሚገነቡ ሁለት ግዙፍ የመኖሪያ መንደሮች ይፉ መደረጋቸው ይታወቃል።ከዚህ ጎን ለጎንም የመኖሪያ መንደር ግንባታዎቹ ላይ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች እየተሳፋ ይገኛሉ።ይህን አፋር መንደር የተባለ ስያሜ የተሰጠውን መንደር ጨምሮ 8 የመኖሪያ መንደሮች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በቅርብ ጊዜያት ይጀመራሉ።እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን ከማበረታታት ባሻገር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ያለሙ ናቸው።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ተፈራ እና የከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እዮብ አቤቶ በጋራ በሰጡት መግለጫ ዓመታዊዉ የቅዱስ ገብርኤል በዓል ከዋዜማው ጅምሮ ያለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩን ገልፀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
⚽️ የእግር ኳስ ውርርዶችን ከኛ ጋር ያሸንፉ!⚽️

ከሀገር ዉጪ በመወራረድ ብዙ ብር ካተረፉ የእግር ኳስ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር እጅግ አስተማማኝ የሆኑትን የቀኑን ምርጥ የ እግር ኴስ ቅድመ ጨዋታ ውጤቶችን ለናንተ እናደርሳለን::

ውጤቶቻችን በባለሙያዎች የተመረጡ ስለሆኑ በራስ መተማመናችን የላቀ ነው::

ስለዚህም ከኛ ጋር ብዙ አትራፊ ይሁኑ እንልዎታለን::

T.me/oddcrackerET
T.me/oddcrackerET
ባንኮች የገጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ለማቃለል ብሄራዊ ባንክ 5.5 ቢሊየን ብር ሊያበድራቸው ነው፡፡

ዛሬ ለህትመት የበቃችው የእንግሊዘኛዋ ፎርቹን ጋዜጣ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ባንኮች የገጠማቸውን የገንዘብ እጥረት ለማቃለል ብሄራዊ ባንክ 5.5 ቢሊየን ብር በጨረታ ሊያበድራቸው መሆኑን በፊት ገጿ አስነብባለች፡፡ በጉዳዩ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ካፒታል ጋዜጣ ግዙፉ መንግስታዊ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ በሁሉም የገንዘብ ተቋማት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ዕጥረት መከሰቱን እና ያንን ተከትሎ ባንኮቹ ባልተለመደ ሁኔታ የተቀማጭ ሂሳባቸውን ለማሳደግ አቅም አላቸው የተባሉ አካላትን በማግባባት ላይ ናቸው ስትል መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡

ወቅቱ የኮርፖሬት ግብር መክፈያ እንዲሁም ባንኮች ራሳቸው ለባለ አክሲዮኖቻቸው የትርፍ ክፍፍል እና የታክስ ክፍያ የሚፈፅሙበት በመሆኑ እንዲህ አይነት የገንዘብ ዕጥረት ሊከሰት እንደቻለ ጋዜጦቹ ያነጋገሯቸው የባንክ ኃላፊዎች አስረድተዋል፡፡

አሁን ቀረበ የተባለው 5.5 ቢሊየን ብር ይህንን እጥረት የሚያቃልል እንደሚሆን ተስፋ ተደርጓል፡፡

via:- Sheger Times
@Yenetube @Fikerassefa
የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የሽብር ጥቃት በማውገዝ አገሪቷን ለማረጋጋት የሚያደርገን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

ትላንት በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሰዎች ለስራ በሚሯሯጡበት ማለዳ መኪና ላይ በተጠመደ ቦንብ በደረሰ የሽብር ጥቃት የ76 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ90 በላይ ሰዎች ትመቁሰላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

via- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
የዓመቱ ታህሳስ 19 ቀን የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ዛሬ በደማቅ ስነ ስርዓትና በሰላም መከበሩን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

@Yenetube @Fikerassefa
#ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች ሞጣ ከተማ በመገኘት ባለፈው ሳምንት ጥቃት የደረሰባቸውን የእምነት ተቋማት እና የንግድ ቤቶች ጎበኙ።

ጉብኝቱን ያደረጉት የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ እና የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ከውሰር እድሪስ ከአካባቢው የኢዜማ አደራጆች ጋር በጋራ በመሆን ነው።

በጉብኝቱ ወቅት አመራሮቹ በእምነት ተቋማት ላይ እና በንጹሃን ዜጎች ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው ድርጊቱን አውግዘዋል። ከፍተኛ አመራሮቹ ከተማዋን ለማረጋጋት እና የሃይማኖት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት ከተዋቀረው ኮሚቴ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ ላይ ተገኝተው የነበሩ የአካባቢው ባለሃብቶች ለመልሶ ግንባታ የሚሆን እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

የከተማው ወጣት በወንድማማችነት ሰላሙን እንዲያስከብር፣ ጥቃቱን ያደረሱ ሰዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የእምነት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት ሁሉም ማኅበረሰብ የተቻለውን እንዲያግዝ ኢዜማ መልዕክት እንዲያስተላለፍ ከኮሚቴው የቀረበውን ጥያቄ አመራሮቹ በሙሉ ልብ ተቀብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነዉ ጉዳት ለደረሰበት ለሞጣ ቅድስ ጊዮርጊስ 2 ሚሊዮንና ለመስጊዶች ደግሞ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ቃል ገቡ። ቃል የገቡትን ማክሰኞ እንደሚያስገቡ ተናግረዋል።

Via:- AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
"የኢትዮጵያዊያን የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ እየተደረገ ላለው የሶሻል ሚዲያ ካምፔን ሁላችሁንም ላመሰግን ወዳለው"

የተከበራችሁ!,ድምፃችን እንዲሰማ ከጎናችን ሁኑ 🙏

Via:- Loza Abera | ጀግኒት
@Yenetube @Fikerassefa