YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አዲሱ ኤክሳይስ ታክስ ንድፈ መመርያ በመኪኖች ላይ እሰከ 500 %በምግብና መጦች ላይ ደግሞ እሰከ 50% ታክስ ለመጣል አቅዷል።

ለተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበው አዲሱ ኤክሳይስ ታክስ ከሰባት አመት በላይ ያገለገሉ መኪኖችን 500% ፣ ከአንድ አስከ አራት አመት ያገለገሉትን መኪኖች ከ 100 አስከ 150 % ፣መገጣጠሚያቸው ከውጭ የሚመጣ ወይንም እዚህ የሆነ መኪኖችን 100% ታክስ ለመጣል አቅዷል። በለስላሳና መጠጦች ላይ 25% በታሸጉና በጣፋጭ ብስኩቶችና ምግቦች ላይ ከ20 አስከ 50 % ኤክሳይስ ታክስ ለመጣል አቅዷል።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በዚህ ዓመት የሚሰጠው 12ኛ ክፍል ላይ ብቻ ነው | EBC

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ አስቀድሞ ቢነገርም አንዳንድ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለ10ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎችን እያዘጋጁ መሆኑን መረጃ እየደረሰው ነው፡፡

የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ለኢቲቪ እንደገለፁት ለአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ዝግጅት ማድረግ እንደማይገባ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች መደበኛ የክፍል ፈተና ብቻ እንደሚፈተኑ ለማስታወስ ለሁሉም ክልሎች ተቋሙ ድብዳቤ ፅፏል ብለዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ብሄራዊ ፈተና የሚወስደው 12ኛ ክፍል ላይ መሆኑን ተማሪዎችም ወላጆችም ሆነ ትምህርት ቤቶች ሊያውቁት እንደሚገባ አቶ አርአያ ተናግረዋል።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን ከቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ከወዳደቁ የፕላስቲክ ዕቃዎች ጋር በማደባለቅ ከገብረ ጉራቻ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

(አብመድ)
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ለኹለት የሥራ ኃላፊዎች የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጠ። የሥራ ኃላፊዎቹ በማረሚያ ቤት ፖሊስነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሲሆኑ ማረሚያ ቤት ኮሚሽኑ ለምክትል ኮሚሽነር ውቤ ወንዴ እና ለኮማንደር አማረ ወርቁ ነው የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ የተሰጠው።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የተለያዩ የባህር ዳር ዩንቨርስቲ የፓሊ ከምፓስ ተማሪዎች የግቢው በር ዝግ በመሆኑ መቸገራቸውን ለየኔቲዩብ አቤቱታቸውን ገልፀዋል።

ነገሩ እንዲህ ነው ዛሬ በዩንቨርስቲው የምግብ አገልግሎት እንዳልነበረ እንዲሁም የግቢው መግቢያ እና መውጪያ በሮች ዝግ መሆናቸውን በተጨማሪ ግቢ ውስጥ ያሉ አገልግሎት የሚሰጡ የATM ማሽኖች ዝግ መሆናቸው የተማሪዎች ብር አውጥተው ለመመገብም እንደተቸገሩ ገልፀዋል ለ የኔቲዩብ።

ሆኖም ግን ከ11 ሰዐት ብኃል በሮች ተከፍተው ተማሪዎች መግባት መውጣት ችለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ታስረው የነበሩ 1 ሺህ 443 ስደተኞችን ከሀገሪቱ ሊመልስ መሆኑን በፉስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ ለዚሁ ተግባር አውሮፓ ኅብረት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫ ኪር እና የተቀዋሚዎች መሪ ሬክ ማቻር የአንድነት ሽግግር መንግሥት ለማቋቋም ዛሬ መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በሚያለያዩዋቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ግን አሁንም ከስምምነት አልደረሱም፡፡ ቀደም ሲል የኅዳሩን ቀነ ገደብ በ100 ቀናት አራዝመውት ነበር፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ አሰሪዋን በመግደል እና በስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ኹለት ክስ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣች፡፡

Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
ለ90 ሺህ ኢትዮጵያዊያን እና ስደተኞች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለመፍጠር እንዲሁም ለ20 ሺህ ስደተኞች እና ኢትዮጵያዊያን ጥራት እና ተቀባይነት ያለው የክህሎት ስልጠና ለመስጠት መታቀዱን የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

Via:- ፋና ብሮድካስቲንግ
@Yenetube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ለኹለት የሥራ ኃላፊዎች የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጠ።

የሥራ ኃላፊዎቹ በማረሚያ ቤት ፖሊስነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሲሆኑ ማረሚያ ቤት ኮሚሽኑ ለምክትል ኮሚሽነር ውቤ ወንዴ እና ለኮማንደር አማረ ወርቁ ነው የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ የተሰጠው።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
በአማራና ኦሮሚያም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ዋነኛ ምክንያት የፖለቲካ ልሂቃን የሚፈጥሩት ያልተገባ ፉክክር ነው ሲሉ አክቲቪስት #ጃዋር_መሃመድ አስታወቁ።

@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የፀጥታ ሃይሎችን በልዩ ሁኔታ መድቤአለሁ አለ፡፡

የፀጥታ ኃይሎች በሌሎችም ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ይመደባሉ ተብሏል፡፡

Via:- Shager fM
@Yenetube @FikerAssefa
በምርጫ ወቅት የተሳሳተና የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ!

በምርጫ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ የተሳሳተ እና የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡የጋራ እሴቶችን ለማደናቀፍ ሆን ብለው ጥላቻንና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያሰራጩ አካላት ከወዲሁ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ተብሏል፡፡አዋጁ ጸድቆ ወደ ስራ ሲገባ ከምርጫ ጋር ብቻም ሳይሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ ውስጥ በሚኖሩ ጉዳዮች ላይ በሙሉ ተፈጻሚ የሚሆንበት ሂደት መኖሩን የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚዩንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

የማህበራዊ ሚዲያዎችን ከሚያስተዳድሩ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ጥናት ሲካሄድ መቆየቱን የገለጹት አቶ ዝናቡ አዋጁ ሲጸድቅ ህጉን ተላልፈዉ የተገኙ አካላት ላይ ተገቢና አስተማሪ የሆነ የቅጣት እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡በችግሩ ውሰጥ የሚገኙ አካላትም ከወዲሁ ከድርግታቸዉ እንዲቆጠቡና ራሳቸዉን ቆም ብለዉ በማየት ማስተካከል አለባቸዉ የሚል ምክረ ሀሳብ አቶ ዝናቡ አቅርበዋል፡፡የተሳሳቱ መረጃዎችን በማውጣት የህዝብን አንድነት፤ ሰላም፤ አጠቃላይ የሀገሪቷን ሉዓላዊነት ሊያዳናቅፍ የሚችል፤ ለብጥብጥና መሰል ጉዳዮች ሊያነሳሱ የሚችሉ አደገኛ የሆኑ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍም እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

የህግ ማዕቀፉ ዋነኛው ዓለማ ሰብዓዊ ክብርን የሚገረስሱ፣ ሆን ተብለዉ በዜጎች ላይ ወይም ቡድኖች ላይ ጥላቻና ሀሰተኛ ንግግሮችን በማሰራጨት አጠቃላይ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መረጋጋት፤ ሀገራዊ አንድነት ሰብዓዊ ክብርን፤ ከምንም በላይ ደግሞ ለብዘኃነትና ለእኩልነት ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን ለመከላከል ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጃ መሆኑንም ተገልጿል፡፡ረቂቅ አዋጁ በርካታ ባለድርሻ አካላት ውይይት ከደረጉበት በኋላ በቅርቡ ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ይታወሳል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታ አል-ሲሲ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ላለው ግድብ አለመግባባት ጦርነት መፍትሄ አይሆንም አሉ!

አል-ሲሲ በግብጿ የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው ሻርመ ኤል ሼህ ከተማ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ በግድቡ ዙሪያ በቀጣይ ወር የአሜሪካ ተወካዮች በሚገኙበት በዋሽንግተኑ ስብሰባ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ነው ትኩረት መሰጠት ያለበት ብለዋል።

"ያሉን ውስን ሃብቶች በጦርነት እና በግጭት መባከን የለባቸውም። ህዝቡን እና ሃገራችንን ለማልማት ልንጠቀምበት ይገባል"

ጦርነት መልስ አይሆንም የሚለው የአል-ሲሲ ንግግር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ፓርላማ ላይ ለተደረገው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ንግግር ምላሽ የሰጡ ይመስላል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥቅምት 11፣ 2012 ዓ. ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ "የማንንም ፍላጎት ለመጉዳት የጀመርነው ፕሮጀክት አይደለም" ያሉ ሲሆን፤ "ቁጭ ብለን እናወራለን፤ ማንም ይህንን ግንባታ ማስቆም አይችልም። ይህ ሊሰመርበት ይገባል" ብለው ነበር።

በወቅቱ ከግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚሰነዘሩ የጦርነት እንከፍታለን መልዕክቶችን አስመልክተው ሲናገሩ፤ "ማንንም አይጠቅምም [ጦርነት] ብለን እናምናለን . . . ጦርነትም ከሆነ ኢትዮጵያ ብዙ ሕዝብ አላት፤ በሚሊዮን ማሰለፍ እንችላለን" ማለታቸው ይታወሳል።

Via:- BBC News Amharic
@yenetube @Fikerassefa
የሳዑዲ አረቢያ የንግድ ተልዕኮ በኢትዮጵያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ።

በርካታ የሳዑዲ ዐረቢያ የንግድ ማሕበረሰብ የተሳተፉበት የሳኡዲ ዐረቢያ የወጪ ንግድ ልማት የንግድ ተልዕኮ በኢትዮጵያ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተካሄደ።በመርሃ ግብሩ ላይ ከኢትዮጵያም ወገንም የተለያዩ የንግዱ ማህበረሰብ እና ባለ ድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትና ዘርፍ ማህበራት ፕሬዘዳንት መሰንበት ሸንቁጤ መርሀ ግብሩን በንግግር ከፍተዋል። በኢትዮጵያ የሳኡዲ አምባሳደር ሳሚ ጃሚል በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለንግድ ደህንነት ማረጋገጫ ሊሰጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የውኃና የለስላሳ መጠጥ አምራቾች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቃውሞ ደብዳቤ አቀረቡ!

በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረበ አንድ ሳምንት ያሳለፈውን የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የተቃወሙ የውኃና ለስላሳ መጠጥ አምራቾች፣ ተቃውሞአቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቀረቡ፡፡አምራቾቹ ተቃውሞአቸውን ያቀረቡት በኢትዮጵያ የታሸገ ውኃና ለስላሳ መጠጦች አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር አማካይነት ነው፡፡

https://telegra.ph/complaint-12-18
ለሰራተኞች በሚከፈል ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማነስ ምክንያት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ ፡፡

ለሰራተኞች በሚከፈል ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማነስ ምክንያት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ሊዘጋ እንደሚችል የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ልማት ፓርክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሕመድ ሰይድ ገልጸዋል ፡፡ፓርኩ 2147 ሰራተኞችን ያቀፈ ሲሆን ፣ በአንደኛው ሩብ አመት 628 ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ 579 የሚሆኑ ወጣቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ይሁን እንጂ በደመወዝ ማነስና ተያያዥ ምክንያቶች በሩብ አመቱ 526 ቱ ፓርኩን ለቀው እንደወጡ ኃላፊው አክለዋል ፡፡

የችግሩ አሳሳቢነት ፓርኩን ሊያዘጋው እንደሚችልና በፍጥነት የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማሻሻያ ይደረግ ብለን ለሚመለከተው አካል ብናሳዉቅም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል አቶ አህመድ ፡፡ፓርኩ በአንድ አመት ከአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ሰባት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት የተለያዩ ምርቶችን ወደ ዉጭ ኤክስፖርት ማድረግ እንደቻለ አቶ አሕመድ ገልጸዋል ፡፡አንድ የአለቀለት ሙሉ ሱፍ ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ሲወጣ ከ 5 እስከ 8 የአሜሪካን ዶላር እንደሆነ የገለጹት አቶ አህመድ ፣ በአለም ገበያ ግን ከ 300 እስከ 1700 የአሜሪካን ዶላር እንደሚሸጥ ጠቅሰዋል፡፡
እንዲህ አይነት አሰራሮችን ፓርኩን ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረጉት ስለሚገኙ እንዲቆሙ የሚመለከተው አካል ሊሰራበት ይገባል ብለዋል አቶ አህመድ፡፡

ይህ የተገለጸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለበትን ሁኔታ ለመመልከትና ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የገቡ አምራች ኩባንያዎች አፈጻጸማቸውን ከማሳደግ አኳያ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ነው ፡፡የኤክስፖርት አፈጻጸሙ የተሻለ መሆኑ ፣ ኤክፖርት ተኮር ምርቶች መመረታቸው ፣ የፓርኩን ደህንነት ለመጠበቅ ጥብቅ ክትትል መደረጉ ፣ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋራ ስራዎች በጋራ እየተሰሩ መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ ከገለጻቸው መካከል ተጠቃሾች ናቸው ፡፡

ቋሚ ኮሚቴ የቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር ፣ የስራ እድል ፈጠራ አነስተኛ መሆኑ ፣ የሰራተኞች የቤት ግንባታ መጓተትን በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ ጠቁሟል ፡፡የስራ ኃላፊዎቹ በበኩላቸው በቋሚ ኮሚቴው በኩል የተገለጹላቸውን አስተያየቶች ተቀብለው በትኩረት እንደሚሰሩባቸው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ: የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ እየተሰራ ያለው ባለ 8 ፎቅ እና 450 መኝታ የእናቶችና ህፃናት ማዕከል ግንባታ መጠናቀቁን እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተመርቆ ስራ እንደሚጀምር የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን አስታወቁ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa