ታዋቂው ፎርብስ መፅሔት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ከዓለማችን 100 ተፅእኖ ፈጣሪ ሴቶች አንዷ አድርጎ መረጠ፡፡
ፕሬዝዳንቷ በ2019 የአፍሪካ ብቸኛዋ ተመራጭ ናቸው፡፡መፅሔቱ ለያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ባወጣው የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅን በ93ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡መፅሔቱ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በአፍሪካ ብቸኛዋ በስልጣን ላይ ያሉ ሴት የአገር መሪ እንደሆኑ አስፍሯል፡፡
ፕሬዝዳንቷ ወደዚህ ታላቅ ኃላፊነት በተሾሙ ጊዜ ለህዝብ እንደራሴዎች ባደረጉት ንግግር የሴቶች ድምፅ ለመሆን ቃል መግባታቸውንና የአንድነትን አስፈላጊነት አስረግጠው መናገራቸውን መፅሔቱ አስታውሷል፡፡የጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ መርክል፣ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ መሪ ክርስቲያን ላጋርድ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴት ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ እንደያዙ መረጃው አመልክቷል፡፡
Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa

የሰው መግደል ወንጀል የፈፀመው የፖሊስ አባል ጽኑ እስራት ተፈረደበት!
የትራፊክ አባሎች ቁም ሲሉት እንቢ ብሏል በሚል ምክንያት በቦሌ ክፍል ከተማ ወረዳ 07 አካባቢ የሰው መግደል ወንጀል የፈጸመው የፖሊስ አባል ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ተከሳሽ ም/ሳጅን ታዘባቸው ንጋቱ የፖሊስ አባልት መተዳደሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 268/2005 አንቀጽ 3/2፣ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 539/1/ሀ ስራ ላይ የተመለከተዉን በመተላለፍ በሌላ የክስ ጉዳያቸው በመታየት ላይ ካሉት ሶስት ተከሳሾች ጋር በመሆን ተከሳሽ የፖሊስ ሰራዊት እንደመሆ የሌለውን ሰው ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እያለበት ስራውንም በማስተዋል፣ በትህትና እና በታጋሽነት ማከናወን እንዲሁም ከሀይል አጠቃቀም እንጻር የተለየ እንቢተኝነት ያላሳየውን ሟች ከሕግ ተገዢ እናደርጋለን በሚል ሰውን ለመጉዳት ፍፁም ፈቃደኛ በመሆን ጨካኝነቱን፣ ነውረኝነቱን እና አደጋኛነቱን በሚያሳይ ሁኔታ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል፡፡
ተከሳሽ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው አለማየሁ ህንጻ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሟች ወጣት ሮቤልን ጃካሮስ አደባባይ ለመንገድ ስራ ተዘግቶ የነበረን መንገድ ሟች በሚያሽከረክረው መኪና ጥሶ አልፏል የትራፊክ አባሎች ቁም ሲሉት እንቢ ብሎ አምልጧል በሚል ምክንያት ኮ/ብል ከፍያለው ደምሴ እና ኮ/ብል አብረሀም በቀለ የተባሉት በያዙት የጦር መሳሪያ ጀርባውን ደጋግመው ሲመቱት ኮ/ብል ላቃቸው ባምላክ የተባለውን በዱላ እና በጫማ በመረጋገጥ በጭቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ ተከሳሽ በወንጀል ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን በዋና ወንጅል አድራጊነት በፈጸመው ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅርቡን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽ በፈፀመዉ ወንጀል ተጠያቂ መሆን የሚችልበትን በፖሊስ የምርምራ መዝገብ መሰረት የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎችን በመያዝ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል::ተከሳሽ በሌለበት ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል:: የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን በማቅለያ በመቀበል በ20 ዓመት ጽኑ እስራት አንዲቀጣ ሲል ወስኗል::
Via Attorney General

ምርጫ 2012 በስኬት ለማጠናቀቅ የምርጫ ቦርድ ውዝፍ ስራዎች በፍጥነት እንዲያከናውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ፡፡
ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንዲደረግ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፅኑ ፍላጎት እንዳለው የገለፁት የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ፤ ኦነግ ለምርጫው አስፈላጊው ዝግጅት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ቀጀላ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ 2012 ራሱን በፍጥነት ማደራጀት እና ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ኮንግረስ ሊቀ-መንበር አቶ ገረሱ ገሳ በበኩላቸው፤ ምርጫ 2012 ሀገሪቱ አሁን ባለችበት ሁኔታ ይደረጋል ወይ የሚለው ጉዳይ ጥያቄ እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማከናወን ትክክለኛ አቋም ላይ አደለም የሚሉት አቶ ገረሱ፤ ለዚህም ቦርዱ የዞን እና የወረዳ ጽ/ቤቶችን እስካሁን አለማደራጀቱን በማስረጃነት ይጠቅሳሉ፡፡
ምርጫውን ለማከናወን ገለልተኛ ተቋማትም ማጠናከር ጊዜ የማይሰጠው ተግባር ነው ያሉት የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ስብሰቢ አቶ ናትናኤል ፈለቀ፤ ምርጫ ቦርድ ከቀረው አጭር ጊዜ አንፃር ራሱን ማደራጀት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
አክለውም ምርጫ ቦርድ ለምርጫ በቀረው አጭር ጊዜ ውስጥ እራሱን ያደራጃል ብለው እንደማያምኑም ገልፀዋል፡፡
በመንግስት በኩል ምርጫውን ለማድረግ እቅድ ቢያዝም የምርጫው መደረግ እና አለመደረግ ግን ፓርቲዎችን ለሁለት ክፍሎ እያወዘገበ ይገኛል፡፡
Via:- አሐዱ ሬዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ እና የህንድ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች አብረው መስራት የሚያስቻላቸውን ጥምረት ተመሰረተ። ባለፉት 5 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል፡፡
Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
የኦሮሞ እና የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች በክልሎቹ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች በተፈጠሩ ችግሮች የመፍትሔ አካል ለመሆን ውይይት እያካሄዱ ነው።
Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ከጃፓን መንግሥት ጋር የ12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር የዕርዳታ ስምምነት ተፈራረመች። የተገኘው ዕርዳታም በአዲስ አበባ ከተማ ለሚደረጉ የመንገድ ግንባታዎች እና ጥገናዎች እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል።
Via:-አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
Via:-አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ 59 ነጥብ 5 ከመቶ የሚሆኑት ስልክ ቁጥርን እንደ ይለፍ ቃል ይጠቀማሉ!
በኢትዮጵያ ካሉ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ውስጥ 59 ነጥብ 5 ከመቶ የሚሆኑት ስልክ ቁጥርን እንደ ይለፍ-ቃል /password/ እንደሚጠቀሙ ጥናት አመለከተ። ተጠቃሚዎች የስልክ ቁጥርን መጠቀማቸው ጠንካራ የይለፍ-ቃል እንደተጠቀሙ እንደሚሰማቸውም በጥናቱ ተመላክቷል።በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ መጠን እያደገ መምጣቱም ነው የተነገረው።
በኢትዮጵያ ያለው በሳይበር ደህንነት የግንዛቤ መጠንም ዝቅተኛ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ ጥናት ያመለክታለል።ኤጀንሲው በ2011 ዓ.ም 1 ሺህ 635 የሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ሀገር-አቀፍ የሳይበር ደህንነት ምዘና ጥናት አከናውኗል።በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል 975 (59 ነጥብ 5 በመቶ) ያክሉ ስልክ ቁጥርን እንደ ይለፍ-ቃል/password/ በመጠቀም ጠንካራ የይለፍ-ቃል እንደተጠቀሙ እንደሚሰማቸው ጥናቱ ያመለክታል።
በተጨማሪም 59 ነጥብ 1 በመቶ ያክሉ የጥናቱ ተሳታፊዎች የይለፍ ቃሎቻቸውን የሚታይ ቦታ ላይ ጽፈው ማስቀመጥን እንደ ማስታወሻ መንገድ እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል።67 ነጥብ 6 ከመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክለኛ ናቸው ብለው እንደሚያምኑም ነው የተነገረው።በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ጉዳይ በቸልታ ሊታለፍ የማይገባውና የለት ተለት የህይወታችን አካል እየሆነ በመምጣቱ ተገቢውን ትኩረትና ጥናቃቄ ልናደርግ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ የሰራውን ጥናት አስመልክቶ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
Via FBC

በደቡብ ከልል የዎላይታ ሶዶ ከተማ ሴቶች "የዎላይታ ህዝብ በክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ይሰጠው" ሲሉ ዛሬ አደባባይ ወጡ።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የቀድሞው የሱማሌ ክልል ደኅንነት ሃላፊ ኮሎኔል ሙክታር ሙሐመድ ሱባኔ ሐርጌሳ ላይ መያዙን ሆርን ዲፕሎማት ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡ ሙክታር በቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ ዘመን፣ በንጹሃን ላይ ግርፋት እና ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶችን በመፈጸም እና በማስፈጸም ይጠረጠራል፡፡ በዚሁ ወንጀልም በፖሊስ ሲፈለግ የነበረ ነው፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትግራይ እና አማራ ብሎም የኦሮሞ እና አማራ መሪዎች እንዲነጋገሩ ማስቻል አለባቸው (አይሲጄ)
ዐለም ዐቀፉ የግጭት አጥኝ ቡድን (አይሲጄ) ባወጣው ዘለግ ያለ ሪፖርት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትግራይ እና አማራ ብሎም የኦሮሞ እና አማራ መሪዎች እንዲነጋገሩ ማስቻል አለባቸው፤ ከኦዴፓ አፈንጋጭ ጓዶቻቸውም ጋር መነጋገር አለባቸው ሲል አሳስቧል፡፡ ዐቢይ ለሕወሃት አቀራረባቸውን ይቀይሩ፣ ከምርጫው በፊትም ከሁሉም ፖለቲከኞች እና ሲቪል ማኅበራት ጋር ሰፊ ውይይት ይጀምሩ ሲል መክሯል፡፡
አጋር ሀገራት የኢሕአዴግ አወቃቀር ለውጥ በጥንቃቄ እንዲያዝ እና ፖለቲከኞች ግጭት ቀስቃሽ ንግግር እንዲቆጠቡ ከጀርባ ማግባባት አለባቸው፡፡
Via:- Wazema

የኢትዮጵያ የባህል ቡድን አስመራ ኤርፖርት ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።
በኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የተመራው የአገራችን የባህል ቡድን ዛሬ ታህሳስ 6 ቀን 2012 ዓም ከስዓት በኋላ አስመራ ገብቷል።ቡድኑ አስመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በኤርትራ የባህል እና ስፖርት ኮምሽነር አምባሳደር ዘመዴ ተክሌ፣ በኤርትራ የኢፌዲሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ በአፍሪካ ህብረት የኤርትራ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር አርዓያ ደስታ፣ ታዋቂ የኤርትራ አርቲስቶች፣ የኤርትራ የሴቶች ማህበር እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።ከ60 በላይ አባላትን የያዘው የባህል ቡድን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ድምጻዊያንና የጃኖ ባንድ የተካተቱበት ሲሆን ለአንድ ሳምንት በኤርትራ ይቆያል።
ምንጭ: ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ማምረቱን ከጥር ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማቆሙን አስታወቀ። ከኢትዮጵያው አደጋ በኋላ የታገደው 737 ማክስ በአሜሪካ ፌድራል የበረራ መቆጣጠሪያ ባለሥልጣንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የደህንነት ማረጋገጫ እየጠበቀ ነው።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ምክር ቤቱ ዛሬ በሚያደርገው ውይይት የኢንቨስትመንት፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ስለማዛወር እና የኤክሳይዝ ታክስ ላይ የቀረቡ ሶስት ረቂቅ አዋጆች መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የዛምቢያው ፕሬዝዳንት በሀገራቸው ያሉት የአሜሪካ አምባሰደር ግብረሰዶማውያንን በመደገፋቸው ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አደረጉ
ባለፈው ወር በዛምቢያ በግብረ ሰዶም ወንጀል ተከስው ወደወህኔ ያመሩትን ሁለት ወንዶች ፍርድን በመቃወም " ፍርዱን ስሰማ ደንግጫለው ፣ዛምቢያ በግብረሰዶም ላይ ያላትን ህግ ልትፈትሽ ይገባል" ያሉትን በዛምቢያ የአሜሪካ አምባደርን ዳንኤል ፉትን የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ኤድጋር ቻጋር ሉውንጉ ከስካይ ቲቪ ጋር ባለፈው እሁድ ባደረጉት ቃለ ምልልስ "ሀገራችንን ለቆ እንዲወጣ አዘነዋል ።እንዲህ አይነት ሰው በሀገራችን እንዲኖር አንፈቅድም" ብለዋል።
Via :- Tesfay Getnet

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ብዛቱ 250፣4753 የብሬን ጥይት፣32 ክላሽ ፣ 2053 የክላሽ ጥይት በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብራሃጅራ ከተማ በትላንትናው ዕለት የተያዘ ሲሆን የጸጥታ ኃይላችን ቁርጠኝነት የተሞላበት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
ምንጭ: ከአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስድስት ወራት ውስጥ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በስርቆት እንደወደመበት ገለፀ
ከግንቦት 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች በትራንፎርመር፣በኤሌክትረክ ገመድ እና በታውሮች ላይ በተፈፀመበት ስርቆት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተዘረፈ የአገልግሎቱ የኮርፖሬት ከሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለአሐዱ ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ እና ዙሪያው በተከሰተው የኤሌክትሪክ መስመር ወይም ኬብል ስርቆት ሀገሪቱ ከ6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ማጣቷንም አቶ መላኩ ተናግረዋል፡፡
ይህ የስርቆት ተግባር በመላው ሀገሪቱ ተስፋፍቶ ከ38 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ለኪሳራ እንደተዳረገ አቶ መላኩ ይገልፃሉ፡፡
በመንግስት ላይ ከሚደርሰው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ የኃይል አቅርቦት እንዲስተጓጎል እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች ላይም ከፍተኛ ኪሳራ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

አሰሪዋን የገደለችው የቤት ሰራተኛ በፈፀመችው ወንጀል ጽኑ እስራት ተፈረደባት!
ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ አሰሪዋን በመግደል እና በስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ሁለት ክስ በጽኑ እስራት ተቀጣች፡፡በ1ኛ ክስ ተከሳሽ መሰረት ነገሰ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ከምሽቱ 4 አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው ሉዋም ሱቅ ውስጥ ሟች እርግብ ገ/ክርስቶስ ቤት ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ እየሰራች በነበረችበት ወቅት ለጊዜው ያልተያዘው ግብረአበሯ በተደጋጋሚ ጊዜ ስልክ በመደወል ሟችን በተኛችበት ግደያት በማለት ሲነግራት እሷም በእለቱ ሟች ወደ ተኛችበት ክፍል በመሄድ በብርድ ልብስ አፍና የጉሮሮዋ ቧንቧ እንዲደፈን በማድረግ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጓ በፈጸመችው የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳለች፡፡
በ2ኛ ክስ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ለ) እና 669 (2) (መ) በመተላለፍ ተከሳሽ በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ሟችን ከገደለቻት በኋላ ያልተያዘውን ግብረአበሯ ስልክ በመደወል ጠርታ ወደ ሟች ሱቅ በመግባት 6000 ብር እና ግምቱ ያልታወቀ ገንዘብ እንዲሁም የዋጋ ግምቱ ብር 1650 ብር የሆነ ስልክ ከወሰዱ በኋላ ግብረ አበሯ ለተከሳሽ 2000 እና የሟችን የእጅ ስልክ የሰጣት የወሰደች በመሆኑ በፈጸመችው የግድያና ከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሳለች፡፡ተከሳሽ የዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ተነቦላት እንድትረዳው ከተደረገ በኃላ በ2ቱም ክስ ላይ የተጠቀሱትን ድርጊቶች አልፈፀምኩም በማለት የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታለች፡፡
ዐቃቤ ሕግም እንደክሱ አቀራረብ የምስክሮች ቃል እንዲሳማ ለፍርድ ቤቱ ያመለከተ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽ በቀረበባት 2 ክስ ጥፋተኛ ተባለች::በመጨረሻም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽን የዘወትር ፀባይ መልካም እንደነበር እና የቤተስብን የምትረዳ መሆኑን በማቅለያ በመያዝ በ2ቱ ክስ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል፡፡

የሰው ፀጉር፣ ውዳቂ ዊግ፣ የውሸት ጢም፣ የውሸት ቅንድብ፣ የውሸት ሽፋል እና ሌሎችም አርቴፊሸል ማጌጫዎች ደግሞ 40 በመቶ ቀረጥ እንዲጣልባቸው ተደንግጓል!
ተሻሽሎ ረቂቁ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይዝ ታክስ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍ ያለ ቀረጥ እንዲከፈልባቸው ደንግጓል፡፡
ይህም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለመለዋወጫ አገሪቱን ከሚያስወጧት የውጪ ምንዛሬ ባሻገር ለህብረተሰብ ጤና እክል ይፈጥራሉ፣ ለትራፊክ አደጋም ምክንያት ይሆናሉ በሚል በገፍ ከውጪ እየገቡ ያሉ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ለመግታት ያለመ ነው ተብሏል፡፡የቪዲዮ መቅረጫ፣ ቴሌቪዥን፣ ካሜራ፣ ድምፅ መቅረጫና የሬዲዮ የድምፅ ስርጭት መቀበያ መሳሪያዎች ላይም 10 በመቶ ቀረጥ ተጥሏል፡፡
የሰው ፀጉር፣ ውዳቂ ዊግ፣ የውሸት ጢም፣ የውሸት ቅንድብ፣ የውሸት ሽፋል እና ሌሎችም አርቴፊሸል ማጌጫዎች ደግሞ 40 በመቶ ቀረጥ እንዲጣልባቸው ተደንግጓል፡፡የቅንጦት ዕቃ ተብለውና ለህብረተሰብ ጤናም ጉዳት እንደሚያስከትሉ ታምኖባቸው በተሻሻለው የኤክሳይዝ ታክስ ከተካተቱት መካከል ቴሌቪዥን፣ ስኳር፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ሽቶዎች፣ ወርቅና አልማዝን ጨምሮ ከከበሩ ማዕድናት የተመረቱ ማጌጫዎች፣ ትንባሆ፣ የሲሊንደር ዘይት እና ሌሎችም ተካትተውበታል፡፡ረቂቅ ሕጉ ከመፅደቁ በፊት በዝርዝር እንዲፈተሽ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
Via Sheger