የ13 ዓመቷን ታዳጊ አስገድዶ የደፈረው ተከሳሽ ስምንት ዓመት በፅኑ እስራት ተቀጣ።
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 624 /4/ ሀ እና አንቀፅ 628/ሀ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ አቃቤ ህግ የቂርቆስ ምድብ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ተከሳሽ አብነት ለገሰ በኤሌክትሪክ ስራ የሚተዳደር የ26 አመት ወጣት ሲሆን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ በአንቀፅ 624 /4/ ሀ እና በአንቀፅ 628/ሀ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ እድሜዋ ከ13 አመት በላይ ሆኖ 18 አመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ለመፈፀም በማሰብ፤ መስከረም 30 ቀን 2010ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 4፡00 ሰአት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ማሚ መኪና መሸጫ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ውስጥ በእርሱ ቁጥጥር ስር የምትገኘውን የግል ተበዳይ የሆነችዋን ታዳጊ ልጅ ትወልጅልኛለሽ በማለት የለበሰችውን ልብስ አውልቆ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞባታል፡፡
ተከሳሹ ይህን ድርጊቱን በመቀጠል የግል ተበዳይዋን በተለያዩ ቀናት በተደጋጋሚ የግብረ ስጋ ግንኙነት እየፈፀመባት እንድታረግዝ ካደረጋት በኋላ ፅንሱን እንድታስወርደው በማድረግ የወሊድ መከላከያ ክንዷ ላይ እንዲቀበርላት ያደረገ በመሆኑ ተከሳሹ በፈፀመው እድሜያቸው ከ13 አመት በላይ እና 18 አመት ባልሞላቸው ልጆች ላይ በሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል መከሰሱን አቃቢ ህግ ያቀረበበት የክስ ዝርዝር ያስረዳል፡፡
የክስ መዝገቡ ቀርቦለት ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ በእማኝነት የቀረበበትን የሰው ምስክሮችና የኢግዚቢት ማስረጃን አስመልክቶ ራሱን እንዲከላከል ቢያደርግም ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ተመልክቶ ተከሳሽ አብነት ለገሰ በ8 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
Via:- የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ
@Yenetube @Fikerassefa

የፊታችን እሁድ በጃፓን ካሳማ ከተማ ለጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ በሚካሄደው ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ለመካፈል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ም/ ፕሬዘዳንት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ የተመራ ልኡካን ቡድን ወደ ስፍራው ያቀና ሲሆን የቶኪዮ ኦሎምፒክና ፖራኦሎምፒክ ሚኒስቸር ሚኒስተር ሀሺሚቶ ሴኮ እና በጃፖን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተ/ብርሃን ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በቶኪዮ ኦሎምፒክ እና በሌሎች ጉዳዮች ገንቢ ውይይት ተካሂዷል። በመጨረሻም ክብርት ኮ/ር ደራርቱ አበበ ቢቂላን ለመዘከር በጃፖን መንግስት ውድድር በመዘጋጀቱና ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል በፌዴሬሽናችን ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ምንጭ:EAF
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:EAF
@YeneTube @FikerAssefa
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ጉዳት ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠየቀ!
የመኸር ሰብል በመሰብሰብ ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ አካባቢዎች ገበሬዎች፤ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ከሚያስከትለዉ ችግር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ ። ይሁንና በአገሪቱ የተከሰተው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እየቀነሰ መሆኑን ኤጀንሲዉ ለዶቼ ቬለ «DW» ገልፆአል። በበጋ ወቅትም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሃገሪቱ አንዳንድ ቦታ ላይ ሊከሰት እንደሚችል የብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ የሚትሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ጫሊ ደበሌ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ወቅቱ የበጋ ወራት በመሆኑ ከደቡብ እና ከደቡብ ምስራቅ ቆላማ የሃገሪቱ ክፍል በስተቀር ሌላዉ የሃገሪቱ ክፍል በመደበኛ ሁኔታ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚጠበቅ ተገልጾአል። በአማራ፤ በኦሮምያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምስራቃዊ ክፍል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ አሁንም በደረሱ አልያም ባልተሰበሰቡ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ የሚትሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር ገልፀዋል።
Via DW

Forwarded from YeneTube
🐴ፈረስ የታክሲ አገልግሎት🐴
ኮድ 1 ወይም 3 መኪና ካሎት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አሁኑኑ በነፃ መኪናዎን ያስመዝግቡ።
🎯ቦታችን ጌቱ ኮሜርሻል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።
ይህንን ያውቃሉ? ፈረሰ ኮምሽን የሚወስደው 5% ብቻ ነው፣ ይህም ተመራጭ አድርጎታል።
ለበለጠ መረጃ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@feresapps

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በፌደራል ፖሊስ ለማስጠበቅ በታቀደው መሰረት ስራው እየተካሔደ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
#Visa
ናይጀሪያ ወደ አገሯ ለሚጓዙ ኹሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ መስጠት ልትጀመር መሆኗን አስታውቃለች። የመዳረሻ ቪዛውም በመጪው ጥር ወር እንደሚጀምር ታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ናይጀሪያ ወደ አገሯ ለሚጓዙ ኹሉም የአፍሪካ አገራት ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ መስጠት ልትጀመር መሆኗን አስታውቃለች። የመዳረሻ ቪዛውም በመጪው ጥር ወር እንደሚጀምር ታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሜካኒካል እና በኤሌክትሪካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ተማሪዎችን ተቀብሎ በባህር ላይ በመካኒካል እና በኤሌክትሪካል ምህንድስና ኦፊሰርነት ለስድስት እና ለስምንት ወር ተኩል ያሰለጠናቸውን 43 ባለሙያዎች ዛሬ ታህሳስ 2/2012 አስመረቀ፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የሙዚቀኞች የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ማኅበር መቋቋሙን ሸገር ዘግቧል፡፡ ማኅበሩን ማቋቋም ያስፈለገው ለተለያዩ ተዘማጅ ሙያዎች የተቋቋሙ ማኅበራትን በጋራ ለማስተዳደር ነው፡፡ ማኅበሩ ሮያሊቲ ክፍያዎችን ሰብስቦ ለሙያተኞች ያከፋፍላል፡፡ መንግሥት ቀደም ሲል የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች አዋጅን ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሻደይ አሸንድየ እና ሶለል የተባሉ በክልሉ በሰፊው የሚከበሩ በዓላትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በትጋት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አቀባበል እና የራት ግብዣ ስነ ስርዓት በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት እየተካሄደ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአቅም ግንባታ እና ስልጠና የሚውል 150 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አፅድቋል::
ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የኖቤል የሰላም ሎሬቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ምሽቱን በብሔራዊ ቤተመንግስት በተዘጋጀላቸው አቀባበል እና የእራት ግብዣ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች
• በዚያ ፀሀይ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልኝ ሁሉ ምሥጋናዬ የላቀ ነው
• ለውጡን ጀምረነዋል እንዲቀጥል እጅ ለእጅ መያያዝ ያስፈልገናል
• ከፍቅር ከመስጠት ከይቅርታ የሚጎድል ነገር የለም
• ክቡር ኢሳያስ አፈወርቂን እና የኤርትራን ህዝብ ማመስገን እፈልጋለሁ
• ትናንት እና ከትናንት ወዲያ የማናውቃትን ኢትዮጵያን ለማወቅ ዕድል አግኝተናል
• ምሁራን ስለ አገራችን ታላቅነት ሲናገሩ ሰምተን አገራችንን በሚገባት ልክ እንደማናውቃት አውቀን ተመልሰናል
• ኢትዮጵያ ድንቅ አገር መሆኗ የሚገባን ከኦስሎ በቀጥታ በረን አዲስ አበባ ስንገባ ነው
• ኖርዌይ ከ5 ሚሊዮን ያልበለጠ ህዝብ ያላት ሀገር ናት፤ በዓመት 9 ወር ጭለማ ነው፣ የኛዋ ኢትዮጵያ ደግሞ የ110 ሚሊዮን ህዝብ ሀገር ናት፤ እንደዚያም ሆኖ ግን እኔ እነርሱን ለመንኳቸው፤ በናንተ ስም እነርሱን መለመኔን ሳልደብቅ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፤ መለመን ያሳፍራል
• ከልመና ወጥተን ወደ ብልፅግና እንድንሄድ ከመላው የአፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ህዝቦች ጋር በትብብር መስራት ይኖርብናል፣ ያኔ ምናልባትም ከ10 ዓመታት በኋላ ከልመና እንወጣለን
• ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳችን መናቆርን ትተን ተግተን ብንሰራ የጎደለን ያልተሰጠን ነገር የለም
• ይህን ለማድረግ ሁላችንም ከአሁኑ ሰዓት ጀምረን መስራት ይኖርብናል - እኔም እናንተም፤ አብዝታችሁ አትተኙ፤ የደሃ አገር ህዝብ አብዝቶ መተኛት አይገባውም
• እንደ ኖርዌይ እና ስዊድን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ብዙ አገራት የሉም፤ ይህ የሆነው አንደኛው ለሌላው በመስጠቱ ነው
• ይህ የእኔ ድል እጅግ ደካማ በሆነ ሰው ላይ ያረፈ ድል ነው፤ ለዚህ ድል ከኔ ይልቅ የተሻለ ዕድል የነበራቸው ብዙ ናቸው፤ ወጣቶች የምታገኟቸውን መልካም አጋጣሚዎች ማባከን አይገባችሁም
• አዳዲስ ድል ማስመዝገብ ጀምረናል፣ በቅርቡ የመጀመሪያውን ሳተላይት እናመጥቃለን
• የፖለቲካ ጨዋታን በቦታው ብቻ በመጫወት፤ በስራ ቦታ በጋራ በመስራት አገራችንን እናበልፅግ፣ ከፍ እናድርግ
via:-EBC

የ2019ን የዓለም የ ሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን ወስደው የተመለሱት ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በብሄራዊ ቤተ መንግስት ከተዘጋጀላቸው የእራት ግብዣ በኋላ ከወራት በፊት የተከሏቸውን ችግኞች ውሃ አጠጥተዋል።
@Yenetube @FikerAssefa
@Yenetube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ መስተዳደር" ገንዘብ የለም" በሚል ምክንያት አዲሱ ደሞዝ ማስተካከያ ሙሉውን ለሰራተኞ አልተከፈለም።
አዲሱ ደሞዝ ማስተካከያ ከሀምሌ ወር ጀምሮ ውዝፍ ክፍያው ቢፈፀምም መስተዳደደሩ "በቂ በጀት" የለውም በሚል ምክንያት በወርሀዊ ደሞዝ ላይ ከ1,500 ብር በላይ ጭማሪ ማድረግ አልቻለም ።ይሄም ማለት ለምሳሌ በአዲሱ ደሞዝ ማስተካከያ ከ 1,300 ብር 3,000 ብር ተጨምሮለት 4,300 ብር የገባ ሰራተኛ አየተከፈው ያለው 2,800 ብር ማለት ነው ።መስተዳደሩ ለቀጣይ አመት ይስተካከላል በማለት ለሰራተኞቹ ገልፇል። እንደ ሰራተኞቹ ገለፃ አዲሱ የደሞዝ ማስተካከያ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ዲግሪን ከሰርተክፌት ያሳነሰ ፣አዲስ ቅጥረኛንም በተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ የስራ መስክ ከነባር ሰራተኛ ያሳነሰ ነው በማለት መልክት አድርሰውኛል ሲል ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት በገፁ አስፍራል።

የሐረማያ ዮንቨርስቲ ማስተማር ካቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው የዩኒቨርስቲዉ ሠራተኛ እና ተማሪዎች አስታወቁ ።
«ከተመዘገብን አንስቶ እስካሁን በአግባቡ የተማርነው አንድ ሳምንት ቢሆን ነው» የሚለው አንድ የዩንቨርስቲው ተማሪ በዚሁ መስተጓጎል ምክንያት ወደ ቤተሰቦቹ ከተመለሰ አንድ ወር እንደሆነው ገልፆልናል። በስልክ ያነጋገርናቸዉ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የዩንቨርስቲው ባልደረባ እንደገለፁልን ደግሞ ትምህርት መልሶ ከተጀመረ 10 ቀን ገደማ ቢሆነውም ክፍል የሚገባው ተማሪ ቁጥር በጣም ውስን ነው። ለዚህም ባልደረባው በምክንያትነት የጠቀሱት አንዳንድ ተማሪዎች በድብቅ በሚያሰራጩት የማስፈራሪያ እና የአድማ ወረቀቶች ምክንያት ነው።
«በሐሮማያ ዩንቨርስቲ ግጭት ከተቀሰቀሰ አንስቶ የከፋ ችግር እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ የሰፈረዉ የፌደራል ፖሊስ ቁጥር እንዲጨምር ተደርጓል ፣መከላከያም ገብቷል። የኦሮሚያ አድማ በታኝ እና የዩንቨርስቲው ጥበቃም በግቢው ይገኛሉ» ተብሏል።
በሐረማያ ዮንቨርስቲ ግጭት የተጀመረው ጥቅምት መጨረሻ ወልዲያ ዩንቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች ከመገደላቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ነው።
የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ሰልፍ በመውጣት ወለጋ ላይ የተደነገገዉ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ይነሳ፣ መከላከያ ሠራዊት ከኦሮሚያ ይውጣ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ይውረዱ በሚል የፖለቲካ ጥያቄዎች አንስተው መንግሥት በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ብለው ትምህርት አቁመው እንደነበር የዩንቨርስቲው ባልደረባ ተናግረዋል።
« በካፍቴሪያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ከሚመገቡት 13000 ገደማ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት 5000 ተማሪዎች ብቻ የሚገኙበት ሁኔታ አለ» ብለዋል የዮንቨርስቲው ባልደረባ።
የተለያዩ የዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት እና ዛሬ በጋራ በተለያዩ ዮንቨርስቲዎች የተነሱትን ግጭቶች ተከትሎ በቀጣይ ሂደቱ ላይ በመምከር ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።
Via:- DW

ዴንማርክ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ ለመደገፍ የሚውል የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች።
የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ካሪን ፖልሰን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ተፈራርመውታል።
የዛሬው ስምምነት የዴንማርክ የትብብር ሚኒስትር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት የዴንማርክ መንግስት በገባው ቃል መሰረት የተደረገ ነው ተብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ካሪን ፖልሰን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ተፈራርመውታል።
የዛሬው ስምምነት የዴንማርክ የትብብር ሚኒስትር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት የዴንማርክ መንግስት በገባው ቃል መሰረት የተደረገ ነው ተብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡
የኮሚሽኑ አባላት በሀገሪቱ ብሄራዊ መግባባትን ለማስፈን በሚያከናውኗቸው ተግባራት የከተማ አስተዳደሩ ትብብርና ድጋፍ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ ኮሚሽኑ ቁርሾዎችንና ቅራኔዎችን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ዝግጅትና ጥረት አድንቀው የከተማ አስተዳደሩ ለኮሚሽኑ ሀሳብ ስኬት ድርሻውን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከክልል መስተዳድር አመራሮችና እና ከከተማ መስተዳድር አመራሮች ጋር ትውወቅና ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
Via Mayor Office

ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ!
በዘንድሮው ዓመት ከረጅም ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የተቀላቀለው ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ፡፡የስፓንሰርሽፕ ስምምነቱ በትናትናው ዕለት የክለቡ የበላይ ጠባቂ እና የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ እና የክለቡ ፕሬዚደንት አቶ ኡብሳ ለገሰ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በትናትናው ዕለት ተፈርሟል፡፡ስምምነቱ የገንዘብ እና የስፖርት ቁሳቁስ ያካተተ ሲሆን በስምምነቱ መሠረት ሰበታ ከተማ በማልያው ላይ የሜታ አቦ ቢራ ምርት ያስተዋውቃል ተብሏል።
Via FBC/Soccer Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኦስሎ፣ ኖርዌይ ከሰሞኑ የተቀበሉት የሰላም የኖቤል ሽልማት ሜዳልያ እና ዲፕሎማ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሁለት ሙዚየሞችና በአንድነት ፓርክ ይቀመጣል ተባለ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሸለሙት 3 ሜዳልያና ሦስት ዲፕሎማ መሆኑን ሰምተናል፡፡በሁለቱ ሙዚየሞችና በአንድነት ፓርክ እያንዳንዳቸው አንድ ሜዳልያ እና አንድ ዲፕሎማ ይቀመጣል ተብሏል፡፡ ከአንድነት ፓርክ በተጨማሪ ለሽልማቱ መቀመጫነት የተመረጡት ሁለቱ ሙዚየሞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ስር የሚገኘው ኢትኖግራፊክ ሙዚየም እና ብሔራዊ ሙዚየም ናቸው፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ሜዳልያና ዲፕሎማውን ነገ ከሰዓት በኋላ ተረክቦ በክብር በሙዚየሙ ውስጥ ያስቀምጣል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ደግሞ በመጭው እሁድ ከሰዓት በኋላ ሌላ አንድ ሜዳልያና ዲፕሎማ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ባሉበት ተረክቤ በብሔራዊ ሙዚየም አስቀምጣለሁ ብሏል፡፡በአንድነት ፓርክ ቀሪ አንድ ሜዳልያና አንድ ዲፕሎማ ይቀመጣል የተባለ ሲሆን ሥነ-ሥርዓቱ የሚከናወንበት ቀን ገና አልታወቀም፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የተሸለሙት የኖቤል ሽልማት በግላቸው ስለ ሰላም ፈፅመውታል በተባለ ተግባር ቢሆንም ሜዳልያዎቹና ዲፕሎማዎቹ በተጠቀሱት ሙዚየሞች እንዲሁም በአንድነት ፓርክ ተቀምጠው ለህዝብ እይታ ክፍት ይሆናሉ ተብሏል፡፡
Via Sheger