YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመድኃኒት ቅመማ አገልግሎት ጀመረ!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመድኃኒት ቅመማ አገልግሎቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት ጥቅምት 25/2012 ዓ.ም በይፋ ጀምሯል፡፡ በፕሮግራሙ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሲሳይ ይፍሩ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡አቶ ያዕቆብ ሰማን ፣በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳሬክተር፣ የመድሀኒት ቅመማ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መጀመሩ የመድሀኒቶችን ሁኔታ በቅርብ ክትትል ለማጥናትና የመድሀኒት ግዥ ወጭን ለመቀነስ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየሠራ ለሚገኘው የመድሀኒት ቅመማ ከፍተኛ ክብርና እውቅና ከመስጠት ባለፈ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

-የዩንቨርስቲው ህ/ግ/ዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን የፊታችን ማክሰኞ ይቀበላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን የፊታችን ማክሰኞ በኖርዌይ ኦስሎ በመገኘት እንደሚቀበሉ ታውቋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነው ባለፈው መስከረም ወር መመረጣቸው ይታወሳል።ዶ/ር ዐቢይ በኖርዌይ ቆይታቸው በኖቤል መርሃ-ግብሩ ዋና ዋና ሁነቶች ላይ ብቻ እንደሚሳተፉ እና ሁሉን ለማዳረስ በአገር ቤት የሚጠብቋቸው አስቸኳይ ስራዎች እንደማይፈቅዱላቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢለኔ ስዩም ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
ከትላንት ማምሻውን ጀምሮ የእርድ በሬዎች በተለመደው መጠን እየገባለት አለመሆኑን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለፀ፡፡

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃለፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል እንደገለፁት ከሆነ ድርጅቱ ከ700 በላይ የቁም ከብቶች የእርድ አገልግሎት ለመስጠት ቢዘጋጅም 200 የቁም ከብቶች ብቻ ወደ ድርጅቱ መምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡የእንስሳቱ ቁጥር የቀነሰበትን ምክንያት በቃል አልተነገረኝም ያሉት አቶ አታክልቲ ጉዳዩን ለማጣራት ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሉካንዳ ቤቶች ማኅበር ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ እንደገለፁት የሉካንዳ ቤቶች አድማ አድርገዋል ስለተባለው ጉዳይ እንደማያውቁ ገልፀው ፤ በሉካንዳ ቤቶች ላይ መንግሥት እንዱከፍሉ ባስቀመጠው የገቢ ግብር ቅሬታ አድሮባቸው እንደነበር እና ቅሬታቸውንም ለተለያዩ ተቋማት ሲያቀርቡ መቆየታቸን አስታውቀዋል፡፡ነገር ግን በተቋማቱ አመርቂ ምላሽ ባለመሰጠቱ ሉካንዳ ቤቶቹ ወደ አድማ ሳይገቡ እንዳልቀረ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

Via Ahadu Radio
@YeneTube @FikerAssefa
በገብረ ጉራቻ ከተማ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አራት የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አባላት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ትናንት (ሃሙስ) ምሽት 2፡30 ገደማ በሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገብረ ጉራቻ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ ደንደዓ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቱ የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪ አካላትን ለመግደል ያለመ መሆኑን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ የግድያ ሙከራው ኢላማ ከነበሩት መካከል የኩዩ ወረዳ ፖሊስ ኃላፊ ዋና ሳጅን አዱኛ ደቀባ እና አብረዋቸው የነበሩ ሌላ የወረዳው ፖሊስ አባል እንደሚገኙበት አስተዳዳሪው ይናገራሉ።

ጥቃቱ የተፈጸመው የፖሊስ አባላቱ እራት በልተው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ እየገቡ ሳለ እንደነበር የሚናገሩት የኩዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ፤ በፖሊስ አባላቱ ላይ በሁለት አቅጣጫ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ያስረዳሉ።"ዋና ሳጅን አዱኛ እግራቸውን ነው የተመቱት። አብሯቸው የነበረው የፖሊስ አባል ደግሞ እጁን ነው የተመታው" የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ የተኩስ ድምጽ ሰምተው ወደ በስፍራው የተገኙ ሌሎች ሁለት የቀበሌ ሚሊሻዎች ላይም ተኩስ ተከፍቶ ጉዳት ደርሶባቸዋል" በማለት ትናንት ምሽት በገብረ ጉራቻ ከተማ የተፈጠረውን ክስተት ያስረዳሉ። አቶ ደረጄ በአራቱም የጸጥታ አስከባሪ አካላት ላይ የደረሰው ጉዳት ለህይወት የሚያስጋ አለመሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤ ሶስቱ እግራቸው ላይ አንዱ ደግሞ እጁ ላይ ጉዳት ማጋጠሙን አስረድተዋል።

"ሁለቱ በከተማችን በሚገኘው ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ ለተጨማሪ ህክምና ወደ አዲስ አበባ ተልከዋል" ብለዋል። በኩዩ ወረዳ ጸጥታ አከባሪዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።የቀድሞ የወረዳው ፖሊስ ኃላፊ ጨምሮ ሁለት የፖሊስ አባላት ከወራት በፊት በታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።

በተጨማሪም በወረዳው ቆላማ ቀበሌ ውስጥ ሁለት የቀበሌ ሚሊሻዎች ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ተገድለው እንደነበር አስተዳዳሪው ያስታውሳሉ። የኩዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂ የሚያደርጉት "በቀድሞ የኦነግ ጦር ስር የነበሩ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን" ነው።ትናንት ጥቃት ያደረሱት ታጣቂዎች ተከታትሎ መያዝ አለመቻሉትን የተናገሩት አስተዳዳሪው ፖሊስ የግድያ ሙከራውን እየመረመረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«ኢትዮጵያን ለማዳን» በሚል ዓላማ ባንድ ያበሩ ኢትዮጵያዉያን ለስድስት ወራት በሚስጥር ያደረጉትን ዉይይት ባለፈዉ ሮብ አጠናቀቁ።በተከታታይ በተደረገዉ ዉይይት የምክር ቤት እንደራሴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የተለያዩ መስኮች ባለሙያዎች፣ ነጋዴዎችና የመብት ተሟጋቾች ባጠቃላይ 50 ሰዎች ተካፍለዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
አቶ ለማ መገርሳ የስራ መልቀቂያ አላስገቡም!!

አቶ ለማ መገርሳ የስራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሐሰት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የመከላከያ ሚንስትር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላስገቡም ብሏል።

አቶ ለማ በአሜሪካ ስራቸውን በማከናወን ላይ ናቸው የስራ መልቀቂያ አስገቡ ተብሎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከአውነት የራቀ መሆኑን አስታውቋል።

የኮሚንኬሽን ክፍሉ ለጣቢያችን እንዳለው በተቋም ደረጃ እንደዚህ አይነት መረጃ የለም ውሸት ነው ሲል የነገረን ሲሆን ከዛ ውጪ የሚናፈሰው ወሬ የፖለቲከኞች እንጂ በተቋም ደረጃ ስለዚህ ጉዳይ የተነሳ ነገር የለም ብሎናል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
10 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አብረው ለመስራት የተስማሙ ሲሆን፣ ከአስሩ ሰባቱ የስምምነት ሰነዱን ዛሬ ተፈራርመዋል፡፡

በጋራ ለመስራት የተስማሙት ፓርቲዎች
1. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
2. የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር
3. የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
4. የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
5. የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
6. የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
7. የካፋ አረንጓዴ ፓርቲ
8. የአፋር ነፃነት ግንባር
9. የአገው ብሔራዊ ሸንጎ
10. የሲዳማ ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ ናቸው

በጋራ ለመስራት ከተስማሙት ፓርቲዎች ሰባቱ በዛሬው ዕለት በኢሊሊ ሆቴል ተፈራርመዋል።ፓርቲዎቹ ላለፉት ስድስት ወራት በመምከር የሚመሩበት የጋራ ሰነድ አዘጋጅተው በዛሬው ዕለት አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የሀረሪ ጉባኤ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አዲስ አፈ-ጉባኤ ሾመ።

የጉባኤው ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አሚራ አሊ እንደገለፁት ዛሬ የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የቀድሞው የሀረሪ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ ያቀረቡትን የስልጣን መልቀቅያ ጥያቄ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ነው።በዚሁ መሰረትም የቀድሞው አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ ያቀረቡት የመልቀቂያ ጥያቄ በጉባኤው በሙሉ ድምፅ ፀድቆ አዲስ አፈ-ጉባኤ ተመርጧል።በጉባኤው አዲስ አፈጉባዔ ሆነው የተሾሙት አቶ ኻሊድ አልዋን ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡አዲሱ ተሿሚ አቶ ኻሊድ አልዋን ከሹመታቸው በኋላ ባደረጉት ንግግር ከዚህ ቀደም በጉባኤው የተከናወኑ በርካታ ተግባራት ቢኖሩም የታዩ ክፍተቶችም እንደነበሩ አንስተው ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር ፤ ክፍተት የነበረባቸውን ለመለወጥ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ጋንታ ካንቻማ ቀበሌ ትናንት ሌሊት የጣለው ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምርያ አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንዳሉት ትናንት ከምሽቱ 8 ሰዓት ገደማ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በ300 አባወራ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡በጎርፉ 500 ሄክታር የሙዝ ምርት መውደሙን አዛዡ ገልጸው ከዞኑ የተውጣጣ የፖሊስና አመራር አካላት ተጎጂዎችን በመጎብኘትና ወደ ሌላ አካባቢ በማሸጋገር ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡የአደጋው መንስኤ በመንገድ ስራ ወቅት የጎርፍ ማፋሰሻ ትላልቅ ቱቦዎች በመደፈናቸው ምክንያት ነው ብለዋል ኮማንደሩ፡፡በጎርፉ አደጋ የሰው ህይዎት እንዳያልፍ የአካባቢው ህብረተሰብ አስቀድሞ ጥረት ማድረጉን ተናግረው ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ አዛዡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ: ደቡብ ቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
840 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ተመለሱ!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ከአምስት እስከ ስምንት አመት ተፈርዶባቸው በሳውዲ እስር ቤቶች ይገኙ የነበሩ 840 ኢትዮጵያውያን በፈቃዳቻው ዛሬ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ኢትዮጵያውያኑ ቀይ ባህርን አቋርጠው የሳውዲን ድንበር ሲሻገሩ የተያዙ እና በሳውዲ አረቢያ በጂዳ እና ጂዛን ግዛት በሚገኙ እስር ቤቶች ይኖሩ የነበሩ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ናቸው። ተመላሾቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት አቶ ዮሃንስ ሾዴ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከዚያ በኋላም ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርድት (IOM) የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ አድርጎላቸዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ጣሊያን ኤርትራዊያን ስደተኞችን ወደ ሊቢያ በግዴታ መመለሷን ሕገ ወጥ ነው- ሲል አንድ የሮም ፍርድ ቤት ወስኗል፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር እና መከላከያ ሚንስትር 210 ሺህ ዩሮ ካሳ ለተጎጅዎቹ እንዲከፍሉም አዟል ፍርድ ቤቱ፡፡ እኤአ በ2009 ገና ከባሕር የተመለሱት 14ቱ ስደተኞች በጣሊያን ጥገኝነት የመጠየቅ መብት እንዳላቸው እንደተወሰነላቸው ኢንፎ ማይግራንት ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡ ፍርዱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግሥት ላይ ለመሰረተው ክስ ምላሽ ነው፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ራይድ ታክሲ ምርጥ አገልግሎት ሰጪ በመባል ሽልማት አገኘ። የራይድ ታክሲዎችም ቁጥርም 9,000 አልፏል።

Center for Accelerated Women's Economic Empowerment (CAWEE) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት የ2019 በኢትዮጵያ ምርጥ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በማለት የራይድ ታክሲ ሀሳብ አመንጪና የሀይብሪድ ዲዛይን ባለቤትን ወይዘሪት ሳምራዊት ፍቅሩን በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ሸልሟል።

-Tesfaye Getnet
@YeneTube @FikerAssefa
💥ማስታወቂያ💥
PUMA (GV SPECIAL)

📎ORIGINAL

Size 40-41-42-43

📌 Made in Vietnam
📌 Price 2200 birr
📌 With delivery
📌 በ 5 አይነት ከለር
📞 0912732493

ቴሌግራም ለማግኘት ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉን👇👇
@Hkaeg
ኢትዮጵያ 173 ቀን በሚቆየውና 25 ሚልየን ህዝብ በሚጎበኘው በዱባይ 2020 ኤክስፓ ትሳተፋለች።

በዪናይትድ አረብ ኢመሬትሷ ዱባይ በኦክተበር 2020 በሚከፈተው እና 25 ሚልየን ህዝብ ይጉበኘዋል ተብሎ በሚጠበቀው የዱባይ2020 የንግድ ትእይንተና ባዛር ኢትዮጵያ የምትካፈል ሲሆን በመጪው ታህሳስ 2 የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር እና ከዱባይ የተወከሉ የኤክስፓው አዘጋጆች በጉዳዩ ላይ መግለጫ ይሰጡበታል መባሉን ሰምቻለው።

ኢትዮጰያ ያላትን ምርት፣ባህልና የኢንቨስትመንት አማራጮቿን በኤክስፓ ታቀርባለች።
የዱባይ ኤክስፓ 192 ሀገራት ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዱባይና በአቡዳቢ ከተሞች መሀከል በተዘጋጀ 438 ሄክታር ላይ ኤክስፓ ይካሄዳል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌይን አዲስ አበባ ገብተዋል!
ቦሌ ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል ያደረጉላቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው።

ፎቶ: Ethiopian Airlines | Elias Meseret
@Yenetube @Fikerassefa
ኦባንግ ሜቶ "ለመተማመን እንነጋገር" በሚል ርዕስ በኤልያና ሆቴል ውይይት እያካሄደ ነው።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራች አቶ ኦባንግ ሜቶ ከተለተያዪ ምሁራንና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የተሻለ ለውጥ ለማምጣት " ለመተማመን እንነጋገር" በሚል ርዕስ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 27 በኤልያና ሆቴል ወይይት እያካሄደ ነው ።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
በኦሮሚያ ለሚከሰቱ የጸጥታ መደፍረስ ዋነኛው ምክንያት የስራ አጥነት እንደሆነ የኦሮሚያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር አስታወቀ።

የኦሮሚያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቱ ቴሶ እንዳሉት በየቦታዉ ለሚነሱት ግጭቶች የስራ አጥነቱ ሚና ከፍተኛ ነዉ ብለዋል፡፡ከከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀዉ የሚወጡ ተማሪዎች የስራ እድል ባለማግኘታቸዉ በትንሽ ገንዘብ ይታለላሉ ነዉ ያሉት፡፡እነዚህን ወጣቶች ወደ ስራ ማስገባት ችግር ፈጣሪዎች ማስፈፀሚያ እንዳይሆኑ ያደረጋል የሚሉት ዶክተር ጉቱ የስራ አጥነቱን ችግር ለመቀነስ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ሥራ የፈታዉ ወጣቱ ትዉልድ መሄጂያ ሲያጣ አማራጭ የሚያደርገዉ ጥፋትን ነዉ ፣ወጣቱ ለሀገሩ ያለዉ አመለካከት በብሄር ተገድቧል፣ ለዚህም የወጣቱን ርዕዮት አለም በማሻሻል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይገባልም ብለዋል።ወጣቶች ህይወታቸውን በስራ ካልመሩ ድብርት ዉስጥ ይገባሉ፤ በራስ መተማመናቸውም ይነጠቃል ፣ጥርጣሬ፣ ፍራቻ፤ ለአእምሮ ህመም ተጠቂ ከመሆን አልፎ መጨረሻዉ ወደ ዝርፊያ እና አገርን ወደ ማወክ ይሰማራል ብለዋል።

መንግስት በራሱ ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ጀምሮ የግል ባለሃብቶችና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በተጨማሪ ሃብት መፍጠር የሚያስችሉ እቅዶችንና የኢንቨሰትመንት አማራጮችን መፍጠር ላይ እንዲያተኩር አሳስበዋል። በኢትዮጵያ እድሜያቸው ለስራ ዝግጁ ከሆኑ ዜጎች መካከል ከ11 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሥራ እንደሌላቸው የፌደራል ስራ እድል ኮሚሽን መረጃ ያስረዳል። ከዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከኦሮሚያ ክልል መቱ ከተማ ወደ ባህርዳር ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ደጀን ከተማ አቅራቢያ በተደረገ ፍተሻ 57ክላሽንኮቭ መሳሪያዎች መያዛቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa